Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የጸሎት ያለህ
የጸሎት ያለህ
የጸሎት ያለህ
Ebook423 pages3 hours

የጸሎት ያለህ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ይህ መጽሐፍ የተጻፈዉ ለመጨረሻዉ ዘመን ትዉልድ ነዉ። ይህ የመጨረሻዉ ዘመን ትዉልድ፣ በመጨረሻዉ ዘመን ላይ ባለችው ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር በኃይል እንድትገለጥ የሚያገለግል አገልጋይ ትዉልድ ነዉ። ከአገልግሎቱ ዋናዉ ደግሞ የጸሎት አገልግሎት ነዉ። ጸሎት የእግዚአብሔር መንግሥት እንድትገለጥ መማለጃው መንገድ ነዉ። ያኔ ጌታ ኢየሱስ ይከብራል። ይህን ማዕከላዊ ሃሳብ በመረዳት መንግሥትህ ትምጣ በማለት ልንጮህ ግድ ነዉ። 

ብዙ ሌሎች ሃሳቦችን ከመጽሐፉ በጥልቀት ያገኛሉ። ለጸሎት ያለዎትን ምልከታን ይቀይራሉ። ላልከበረዎ ጌታ ክብር ይጮኻሉ። ያኔ እንደ እኔ የጸሎት ያለህ ይላሉ።

Languageአማርኛ
Release dateOct 30, 2020
ISBN9781393381549
የጸሎት ያለህ

Related to የጸሎት ያለህ

Related ebooks

Reviews for የጸሎት ያለህ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የጸሎት ያለህ - Yared Tsegu

    በያሬድ ፀጉ

    የጸሎት ያለህ !!

    ጸሐፊ ያሬድ ፀጉ

    የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ

    የመጀመሪያው ዕትም በወርሃ ኅዳር 2013 ዓ.ም ታተመ

    ይህን መጽሐፍ በማንኛውም ዓይነት መንገድ በከፊልም ሆነ በሙሉ ለማበዛት በቅድሚያ የጸሐፊውን ይሁንታ ማግኘት ይጠይቃል፡፡

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ በ1954 ዓ.ም ከታተመው የቀ. ኃ. ሥ. መጽሐፍ ቅዱስ ዕትም የተወሰዱ ናቸው፡፡

    ––––––––

    የሽፋን ንድፍ፡-  ሰራፕታ ዲዛይን

    ለአስተያየትዎ ኢ-ሜይል፡- yegeta2014@gmail.com

    ስልክ +251-911 44 13 21

    አዲስ አበባ

    2013 ዓ.ም

    ማውጫ

    አበርክቶት ................................... vii

    የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት ........................... viii

