Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች
ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች
ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች
Ebook255 pages1 hour

ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች

Rating: 2 out of 5 stars

2/5

()

Read preview

About this ebook

ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ሊያጠፉህ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ትተውህ በሚሄዱበት ጊዜ ባንተ ላይ የሚመጣብህ መቆዘም፣ ግራ መጋባትና ጭንቀት በቃላት ሊገለፅ አይችልም፡፡ ይህ መጽሐፍ ሰዎች ትተውህ ሲሄዱ ሊያስከትል የሚችለውን ጥፋት እንድትቋቋም የሚረዳህ ነው፡፡ አትሳሳት፡፡ለብቻህ ስትተውና ስትጣል ባንተ አገልግሎት ላይ ብቻ የደረሰ እንዳይመስልህ፡፡ ብዙዎች ይህንን ዓይነት መከራ ተካፍለዋል፡፡ ሰይጣን የመጀመሪያው ዓመፀኛ ነበር ከውድቀቱ ቀን ጀምሮ ብዙ ሰዎች ዓመፀኞች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህን መጽሐፍ በእጅህ ውስጥ በማድረግ ትተውህ በሚሄዱ ሰዎች የሚነሳውን ታማኝ ያለመሆንን መንፈስ ተነስተህ እንድትዋጋው ያደርግሃል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954607
ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች

Related ebooks

Reviews for ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች

Rating: 2 out of 5 stars
2/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች - Dag Heward-Mills

    ትርጉም፡- ደረጀ በቀለ

    አርትዖት፡- ብስራት ተክሌ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    Email Dag Heward-Mills:

    evangelist@daghewardmills.org

    Find out more about Dag Heward-Mills at:

    www. daghewardmills.org

    www. lighthousechapel.org

    www.healingjesuscrusade.org

    Write to:

    Dag Heward-Mills

    P.o.Box 114

    Korle-Bu

    Accra

    Ghana

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    ስልክ +25192063819

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህንን መፅሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከተለ ነው፡፡

    Table of Contents

    1. ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ እግዚአብሔር ለምን ይፈቅዳል?

    2. በዓመጽ ትተው በሚሄዱ ውስጥ የሚሰራው አጋንንት

    3. ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ድምጽ አልባ መልዕክት

    4. ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ክስ

    5. ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች በመጥፎ ምሳሌነት እንዴት እንደሚገልጹህ

    6. ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች ያለመረጋጋትን ዘር እንዴት እንደሚዘሩ

    7. የመረጋጋት ዘር

    8. ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች አሳዛኝ ፍጻሜ

    9. ትተውህ የሚሄዱትን እንዴት ለይተህ እንደምታውቅ

    10. ተኩላዎቹን እንዴት እንደምትዋጋቸው

    11. ልጆቻችንን ነጥቀው የወጡ ከእኛ የሚጠብቁት ምላሽ

    12. ትተውህ በሚሄዱበት ጊዜ ችግርን ለሚፈጥሩብህ እንዴት እንደምትጸልይ

    ምዕራፍ 1

    ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ እግዚአብሔር  ለምን ይፈቅዳል?

    ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ እግዚአብሔር የሚፈቅድባቸው አስራ አምስት ምክንያቶች፤

    ጌታ ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ ከዚህ ሲከፋም እንዲጎዱህ የሚፈቅድባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡

    1.         ጌታ ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ የሚፈቅደው ምናልባትም በአገልግሎትህ ውስጥ ያለውን የመሠረት ችግር ለማረም ሊሆን ይችላል፡፡

    በአገልግሎት መጀመሪያ ላይ፣ አብዛኛውን ጊዜ በውድቀት ስጋት  እንሞላለን፡፡ ይህ የውድቀት ስጋት ደግሞ ወደ እኛ የተዘረጋልንን የእርዳታ እጅ ሁሉ አፈፍ አድርገን እንድንይዝ ያደርገናል፡፡  እርዳታን ለመፈለግ በሚያደርጉት ሂደት ውስጥ፣ በርካታ አገልጋዮች ትክክለኛ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ራሳቸውን ያቆራኛሉ፡፡

