Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው
እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው
እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው
Ebook170 pages2 hours

እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

ኢየሱስ ሲናገር፡- እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። በእውነትም እባቦች ልባሞች ናቸውን? ኢየሱስ ለምንድን እንደዚህ ያለ ምክር ሰጠ? ግልጥ አድርጎ የሚያስረዳውን የዳግ ሂዋርድ ሚልስን መጽሐፍ ያዝና ድብቅ የሆኑትን የእባብ ብልሀቶች ተማ

Languageአማርኛ
Release dateNov 8, 2018
ISBN9781641357548
እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው

Related ebooks

Reviews for እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው

Rating: 4.833333333333333 out of 5 stars
5/5

6 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው - Dag Heward-Mills

    ምዕራፍ 1

    የእባቦች ጥበብ

    ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።

    ማቴዎስ 1016

    እባቦች ጥበበኞች ናቸው

    ሰዎች እባቦችን መፍራታቸው የሚደነቅ ነገር አይደለም።  ሰዎች ለእባቦች የሚገባውን አክብሮት መስጠታቸውም አይገርምም። እባቦች በሰዎች ሁሉ ዘንድ የተጠሉ ቢሆንም ሁሉን ተቋቁመው የሚኖሩ አስደናቂ ፍጡራን ናቸው።

    ኢየሱስ ስለ እባቦች ጥበብ ባይናገር ኖሮ የእነርሱን ጥበብ ላናስተውለው እንችል ነበር። ኢየሱስ ስለ እባቦች ጥበብ በመናገሩ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን ከእነዚህ ፍጥረታት ልንማር የምንችለውን መማር ይኖርብናል። ጥያቄው እንግዲህ የእባቦች ጥበበ ምንድነው? እባብን ጥበበኛ ያሰኘው ምንድነው?

    ከባልደረቦችህ ሁሉ በላይ እንድታብብ ሊያደርግህ የሚችለውን ጥበብ ለመቀበል አትፈልግምን?

    በብርቱ ጥላቻ እና ተቃውሞ መካከል ስኬታማ ሊያደርግህ የሚችለውን ጥበብ ለማግኘት አትፈልግምን?

    በተለዋዋጭ የሕይወት ገፅታዎች መካከል እንድታብብ ሊያደርግህ የሚችለውን ጥበብ ለማግኘት አትፈልግም? ተለዋዋጭ በሆኑት የሕይወት ወቅቶች ሁሉ ሀብትን እና ስኬትን ይዘው መቀጠል የቻሉስ ስንቶች ናቸው?

    ሰዎች እንዲፈሩህ እና በአግባቡ እንዲያከብሩህ ሊያደርግ የሚችለውን ጥበብ አትፈልገውምን? የሕይወትህ ግቦችህን በፀጥታ ልታስብበት የምትችለውን ጥበብ የራስህ ለማድረግ አትፈልግም?

    እርግጠኛ ነኝ እንዲህ ዓይነቱን ጥበብ ትፈልገዋለህ። ይህም የእባብ ጥበብ ነው! ኢየሱስም እንደ እባብ ጥበበኛ ሁኑ ያለው ለዚህ ነው።

    እባቦች ጥበበኛ ያሰኛቸው ሰባት ምክንያቶች

    1. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም ከየትኛውም የዱር አራዊት ይበልጥ መባዛተቸው እና መስፋፋታቸው ነው።

    2. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም በዘመናዊነት ጐዳና በምትገሰግሰው ዓለም ውስጥ ሕልውናቸውን አስጠብቀው መኖራቸው ነው። በዚህ በዘመናዊው ዓለም ብዙ የዱር እንስሶት እየጠፉ መሆናቸውን ልብ ትላለህ።

    3. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም  በእያንዳንዱ የተጠሉ ቢሆንም እንኳን ሕልውናቸውን መራባታቸውን መቀጠል ችለዋል።

    4. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም ሰዎች የሚፈሯቸው እና የሚያከብሯቸው መሆኑ። ሰዎች ብዙ እንስሳቶችን አይፈሩም ነገር ግን እባቦችን ይፈራሉም ያከብራሉም።

    5. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም በሁሉም አህጉርና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መሆናቸው ነው።