    ምስጋና ......................................ix

    ቀዳሚ ቃል  ..................................... x

    መቅድም...................................... xii

    መግቢያ....................................... xiv

    መንደርደሪያ ..................................xix

    ክፍል አንድ

    የጸሎት መሠረታዊ ነገሮች

    1.  ጸሎት ምንድር ነው? .............................. 4

    ሀ.  ለምንድር ነው የምንጸልየው?..................... 14

    ለ.  የጸሎት ዓላማ ............................ 16

    2.  ሳያቋርጡ መጸለይ .............................. 20

    ሀ.  ሳያቋርጡ መጸለይ ............................ 20

    ለ.  ብዙ ጸሎት በስደት እና በመከራ ጊዜ ................... 22

    3.  የጸሎት ታሪካዊ ዳሰሳ .............................. 26

    ሀ.  ጸሎት በብሉይ ኪዳን ......................... 26

    I.  ጸሎት በጥንት ሩቅ ምሥራቅ .................... 26

    II.  ጸሎት በእስራኤል ፤ ከነገሥታት ዘመን በፊት............ 30

    III.  ጸሎት በእስራኤል ነገሥታት ዘመን................ 34

    VI.  ጸሎት በእስራኤል በስደት እና ከስደት ዘመን በኋላ........ 37

    ለ.  ጸሎት በአዲስ ኪዳን........................... 39

    I.  የጌታ የጸሎት ሕይወት..................... 39

    II.  የጌታ ጸሎት ዓይነቶች..................... 44

    III.  የጌታ ጸሎት ተምሳሌት.................... 54

    4.  ጸሎት በቤተክርስቲያን........................... 64

    ሀ.  የጥንቷ ቤተክርስቲያን ጸሎት..................... 65

    ለ.  ጸሎተ ሐዋርያት............................ 66

    ክፍል ሁለት

    ተግባራዊ የጸሎት ሕይወት

    1.  የጸሎት ዓይነቶች.............................. 76

    ሀ.  የልመና ጸሎት.............................. 76

    ለ.  የምስጋና ጸሎት.............................. 78

    ሐ.  የውዳሴ ጸሎት.............................. 78

    መ.  የምልጃ ጸሎት.............................. 78

    ሠ.  የውጊያ ጸሎት.............................. 80

    ረ.  የመሥዋዕትነት ጸሎት........................... 80

    ሰ.  የምጥ ጸሎት............................... 81

    ሸ.  የአገዛዝ ጸሎት.............................. 83

    2.  የምልጃ ጸሎት.................................. 85

    ሀ.  እንዴት እንማልድ?.......................... 86

    ለ.  እግዚአብሔር ማላጆችን ይፈልጋል................... 87

    3.  የውጊያ ጸሎት................................ 89

    ሀ.  ተፈጥሮአዊ እና መንፈሳዊ ግዛቶች..................... 91

    ለ.  ሁለቱ መንግሥታት............................. 93

    ለ.1  ተፈጥሮአዊ መንግሥታት....................... 93

    ለ.2  መንፈሳዊ መንግሥታት........................ 94

    4.  የጸሎት እልፍኝ................................. 103

    ሀ.  የጸሎት እልፍኝ ባህርያት...................... 105

    5.  መንግሥትህ ትምጣ................................ 115

    ሀ.  መገለጡን የሚናፍቅ ልብ....................... 121

    ለ.  መንፈስና ሙሽራይቱ......................... 121

    6.  እግዚአብሔርን በጸሎት መጠበቅ....................... 127

    ሀ.  የመንፈሳዊ ሕይወት ዑደቶች........................ 127

    ለ.  እግዚአብሔርን የመጠበቅ ጥበብ...................... 128

    ሐ.  በእግዚአብሔር መታደስ.......................... 129

    ክፍል ሦስት

    ውጤታማ የጸሎት መርሆዎች

    1.  እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን....................... 133

    2.  የጸሎት ውጤቶች................................. 147

    3.  ምላሽ ያገኘ ጸሎት............................. 151

    4.  የጸሎት እንቅፋቶች............................... 156

    5.  ምላሽ አልባ ጸሎቶች............................ 169

    6.  የምትጸልይ ቤተ ክርስቲያን........................... 179

    ሀ.  የአንድነት ጸሎት.......................... 179

    ለ.  የአንድነት ጸሎት ጥቅም....................... 181

    ሐ.  የአንድነት ጸሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ............... 186

    7. የሐዋርያው ጳውሎስ የጸሎት አስተምህሮ...................... 193

    ሀ.  እግዚአብሔርን ማወቅ........................ 203

    ለ. የመጥራቱን ተስፋ ማወቅ....................... 204

    ሐ. የርስት ክብሩን ባለጠግነት ማወቅ.................. 205

    መ.  ታላቅ የሆነውን ኃይሉን መረዳት................... 206

    ––––––––

    ክፍል አራት

    ጸሎት በመጨረሻው ዘመን ለሚመጣው ሪቫይቫል

    1.  ጸሎት የሪቫይቫል ቁልፍ .......................... 215

    ሀ.  የጸሎት ድርሻ ለሪቫይቫል ........................ 216

    ለ.  የሪቫይቫል አስፈላጊነት......................... 217

    ሐ.  ለሪቫይቫል መጸለይ ........................... 220

    መ.  የአንድነት ጸሎት ለመጨረሻው ዘመን ሪቫይቫል............... 222

    2.  ለመጨረሻው ዘመን መጸለይ............................ 224

    ሀ.  የመጨረሻው ዘመን.......................... 225

    ለ.  ለመጨረሻው ዘመን መጸለይ...................... 227

    ሐ.  የመጨረሻው ዘመን ጸሎት ባህርያት.................. 228

    3.  የጾም ጸሎት ኃይል................................ 234

    ሀ.  ጾም እና ጸሎት........................... 236

    ለ.  ለምን እንጾማለን?......................... 238

    ሐ.  የጾም መርህ............................ 238

    መ.  ሰባቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የጾም ጥቅሞች................. 241

    4.  የጸሎት ያለህ!! .............................. 257

    ሀ.  በእግዚአብሔር ቃል እንጸልይ ...................... 264

    ለ.  ቤተ ክርስቲያን ሆይ ንቂ!! ..................... 267

    ሐ.  በክፍተቱ መካከል እንቁም!! .................... 269

    ዋቢ መጻሕፍት................................. 277

    የጸሐፊው ቀደምት ሥራዎች.............................. 283

    አበርክቶት

    በምድር ላይ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲገለጥ በጸሎት እየተጋደሉ ለሚገኙ የጸሎት ሠራዊቶች ይሁንልኝ!!

    የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት

    ወዳጆች! ለካስ መጸለይ እና ስለ ጸሎት መረዳት ይለያያል? እኔን  ጨምሮ አብዛኛዎቻችን ጸሎትን እንጸልያለን፡፡ ግን ስለ ጸሎት ያለን እውቀት እና ግንዛቤ ይህን መጽሐፍ ባነበብኩበት ወቅት ጥቂት ሆኖ ተሠማኝ፡፡

    ይህን መጽሐፍ ማንበብ ስጀምር በውስጡ ካሉት ጥቅል እውቀቶች የተነሣ አነባበቤን በጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብኝ፣ ያነበብኳቸውን ሥፍራዎች በሙሉ በጥልቀት እንዳጠና እና  እንዳሰላሰል ተገደድኩኝ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የጸሎት ጭብጥ ሀሳብ  ወይም የጸሎት እውቀት፣ ለጸሎት የሚመጥን ህይወት እና የጸሎት ውጤት የሚሉ ትልልቅ ሀሳቦች በህይወታችን ሊተገበሩ እንደሚገባቸው አስተውያለሁ፡፡

    እንዲህ ልበልዎት፡- ይህንን ድንቅ መጽሐፍ ያንብቡት፤ እኔ ያገኘሁትን እና ከዛም የሚልቅ የሰማይ እውነት እና በረከት ያገኙበታል፡፡ በመጨረሻም በብዙ ድካምና በብዙ ትዕግስት ያዘጋጀልንን በጣም የምወደውን ወዳጄን ያሬድ ፀጉን እግዚአብሔር በብዙ ይባርክህ ልለው እወዳለሁ፡፡ ብዕርህ አይንጠፍ!!፡፡