    ለዚህ አብራሃም መልካም ምሳሌ ነው፡፡ ራሱን ከቤተሰቦቹ ነጥሎ ስፍራው በውል ወደማይታወቅ የተስፋ ምድር ረዥምና መንፈሳዊ አላማ ያለው ጉዞ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ተናገረው፡፡ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር እንደተናገረው ራሱን ከቤተሰቦቹ ከመለየት ይልቅ፣ አብርሃም ከተወሰኑ የቤተሰቡ አባላት ጋር አብሮ ወጣ፤ከነዚህም መካከል ሎጥ በስም ተጠቅሶ ይገኛል፡፡

    እግዚአብሔርም አብራምን አለው፡-ከአገርህ፣ከዘመዶችህም፣ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ ፡፡

    ዘፍጥረት 12፡1

    አብራምም ከግብፅ ምድር ወጣ፣እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ፡፡

    ዘፍጥረት 13፡1

    አብርሃም በጉዞው ወቅት ያጋጠሙት ችግሮች ሁሉ ምክንያታቸው ሲፈተሸ ፤ ሎጥ በእርሱ ህይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባቱ ምክንያት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ሎጥ በህይወቱ ውስጥ ጣልቃ በመግባቱ ምክንያት አብርሃም ያጋጠሙትን ችግሮች አስተውል፡፡

    1.         አብርሃም በሎጥ ምክንያት የከረረ ውዝግብና ግራ የመጋባት ችግር ገጥሞታል፡፡ በመጨረሻውም በሎጥ ምክንያት ከዘመዶቹ ተለያይቷል፡፡ (ዘፍጥረት 13፤7-8)

    2.         አብርሃም በሎጥ ምክንያት ፈጽሞ መዋጋት ወደ ማይግባው ጦርነት ውስጥ ገብቷል፡፡ አብርሃም በጦርነት ሎጥን ኮሎደጎምር ምርኮኝነት ነፃ አውጥቶታል (ዘፍጥረት 14፤1-16)

    3.         አብርሃም በተለይ በሎጥ ምክንያት ምልጃን አድርጓል፡፡አብርሃም በሰዶምና በጎሞራ ላይ ሊወርድ ካለው ጥፋት የወንድሙን ልጅ ማዳን ነበረበት፡፡ (ዘፍጥረት18፤23-33)                      

    እኔ በአገልግሎት ውስጥ መሠረታዊ ስህተት ነው ብዬ የምጠራው ይህንን ነው፡፡ በአግልግሎትህ መጀመሪያ ላይ የምትሠራው ትልቁ ስህተት  ይህ ሲሆን፤አብዛኛውን ጊዜ ከፍርሃት የተነሳ የሚመጣ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ስህተት ትክክለኛ ያልሆነ ሰው በምትሠራው ሥራ ሁሉ ላይ እንደ ቀንበር ተጣብቆ እንቅፋት ይሆንብሃል፡፡

    አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ወደ አግልግሎት በሚገቡበት ወቅት ትክክለኛ ካልሆነው ሰው ጋር እንኳን በጋብቻ ሊተሳሰሩ ይችላሉ፡፡ ያንን ትክክለኛ ያልሆነ ሰው እግዚአብሔር ከምድር ላይ በማንሳት በአንገትህ ላይ ከታሰረው ቀንበር ነፃ ሊያደርግህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ሰው ከህይወትህ ካላስወገደው ግን  ባገልግሎትህ ዘመን ሁሉ ቀንበሩን በጫንቃህ ላይ ተሸክመህ  ለመጓዝ ትገደዳለህ፡፡

