Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል
ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል
ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል
Ebook250 pages1 hour

ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

ኢየሱስ ክርስቶስ ብልጽግናንና ሀብትን የሚገዛውን አስደንጋጭ መርህ ገልጦልናል፡፡ ያለው ይበልጥ ይኖረዋል! እንዴት አግባብ ያልሆነ ነገር ይመስላል! ሆኖም ግን በየእለቱ በፊታችን የሚሆነው ነገር ይህ እውነታ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ጥቂት የተረዳነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለማብራራት ይሞክራል፡፡ ይህንን የዳግ ሂዋርድ ሚልስ አዲስ መጽሐፍ ስታጠና ስለ ብልጽግናም ምሥጢራት ታላላቅ እይታዎችን ትቀበላለህ፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954355
ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል

Related ebooks

Reviews for ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

3 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል - Dag Heward-Mills

    ያለው እና የሌለው

    እውነት ነው?

    ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።

    ማርቆስ 4፡25

    እንግዳየሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ቢሆንም እውነት መሆን አለበት! እንዴት አግባብ የማይመስል ቃል ነው! የበለጠ ገንዘብ የሚያገኙት ገንዘብ ያላቸው ለምን ሆኑ? ያላቸውን እንኳ የሚያጡት ደግሞ ጥቂት ያላቸው ለምን ሆኑ? በገሀዱ ዓለም ሌላ ተጨማሪ የሚያገኙት ያላቸው ለምን ሆኑ? ነገሮች እኛ ከምንጠብቀው ፍጹም ተቃራኒ ለምን ሆኑ?

    ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አግባብ ባይመስል እንኳ በሁለት ምክንያቶች እውነት ነው፡፡ኢየሱስ ስለተናገረው እውነት ነው፡፡ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። (ማቴዎስ 24፡35) የኢየሱስ ቃላት ከተነገሩ ቃላት ሁሉ እጅግ ኃይለኞች ናቸው፡፡

    ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እውነት የሆነበት ሁለተኛው ምክንያት በዙሪያችን ሁሉ ስለምናየው ነው፡፡ ሰው ሁሉ ተጨማሪ ይፈልጋል ግን ሁሉም ተጨማሪ አያገኝም፡፡ ስለዚህ በእርግጥ ብዙ የሚያገኘው ማን ነው?

    ብዙ ከሌላቸው በስተቀር ሁላችንም ወደእኩልነት ከፍ መደረግ አለብን፡፡ ሁሉም ሰው ቢያንስ መሠረታዊ የሆኑት ነገሮች እንዲኖሩት እንፈልጋለን፡፡ ግን ሕይወትም ታሪክም ከሁሉም ነገር ተጨማሪ የሚያገኘው ያለው እንደሆነ ያመላክቱናል፡፡ ዝም ብለህ ዙሪያህን ብትቃኝ ብዙ የሌላቸው ያለቻቸውን ጥቂት እንኳን እያጡ እንደሆነ ትመለከታለህ! የኢየሱስ ቃላት እውነት መሆናቸውን ሁላችንም ልንመለከት እንችላለን፡፡

    ይህ መጽሐፍ ባጠቃላይ በዚህ እንግዳ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ይህ እንግዳ የሚመስል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመንፈሳዊም ሆነ በቁሳዊ ነገሮች ላይ ተፈጻሚነት እንዳለው ትደርስበታለህ፡፡ ያለው ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት፡፡

    ቁሳዊ ነገሮች ያሉት

    1. ገንዘብ፣ ቤቶች እና መኪኖች ያሉት የበለጠ ገንዘብ፣ ተጨማሪ ቤቶችና ተጨማሪ መኪኖች ይኖሩታል፡፡

    ሀብታም ሰዎች (ያለው) ሀብታቸው የበለጠ እየጨመረና ምንም የማይጎድላቸው እየሆኑ ሲሄዱ ድሆች ደግሞ በየቀኑ የበለጠ እየደኸዩ ይሄዳሉ፡፡ በዓለም የመጨረሻ ደሃ አህጉር የሆነቸው አፍሪካ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ያለማቋረጥ የበለጠ እየደኸየች የሄደች ብቸኛዋ የዓለማችን ክፍል ናት፡፡ ቀድሞውኑ ሀብታም የነበሩት አሜሪካና አውሮፓ የበለጠ ባለጠጎች ሆነዋል፣ የወርቅ ክምችታቸውን፣ ነዋይና ንብረቶቻቸውን አብዝተዋል፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ የበለጠ መሠረተ ልማት የሚያስፈልጋት አፍሪካ ያላትን ጥቂት መሠረተ ልማት በሚከሰቱ የእርስ በእርስ ጦርነቶችና የጎሳ ግጭቶች ምክንያት አውድማለች፡፡