    መልካሙ ጌታቸው

    የወንጌል አገልጋይ

    መጽሐፍዋ፤ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ የጸሎት ትምህርትን የምታስተምር ስትሆን ጸሐፊው በጸሎት ህይወት የተቃኘ ህይወት ያለው እንደሆነ ከመጽሐፉ መረዳት ችያለሁ፡፡ ስለዚህ ይህ ድንቅ መጽሐፍ የማስተማር እና የማሰልጠን ሽክሙ ላላቸው እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ሁሉም በጸሎት ህይወቱ ሊበረታ እንዲችል ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ጌታን ስለዚህ መጽሐፍ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ቢነበብ እና በግል ህይወት ቢተገበር ምክሬ ነው፡፡

    አያንሳ ጉተማ

    የወንጌል አገልጋይ

    ምስጋና

    ይህ መጽሐፍ በዚህ መልኩ ተሰናድቶ እንዲቀርብ የብዙዎች አስተዋጽኦ አለበት፡፡ በተለይ ከጥንስሱ እስከ ፍጻሜው ድረስ ውድ ጊዜያቸውን መሥዋዕት አድርገው ለሰጡኝ ለሜሊይ፣ ለጃን፣ ለቃል እና ለ ዮዮ እጅግ የከበረ ምስጋናዮን አቀርባለሁ፡፡ ያለ አንዳች ማጋነን ያለ እናንተ ርዳታና እገዛ ይህ መጽሐፍ እውን መሆን አይችልም ነበር፡፡ ብዙ ጊዜያችሁን ወስጄያለሁ እና እግዚአብሔር በብዙ ይባርካችሁ፡፡

    የመጀመሪያ ረቂቁን በማንበብ ገንቢ ሃሳብ ለሰጡኝ ለመጋቢ በቀለ ወልደ ኪዳን፣ ለሐዋርያው ቶማስ ምትኩ፣ ለመጋቢ መስፍን ሙሉጌታ፣ ለወንድም ሰለሞን አሰፋ፣ ለወንድም መልካሙ ጌታቸው እና ለወንጌላዊ አያንሳ ጉተማ ላቅ ያለ ምስጋናዮን በጌታ ፍቅር  አቀርባለሁ፡፡ በተለይ መጋቢ መስፍን ሙሉጌታ ይህ መጽሐፍ ለአንባቢያን እንዲህ ሆኖ እንዲደርስ ከቅንነት ጋር በብዙ ደክመህበታል፤ ጌታ ብድራትህን በብዙ ይክፈልህ፡፡ በመቀጠልም ለዚህ መጽሐፍ ማመሳከሪያ የተጠቀምኳቸውን መጽሐፍትን ደከምኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ዘመናቸውን መሥዕዋት አድርገው ለጻፉልን ቀዳሚ ምሁራን ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡ እነርሱ እንደ ሻማ ቀልጠው ትውልዱ የእግዚአብሔር ቃል ሙላት እንዲኖረው አግዘዋልና፤ ታላቅ ክብር ይገባችኃል፡፡

    ይህ መጽሐፍ እዚህ ይደርስ ዘንድ በሃሳብ እና በምክር እንዲሁም በሚያስፈለገኝ ነገር ሁሉ ከአጠገቤ በመሆን ላገዛችሁኝ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ማለት እወዳለሁ፡፡ 

    በመጨረሻም በዓለም ላይ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲገለጥ በጸሎት እየተጋደሉ ለሚገኙ የጸሎት ሠራዊቶች ምስጋናዬን በያሉበት አቀርባለሁ፡፡ ሕይወታችን እንዲቃና የእናንተ ድርሻ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ብድራታችሁን የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ይክፈላችሁ፡፡

    ቀዳሚ ቃል

    የጸሎት ያለህ!

    አንባቢው - ከመጽሐፍ ቅዱስዎ ሌላ - «በጸሎት» ላይ የተጻፉ፣ ቢያንስ ሁለት ሦስት መጻሕፍት፣ ሳያነብቡ እንዳልቀሩ እገምታለሁ፡፡ «የጸሎት ያለህ!» የተሰኘውን ይህንን መጽሐፍ ሲያዩትም፣ በውስጥዎ የሚነሣው የመጀመሪያው ጥያቄ፣ «በጸሎት ላይ. . . ደግሞ ሌላ መጽሐፍ. . . ለምን?» የሚል ሳይሆን እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ በዚህች «መቅድሜ» ይህንን ጥያቄዎን - በጣም በመጠኑም ቢሆን - ለመመለስ ነው የምሞክረው፡፡ መልሶቼም ሁሉ፣ «የጸሎት ያለህ!» ከተሰኘው ከዚሁ መጽሐፍ ውስጥ የቃረምኳቸው ናቸው፡፡

    ጸሎት፣ «ልዑሉ» እግዚአብሔር እና «ደካማው» ሰው፣ በሽርክና (in partnership) ለእግዚአብሔር መንግሥት፣ ለግለሰብ፣ ለቤተሰብ፣ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለአገር እና ለዓለም፣ የሚሰጡት «መንፈሳዊ» አገልግሎት ነው (1ኛ ቆሮ. 3፥9)፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ ስለዚህ «አገልግሎት» የሚሰጣቸው ትምህርቶች ፈርጀ-ብዙ በመሆናቸው፣ ማንም ሰው ቢሆን - በጸሎት ጉዳይ - «ሁሉን-ዐውቃ» (authority) ሊሆን አይችልም፡፡ ሊሆን የሚችለው - እግዚአብሔር ቢረዳው - ከቅዱስ ቃሉ እና ከቅዱስ መንፈሱ አዲስ ነገር ለመማር ሁልጊዜም የተዘጋጀ  መሆን ብቻ ነው፡፡

