Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መንፈሳዊ አደጋዎች
መንፈሳዊ አደጋዎች
መንፈሳዊ አደጋዎች
Ebook121 pages50 minutes

መንፈሳዊ አደጋዎች

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ክርስቲያን በብዙ አደጋዎች፣ እንቅፋቶችና ወጥመዶች መካከል ነው የሚመላለሰው፡፡ ይህ መጽሐፍ በእኛ ላይ ክፋት ለማድረግ፣ ለመጉዳትና ለማጥፋት አድፍጠው የሚጠባበቁትን በርካታ ስልታዊ አደጋዎችን እንድታይ ዓይኖችህን ይከፍታል። መንፈሳዊ አደጋዎችን በሚመለከት በተጻፈው በዚህ ኃይለኛ መጽሐፍ አማካኝነት ራስህን እርዳ፣ ራስህን አድን ደግሞም ራስህን ነፃ አውጣ!

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954447
መንፈሳዊ አደጋዎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to መንፈሳዊ አደጋዎች

Related ebooks

Reviews for መንፈሳዊ አደጋዎች

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መንፈሳዊ አደጋዎች - Dag Heward-Mills

    ምዕራፍ 1

    አንዳንድ ነገሮች በቅድሚያ ሊደረጉ የሚገባበት ምክንያት

    ትክክለኛ ያልሆኑ ነገሮችን  ቅድሚ መስጠት ለክርስቲያኖች ትልቅ አደጋ ነገሮችናቸው፡፡ ኃጢያተኛ ስትሆን በዋናነት ከሁለት ነገሮቸ ነው የምትመርጠው፡-መልካም እና ክፉ፡፡ በጌታ እያደግህ ስትሄድ አማራጮችህ ይጨምሩናየምታማርጣቸው ብዙ ነገሮች ይኖሩሃል፡፡

    በዚህ ጊዜ ምርጫዎችህ በመልካምና በክፉ መካከል ሳይሆኑ በመልካምናበመልካም መካከል ነው፡፡ መደረግ የሚገባውን ነገር በተመለከተ በአብዛኛውየምታማርጣቸው በርካታ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ እዚያ ነጥብ ላይ ስትደርስየቅድሚያዎችን ጽንሰ ሀሳብ መረዳትህ ጠቃሚ ነው፡- አስቀድሜ የትኛውንላድርግ? ኢየሱስ ከሌሎች አስቀድመው ሊደረጉ ስለሚገቡ አንዳንድ ነገሮችታላቅ መገለጥ ሰጥቶናል፡፡

    ኢየሱስ ምን ያህል ነገሮችን ቀድመው መደረግ አለባቸው እንዳለ ማጥናቱየሚያስደንቅ ነገር ነው፡፡ ኢየሱስ ስለመጀመሪያው ወይም ስለተቀዳሚው ጉዳይሲያወራ ፕሮቶን የሚለውን የግሪክ ቃል ነው የሚጠቀመው፡፡ በዚህ መጽሐፍውስጥ ስለ ፕሮቶን ጉዳዮች እንመለከታለን፣ ኢየሱስ መጀመሪያ መደረግአለባቸው ስላላቸው ነገሮች ማለት ነው፡፡

    እንደክርስቲያን የመጀመሪያ ነገሮችን መጀመሪያ ማድረግ አለብህ፡፡ የመጀመሪያበቅደም ተከተል፣ በቁጥር፣ በደረጃ እና በዋጋ የመጀመሪያ ነው፡፡

    ክርስቲያን እጅግ ወሳኝ የሆኑትን ነገሮች መጀመሪያ ማድረግ   አለበት፡፡

    አንዳንድ ነገሮች መጀመሪያ ሊደረጉ የተገባበት ምክንያት

    መጀመሪያየማይደረግማንኛውምነገርጠቀሜታውንየሚያጣይመስላል፡፡

    እግዚአብሔር እኛን እጅግ ይታገሰናል፡፡ በርካቶች አልታዘዙትም፤ ይህምያዋጣቸውም ይመስላል፡፡ ባለመታዘዝ ስንገፋበት የእግዚአብሔር ቃል ጠቀሜታየደበዘዘ ይመስላል፡፡ ወዲያውኑ ከሌላ ከምንም ነገር ይልቅ ጠቃሚ የሆነው ነገርየተናቀና እርባና ቢስ ይሆናል፡፡

    ዛሬ በቅባት አገለግላለሁ፤ በርካቶችም በአገልግሎቱ ምክንያት ያከብሩኛል፡፡ ነገርግን እግዚአብሔርን ያኔ ባልታዘዝ ኖሮ ሙሉ ሕይወቴን በሐኪምነት ተራ ሆኜእጨርሰው ነበር፡፡ ስለ እግዚአብሔር ጥሪ የሚደረጉ ውይይቶች ጥቅም አልባ እናተገቢ ያልሆኑ ይመስሉ ነበር፡፡

    በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ ካሉ የሕክምናው ዘርፍ ባልደረቦች ጋር ተቀምጦመጋቢ ስለመሆን ማሰብ አሳፋሪ ይሆን ነበር፡፡ ለጓደኞቼ እንዲህ ነበር የምላቸውአንድ ጊዜ ስለነበረኝ የሞኝ ሀሳብ ልንገራችሁማ፡፡ አንድ ጊዜ መጋቢ መሆን ፈልጌእንደነበር ታውቃላችሁ? ወጣት ሳለን አጉል መንሳውያንና ሁኔታዎችንየማናገናዝብ ነበርን፡፡

    መጀመሪያ ለክህነት ተሰልፈን ነበር የሚሉ አዋቂ ሰዎች ገጥመውህ አያውቁም? በሽምግልናቸው የእነርሱን አለመታዘዝ በልጆቻቸው በኩል ለማካካስ ይፈልጋሉ፡፡

    ከልጆቹ አንዱን ለክህነት እዲሆን ሊያስገድደው የሞከረን አንደ ሰው አውቃለሁ፡፡

    ልጁን አንዲህ አለው እግዚአብሔር ካህን እንድሆን ቢጠራኝምአላደረግሁትም፡፡ አንተ ካህኑ ሁንና ምንም እንዳይጎድልህ እኔ ንብረትና ገንዘብእሰጥሃለሁ፡፡ በህይወታቸው መጨረሻ ላይ እግዚአብሔርን ያለመታዘዝና ከእርሱጋር ያለመተባበር ህይወታቸውን ማካካስ ይፈልጋሉ፡፡

    ወዳጄ ሆይ በገዛ መንገድህ ርቀህ በተጓዝህ ቁጥር የእግዚአብሔር ትዕዛዛትየበለጠ የራቁና ሊሰሩ የማይችሉ እየመሰሉ ይሄዳሉ፡፡ ፕሮቶን የተባለበት ምክንያትአለ፡፡

    ፕሮቶን፤ ወይም የመጀመሪያውን ነገር መጀመሪያ ማድረግ ከመታለል ያድንሃል፡፡ፈቃዱን ስትከተል እግዚአብሔር ይጠነቀቅልሃል ከአንተም ጋር ይሆናል፡፡

    2. መጀመሪያ የማይደረግ ማኛውም ነገር ጭራሹኑ ላይደረግ ይችላል፡፡

    መዘግየት በአብዛኛው መሰረዝ ማለት ነው፡፡ መጀመሪያ የማይደረግ ማንኛውምነገር ጭራሽ ላይደረግ ይችላል፡፡ አንድን ነገር ማዘግየት ነገሩን ወደ መሰረዝበእርግጥ ሊያደርስ እንደሚችል አላውቅም    ነበር፡፡

    ከለንደን ወደ ኒው ዮርክ ለማገልገል ጉዞ ማድረግ የነበረብኝ አንድ ቀን ነበር፡፡በዚያ ምሽት ሜሪላንድ ውስጥ ለማገልገል ቀጠሮ  ነበረኝ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታከለንደኑ ሂትሮው አየር ማረፊያ ወደ አምስተርዳም ሄጄ ከዚያም ወደኒው ዮርክልሄድበት የነበረው በረራ እጅግ በጊዜ ነበር፡፡ ብቻ በደረሰኜ ላይ ያየሁትን የበረራሰዓት አላመንኩም፡፡ እውነት እስከማይመስለኝ ድረስ አጅግ ከጊዜ በፊት እንደሆነ    አሰብኩ፡፡

    አየር ማረፊያው ስደርስ፣ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ማረፊያው ለመግባትምሆነ አውሮፕላኑን ለመሳፈር እጅግ ዘግይቼ ነበር፡፡ ወደ ማረፊያው ከመግቢያውሰዓት ወደ ሃያ ደቂቃ ገደማ ዘግይቼ ነበር፡፡ አዘንኩ፡፡ ወደ አምስተርዳምየሚሄደውን ቀጣዩን በረራ መጠበቅ ነበረብኝ!