    ገና በአገልግሎትቴ መጀመሪያ ላይ የአገልግሎቴ አካል የነበሩ አንዳንድ ሰዎች አሁን እያካሄድኩ ባለሁት ነገር ውስጥ ተሳታፊዋች አይደሉም፡፡  ምናልባትም፤ ከእነዚህ ሰዎች አንዳንዶቹን አብረውኝ እንዲሠሩ ተቀብያቸው የነበረው ያለእነሱ አገልግሎት ስኬት አይኖረኝም የሚል ስጋት ስለነበረኝ ይሆናል፡፡ የእነርሱ ከአጠገቤ መኖር ለስኬቴ አስተማማኝ ዋስትና እንደሆነ እቆጥር ነበር፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ አንዳንዶቹ ትተውኝ እንዲሄዱ አደረገ፡፡አንዳንዶቹ ትተውኝ ሲሄዱ በእርግጥ ጉዳቱ የተሳማኝ ቢሆንም፤እግዚአብሔር እንዲሄዱ ያደረገበት ምክንያት፤ ገና ከመጀመሪያው ቤተክርስቲያንን ለመመስረት በነበረኝ አዲስ ራእይ  ውስጥ እነርሱን ማካተቴ ስህተት በመሆኑ ምክንያት  እንደሆነ ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡

    1.         ጌታ፤ ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ የሚፍቅደው አንተን                      ትሁት ለማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡

    አምላክህ እግዚአብሔር ትእዛዙን መጠበቅህንና በልብህ ያለውን ለማወቅ ትሁት ሊያደርግህና ሊፈትንህ በእነዚህ አርባ ዓመታት በዚህ ምድረ በዳ ጉዞህ ሁሉ እንዴት እንደመራህ አስታውስ

    ዘዳግም 8፤2 (አ.መ.ት)

    ሰዎች እርግፍ አድርገው ትተውህ ሲሄዱ፣ ሲለዩህና በድርጅትህ ውስጥ ከነበራቸው ስፍራ ራሳቸውን ሲያገሉ የሚፈጠረው ነገር ወደ ትህትና የሚያመጣ ልምምድ ነው፡፡ እያንዳንዱ መለያየት በአፍህ ውስጥ ጎምዛዛ ጣዕም ትቶ የሚያልፍም ነው፡፡ በድንገትና ባልተጠበቀ ሁኔታ የሚለይህ አንዳንድ ሰው ምን ጊዜም የማይመለሱ ጥያቄዋችን አሻራ ከበስተኋላው ትቶ ያልፋል፡፡ ትተው በሚሄዱ ሰዎች ምክንያት የሚከሰተው ግራ መጋባትና አለመረጋጋትን እና እውነተኛ  ትህትና የሚፈጥር ነው፡፡

    አብያተክርስቲያናትን በመመስረት ባሳለፍኳቸው በርካታ ዓመታት   ውስጥ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማኝ መጋቢዎች፤  ወንዶችና ሴቶች ልዶች ተባርኬያለሁ፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ የስጋ ዘመዶቼ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጋቢ መሆን በመቻላቸው ተባርኬያለሁ፡፡

    ይሁን እንጂ፤ አንድ ቀን አንዳንዶቹ ዘመዶቼ በአገልግሎት ውስጥ እርግፍ አርገው ተውኝ፤ ከዚያም አልፈው እኔ ሳስተምረው ከቆየሁት ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ድርጊት ፈጸሙ፡፡ የራሴ ቤተስብ አባላት በቤተክርስቲያን ውስጥ በዓመጽና ታማኝነትን በማድጉደል የሰዎች ትኩረት ማረፊያ ሆነው ማየት ለእኔ ሃፍረት ነበር፡፡ በመሆኑም ከራሴ ቤተሰቦች ጋር ለመፋለም ተገደድኩ፡፡ በበርካታ ሰዎች ውስጥ ታማኝነትን ማሥረፅ  የቻልኩባቸው ሁኔታዋች በተዳጋጋሚ አጋጥመውኛል፤ ነገር ግን በራሴ ቤተሰቦች ይህን ማድረግ  አልቻልኩም ፡፡