    ደቀ መዛሙርቱ ከመምህራቸው ሕይወት ያስተዋሉት፣ የገዛ ራሳቸውም ሊያደርጉት የተመኙት አንድ ነገር፣ «የጸሎት ሕይወቱ» ይመስለኛል፡፡ ባይሆንማ ኖሮ፣ ለምን «. . . እንጸልይ ዘንድ አስተምረን» ይሉት ነበር? እርሱም ደግሞ፣ ለምን ጥያቄአቸውን በደስታ ይቀበል እና ሰፊ መልስ ይሰጣቸው ነበር (ሉቃ. 1፥1-4፣ ማቴ.6፥9-13)? እኔ እንደሚመስለኝ፣ ያ ጸሎት በዝርዝር የተሰጠን፣ በጠዋትና በማታ  «እንድናነበንበው» ሳይሆን፣ የጸሎቶቻችን ሁሉ «ናሙና» (sample) እንድናደርገው ነው፡፡

    እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ቤተሰብ፣ እንደ ማኅበረሰብም ሆነ እንደ አገር፣ በጣም የሚያስፈልጉን ዳሩ ግን የሌሉን፣ ብዙ ሥጋዊና መንፈሳዊ አስፈልጎቶች (needs) አሉን፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ አስተምህሮ የሆነ እንደ ሆነ፣ እነዚህ ነገሮች የሌሉን ስለማንሠራ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ ያለ ጥርጥር፣ እግዚአብሔርን ስለማንለምነውም ጭምር ነው ሊሆን የሚችለው (ያዕ. 4፥1-2)፡፡

    ከጸሎት ጋር ትውውቅ ያለን ሰዎች ሁሉ በእርግጠኛነት የምንመሰክረው፣ ወደ እግዚአብሔር ያቀረብናቸው ጸሎቶች እጅግ በጣም ብዙ ሲሆኑ፣ የተቀበልናቸው የጸሎት መልሶች ግን በጣት የሚቆጠሩ መሆናቸውን ነው፡፡ ያልተመለሱልንን ጸሎቶቻችንን ምን ዋጣቸው እንበል? ለምን ሳይመለሱልን ቀሩ? ማለቴ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሚስቶቻቸውን የማያከብሩ ባሎች ጸሎታቸው እንደሚከለከል መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (1ኛ ጴጥ. 3፥7)፡፡ መርሑ ባሎቻቸውን ለማያከብሩ ሚስቶችም የሚሠራ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በመነሣት፣ እስከ ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ፣ ቤተ ክርስቲያን እና መንግሥት ድረስ ያሉትን ግንኙነቶቻችንን - በመጽሐፍ ቅዱሱ መነጽር - ልንፈትሻቸው እንችላለን፡፡

    ይበቃኛል፡፡ በአገራችን፣ «ለብልህ አይነግሩም፣ ለአንበሳ አይመትሩም» ይባላል፡፡ ምናልባት ሁላችንም፣ ስለ ጸሎት ገና ያላወቅናቸው ብዙ ቁም ነገሮች ይኖሩ ይሆናል፡፡ «የጸሎት ያለህ!»ን በማንበብ፣ ግንዛቤአችንን እናስፋ፡፡ ማን ያውቃል? የራሳችን እና የብዙዎች የሕይወት እና የአገልግሎት ዕጣ ፈንታ (destiny) ይለወጥ ይሆናል፡፡ መልካም ንባብ! 

    በቀለ ወልደ ኪዳን (መጋቢ)

    ––––––––

    መቅድም

    ለጌታ የተሸነፈ ልብ፣ የእግዚአብሔርን የልብ ትርታ የሚያደምጥ ልብ እና የጌታን ቅንዐት የሚቀና ልብ የጸሎት ያለህ! ማለት ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ዓለም ክርስቶስን ስለማታውቅ ለመለኮታዊ ድንጋጌዎች ጆሮ ዳባ ብትል የጥጅቷ ውጤት ነውና አይደንቅም፡፡ አማኞች ግን ፍሬ ነገሩን ቸል ቢሉ ውድቀትን ብቻ ሳይሆን የባሰውን መለኮታዊ ፍርድ ይቀሰቅሳሉ፡፡ በገሃድ እየሆነ ያለው ይሄንኑ እያንፀባረቀ ይገኛል፡፡ ለዚሁ ይመስላል የጸሎት ያለህ! የሚሉ ቅዱሳን አኻዝ አንሶ ዓለማዊውንና ሥጋዊውን ፍላጎት የማርካት ጩኸት ከየማዕዘናቱ የሚስተጋባው፡፡

    የጸሎትን አስፈላጊነት ማወቅ ብቻ ሳይሆን ጸሎት ይቅደም! (Prayer First!) የሚል የውስጥ ግለት መታጠቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን ዓይነቱን የከበረ ዕሴት ለመላበስ ጸሎትን የሕይወታችን ወይም የስብዕናችን አካል ማድረግ ግድ ነው (Prayer must become a part of our life) ፡፡ በማር. 1÷35 ጌታ ኢየሱስ በሌሊት ከቤት ወጥቶ ከአምላኩ ጋር ለመገናኘት ምቹ ወደ ሆነ የጸሎት ቦታ መሄዱን ይነግረናል፡፡ የዛሬዎቹ አማኞች በተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ ለመገኘት በጸሎት የተቃኘ ሕይወት መፍጠር ይኖርብናል (creating a life style of prayer) ፡፡ ወደዚህ ልምምድ ለመግባት፡-

