Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
Ebook178 pages59 minutes

ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች

Rating: 4 out of 5 stars

4/5

()

Read preview

About this ebook

እንደ ክርስቲያን በሕይወትህ ካሉ ተጽዕኖዎች ሁሉ እጅግ ታላቁና ጣፋጩ መንፈስ ቅዱስ መሆን አለበት፡፡ ይህ መጽሐፍ ባህርይህ፣ ዕውቀትህ፣ የፈጠራ ችሎታህና የመቀደስ ችሎታህ ሳይቀር እንዴት በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ሊደረግባቸው እንደሚችሉ መረዳት ያስችልሃል፡፡ በዚህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ዓይነተኛ መጽሐፍ አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ እስከ ወዲያኛው በህይወትህ ላይ ተፅዕኖ እንዲኖረው፣ እንዲያነቃቃህ፣ እንዲገፋፋህና እንዲለውጥህ መፍቀድ አለብህ፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954461
ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች

Related ebooks

Reviews for ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች

Rating: 4 out of 5 stars
4/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች - Dag Heward-Mills

    ምን ተፅዕኖ ሊያደርግብህ ይችላል?

    ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።

    ማቴዎስ 13፡33

    እርሾ ሊጡን በማነቃቃት እንዲነፋ፣ ኩፍ እንዲልና የበለጠ ቀላል እንዲሆን የሚያደርግ የማይታይ፣ ድብቅ ተፅዕኖ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስም መንግሥተ ሰማይም በሁሉ ነገር ላይ ተፅዕኖ ለሚኖራቸው ድብቅ ተፅዕኖዎች ተገዥ መሆኗን አስተምሮናል።

    እርሾው በሊጡ ላይ ያለው ተፅዕኖ እውንና አስገራሚ ነው። ሆኖም ግን እርሾው በኃይል ሲሰራ ሊታይ አይችልም። የማይታዩ ተፅዕኖዎች እውነት ናቸው። የማይታዩ ተፅዕኖዎች መልካም ወይም ክፉ ናቸው።

    በአንድ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ታላቁ መልካም፣ የማይታይ ተፅዕኖ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህም መጽሐፍ ስለዚያ የማይታይ ግን እውን የሆነ ተፅዕኖ ነው! የመንፈስ ቅዱስ ጣፋጭ ተጽዕኖዎች!

    በቀላሉ፣ ይህ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ልንጠብቅ የምንችልባቸውን የተለያዩ ነገሮች የሚዘረዝር ነው። ልንጠባበቀውና ስለ እርሱ ልንጸልይ ይገባል። የመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ወሳኝ ነው። ለእለትእለት ኑሮአችን ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው።

    ተፅዕኖ እያደረገብህ ያለው ምንድን ነው? እንደ አገልጋይ ተፅዕኖ የሚያደርግብህ ምንድን ነው? የሚመራህና የምታደርጋቸውን ነገሮች እንድታደርግ የሚያደርግህ ምንድን ነው? በመልካም ተፅዕኖ ሥር ነህ ወይስ በመጥፎ ተፅዕኖ ሥር?

    ክርስቲያኖች የማያውቋቸውና በተሳሳተ መንገድ የተረዷቸው ሦስት የማይታዩ ክፉ ተፅዕኖዎች አሉ። በክርስቲያኖች ላይ ያሉ የመጀመሪያው የማይታዩ ክፉ ተፅዕኖዎች አጋንንት ናቸው። ሁለተኛው በክርስቲያኖች ላይ ያለ የማይታይ ተፅዕኖ ዓለም ወይም ምድር ናት። ሦስተኛው የማይታይ ተፅዕኖ ሥጋዊ ስሜቶቻችን ናቸው። ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ሥር ሳይሆኑ ሲቀሩ ከእነዚህ ሦስት ተፅዕኖዎች በአንዱ ሥር ናቸው። ስለዚህ ወይ ምድራዊ፣ ሥጋዊ ወይም አጋንንታዊ ናቸው።

    ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች ሲጽፍላቸው ቤተክርስቲያን ላይ ተፅዕኖ እያሳደሩ ስላሉ የማይታዩና በስፋት ስለተንሰራፉ ተጽዕኖዎች አስጠንቅቋቸዋል። እነዚህን ተፅዕኖዎች እርሾ የሚል ስያሜ ነበር የሰጣቸው። ጳውሎስ የእርሾን ውጤት አብራርቷል። እርሾ ኃይለኛ ሆኖ የሚያሳምን አይነት ነገር እንደሆነ ተናግሯል። ይህ የማይታይ ተፅዕኖ አንድን ክርስቲያንን ከአገልግሎቱ ማስተጓጎል እስኪችል ድረስ ኃይለኛ ነበር። ክፍሉን አስተውል፤ በመልካም ትሮጡ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ? ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል። (ገላትያ 5፡7-8)

    ይህ መጽሐፍ ስለ መንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች የሚያወራ ነው! በመንፈስ ቅዱስ ሊቀየሩ የሚችሉ የተለያዩ የሕይወትህን ክፍሎች ይገልጥልሃል። እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ አልፎ ሲናገርህ ራስህን ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት ታደርጋለህ። መንፈስ ቅዱስ በሕይወትህ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርግ ትጠባበቃለህ ደግሞም ትፈቅድለታለህ። 

    ምዕራፍ 2

    ሦስት ክፉ ተፅዕኖዎች

    ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤

    ያዕቆብ 3፡15

    የመንፈስ ቅዱስ ጣፋጭ ተፅዕኖ የመጨረሻ ውጤቱ አንተን መንፈሳዊ ሰው ማድረግ ነው። አዲስ ኪዳን ስለመንፈሳዊ ሰዎች አበክሮ ይናገራል። መንፈሳዊ ሰዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ ጠቃሚዎቹ ሰዎች ናቸው። እያንዳንዱ ሰው ግን የሚያማርጣቸው አራት አማራጮች አሉት። ምድራዊ፣ ሥጋዊ፣ አጋንንታዊ አሊያም መንፈሳዊ ይሆናል።

    ነጋዴዎች በንግዱ ዓለም ወሳኝ ናቸው። ሐኪሞች በህክምናው ዓለም ወሳኞች ናቸው፤ በቤተክርስቲያን ግን ወሳኞቹ መንፈሳዊ ሰዎች ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ እያለ ያለው ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሁን አይሁን ሊያውቁ የሚችሉት መንፈሳዊ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ያውቅ ስለነበር ጽሑፎቹን ያደረገው ለመንፈሳዊ ሰዎች ነበር። ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤ (1ኛ ቆሮንቶስ 14፡37)

    በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ሥር የሚኖር መንፈሳዊ ሰው ለመሆን ማለም አለብህ። የመንፈስ ቅዱስ ጣፋጭ ተፅዕኖዎች ወደ መንፈሳዊ ሰውነት ይቀይሩሃል። በሌላ ጎኑ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ሥር የማትኖር ከሆነ በእርግጠኝነት በሌላ ነገር ተፅዕኖ ሥር ትሆናለህ።

    ምድራዊ፣ሥጋዊ ወይስ አጋንንታዊ!

    ወይ በምድራዊ ተፅዕኖ፣ በሥጋዊ ተፅዕኖ ወይም በአጋንንታዊ ተፅዕኖ ሥር ትሆናለህ። ምድራዊ፣ ሥጋዊ፣ ወይም አጋንንታዊን ሰው መለየት አስቸጋሪ አይደለም። በየጊዜው በዙሪያችን እናያቸዋለን። መንፈሳዊ በመሆን ፈንታ በርካታ ክርስቲያኖች ምድራዊ፣ ሥጋዊ ወይም አጋንንታዊ ናቸው!

    ሥጋዊ ሰው ምን ዓይነት ነው?

