Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ትልቅ ቤተክርስቲያን
ትልቅ ቤተክርስቲያን
ትልቅ ቤተክርስቲያን
Ebook211 pages1 hour

ትልቅ ቤተክርስቲያን

Rating: 2 out of 5 stars

2/5

()

Read preview

About this ebook

"...ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤"ሉቃስ 14:23 የእግዚአብሔር የልብ ጩኸት ዓለም እንዲድንና ቤቱ (ቤተ ክርስቲያን) እንድትሞላ ነው! “ትልቅ ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ከጋና ትላልቅ ቤተ ክርስቲያኖች የአንዱ መጋቢ የሆኑት የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ የተወለደው ከዚህ መገለጥ ነው፡፡ ይህንን አነሳሽ መጽሐፍ ካነበብክ በኋላ ቤተ ክርስቲያንህ እና አገልግሎትህ ዳግም እንደነበር አይሆንም! “ዶክተር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌልን ለዓለም በማዳረስ ውስጥ ላለው ሥራ የተሰጡ ሰው ናቸው፡፡ ታላቅ መሪ እና በአገልግሎት ላሉ ሁሉ አርአያ ናቸው፡፡ እኛም “ቸርች ግሮውዝ

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954539
ትልቅ ቤተክርስቲያን
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ትልቅ ቤተክርስቲያን

Related ebooks

Reviews for ትልቅ ቤተክርስቲያን

Rating: 2 out of 5 stars
2/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ትልቅ ቤተክርስቲያን - Dag Heward-Mills

    ሜጋ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖርህ ግድ የሚሆንበት ሃያ አምስት ምክንያቶች

    1. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖርህ መሻት ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም ይህ ለአንድ መጋቢ እጅግ ተገቢ የሆነ ራእይ እና ግብ ነው። የመጋቢዎች ሁሉ ከሁሉ የተሻለ ራእይ እና በውስጣቸው ሊቀጣጠል የሚገባ መሻት ትልቅ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖራቸው ነው። ቤተ ክርስቲያን ካለቸው ላይቀር ለምን ትልቅ አይሆንም?

    ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው።

    ምሳሌ 29፡18

    2. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖርህ መሻት ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም ሜጋ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖርህ ያለህ መሻት፣ ቤተ ክርስቲያንህ እንድታድግ በሚያደርግ ጉዞ ላይ እንድትሆን ይመራሃል። ተአምራት እንዲኖር ያለህ መሻት በአገልግሎትህ ውስጥ የተአምራት መኖርን ውጤት ያስከትላል። ቅባት እንዲኖርህ ያለህ መሻት ቅባት እንዲኖርህ ያደርጋል። ለቤተ ክርስቲያን እድገት ያለህ መሻት ቤተ ክርስቲያንህ እንድታድግ የሚያደርጉ ነገሮች ምን እንደሆኑ ማግኘት ወደምትችልበት ጎዳና ያመራሃል።

    ስለዚህ እላችኋለሁ፣ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፣ ይሆንላችሁማል።

    ማርቆስ 11፡24

    3. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም ጌታ የሚገነባት ማንኛይቱም ቤተ ክርስቲያን ትንቢታዊ ፍጻሜ ከጅማሬው ይልቅ ፍጻሜዋ ታላቅ ይሆን ዘንድ ነው። ዛሬ ቤተ ክርስቲያንህ አነስተኛ በመሆኗ ተስፋ አትቁረጥ። የአገልግሎትህ ፍጻሜ እጅግ የላቀ ክብር ያለው እንደሚሆን የትንቢት ቃል አለህ።

    የእግዚአብሔር ቃል የኋለኛው ቤት ክብር ከፊተኛው ቤት ክብር ትልቅ እንደሚሆን ስለሚተነቢይ፣ በጅማሬው ላይ ካየኸው ይልቅ የከበረ ነገር ልትጠባበቅ ይገባል። እግዚአብሔር ታላቅን ነገር ያደርጋል፣ ጉባኤህንም ያሳድጋል።

    ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።

    ኢዮብ 8፡7

    4. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ መጋቢዎች ሥራው ገና ሳይሠራ እንደተሠራ አድርገው በማሰብ ተታለዋል።