    -  የምንጸልይበትን ርዕስ ማወቅና መለየት (ከመንፈስ ቅዱስ፣ ከቃለ እግዚአብሔር እና ከወቅታዊ ሁኔታዎች)፣

    -  የምንጸልበትን ሰዓት መወሰን፣

    -  ምቹ የጸሎት ስፍራ መምረጥ / ማዘጋጀት፣

    -  በእግዚአብሔር ፊት ስለ መሆናችን እርግጠኛ መሆን (1ኛ ነገ. 17÷1)፣ እና

    -  የሚጠበቀውን ውጤት በመንፈስ መረዳት፡፡ በሌላ አባባል ከእግዚአብሔር ትልቅ ውጤት በመጠበቅ መጸለይ (ኤር. 33÷3) ተመራጭ እርምጃዎች ናቸው፡፡

    የጸሎት ሕይወትን እና አገልግሎትን በዚህ መልኩ ካዳበርነው ጸሎትን እንደ ሥራ ሳይሆን ግንኙነታዊ ስጦታ እናደርገዋለን (connect with God relationally)፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ከእርሱ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ሲጠነክር በመሆኑ የእርሱን ፈቃድ የማወቅ አቅማችን ያድጋል፡፡ በግንኙነት ያልተመሠረተ ጸሎት የባከነ ጸሎት (dally prayer) ስለሚሆን በፍሬ ነገሩ ላይ ትኩረት መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔርን መገናኘት እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ ከመፈለግ የሚመነጭ ባርኮት መሆኑን ነቢያት ጠቁመውናል (ኤር. 29÷13)፡፡

    ወንድማችን ያሬድ ፀጉ የጸሎት ያለህ! በሚል ርዕስ ያበረከተልንን መጽሐፍ በ6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ የማየት ዕድል ገጥሞኛል፡፡ የመጀመሪያውን ረቂቅ መጽሐፍና ኅትመት ቀረሹን ረቂቅ መጽሐፍ ከኅትመት በፊት በማንበብ ለዳብሮት የሚሆኑ ግብዐቶችን ለማተም ችያለሁ፡፡ መጽሐፉ ከላይ የተባሉትን ፈርጥ ምልከታዎች አጉልቶና ተንትኖ በመቅረቡ የጸሎት ያለህ! ለሚለው አምላካዊ ጩኸት ምላሽ የሚሰጡ ጉበኞችን ከማስነሳት  አልፎ ለውጥ ፈላጊ አማኞችን በሙሉ ቃታች የማድረግ አቅም ያጋባል የሚል ዕምነት አለኝ፡፡ በተለይም የእግዚአብሔር ምሪት እና ትድግና ለሚያስፈልገው ለእኛ ዘመን አጀንዳው አስፈላጊ ከመባል ያለፈ መሆኑን ስመሰክር በጽድቅ ድፍረት ነው፡፡ የደራሲው አበርክቶት በጸሎት አገልግሎት ለተሰለፉ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ለሚኒስትሪዎች እና ለቅዱሳን በሙሉ ወሳኝ ጥንቅር ይዞ በመቅረቡ ራሳችንንና ትውልዳችንን ከሚለወጡ መሣሪያዎች  አንዱ እንደሆነ በማመን እንድንጠቀምበት በአክብሮት አበረታታለሁ፡፡ በጹሑፍ ሥራ ሦስተኛው የሆነውን ይህን መጽሐፍ እንካችሁ ያለንን ሥጦታችን የሆነውን ያሬድ ፀጉን እና ቤተሰቡን እግዚአብሔር ያስፋችሁ፣ ይባርካችሁ እላለሁ፡፡

    መስፍን ሙሉጌታ (መጋቢ / ደራሲ)

    ከቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

    ––––––––

    መግቢያ

    ይህ መጽሐፍ ስለ ጸሎት የሚያስተምር ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ገፅ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አካል መታነጽ የሚያግዙ ጥልቅ ሃሳቦችን በውስጡ አካቶ ይዟል፡፡ መጽሐፉም ከብዙ ጾም እና ጸሎት በኋላ ለዚህ በቅቷል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሸክሙን በልቤ በኃይል አስቀመጠ፤ ከዚያ በኋላ ለረጅም ዓመታት በጥናት እና በዝግጅት ሂደት ማለፍ ግድ ሆነ፡፡ በዚህ የዝግጅት ጊዜ ውስጥ በብዙ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ጸሎትን አስመልክቶ እግዚአብሔር በልቤ ያስቀመጠውን ሐሳብ አስተምሬአለሁ፡፡ እግዚአብሔር በከፈተልኝ የአገልግሎት ደጆች ሁሉ የጸሎት ኃይል እና አስፈላጊነትን አስመልክቶ ሥልጠናዎችን ሰጥቼአለሁ፡፡ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትም ለጸሎት አገልጋዮች፣ የጸሎት ሲሚናሮችን በተከታታይ አዘጋጀቶ በመስጠት ለእግዚአብሔር መንግሥት የድርሻዬን ሳበረክት ቆይቻለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍም በሂደት የተወለደው የጸሎት ሠራዊትን ለማስነሣት ከቀረበ ተከታታይ የአገልጋዮች ትምህርት፣ ሥልጠና እና ሲሚናሮች መነሻ ነው፡፡ እነዚህን ተግባራት መፈጸም እችል ዘንድ፥ ጸሎት በሕይወቴ እና በአገልግሎቴ የነበረው ድርሻ በቃላት ሊገለጥ ከሚችለው በላይ ነው፡፡