    በዚህ ሂደት ውስጥ እግዚአብሔር ትሁት እያደርገኝ አንደሆነ ተሰማኝ፡፡ በኃይል ወይም በጉልበት ወይም በአስተምህሮ ወይም በመርሆች ሣይሆን በእርሱ ፀጋ ብቻ እንደሆነ ሊያሳየኝ ፈልጎ ነበር፡፡ ምናልባትም፤ አንዳንድ ሰዎች ጥለውህ ሄደው ይሆናል፡፡  እግዚአብሔር ለአገልግሎቱ ቀና ትሆንለት ዘንድ ትሁት የማድረግን መንፈሳዊ ሥራ በአንተ ህይወት እንዲሰራ ፍቀድለት፡፡

    2.         ስለ ታማኝነትና ታመኝ አለመሆን ባለማስተማርህ ምክንያት ፤አባላትህ ግንዛቤ የሌላቸው እንዲሆኑ በመፍቀደህ ጌታ ሰዎች ትተውህ  እንዲሄዱ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

    የተጠሩትም ሁለት መቶ ሰዎች ከአቤሰሎም ጋር በየዋህነት ሄዱ ፤የሚሆነውንም ነገር ከቶ አያውቁም ነበር

    2ኛ ሳሙኤል 15፡11

    ሰይጣን በሰዎች ውስጥ አለማስተዋል እየጨመረ እንዲሄድ  ያበረታታል፡፡ ሁልጊዜም ሰዎች መሳታቸው እየጨመረ የሚሄደው  የቃሉን እውነት ባለማወቃቸው ምክንያት ነው፡፡ አቢሰሎም ወደ ስህተት መምራት የቻለው በልባቸው የዋህነት የተከተሉትን ሁለት መቶ ሰዎች ብቻ ነበር፡፡ ይህ የዋህነት እኛ በተጨማሪ አለማስተዋል ብለን የምንጠራው ነው፡፡

    የታማኝነትና ታመኝ አለመሆን እንዲሁም የአባትነት እና የማስተዋል መርሆች ብዙ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ  አይሰብኩም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባላት፣ አለማስተዋላቸው እየጨመረ እንድሄድ በሚያደርጉ አሳች አጋንንትቶች ጉዳይ ዙርያ አያስደንቅም፡፡ ምናልባትም አንተም በዚህ ጉዳይ ላይ በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ አለማስተዋል እንዲስፋፋ ፈቅደህ ሊሆን  ይችላል፡፡ ሰይጣን በዚህ አለማስተዋል ሊጠቀምበትና በመካከልህ መጠነ ሰፊ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

    አዎ፣ ምናልባትም ቤተክርስቲያንህ በብልጽግና፤ በጋብቻና በፈውስ መልዕክቶች ተባርካ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከእነዚህ ርዕስ ጉዳዮች ማናቸውም መንጋውን ታመኝ ካለመሆንና ከአሳች አጋንንቶች ጥቃት በበቂ ሁኔታ ለመከላከል አይችሉም፡፡

    አንድ ቀን፤ አንድ መጋቢ ስለታማኝነትና ታመኝ አለመሆን ብቻ ለምን እንደማስተምር ጠየቀኝ፡፡ ፌዝ በተሞላበት ሁኔታም፤ ታማኝነት የምታስተምረው ነገር ሳይሆን፤ ልታዘው የምትችል ነገር ነው› አለ፡፡