    6. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም በሁሉም ሥፍራ  በመሬት፣ በባሕር፣ በንፁህ ውሃ እና በአየር ላይ እንኳን መንቀሳቀስ መቻላቸው ነው።

    7. እባቦች ብልህ(ጥበበኛ) እንደሆኑ ይታወቃል ምክንያቱም በዚህ ዓለም ግባቸውን ለማሳካት ችሎታ ስላላቸው ነው። እጅግ ፈታኝ ተግዳሮቶች ቢጋረጥባቸውም ለመኖር ለመመገብ እና ለመባዛት ይችላሉ።

    ጠቢብ ለመሆን እርግጠኛ ስለሆኑ ነገሮች፣ እውነቶች እና አባባሎች ማሰብ ማሰላሰል ማውጣት ማውረድ ይኖርብሃል። ጥልቅ ትርጉም ያላቸውን አባባሎች ገረፍ አድርገህ ልታልፋቸው አይገባም።  ኢየሱስ እንደ እባብ ጠቢብ ሁኑ ሲል በጥበብ የተሞላ፣ በትርጉም ያለው እና ምሪት ያለበት ጠለቅ ያለ ምሳሌያዊ አነጋገር ነበር። ይህ መጽሐፍ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ እባብ ከሌሎች የዱር አራዊት የሚጠበቁበት ቦታ ውስጥ ካሉ የዱር እንስሳት ሁሉ ይበልጥ ስኬታማ ያደረገውን ጥበብ የያዘ ነው።

    በቤትህ ዙሪያ የሚዞሩ አንበሶች እንደሌሉ አስተውለሃልን? እባቦች ግን በምትኖርበት ቦታ ሊኖሩ ይችላሉ። በትንሹ፣ እኔ በኖርኩባቸው ቤቶች በሙሉ እባቦች አይቻለሁ። አንበሶች በአንተ ሰፈር በቀላሉ አይገኙምን። በእባብ ጥበብ ስለማይመላለሱ ከአካባቢያችሁ ተባረዋል። እነርሱ የሚመላለሱት(የሚሰሩት) በሌላ ዓይነት ጥበብ ነው፣ የአንበሳ ጥበብ።

    የአንበሳ ጥበብ አንበሳን እንድንፈራ እንድናከብር ያደርገናል። የአንበሳ ጥበብ ግን አንበሶችን በዓለም ዙሪያ በከተሞች እንዲስፋፉ እና ውጤታማ ሆነው እንዲባዙ አላደረጋቸውም። የአንበሶች ቁጥር እያሽቆለቆለ ነው! አንበሶች እየመነመኑ መጥተዋል!  እባቦች ግን በተቃራኒው በሚደንቅ ሁኔታ በእያንዳንዱ ከተማ እና ሰፈር ውስጥ ይገኛሉ። እባቦች ተቃውሞን ድል ነስተው ስለ በዙ እና ስለተሳካላቸው አንበሶች ደግሞ ቁጥራቸው እየመነመነ ወደ መጥፋቱ ስለተቃረቡ እባቦች ከአንበሶች ይልቅ ጥበበኞች ያደርጋቸዋል።

    ምዕራፍ 2

    ጥገኛ ያለመሆን ጠበብቶች

    እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።

    1ኛ ተሰሎንቄ 411

    እባቦች ጥበበኞች ናቸው ምክንያቱም በሌሎች አይደገፉም

    አንድ መሪ ከውጪ ያሉ ሰዎች እንዲያከብሩት በማንም ላይ መደገፍ አይኖርበትም። አንድ አገልጋይ በየትኛውም መልኩ ማንንም እንዳይለምን ተግቶ መስራት ይኖርበታል። ልመና በፕሬዝዳንቶች በፖለቲከኛዎችም ሆነ በመጋቢዎች ቢፈፀም ያው ልመና ነው! ልመና እንደ ኢንቬስተሮችን መፈለግእርዳታ ፍለጋ ወይም የአጋር ኮንፈረንሶችን መሳተፍ የሚሉ የተከሸኑ ስሞች ቢወጣለትም ያ ልመና ነው። በሌሎች ከመደገፍ ይልቅ ሌላው አማራጭ በራስ ሥራ ላይ ማተኮር እና በገዛ እጅ መስራት ነው።

