Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ
መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ
መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ
Ebook96 pages36 minutes

መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

የመጽሐፉ አረስት ህጻን ሆነህ በደስታ የምትዘምረውን መዝሙር ያስታውስሃል.. .
መጽሐፍ ቅዱስህን በየቀኑ ታነባለህ? በየቀኑ ትጸልያለህ?
ይህ ምጽሐፍ ድንቅ እና ብቸኛ ለሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አይኖችህን ይከፍትልሃል። እንዲሁም በየቀንይ መጽሐፍ ቅዱሰን ስታነብና በየቀኑ ስትጸልይ በየቀኑ ወደ አንተ ተአምራቶች እንዲመጡ ይከፍትልሃል። የየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ እና የየቀኑ ጸሎትህ ያስደስትህ!

Languageአማርኛ
Release dateNov 8, 2018
ISBN9781641357524
መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ

Related ebooks

Reviews for መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

2 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ - Dag Heward-Mills

    ምዕራፍ 1

    መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ፡ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው?

    መጽሐፍ ቅዱስ በጽሑፍ የሰፈረ የእግዚአብሔር ቃል ነው።በዘመናት ሁሉ መካከል ከመጽሐፍት ሁሉ በላይ ታላቅ በሆነው መጽሐፍ ላይ ያለህን እምነት አሳድግ!

    ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

    2ኛ ጴጥሮስ 1፡20፣21

    1. መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢታዊ መገለጥ ነው።

    የእግዚአብሔርን ማንነት ለሰው ይገልጣል። የሰው ልጅን አመጣጥ ያብራራል። ሰውም ለምን በምድር ላይ አንደሚኖር ትርጉሙን ይሰጣል። የፍጥረትን ሁሉ የወደፊት ፍፃሜም ይገልጣል። ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔር መሃሪነትና እኛን ከመርገም ለማንፃት ያለውን ዕቅድ ይገልፃል።

    ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።

    2ኛ ጴጥሮስ 1፡20፣21

    ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤

    ዕብራውያን 1፡1፣2

    2. መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች የድነት ወንጌል አብሳሪ ነው።

    ወንጌል የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ኃይል የሚገልጥልን የምሥራች ቃል ነው። ሰው እንዴት መዳን እንደሚችል የሚያሳይ ብቸኛ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ለሚያምኑ በሙሉ የዘላለሙን ድነት እና በወንጌል ለማያምኑ የዘላለሙን ፍርድ መልዕክት የያዘ ነው።

    በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።

    ሮሜ 1፡16

    3. መጽሐፍ ቅዱስ ለእኛ የእግዚአብሔር ማስጠንቀቂያ  ነው።

    መጽሐፍ ቅዱስ የአስተሳሰቦች ወይም የንድፈ ሀሳቦች ውይይት አይደለም። ተጨባጭ እውነቶችን በሥልጣን የሚያውጅ ነው። በውስጡ የተብራሩ እውነቶች አስደናቂ እና ድርድር ውስጥ የማይገቡ ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ያለ የክብር መንፈስ የሚመነጨው ካለው ሥልጣንና የማይቀለበስ እውነት ነው።

    ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል። በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ አጸኑት፥ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት።

    ዕብራውያን 2፡ 1-4  

    4. መጽሐፍ ቅዱስ በመለኮታዊ ኃይል መገለጥ የተሞላ ነው።

    መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጽሐፍቶች ልዩ የሚያደርገው ይህ  ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በእግዚአብሔር እንደ ተነሳሱ እና እንደ ተነዱ ይናገራል። በሌላ አባባል፣ ፍጡር የሆኑና ሟች የሆኑ ሰዎችን ጣት በመጠቀም እግዚአብሔር ጽፎታል።

    ቅዱሳን መጽሐፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤

    2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

    5. መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር በቀጥታ የተላከ ነገሮችን የሚለይ መልዕክት ነው።

    ቀላል የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ  እውነቶች ለሰዎች ሲነገሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይለወጣሉ። እኔ የተለወጥኩት ቃሉ ሲተላለፍ በመስማቴ ነው።

    የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤

    ዕብራውያን 4፡12

    6. መጽሐፍ ቅዱስ  ለብልፅግናችን የሚሆን የእግዚአብሔር ጥበብ ነው።

    እግዚአብሔር ለብልፅግና ያዘጋጀው መንገድ የዳበሩ አስተሳሰቦችና የሰው ልጆችን ብልጠት አይደለም። በእርሱ ቃል ውስጥ ነው።

    የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።

    ኢያሱ 1፡8

    ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።

    ምሳሌ 4፡20-22

    7. መጽሐፍ ቅዱስ የመሬት፤ የጸሐይ፤ የጨረቃ፤ የክዋክብቶች እና የፕላኔቶች የፍጥረት መጀመሪያ የሚያብራራ ነው።

    በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።

    ዘፍጥረት 1፡1-2

    8. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ፤ ስለ ሰማይ፤ ስለ ገሃነም እና ስለ ዘላለማዊ ህይወት እውነታ ይሰጠናል።

    ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።

    ሞትና ሲኦልም በእሳት

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1