    ኢየሱስ በአገልግሎት ዘመኑ በጣም ጠቃሚ የሆነ ዓረፍተ ነገር ተናግሯል።

    . . . መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤

    ማቴዎስ 9፡ 37

    ብዙ መጋቢዎች ትንሿ አዳራሻቸው በመሙላቷ ተታለዋል። ብዙ አገልጋዮች በአገልግሎታቸው የበቁ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ጥሩ ደመወዝ በማግኘትህ፣ የሚያምር መኪና በማሽከርከርህ እና ወጪዎችህ ሁሉ በመሸፈናቸው እግዚአብሔር ባርኮሃል። ይህ ማለት ግን የአገልግሎት ጫፍ ላይ ደረስህ ማለት አይደለም። ልንሠራ የተገባንን እውነተኛ ሥራ ማየት እንዳትችል ሰይጣን እንዲያሳውርህ አትፍቀድለት። ቤተ ክርስቲያን እንድትተኛ የሚያባብላት ሰይጣን ነው!! ለብዙ አገልጋዮች ልብ ሁሉ ነገር መልካም ነው!ይኼ ነው! ተችሎሃል!መድረስ የሚገባህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል! ለእግዚአብሔር መሥራት የምትችለው ይህን ያህል ነው! ሲል ሹክ ይላቸዋል። እንዲህ ያሉ አገልጋዮች መንፈሳዊ እና የራእይ ዓይናቸው በሰይጣን ታውሯል። ጠላት ለልባቸው እንዲህ ሲል ሹክ ይላል፡- ሁሉ ነገር መልካም ነው!ይኼ ነው! ተችሎሃል!

    ሰይጣን ቤተ ክርስቲያንህ ትንሽ ሆና እንድትቀር ይፈልጋል። የቤተ ክርስቲያንህ ሕዝብ ብዛት ጥቂት ነው ማለት በሰይጣን እስራት ስር ያሉ ሰዎች ብዛት በርካታ ነው ማለት ነው። የቤተ ክርስቲያንህ መጠን ምን ያህል ሲዖልን እንዳመናመንህ ያሳያል። ግዙፍ ቤተ ክርስቲያን አለህ ማለት፣ ብዙ ነፍሳትን እያፀናህ ነው ማለት ነው። ግዙፍ ቤተ ክርስቲያን አለህ ማለት ብዙ ነፍሳት ከሰይጣን መዳፍ አመለጡ ማለት ነው።

    5. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ቤቱ ይሞላ ዘንድ ነው። ቤተ ክርስቲያናት ያልሞሉት ሜጋ ቤተ ክርስያናት ባለመሆናቸው ነው።

    ጌታውም ባሪያውን፡- ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤

    ሉቃስ 14፡23

    በሉቃስ 14 ውስጥ ጌታ አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ መገለጥ ሰጥቶናል። ጌታው ባርያውን፣ ቤቴ እንዲሞላ እፈልጋለሁ አለው። በዚህ ታሪክ ውስጥ ያለው ጌታ የሚወክለው ጌታ ኢየሱስን ነው። ኢየሱስ ቤቱ እንዲሞላ ይፈልጋል። በሌላ አነጋገር፣ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያኑ እንድትሞላ ይፈልጋል። እግዚአብሔር በሰዎች የተሞሉ አብያተ ክርስቲያናትን ይፈልጋል! በዚህ ታሪክ ውስጥ ያለው ጌታ በግብዣው ላይ በተገኙ ጥቂት ሰዎች አልረካም። እንደ ሆነ ይሁን ብሎ፣ ግብዣውን በተገኙት ጥቂት ሰዎች ማካሄድ ይችል ነበር ግን አላደረገውም፣ ብዙ ሰዎች እንዲጨመሩ ፈለገ። በተለይ ደግሞ ቤቱ በሰዎች እንዲሞላ ፈለገ።

    በዚህ ታሪክ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ ያለውን ፈቃዱን እየገለጠ ነው። ፈቃዱ በቤቱ ውስጥ ብዙ ሰዎች እንዲኖሩ ነው! የእርሱ ፈቃድ በሰዎች የተሞሉ ክፍሎችን ማየት ነው! ፈቃዱ የተትረፈረ ቤተ ክርስቲያናት ማየት ነው! ቤተ ክርስቲያን ሜጋ ትሆን ዘንድ ፈቃዱ ነው!