    ለምንድነው እየዞርክ የምትለምነው? ስጡኝ የምትለው? ዳዊት ...ፃድቅ ሲጣል ዘሩም እህል ሲለምን አይቼ አላውቅም (መዝሙር 37፣25) ያለውን አላነበብክምን? ይህ ሰው ይህንን በሰጠኝ እያልክ ተስፋ እያደረክ መኖር አያሳፍርህም? ከእምነት ውጪ ያሉ ሰዎች ሁሌ ከእነርሱ ስትፈልግ የሚያከብሩህ ይመስልሃል? አያከብሩህም! ይህን ቃል አንብብና አሰላስለው።…በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ 4፡11

    እባቦች በሌሎች ላይ ባልተደገፈ ህይወት የተካኑ መሆናቸውን ያሳያሉ። ከልደት ቀናቸው ጀምሮ ራሳቸውን ይችላሉ። እንደ እባብ ጠቢብ ለመሆን ራስን መቻል  ወይም በሌሎች ላይ ያልተደገፈ መሆንን ይጠይቃል። የድሀ አገር ፕሬዝዳንቶች በሀብታም አገሮች እየዞሩ ስጦታ እና እርዳታ ሲጠይቁ ማየት አሳዛኝ ነው።

    የሚያሳዝነው በቅኝ ግዛት ሥር ከነበሩት አገሮች ብዙዎች ያለ ቅኝ ገዢዎቻቸው በእግራቸው መቆም አልቻሉም። ነፃ ለመሆን ብቃት የላቸውም ብዙ ደሀ አገሮች ራሳቸውን ለማስተዳደር ተስኗቸዋል! ለነፃነት ታግለዋል ነፃ ግን አይደሉም። በየዓመቱ የነፃነት ቀን ያከብራሉ፤ እንደ እውነቱ ግን ዛሬም ጥገኛ በመሆናቸው ሊያዝኑ በተገባቸው ነበር!

    ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ብቃት የሌላቸው መሪዎች አገራትን ወደ ከፋ ድህነት ቁልቁል አውርደዋል። መሪዎች በሁለት ከተሞች መካከል መንገድ መስራት ሲያቅታቸው የኤሌትሪክ ኃይል፣ ውሃ፣ ትምህርት ቤቶችን ሆስፒታሎችን ማቅረብ ሲሳናቸው የአመራር ብቃት እንደሌላቸው በግልፅ ይታያል። የአንዳንድ ድሀ ሀገራት መሪዎች አመራር ማለት እየዞሩ ገንዘብ መለመን ይመስላቸዋል።

    እባቦች ግን ውልደታቸው ቀን ጀምሮ ያለ ወላጆች እርዳታ እራሳቸውን ችለው መኖር ይችላሉ። ብዙ እባቦች ከልደት ቀናቸው ጀምሮ መግደል ይችላሉ፤ ብዙውን ጊዜም ከልደት ቀናቸው ጀምሮ የሚኖሩት ብቻቸውን ነው። በሕይወት ለመሰንበት ከሌሎች ሀገራት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እንደ አንዳንድ አገሮች ሳይሆን እባቦች ያለ አንዳች እርዳታ በራሳቸው ስኬታማ መሆን ይችላሉ።

    ራስህን ለመቻል ብቃት እንዳለህ ስለማሳየት

    1. እንደ እባብ ጠቢብ ከሆንክ ከሌሎች ገንዘብ፣ ስጦታ፣ ብድር እንኳን አትጠብቅም።

    አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን

    የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።

    ዘፍጥረት 1422-23

    አብርሃም ማንም ሰው እንዲያበለጥገው አይፈልግም ነበር። ማንም አብርምን አበለጠግሁት ብሎ እንዲያስብ አይፈልግም ነበር።

    ሁልጊዜም አባባ እና እማማ አንዳች ነገር ሰጥተዋቸው መፍትሄ እንዲያደርጉላቸው የሚፈልጉ ሕፃናት ናቸው። አንድ ሰው ራሱን ችሎ መኖር ሲሳነው ሰዎች አንዳች ነገር እንዲሰጡት ይጠብቃል። ብዙዎች አንዳች ነገር ለመቀበል ፊታቸውን ወደ አሜሪካን እና ኢንግላድ ያዞራሉ። አሜሪካኖች እና አውሮፓውያን ሊረዱህ እንደሚመጡ ማሰብህ እራሱ ራስህን ችለህ መኖር እንደተሳነህ ያመለክታል።