    እዚህ ዕድሜ ላይ መድረስ የቻልኩት ራሴን መጥቀም የማልችል ደካማ መሆኔን በማወቅ የእግዚአብሔርን ጸጋ ዘወትር በጸሎት በመጠየቄ እና በዙፋኑ ሥር በመሸሸጌ ነው፡፡ ይህን ማድረጌ በእርግጥ አያስደንቅ ይሆናል! ምክንያቱም የአንድ አማኝ የሕይወቱ አንዱ አንጓ ስለሆነ፣ አንደ እኔ ላሉ ደካሞች ደግሞ ጸሎት የኃይል መቀበያ ሥፍራ ነው፡፡ ያለ እርሱ እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ!! እግዚአብሔር   ይህን መጽሐፍ ለእርሱ ክብር እንዲጠቀምበት እጸልያለሁ፡፡ በቀጣይ የጸሎት ሠራዊት በመሆን በምድራችን ለተነሡ እና ወደፊትም ለሚነሡ አገልጋዮች  በእውነት እግዚአብሔር በጥልቀት እንዲያስተምራቸው፤ በአገልግሎታቸው እና በሕይወታቸውም ድልን እንዲያስጨብጣቸው እጸልያለሁ፡፡

    የጸሎት ሕይወት ለአማኝ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ረጅሙን የዕድሜዬን ክፍል ያሳለፍኩበት የክርስትና ሕይወቴ የሰጠኝ ታላቅ ሐብት ቢኖር መጸለይ ነው፡፡ ጸሎት ከአባቴ ጋር ስደሰት፣ ሳዝን፣ ምሪትን ስፈልግ በሕይወቴ የእርሱን ጣልቃ ገብነት ስሻ፣ ሕልውናው ሲናፍቀኝ፣ ጠረኑን ማሽተት ስፈልግ ሁልጊዜ የማከናውነው ተግባሬ ነው፡፡ መጸለይ እወዳለሁ፣ ጌታዬ ይናፍቀኛልና!! ጌታ እስኪመጣ ወይም እኔ ወደ ጌታ እስክሄድ ድረስ መጸለይን እቀጥላለሁ፡፡

    አገልግሎት ከጀመርኩ በኋላ አንድ የተማርኩት ታላቅ ቁም ነገር ቢኖር፥ በአገልግሎት ሕይወቴ ስኬታማ ለመሆን በጸሎት መደገፍ እንዳለብኝ ነው፡፡ የአገልግሎት፣ የኑሮ፣ የትዳር፣ የሥራ፣ የልህቀት፣ የስኬት ቁልፍ እና መሠረቱ ውጤታማ ጸሎት ነው፡፡

    የጸሎት ሕይወታችን ዓላማ መሆን ያለበት ውጤታማነት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ እንዴት መጸለይ እና ውጤት ማግኘት እንዳለብን ያስተማረን ሕያው መምህራችን ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከሕዝቡ ተለይቶ ለብቻው በመሆን ብዙ ሰዓታትን በጸሎት ያሳልፍ ነበር፡፡ ከአባቱ ጋር በጸሎት ኅብረትን ያደርግ ነበር፡፡ ለአገልግሎቱም በጸሎት ሁልጊዜ ራሱን ያዘጋጅ ነበር፡፡

    ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረው አገልግሎቱ ውጤታማ ነበረ፤ እኛም ውጤታማ በመሆን የተሰጠንን የተልዕኮ ግብ  ማከናወን እንችል ዘንድ የእርሱን የጸሎት መርህ እንከተል፡፡ ለዚህ ደግሞ እውነተኛ የሆነ የጸሎት ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ያስፈልገናል፡፡ እያንዳንዷ ቀናችን በእግዚአብሔር ፊት የመጀመሪያ ቀን አድርገን በጸሎት መጀመር አለብን፡፡

    እግዚአብሔር እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ለሕዝቡ ጸልዩ በማለት ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ቀላል እውነት ዓይናችንን እንድንከፍት ይፈልጋል፡፡ ጸሎት በመንፈሳዊው ግዛት የነገሮች መጀመሪያ እና መደምደሚያ ነው፡፡ ጸሎት የቤተ ክርስቲያን የሥነ ባህርይ ደምብ ነው፡፡

    በምድር ላይ የተነሡ ታላላቅ አገልጋዮች እንዲሁም ታላላቅ መንፈሳዊ መነቃቃቶችን ብንመለከት፥ ላመጡት ታላቅ መንፈሳዊ ተፅዕኖ የጸሎት ድርሻ የትየለሌ ነው፡፡

    በምድራችን የእግዚአብሔር ክብር በሙላት እንዲገለጥ፣ ብዙዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲፈልሱ፣ ታላላቅ የተአምራት አገልግሎቶች በድንቅ እና በምልክት ታጅበው ቤተ ክርስቲያን እንድትደምቅ ልብዎ እየተቃጠለ ነውን? ይህ ናፍቆት ካልዎት አንዱና ብቸኛው መንገድ ጠንካራ የጸሎት ሕይወት ነው፡፡ እግዚአብሔር በየዘመኑ ጒበኞችን ይፈልጋል፡፡

    ይህ ትውልድ የመጨረሻው ዘመን ትውልድ አካል ነው፡፡ የጌታ ዳግም ምፅዓት መቼ እንደሆነ የሚያውቅ ማንም የለም፡፡ ሆኖም፥ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የጌታን ዳግም ምፅዓት አስመልክቶ የምፅዓቱን ዘመናት እና ወራት እንደምናውቅ ይናገራል (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥1-6) ፡፡ ጌታ ምናልባትም ዛሬ ሊመጣ ይችላል፡፡ እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው ነገር እኛ የመጨረሻው ዘመን የመጨረሻው ትውልድ መሆናችንን ነው፡፡