    ወጀመሪያ ቀጥለህ ወደ ኒው ዮርክ ሊወስድህ የነበረውን በረራ ባትደርስበትምከእርሱ በኋላ ያለውን ማግኘት ትችላለህ፤ አሉኝ። ከጊዜው አንጻር አሁንም ኒውዮርክ ደርሼ ልክ በሰዓቱ ወደ ሜሪ ላንድ በመኪና መጓዝ እንደምችል አስተዋልኩ፡፡ስለዚህ ወደ ኒው ዮርክ ደውዬ ለመጋቢው መቼ እንደምደርስና ወደ ሜሪ ላንድበፍጥነት መንዳት እንደሚኖርብን ነገርኩት፡፡ ጥሩ ሰዓት ላይ እንደሆንንና ጥቂትመዘግየት ቢከሰትም ፕሮግራሙ እንደሚሳካ አረጋገጥኩለት፡፡

    አምስተርዳም ስደርስ ወደ ኒው ዮርክ የሚያደርሰኝን አውሮፕላን ቶሎእንደሚነሳና መንገዴን እንደምጀምር በማወቅ በልበ ሙሉነት ተሳፈርኩ፡፡ከአፍታ ቆይታ በኋላ በመስኮት ወደ ውጭ ስመለከት ሰዎች የአውሮፕላኑንክንፎች ውሃ ሲረጩ ተመለከትኩ፡፡ ከዚያም ማስታወቂያው ተነገረ፡- በሞተሩ ላይእጅግ ብዙ በረዶ ስላለ መብረሩ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በረዶውን ለማስወገድአንድ ሰዓት ይፈጅብናል፡፡ እባካችሁ ታገሱን፡፡

    ሌላ ስሌት አሰላሁና አሁንም ሜሪላንድ ለፕሮግራሙ ልደርስ እንደምችልተሰማኝ፡፡ ሙሉ ቤተክርስቲያኑ እኔን ይጠብቀኛል፡፡ ለሳምንታት ሲጠብቁኝ ነበር፡፡የሚያሳዝነው ታዲያ፣ ላይሳካ ነው።

    የበረዶው ችግር ከተፈታ በኋላ ሌላ ተፈጠረ፤ ጭራሽ ሌላ የሚያዘገዩ ነገሮችተነገሩ፡፡ አሁን ደግሞ በአውሮፕላኑ ውስጥ ያሉ መጸዳጃ ቤቶች ስለማይሰሩእነርሱን መሥራት እንዳለባቸው  ተናገሩ፡፡ የአውሮፕላን ሽንት ቤቶች አይሰሩምተብሎ ሰምቼ ባላውቅም አሁን ግን እውን እየተከናወነ ነበር! በመጨረሻ ለበረራዝግጁ እስክንሆን ድረስ ሌላ ተጨማሪ ሁለት ሰዓታት ፈጀ፡፡

    ለፕሮግራሙ ምን ያህል ሰዎች እንደሚሰበሰቡ እያውጠነጠንኩ በጭንቀትተቀመጥኩ፡፡ በመጨረሻም በጊዜ ስለማልደርስ ፕሮግራሙ እደሚሰረዝ መቀበልነበረብኝ፡፡ ወንበሬ ላይ ተቀምጬ ሳለሁ የለንደኑ አምስት ደቂቃ መዘግየትመላው ፕሮግራሜን እንዴት እንደሰረዘብኝ አሰላሰልኩ፡፡ ያኔ ነበር እግዚአብሔርየተናገረኝ፡ "መዘግየት መሰረዝ ማለት ሊሆን እንደሚችል አየህ?"

    ቃሉን መታዘዝ ላይ መዘግየት ፈቃዱን ጭራሹኑ ወደ አለማድረግ ሊመራእንደሚችል ጌታ አሳየኝ! ጌታ ይህ ተሞክሮ እንዲኖረኝ የፈቀደው ፈቃዱንለማድረግ መዘግየት አንዳንድ ጊዜ ጭራሽ ወደ አለማድረግ ሊያመራ እንደሚችልእንድማር እንደሆነ አሳየኝ፡፡

    እግዚአብሔርን ለመታዘዝ የሚያስቡ ብዙዎች የተሳሳተውን ነገርስለሚያስቀድሙ መጨረሻቸው እስከነአካቴው እርሱን መታዘዝ አይሆንም፡፡ጋብቻቸው፣ ፒ ኤች ዲ ዎች፣ ኤም ቢ ኤ ዎች፣ እና የአምስት አመት የውጭ ሀገርጉዞአቸው ሁሉ ጌታን ከመታዘዝ ይቀድማሉ፡፡ ሁለተኛ ቦታ ላይ የሚያስቀምጡትእግዚአብሔርን መታዘዝ ተግባር ሆኖ አያውቅም፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ መሆን የሚገባቸው ሰዎች የሆኑ ነገሮችንእስኪያሳኩ ድረስ ለሌላ ጊዜ ሲያስተላልፉት በኃዘን ተመልክቻለሁ፡፡ የሚያሳዝነውግን መዘግየቱ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ የሚሆኑበትን እድል በቋሚነትዘጋው፡፡ ሰዎች የማያስተውሉት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሊፈጸም የሚችልእስከማይመስል ድረስ ከጊዜ ጋር ሁኔታዎች እጅግ እንደሚቀያየሩ ነው፡፡

    መዘግየት በአብዛኛው

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1