    6. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም የመከር መስክህ ቤተ ክርስቲያን ነች።

    እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።

    ማርቆስ 16፡ 15፣16

    እግዚአብሔር ወደ ከተማችን ዳርቻዎች ብቻ አላከንም። ወይም ደግሞ ወደ ጥቂት ገጠሮች ብቻ አላከንም። የላከን ወደ ዓለም ሁሉ ነው። ያለን የእርሻ ቦታ ትንሽ ከሆነ ብዛት ያለው መከር ለመሰብሰብ አንጠብቅም።

    ዓለሙን ሁሉ በወንጌል መድረስ ይገባናል ማለት ወደ ጌታ ልናመጣቸው የሚገባን ነፍሳት ብዛት እጅግ ብዙ እንደሆነ ያሳየናል። ይህ ደግሞ አብዛኛውን የዓለም ሕዝብ ወደ ወደ ጌታ ማምጣት እንዳለብን ያስገነዝበናል። አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ደግሞ በወንጌል ስብከት ከዳነ፣ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በቦታ ጥበት መፈንዳት አለባቸው ማለት ነው። አስታውስ፣ ከስድስት ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ነፍሳት በወንጌል እንድንደርሳቸው እየጠበቁን ነው።

    7. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም ምሳሌ የሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ነበሯቸው። ልንከተል የሚገባን ምሳሌ የቀድሞዋን ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አይደለምን? የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ሦስት ሺህ እና አምስት ሺህ አባላት ከነበሯት፣ ለእኛስ እነኚህ ቁጥሮች እንደ መንደርደሪያ ሊሆኑን አይገባንም? በእርግጥ እነኚህ ቁጥሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙት የት ለመድረስ ማለም እንደሚገባን ለማሳየት ነው።

    ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፣ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።

    የሐዋርያት ሥራ 2፡ 41-42

    ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፣ የወንዶችም ቊጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ።

    የሐዋርያት ሥራ4፡ 4

    8. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም ትልቅ ቤተ ክርስቲያን አለህ ማለት ብዙ ነፍሳት ለእግዚአብሔር መንግሥት ተማርከዋል ማለት ነው። በትልቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ አገልግሎቶች ይኖራሉ፣ ብዙ የነፍሳት ጥሪ ይደረጋል፣ ከዚህም የተነሳ ከትንሽ ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለብዙ ሰዎች የመዳን እድል ይኖራል። ነፍሳትን ለጌታ መማረክ የእያንዳንዱ አገልጋይ ዓላማ አይደለም? ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ነፍሳት ድነው እንዲጨመሩ ማድረጓ ተጨማሪ በረከት አይደለም?

    9. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም በሜጋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሠራተኞች እና አገልጋዮች ወደ እግዚአብሔር ሥራ ይለቀቃሉ።

    . . . መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።

    ማቴዎስ 9፡37-38

    ሁልጊዜም ቢሆን ከመንጋው ውስጥ የተወሰኑ እውነተኛ ሠራተኞች ይኖራሉ። የትኛውንም ያህል ብትሠራ ወይም ብትናገር፣ ከመንጋው መካከል ፈጽሞ በእውነተኛ የአገልግሎት ሥራ ላይ ተሳታፊ የማይሆኑ አሉ። ሁልጊዜ ተመልካች እና ተችዎች ብቻ የሚሆኑ ሰዎች ይኖራሉ። ተችዎች እንዳሉ ሁሉ ሠራተኞችም ይኖራሉ። ብዙ ሕዝብ ሲኖርህ፣ ብዙ ሠራተኞች ይላካሉ፤ ለእነርሱም የሚያስፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ቀላል ይሆናል።

    10.. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም በሜጋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ የወንጌል አገልጋዮች፣ የሙሉ ጊዜ መጋቢዎች እና ኤጲስ ቆጶሶች ተሹመው መከሩ ወዳለበት መስክ ይለቀቃሉ። በትልቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልጋዮችን የሚያፈራ የሥልጠና መርሃ-ግብር ሁልጊዜ ይኖራል። አስር ሺህ አባላት ያሉበት ጉባኤ አንድ መቶ አባላት ብቻ ካሏት ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ብዙ መጋቢዎችን ያፈራል። በእርግጥ አነስተኛ ጉባኤ ያላት ቤተ ክርስቲያን መጋቢ የወንጌል አገልጋይ መሆን የሚፈልጉ በቂ ሰዎችን ማግኘት ይችላል ማለት የማይመስል ነገር ነው።

    11. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም በሜጋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰዎች በአየር ላይ ያለውን ገዥ ኃይል በመቃወም ይጸልያሉ።

    መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፣ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፣ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፣ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንን ራስ ቊር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤

    ኤፊሶን 6፡12-18

    ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሲኖርህ፣ ብዙ ጸሎት ወደ ጌታ ያርጋል፤ ስለዚህ ብዙ ሰዎች ይድናሉ ይጸናሉም። እግዚአብሔር በአውሮፓ ቤተ ክርስቲያናትን እንድመሰርት ሲልከኝ፣ በአህጉሪቱ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደገና ለመገንባት የምንጫወተውን አንድ ቁልፍ ሚና አሳየኝ። አየህ፣ አውሮፓ እግዚአብሔር ፈጽሞ የተካደባት አህጉር እየሆነች መጥታለች። እግዚአብሔርን ከአዕምሮአቸው አውጥተውታል። ብዙ አውሮፓውያን እግዚአብሔር እስከ መኖሩም አያምኑም።