    የመጨረሻው ዘመን ትውልድ አካል እንደመሆናችን መጠን፥ የመሢሑን ዳግም ምፅዓት መንገድ የመጥረግ ኃላፊነት አለብን፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ግለሰብ እና እንደ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት እንድትመጣ የመጸለይ ኃላፊነት ይጠበቅብናል፡፡ በመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ ከተራሮች ራስ በላይ ጸንታ የምታቆመው ይህን የሚያስፈጽሙ የጸሎት ሠራዊቶች በምድር ላይ ሲገለጡ ነው፡፡ አለበለዚያ ቤተ ክርስቲያን ከምድራዊ ተራሮች በላይ ከፍ ማለት ያዳግታታል፡፡ አሕዛብም ወደ መሢሑ እንዳይሰበሰቡ እንቅፋት ይፈጥርባቸዋል፡፡ መሢሑ እንዲመጣ ማራናታ በማለት መጸለይ የግድ ይላል፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት እንድትመጣ ምልጃን ማድረግ አለብን፡፡ ኢየሱስ የሚከብርበት ዘመን ቅርብ ነው፡፡ ስለዚህ፥ ከግል ፍላጎቶቻችን እንውጣና በጸሎት መሠዊያችን ላይ ምልጃን በማቅረብ መማለድ አለብን፡፡ ጥቂትም ቢሆን የምንጸልየው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምጽዓት እንጸልይ፤ መሢሑ ይናፍቀን፡፡

    መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው፥ የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምፅዓት የሚመለከተውን ትውልድ አስመልክቶ የሚናገሩ ብዙ ትንቢታዊ መረጃዎች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ክብሩን በዚህ ትውልድ ላይ ያፈስሰዋል፡፡ ፍርዱንም በማይጠበቅ መንገዱ በዚያን ጊዜ ያፈስሰዋል፡፡ ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያን በዓለማዊ ምኞት የተያዘች ብትሆንም፥ ጌታ ኢየሱስ በኃይል ይቀናላታል፡፡ ወደ ድልም ሊመራት ይፈልጋል፡፡ ጌታም ቤተ ክርስቲያንን ለዳግም ምፅዓት እንድትዘጋጅ ሊለውጣት ይፈልጋል፡፡

    መንፈስ ቅዱስም ሙሽራውን ለመቀበል ዝግጁ በሚሆንበት በዚያን ዘመን፥ የሚመጣ ክብር እና ተቃውሞ ይኖራል፡፡ ስለዚህ፥ እግዚአብሔር በጸሎት ሥርዓት የታነጸች ቤተ ክርስቲያን ለዳግም ምፅዓቱ ትውልዱን የምታዘጋጅ እና የምታነሣሣ ትሆን ዘንድ ይፈልጋል፡፡ መደበኛ የጸሎት ሕይወት መደበኛ የክርስትና ሕይወት አካል ነው፡፡

    እንግዲህ የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ ቅዱሳንን ለመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር መንግሥት መገለጥ በማስታጠቅ የድርሻቸውን ማበርከት የሚችሉ የጸሎት ሠራዊት እንዲነሡ የመቀስቀስ ዓላማን ማዕከል ያደረገ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ የእግዚአብሔርን ሙላት እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡

    ስለ ጸሎት መጽሐፍን ለመጻፍ የተነሣሣሁበት ዋነኛው ምክንያቴ፥ በምድራችን ባሉ አብያተ ክርስቲያ ዘንድ ጸሎትን አስመልክቶ ያሉ የተዛቡ አመለካከቶችን ለማስተካከል እሳቤን ማዕከል ያደረገ ነው፡፡ በረጅሙ ዘመን የአገልግሎት ተሞክሮዬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጠንካራ የጸሎት አገልጋዮችን የማስነሣት ፋይዳውን በጉልህ ተረድቻለው፡፡ በምድራችን ላይ ጠንካራ የጸሎት ሠራዊትን ለማስነሣት ከቤተ ክርስቲያን ጠንካራ የጸሎት አገልጋዮች መወለድ አለባቸው፡፡ ያን ጊዜ በምድራችን የእግዚአብሔርን የልብ ሐሳብ የሚረዱ፣ ልዩነት የሚፈጥሩ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንድትገለጥ የሚማልዱ አገልጋዮችን ማስነሣት ቀላል ይሆናል፡፡ መጽሐፉም እንዲህ ዓይነት የጸሎት ሠራዊትን ለመቀስቀስ ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

    በምድራችን በብዙ አማኞች ላይ የሚታይ አንድ ትልቅ ሐብት አለ፡፡ ይህም ሐብት የእግዚአብሔርን ፊት አጥብቆ የመፈለግ ናፍቆት ነው፡፡ ብዙ የጸሎት ጉባዔዎች በአብዛኛው የሚካሄዱት የትንቢት አገልግሎትን ከግል ሕይወት አንፃር ለመስማት ካለ ትልቅ ናፍቆት አኳያ ነው፡፡ ነገር ግን፥ ይህን መንፈሳዊ ሐብት አግባብ ባለው መልኩ ቅርፅ ማስያዝ የሚቻል ከሆነ፥ እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን ለሚገልጠው ታላቅ የክብር አገልግሎት ግብዓት ማድረግ ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ባለራእይ የጸሎት አገልጋዮች ያስፈልጉናል፡፡