    ቤት የሰራ ሰው ተጨማሪ ቤቶችን ሊገነባ እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡ ቤት ያልገነባ ሰው ወደፊት ቤት የመገንባቱ ነገር አጠያያቂ ነው፡፡ ቤት የሌለው ሰው አሁን የሚኖርበትን የማጣት አዝማሚያው የሰፋ ነው፡፡ ቤት ያልገነባ ሰው በአከራዩ የመባረር አጋጣሚው የጨመረ ነው፡፡

    መኪኖች ያሏቸው ሰዎች ወደፊት ተጨማሪ መኪኖች ሊኖሯቸው ይችላል፡፡ መኪና የሌላቸው ነገር ግን ሁልጊዜ በአውቶቡስና በታክሲ የሚጓዙ ሰዎች በመጪዎቹ አመታትም በአውቶቡሶችና በታክሲዎች የመመላለሳቸው አጋጣሚ የሰፋ ነው።

    2. ሥራ ያለው ተጨማሪ የሥራ ዕድሎች ይቀርቡለታል።

    ሥራ ያለው ሌሎች ሥራዎች የማግኘት ዕድሉ የጨመረ ነው፡፡ በ ጎልደን ቱሊፕ ሆቴል የምግብ ባለሙያ ከሆንክ አዲሱ የሸራተን ሆቴል የምግብ ባለሙያው እንድትሆን ሊያነጋግርህ ይችላል፡፡ የሚያሳዝነው ግን የምግብ ሙያ ትምህርቱን በአንድ የመስተንግዶ ትምህርት ቤት ገና ያጠናቀቀው ሰው ግን በአዲሱ የሸራተን ሆቴል ለሥራ መፈለጉ አጠራጣሪ ነው፡፡ ሥራ ያለው ሌላ ሥራ የማግኘቱ አጋጣሚ የሰፋ ነው፡፡ የባንክ ገንዘብ ያዥ ሆኖ የሚሠራ ሰው ከዚህ ለሚሻል ሥራ ሌላ ባንክ ሊፈልገው ይችላል፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከዩኒቨርሲቲ ሁለት ዲግሪ የያዘውን ሰው ባንኩ ላይፈልገው ይችላል፡፡ ይህ ሰው በትጋት ሥራ መፈለግና ብዙ ጊዜ ተቀባይነት ማጣት ይኖርበታል፡፡

    3. ልጅ ያለው ተጨማሪ ልጆች ይኖሩታል፡፡

    ልጆች ያሏቸው ሰዎች ያለብዙ ችግር ቀጣዩን ልጅ ይወልዳሉ። አሁን እናት የሆኑ ሰዎች በማርገዛቸው ደስተኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ ማየት የተለመደ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ቀድሞውኑ ልጆች አሏቸው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ምንም ልጆች የሌሏቸው አንድ እንኳን ለመውለድ ይታገላሉ፡፡ ተቃርኖው የሚያሳዝን ቢሆንም በዓለማችን ያለ እውነታ ነው፡፡

    4. የፖለቲካ ሥልጣን ያለው የበለጠ የፖለቲካ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡

    የፖለቲካ ሥልጣን ያላቸው ቤተሰቦች የበለጠ የፖለቲካ ሥልጣን የመያዝ አጋጣሚ አላቸው፡፡ የቡሽ ቤተሰብ ለምን ሁለት የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ኖሩት?የኬኔዲ ቤተሰብ ለምን ሁለት ፕሬዘዳንቶች ኖሩት?ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፡፡

    የሆነ ሌላ ቤተሰብ ታዋቂ ፖለቲከኞች ወይም ፕሬዘዳንቶች እንዲፈልቁባቸው ልትፈልግ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ቀድሞውኑ ታዋቂ ከሆኑት ቤተሰቦች ተጨማሪ ፕሬዘዳንቶች የመፍለቃቸው ዕድል የሰፋ ነው፡፡

    5. ትምህርት ያለው የበለጠ ትምህርት ይኖረዋል፡፡

    የህግ ባለሙያዎችና ሐኪሞች ያሉበት ቤተሰብ ተጨማሪ የህግ ባለሙያዎችና ሐኪሞችን ሊወልድ ይችላል፡፡ መሃይሞችና መንደርተኞች ያሉበት ቤተሰብ ጠበቆች፣ ሐኪሞችና ሳይንቲስቶች የሚሆኑ ሰዎችን የመውለዳቸው አጋጣሚ የጠበበ ነው፡፡