    ከዓመታት በፊት፣ አውሮፓውያን ሚስዮናዊያንን ወደ ዓለም ሁሉ ይልኩ ነበር፤ አሁን ግን በከፍተኛ ሁኔታ በአጋንንት ታውረው ወደ አምላክ የለሽነት ወድቀዋል። እንደ ቤተ ክርስቲያን በአውሮፖ ከባቢ አየር ላይ ጸሎት መልቀቅ ከኃላፊነቶቻችን አንዱ እንደሆነ ጌታ አሳይቶኛል። እንደ ስዊዘርላንድ፣ ኔዘርላንድ እና እንግሊዝ ባሉ አገሮች ውስጥ የእኛ መገኘት በእነኚህ አገሮች ውስጥ ብዙ ምልጃ እንዲደረግ አድርጓል።

    በጄኔቫ በምትገኘው ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዘወትር አርብ ከእኩለ ሌሊት እስከ ማለዳ አስራ ሁለት ሰዓት አዳር ጸሎት ይካሄዳል። እግዚአብሔር በተረሳበት ምድር ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ጦርነት በማካሄድ ላይ ትገኛለች። እንደኛ ያሉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በየአገራቱ እየተስፋፉ በሄዱ መጠን ብዙ ጸሎት ይካሄዳል። ብዙ አጥቢያዎች ያሏት ትልቅ ቤተ ክርስቲያን መኖር አስፈላጊነት ምክንያቶች አንዱ ይህ ነው።

    እኔ የምመግባት ቤተ ክርስቲያን፣ ላይትሃውስ ካቴድራል፣ በተወሰነ መጠን ባደገች ጊዜ፣ በተሳካ ሁኔታ በየቀኑ የአዳር ጸሎት ማድረግ ቻልን። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በርካታ የተለያዩ አነስተኛ ቡድኖች በመኖራቸው እያንዳንዱ ቡድን በተለያየ ጊዜ የዙር አዳር ጸሎት ፕሮግራም እንዲኖረው በማድረግ በየዕለቱ አዳር ጸሎት እንዲካሄድ ማድረግ ቻልን።

    ቤተ ክርስቲያን ትልቅ በሆነች መጠን፣ ብዙ የጸሎት ቡድኖች ይፈጠራሉ። በሜጋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጸሎት ማካሄድ ይቻላል! ለዚያ ነው ሰይጣን ቤተ ክርስቲያን ትንሽ ሆና እንድትቀር የሚፈልገው!

    12.. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሕዝብ ይኖራታል፣ ብዙ ሕዝብ በሚሰባሰብበት ስፍራ ደግሞ ታላቅ ነገርን የመጠባበቅ ስሜት ይፈጠራል።

    ሕዝቡ በጉጉት እየተጠባበቁ ሳሉ፣ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? እያሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ ያሰላስሉ ነበር።

    ሉቃስ 3፡15 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

    ጉባኤው ትልቅ በሆነ መጠን፣ ከፍተኛ የመጠባበቅ ስሜትን እንደሚፈጥር ከልምድ አስተውዬአለሁ። ትልቅ መጠን ያለው የእግዚአብሔር ሕዝብ መሰባሰብ በሚሆንበት ጊዜ፣ በዚያ የመደነቅ፣ የመጠባበቅ ስሜት እና እውነተኛ እምነት ይኖራል። ይህ ለምን ይሆናል? ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉም ሰው እምነት በሚያየው ነገር ከፍ ስለሚል ነው። የትልቅ ስብስብ ዕይታ እምነትን ያነሳሳል እንዲሁም የደስታ ስሜት ይፈጥራል። የብዙ ሕዝብ የተዋሃደ እምነት ከአንድ ሰው እምነት ይበልጣል። ያ ደግሞ በአገልጋዩ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ስጦታ አንዲወጣ ይረዳል።

    እኔ ለትንሽም ለትልቅም ጉባኤ ሰብኬአለሁ። የእነኚህ ሁለት ሁኔታዎች መንፈሳዊ ሁኔታ አብዛኛውን ጊዜ ይለያያል።

    13.. ሜጋ ቤተ ክርስቲያን ሊኖርህ ይገባል፣ ምክንያቱም በሜጋ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1