    እንዲህ በማለትም ንግግሩን ቀጠለ፤ ‹መልካም በሆነ ባህሪህ በአካባቢህ ያሉ ሰዎች ወዲያውኑ ታማኝ እንዲሆኑልህ ታደርጋለህ

    ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የራሱ ከሆኑ የቅርብ የአገልግሎት አጋሮቹ መራራ የሆነ ክህደት ተፈጸመበት፡፡  በራሱ ላይ የደረሰውን ነገር ሊያምነው አልቻለም፡፡ ይህ ነገር ከደረሰበት በኋላ፤ በእኔ ትህምርቶችና መጽሐፍት ላይ የነበረው ንቀት ወደ አድናቆት ተለወጠ፡፡ እርሱ እራሱም ለታማኝነት ርዕሰ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥና የእኔንም መጽሐፍት የሚያስተዋውቅ ሆነ፡፡ ምናልባትም አለማስተዋል የሚያስከትለው ጥፋት እስካላጋጠመህ ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ስለሚሰጥ ትምህርት ጠቃሚነት ላታውቅ ትችል ይሆናል፡፡

    …በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም

    ምሳሌ 17፡5

    3.         ጓደኛህ የሆነ መጋቢ ቤተክርስቲያኑ የመከፋፋል ችግር ባጋጠማት ጊዜ፤ ንቀትን በማሳየትህ ምክንያት፤ ጌታ ሰዎች ትተውህ እንዳሄዱ ሊፈቀድ ይችላል፡፡

    …በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም

    ምሳሌ 17፤5

    ብዙ ጊዜ፣ ሰዎች ወደ ችግር ውስጥ ሲገቡ  በንቀት እናፊዛለን፡፡ ልክ እንደ እዮብ ወዳጆች፤ በሰዎች ላይ የደረሰውን ሁሉ መጥፎ ነገር ምክንያቱ ምን እንደሆነ የምናውቅ ይመስለናል፡፡  በችግር ውስጥ የገቡ ሰዎችን በንቀት እንመለከታለን፤ ምክንያቱም ችግሩን ያመጡት እራሳቸው እነደሆኑ ስለምናስብ ነው፡፡ እንዲህ ያለው አመለካከት ሰይጣን ወደ ህይወታችንና ወደ አገልግሎታችን እንዲገባ በር ሊከፍትለት ይችላል፡፡

    አንድ ቀን፤ በአገልግሎቷ ከፍተኛ ስኬት ላይ የደረሰች ቤተክርስቲያን ሦስት መጋቢዋችን አገኘሁ፡፡ ወሳኝ የሆነው የአገልግሎቱ ቡድን አንድ ዋነኛ መጋቢ እና ሁለት ጠንካራ ረዳት መጋቢዋችን ያቀፈ ነበር፡፡ በሁለቱ ረዳቶቹ አጋዥነት መጋቢው በከተማዋ ውስጥ ትልቅ ከሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት ጋር የተስተካከለች ቤተክርስቲያን ለመመስረት ችሎ ነበር፡፡ ሰው ሁሉ ወደ እነርሱ የሚጎርፍ  ነበር የሚመስለው፡፡ አዲሷ ቤተክርስቲያናቸው ሞልታ ነበር የምትታየው፤ አዳራሹ ሞልቶ ሰዎች በውጭ የሚቀመጡበት በቀን ብዙ አገልሎት ነበራቸው፡፡ በዚህ ወቅታዊ ስኬታቸው ሀሴት ውሰጥ ሆነው፤ ከከተማው ውጭ የምትገኘው እህት ቤተክርስትያን ለምን እንዳላደገች ንድፈ ሃሳቦችን በማመንጨት መነጋገር ጀመሩ ፡፡

    ፌዝና ንቀት በተሞላበት ሁኔታም፤ ሰዎች ቤተክርስትያንን ትተው የሚሄዱት ጥሩ ያልሆነ መሪ ምክንያት ነው፡፡ ሰዎች የእርሱን አገልግሎት እየለቀቁ ወደ እኛ የመጡት ትክክለኛ ባልሆነ አመራር ምክንያት ነው፡፡ አሉ፡፡