    ብዙዎች ወደ እግዚአብሔር ኀልዎት በጥልቀት የመግባት ረሃቡ ቢኖራቸውም፥ ከየት እንደሚጀመር እና ምን እንደሚደረግ ዕውቀቱ የላቸውም፡፡ ለዚህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ ያስፈልጋል፡፡ በጸሎት ለማደግ፥ የጸሎት ሕይወት ልምምድ አስፈላጊ ነው፡፡

    ቅዱሳን በሚጸልዩበት ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማወቅ፥ የሰይጣንን ተግዳሮት ማሸነፍ፥ እና የጸሎት እንቅፋቶችን አውቀው መፍትሔን ማስቀመጥ ይፈልጋሉ፡፡

    መንደርደሪያ

    የጸሎት ያለህ!! በሚል ርዕስ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ የጸሎትን ምንነት፣ ዓላማ እና አስፈላጊነት ታሪካዊ ሂደትን ማዕከል አድርጎ ይዳስሳል፡፡ ከነባራዊ የጸሎት ሕይወት በመነሣትም አማኞችን ስለ ጸሎት ያላቸውን ግንዛቤ ይሞግታል፡፡

    ይህ መጽሐፍ ለቤተ ክርስቲያን እና ለቅዱሳን እጅግ አስፈላጊ ርዕሰ ነገሮችን በመያዝ ስለ ጸሎት በጥልቀት ይዳስሳል፡፡ የጸሎትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትን በጥልቀት ይቆፍራል፡፡ እንዲሁም ከጥንት እስከ ዛሬ ተግባራዊ ትግበራውን፣ ታሪካዊ ሂደትን ማዕከል በማድረግ በትውልድ መካከል የነበረውን ፋይዳ ያጠናል፡፡ ምላሽንም በጥልቀት ለመስጠት ይሞክራል፡፡ የእኔም ዓላማ የጸሎት ሕይወት ማበልጸጊያውን መንገዶች ለአንባቢዎች ማመልከት ሲሆን፣ በተግባራዊ የሕይወት ምልልስ ደግሞ መተግበር የአማኙ ግዴታ ነው፡፡ የግልም ምስክርነትንም አልፎ አልፎ ለአንባቢዎች ጥቅም ጸሐፊው ያጋራል፡፡

    መጽሐፉ በውስጡ አራት ክፍሎች ይዟል፡፡ አራቱ ክፍሎች ደግሞ አስራ ዘጠኝ ምዕራፎችን የያዙ ሲሆን፥ ከመጀመሪያው ምዕራፍ እስከ መጨረሻው ምዕራፍ ድረስ ጸሎትን አስመልክቶው እርስ በርስ እየተሰናሰኑ፣ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ይሸጋገራሉ፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ለአንባቢው ከመነሻው እስከ መጨረሻው ድረስ አንድ ወጥ መልእክትን ያስተላልፋሉ፡፡ በእያንዳንዱ ክፍል መግቢያ ላይ ደግሞ በውስጣቸው ስለሚያነሷቸው ሐሳቦች በቅድሚያ የመግቢያ ሐሳቦችን ያመለክታሉ፡፡

    ይህን መጽሐፍ በምታነቡበት ወቅት እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ትማሩ ዘንድ ጌታ በመንፈሱ እንዲያስተምራችሁ እጸልያለሁ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተዘረዘሩትን እውነታዎች በሕይወታችሁ እውን እንዲሆኑ፣ ወደ ተትረፈረፈ ሕይወት እንዲያደርሷችሁ እመኛለሁ፡፡

    ብዙ ሰው ስለ ጸሎት ያውቃል፡፡ እንዴት መጸለይ እንደሚገባ ግን ብዙ ሰው አያውቅም፡፡ የብዙ ሰው ሕይወት በጸሎት መርህ አልተቃኘም፡፡ እኔ ለብዙ አያሌ ዓመታት ጸልያለሁ፡፡ በጸሎቴ እምብዛም ውጤታማ አልነበርኩም፡፡ ምክንያቱም መርሆዎቹ ላይ ጥልቅ እውቀት በወቅቱ አልነበረኝም፡፡ ነገር ግን እንዴት መጸለይ እንዳለብኝ ከእግዚአብሔር ቃል ከተማርኩ በኃላ በጸሎቶቼ ውጤታማ መሆን ችያለሁ፡፡ ዛሬ በጸሎት ሕይወቴ ላይ ትልቅ ለውጥ አለ፡፡ አሁን እንደ እግዚአብሔር ቃል ስለምጸልይ ውጤትን ከጸሎቶቼ አገኛለሁ፡፡

    በመጨረሻም ይህ መጽሐፍ በምድራችን ለሚገኙ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ስለ ጸሎት መጠነኛ እውቀትን እንደሚያስጨብጥ፥ ከዚህ በፊት በጸሎት ዙሪያ ከተጻፉ መጽሐፎች ጋር ተቀናጅቶ ቢነበብ ጥሩ ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል የግል እምነቴ ነው፡፡

    ይህን መጽሐፍ በምጽፍበት ጊዜ ብዙ መጽሐፎች በአገር ውስጥ እና በውጪ በሚገኙ ጸሐፊያን የተጻፉትን ለማንበብ እና ለማጥናት ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ አንዳንዶቹንም ለግብዓት ተጠቅሜባቸዋለሁ፡፡ ለተጠቀምኩባቸው ዋቢ መጽሐፍት እውቅና በመጨረሻው ገጽ ላይ አስቀምጫለሁ፡፡ ምክንያቱም ረጅም ዘመን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1