    ማንም የውጪ ሰው ሀብታም ያደርገኛል ብለህ ማሰብ የለብህም። አንድ ሰው አንዳች ነገር እንዲሰጥህ ለምን ትፈልጋለህ? ሁልጊዜ ስጦታ ብድር እንዲሰጥህ ለምን ተስፋ ታደርጋለህ? ብቃት የሌላቸው መሪዎች ሥራ ለመስራት ብድር መፈለጋቸው አሳፋሪ ነው። ብዙ ጊዜ ብድር አያስፈልግም የሚያስፈልገው ብክነትን ሙስናን እና ደካማ የሆነውን የንብረት አስተዳደር ማስወገድ ብቻ ነው። እነዚህ ደካማ መሪዎች ብድር ስለመፈለግ እያወሩ ብዙሐኑን ያስታሉ። በሙስና ከጭሱ ባሻገር ማየት የሚችሉ ግን ብድር መጠየቅ እንደማያስፈልግ ይረዳሉ።

    በውጪ እርዳታ ጥገኛ ያልሆነ ሕይወት ሊኖርህ ያስፈልጋል። የለየላቸው ደካማ መሪዎች ስለ እርዳታ በሚወራበት የእርዳታ ኮንፈረንስ ላይ መሳተፍ ያስደስታቸዋል። የሚገርመው እነዚህ መሪዎች የአመራር ክህሎት እንጥፍጣፌው እንኳን ስለሌላቸው እነዚህ ኮንፈረንሶች ላይ ተቀምጠው ያንቀላፋሉ።

    2. እንደ እባብ ጠቢብ ከሆንክ የራስህ ሕይወት ኃላፊ ትሆናለህ፣ ማንም ነገሮችህን እንዲሰራልህ አትጠብቅም

    ጥበብህ እንድትነሳ እና ለራስህ እንድትሰራ ያደርግሃል። ነገሮችን የገነባ ሰው ጠቢብ የሚባለው ለዚህ ነው። መገንባት አለመቻል ጥበብ እንዳሌለህ የሚያሳይ ነው። እንደ እባብ ጠቢብ ከሆንክ የምትፈልገውን ነገር ተነስተህ ትገነባለህ። ሰለሞን ለራሱ ብዙ ነገሮችን ገነባ ቤቶችን ገነባ፣ የወይን እርሻዎችን ተከለ፣ የአትክልት ሥፍራዎችን እና የጣፋጭ ፍራፍሬ የእርሻ ቦታዎች አዘጋጀ እና የተለያዩ ዛፎችን ተከለ።

    ትልቅ ሥራን ሠራሁ፥ ቤቶችንም አደረግሁ፥ ወይንም ተከልሁ፤

    አትክልትንና ገነትን አደረግሁ፥ ልዩ ልዩ ፍሬ ያለባቸውንም ዛፎች ተከልሁባቸው፤

    በዱር የተተከሉትን ዛፎች አጠጣበት ዘንድ የውኃ ማጠራቀሚያ አደረግሁ።

    መክብብ 24-6

    ቤተክርስቲያንን የሚመራ መጋቢ ሌላ ሰው መጥቶ ሕንፃ ይገነባልኛል ብሎ ካሰበ በሳል ራሱን የቻለ መሪ እንዳልሆነ ያሳያል። ያለህን ጥቂት ነገር ይዘህ ባለህ ነገር ለመኖር ዕቅድ የማታወጣ ከሆነ ራስህን ችለህ በአግባቡ ልትኖር አትችልም።

    3. እንደ እባብ ጠቢብ ከሆንክ ስጦታ፣ ብድር አትጠይቅም፣ አትለምንም።

    ስጦታ መጠየቅ የለብህም፣ ገንዘብም መለመን የለብህም። እንደ እባብ ጠቢብ ከሆንክ ከጅምሩም ብቻህን እንደሆንክ ታውቃለህ። እያንዳንዱ እባብ ይህንን ያውቃል። ብድግ ብለህ ተግዳሮቶችህን መጋፈጥ አለብህ። ሌሎችም እንዲሁ ዓይነት ተግዳሮቶችን ተጋፍጠው እንዳሸነፉ ማወቅ አለብህ። ሀገራት ስጦታ እና እርዳታ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1