    በዚያ ጊዜ፤ ሰዎች ያችኛዋን ቤተ ክርስቲያን እየለቀቁ ወደዚችኛዋ ቤተክርስቲያ እንደሚፈልሱ እንኳን አላውቅም ነበር፡፡ ሌላኛዋ ቤተ ክርስቲያን መጥፎ መሪ እንዳላትም የሰማሁት ለመጀመሪያ ጊዜ  ነበር፡፡ መሪዎቹ ስለዚያች ቤተ ክርስቲያንና ስለ መጥፎው መሪ በሚነጋገሩበት ወቅት ንቀታቸው እና ፌዛቸውን ከሁኔታው ለመረዳት አስቸጋሪ አልነበረም፡፡

    አዎ፤ ሰዎች አገልግሎትን ለቀው የሄዱበት ምክንያት ምናልባትም ትክክለኛ ባልሆነ አመራር ምክንያት ሊሆን እነደሚችል ጥርጥር የለኝም፡፡ ነገር ግን፣ አንተ በምትሰጠው ፍርድና በጉዳዩ ላይ በምትደርስበት ድምዳሜ ላይ ጥንቃቄ ልታደርግ ግድ ነው፡፡

    ከጥቂት ዓመታት በኋላ፤ እነዚህ ሦስት መጋቢዎች በአገልግሎታቸው ሌላኛው ገጽታ ውስጥ ማለፍ ጀመሩ፡፡ እያንዳንዱ አዲስ ገጽታ በኃይል ሚዛን ላይ ለውጥ ማስተካከሉ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ በአዲሱ ገጽታ፤ ሁለቱ ረዳት መጋቢዎች የዘለፋ ውርጅብኝና ክስ እየሰነዘሩ ዋናውን መጋቢ ትተውት ሄዱ፡፡ ልክ ሌላኛውን መጋቢ ባንቓሸሹበት ሁኔታ በራሳቸው ላይ ደረሰ፤ ይሁን እንጂ ከቀድሞው ይልቅ ይህኛው እጅግ በከፋ ሁኔታ ነበር፡፡

    ስለተፈጠረው ትልቅ ቀውስ በሰማሁበት ጊዜ፤ መጀመሪያ ወደ ልቤ የመጣው ነገር፤ ስለዚያች እህት ቤተ ክርስቲያንና ስለመጋቢዋ የተናገሩት ነገር ነበር፡፡ …ሰዎች ትትውህ የሚሄዱት መጥፎ መሪ ስትሆን ብቻ ነው፡፡  እስኪ አሁን ዋናው መጋቢያቸው መጥፎ መሪ ነበርን? የግድ እንደዚያ መሆን የለበትም፡፡  ሰዎች አንተን ትተው የሚሄዱበት በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ችግር በገጠመው ጊዜ አንተ በምንም አይነት ሁኔታ እንደማታፌዝ እርግጠኛ ሁን፡፡

    በእኔ አገር ውስጥ፤ እንዲህ ካለው ሁኔታ ጋር የሚዛመድ ምሳሌያዊ አነጋገር አለ የጓደኘኛህ ጺም ሲቃጠል በተመለከትክ ጊዜ በእርሱ ላይ አትሳቅ፡፡ ጺሙ በእሳት እስኪቃጠል ድረስ ምን ይጠብቅ እንደነበረም አትጠይቅ፡፡ ዝም ብለህ ሂድና ውኃ ቀድተህ በአጠገብህ አስቀምጥ፤ ምናልባትም የአንተ ጺም በእሳት ሊያያዝ ተራ እየጠበቀ ሊሆን ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሎ ያስቀምጠዋል …በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም ፡፡ (ምሳሌ 17፤5)

    4.         የአንተ መድረሻ አንዳንዶችን የማያካትት በመሆኑ፤ ጌታ ሰዎች ትተውህ እንዲሄዱ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

    ልጆች ሆይ፣ መጨረሻው ሰዓት ነው የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነስተዋል፤ስለዚህ መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን፡፡

    ከእኛ ዘንድ ወጡ፣ዳሩ ግን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1