    ሥጋዊ ሰው የሚመራው በስሜት ሕዋሳቱ እና በስሜቶቹ ነው። ፍላጎቶቹን ይከተላል፤ ደግሞም ያየውን ወይም የወደደውን ማንኛውንም ነገር ያሳድዳል። ሥጋዊ ሰው ብዙ ይበላል፣ ብዙ ይተኛል፣ በርካታ የግብረ-ሥጋ ግንኙነቶችን ይፈጽማል እንዲሁም በተገኘ በማንኛውም ዓይነት አስደሳች ነገር ውስጥ ይሳተፋል። በርካታ ወጣት ሰዎች ሕይወታቸውን የሚጀምሩት ስሜቶቻቸውን በመከተል ነው። የጭፈራ ቤቶች፣ የምሽት ክበቦች እና ግብዣዎች ሕይወታቸውን በጭፈራ በሚያጠፉና ስሜታዊነታቸውን ወደ ፍጻሜ ማሳረጊያው በሚከተሉ ሰዎች የተሞሉ ናቸው። አደንዛዥ ዕፅ ሻጮችና ተጠቃሚዎች ስሜታቸውን ተከትለው ወደራሳቸው ጥፋት የሚጓዙ ሰዎች ናቸው።

    ማየት የማትችለውን ሰው ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    አካላዊ ያልሆነን ሰብዓዊነት ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    ጥያቄዎችን የማይመልስ ወይም የማይናገርን ሰው ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    አንድን ሰው በተወካይ በኩል ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    ካንተ እጅግ የተለየ ሆኖ ሳለ አንድ ሰው እንዴት ያለ መሆኑን መሳል ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    ልትዳስስ የማትችለውን ሰው ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    ድምጹን ልትሰማው የማትችልን ሰው ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    አግኝተህ የማታውቀውን ሰው ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    ምሥጢራዊ የሆነን ሰው ማወቅ ቀላል ስላይደለ ሥጋዊ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይቸገራል።

    ምድራዊ ሰው እንዴት ዓይነት ነው?

    ምድራዊ ሰው እይታው በዚህች ምድር ላይ የሆነ ሰው ነው። በርካታ ሥጋዊ የሆኑ ሰዎች የሰው ልጆች የተሻለው ደረጃ ነው ብለው ወደሚያስቡት ነገር ይቀየራሉ። እነዚህ ሥጋዊ አዕምሮ ያላቸው ሰዎች በቀላሉ ምድራዊ አዕምሮ ወዳላቸው ሰዎች ይቀየራሉ። ምድራዊ ሰው የመንግሥተ ሰማይም ሆነ የገሃነም ሃሳብ የለበትም። ከዚህ ምድራዊ ሕይወት ያለፈ ሕይወት አይታየውም። እቅዶቹና ሩጫዎቹ ሁሉ ለዘላለማዊ ነገሮች ያለውን አጭር እይታ እና እውርነት ይገልጣሉ። እንዲህ ዓይነት ሰዎች ስለፍርድ አያስቡም፤ ማለት፣ እንቅስቃሴዎቻቸውና ድርጊቶቻቸው ወደብርሃን እንደሚመጡና የኃጢአታቶቻቸውን ዋጋ እንደሚከፍሉ አያስቡም።

    በኦክስፎርድ፣ ካምብሪጅ፣ ሀርቫርድ፣ ወዘተ የተማሩ በርካታ ጨዋ የሚመስሉ ፕሬዘዳንቶች እና ጠቅላይ ሚኒስትሮች በአንድ ወቅት ወጣት ሳሉ ያበደ ሕይወት ይኖሩ ነበር፤ ዕፅ ይጠቀሙ፣ ይጠጡና ያለማቋረጥ ያጨሱ ነበር። ከስሜታዊ ሰውነት በቀላሉ ተቀይረው ምድራዊ ሰዎች ሆኑ። የተከበሩና ከስሜታዊነት ዘመናቸው የራቁ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን እነግርሃለሁ አብዛኞቹ ከስሜታዊ ይልቅ የበለጠ ምድራዊ ናቸው፤ ለዘላለማዊ ነገር ዋጋ አይሰጡትም።

    እንደክርስቲያን አላማህ መሆን ያለበት መንፈሳዊ ሰው መሆን ነው። ምድራዊ፣ ሥጋዊ ወይም አጋንንታዊ መሆን የለብህም።

    አጋንንታዊ ሰው ምን ዓይነት ነው?

    አጋንንታዊ ሰው በኃይለኛ የክፉ መናፍስት ተጽዕኖ ውስጥ ያለ ሰው ነው።

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1