    ስለዚህ አሁንም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተፈጸመ ማለት ነው። በቤተሰቡ ውስጥ የተማሩ ሰዎች ያሉት ቤተሰቡ ውስጥ እንደውም ይበልጥ የተማሩ ሰዎችን በቤተሰቡ ውስጥ ያገኛል፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ የተማሩ ሰዎች የሌሉት ደግሞ ያሉትን እንኳ ያጣል፡፡

    6. በከፍተኛ ሥፍራ ላይ ያሉ ጓደኞች ያሉት ተጨማሪ ጓደኞች ይኖሩታል፡፡

    ወሳኝ ሰዎችን የሚያውቅ ሰው ዓመታት ባለፉ ቁጥር ይበልጥ ጠቃሚ ሰዎችን ሊያውቅ ይችላል፡፡ ምንም መሀንዲስ፣ ሐኪም ወይም የህግ ባለሙያ የማያውቅ መንደርተኛ ወይም የደኸየ መሃይም በቀጣዩ አመት ወሳኝ ሰው የማወቁ ዕድል የጠበበ ነው። እንደውም በድህነቱ ምክንያት ሰዎች በእርሱ ላይ ፍላጎት ያጡና ጓደኞቹ ይበልጥ ይቀንሳሉ፡፡

    7. ታዋቂ የሆነ ይበልጥ ታዋቂ ይሆናል፡፡

    ታዋቂ የሆነ ሰው የሚያደርጋቸውን ነገሮች ማድረግ ከቀጠለ የበለጠ ታዋቂ እየሆነ ይሄዳል፡፡ በመንደር ያለ የማይታወቅ ሰው በመጪው አመት ታዋቂ ላይሆን ይችላል፡፡

    መንፈሳዊ ነገሮች ያሉት

    1. የእግዚአብሔር ዕውቀት ያለው ዕውቀቱን የመጨመር አዝማሚያው ከፍ ያለ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ማወቅና መፍራት ሊጨምር ይችላል፡፡ እንዲህ ዓይነት የተቀቡ ሰዎች በመጪዎቹ አመታት ይበልጥ የተቀቡ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡

    2. ብዙ ነፍሶችን የማረከ አገልጋይ በመጪው አመት ተጨማሪ ነፍሶችን የመማረክ አጋጣሚው የሰፋ ነው፡፡እርሱ ከአሁኑ እጅግ የሚበልጡ ክሩሴዶችን ሲያደርግ እጅግ ጥቂት ጉባዔ ያለው ወንጌላዊ ደግሞ ወደትናንሽ ክሩሴዶቹ የሚመጡ ሰዎች እየቀነሱ ይሄዳሉ፡፡ በመላ የክርስትና ህይወቱ አንድ ነፍስ ብቻ የማረከው ወጣት በአሁኑ አመት ምንም ነፍስ ላይማርክ ይችላል፡፡

    3. ትልቅ ቤተከርስቲያን ያለው መጋቢ በመጪው አመት የበለጠ ትልቅ ቤተክርስቲያን ይኖረዋል፡፡ ትልቅ ቤተክርስቲያን ያለችው መጋቢ ከአሁኑ የምትበልጥ ቤተክርስቲያን ልትኖረው ይችላል፡፡ ትንሽ ቤተክርስቲያን እያነሰች ልትሄድ ትችላለች፡፡ ትንሽ ቤተክርስቲያን ከትልቅ ቤተክርስቲያን ይልቅ አባላትን ልታጣና ልትዘጋ ትችላለች፡፡

    4. የተቀባው የእግዚአብሔር አገልጋይ የበለጠ ተሰጥኦ እና ቅባት ይበዛለታል፡፡ እነርሱ የበለጠ የሚዘረጉና ለእግዚአብሔር ብዙ ምርኮን የሚያስገኙ ናቸው፡፡ ተሠጥኦ የሌላቸው ሰዎች ይበልጥ የማይስቡ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ይበልጥ ያልተቀቡ እየሆኑ የመሄድ አዝማሚያ ይኖራቸዋል።

    5. የቤተክርስቲያን ህንፃዎች ያሏቸው መጋቢያን ተጨማሪ ህንፃዎች ይኖሯቸዋል፡፡ለቤተክርስቲያኖቻቸው ቤት የሌላቸው ከተከራዩት ግቢ እንደሚባረሩ ማስፈራሪያ ይደርሳቸዋል፡፡ የቤተክርስቲያን አባላት ቀድሞውኑ ትንሽ የነበረውን የጉባኤ ቁጥር በማመናመን ከትናንሽ አብያተክርስቲያናት ይበልጥ ትልቅ ወደሆኑ አብያተክርስቲያናት ይጎርፋሉ፡፡

    6. ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ቤተክርስቲያኖች በመጪው አመት ከፍተኛ ገቢ ይኖራቸዋል፡፡ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተክርስቲያኖች በመጪው አመት አባላትንና ገቢን ሊያጡ ይችላሉ፡፡

    7. በርካታ አዳዲስ የሚነሱ መሪዎችን የሚያሰለጥኑ የወንጌል አገልጋዮች ተጨማሪ ሰዎችን ያሰለጥናሉ፡፡ መሪዎችን አሰልጥነው የማያውቁ ሰዎች ወራሽ ጭራሽ ላይኖራቸው ይችላል፡፡

    ይህ ለምን ሆነ?

    ላለው ይሰጠዋል የሚለው የኢየሱስ አረፍተነገር ለምን እጅግ እውነት ሆነ?

    ያለው ተጨማሪ የሚያገኝበት ምክንያት

    ያላቸው ያላቸውን እንዲያስገኙ ያስቻሏቸውን አንዳንድ ነገሮች አድርገዋል፡፡ በአብዛኛው ያላቸውእነዚያውኑ የመጨመር መርሆች መተግበር ይቀጥላሉ፡፡

    የሌለው ያለውን እንኳ የሚያጣበት ምክንያት

    ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤

    ማቴዎስ 25፡28

    ብዙ የሌላቸው ወደብልጥግና የሚያደርሱ አንዳንድ መርሆችን አይተገብሩም ወይም አንዳንድ አስተሳሰቦችን አይከተሉም፡፡ በአብዛኛው የሌላቸው አሁን ላሉበት የድህነት ሁኔታ ያበቋቸውን መጥፎ መርሆችና አስተሳሰቦች ተግተው መከተል ይቀጥላሉ፡፡ ይህ ድህነታቸው ሥር እንዲሰድድና ችግሮቻቸው ይበልጥ እንዲወሳሰቡ ያደርጋል፡፡

    የአፍሪካ ሀገራትንና ኢኮኖሚዎች በፍጥነት ብንቃኝ ከአምሳ አመታት በፊት ከነበረው ይልቅ እጅግ የተወሳሰበና ሥር የሰደደ ድህነት እንመለከታለን፡፡ አፍሪካን ከቅኝ ግዛት ድህነቷ ለማውጣት ተአምራት የሚያስፈልግ ቢሆን ኖሮ አሁን አፍሪካን ካለችበት ለማውጣት አንድ ሺህ ተጨማሪ ተአምራት ያስፈልጋሉ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የአፍሪካ ችግሮችና ተግዳሮቶች ማደጋቸው፣ መብዛታቸው እና እጅግ ውስብስብ መፍትሄ ወደሚያስፈልጋቸው ውስብስብ ችግርነት ማደጋቸው ነው፡፡

    በውድቀት፣ ችግሮችና ድህነት ውስጥ የሚታገል አገልግሎት በአብዛኛው ከሥጋዊ ዓይን እይታ የሚያልፉ ችግሮች አሉት፡፡ ብዙ ጊዜ ሥር የሰደዱ፣ ውስብስብና ብዙ ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች አሉባቸው፡፡ እነዚህ ችግሮች በአብዛኛው ውስብስብ የሆኑ ችግሮች የሚያስከትሏቸው መወሳሰቦች ናቸው፡፡ ኢየሱስ ፡- ላለው ይሰጠዋል ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል ያለው ለዚህ ነው፡፡

    ምን ማድረግ አለብን?

    አሁን ምን ማድረግ አለብን? በዓለማችን የሚገኙ እኩልነት የሌለባቸውን ነገሮች መነሻ የእውነት ማጣራት አለብን- በመንፈሳዊውም ሆነ በተፈጥሮአዊው፡፡ የምናያቸውን ትላልቅ ልዩነቶች የሚያመጡትን ትናንሽ ልዩነቶች ለይተን ማወቅ አለብን፡፡ ካለው የምንማራቸውን ትምህርቶች መተግበር አለብን፡፡ ከድህነት ወደሀብት የሚያስኬድ ፈጣን ማስተካከያ የለም፡፡

    ይህ ስለብለጽግና የሚናገር መጽሐፍ አይደለም፡፡ ስለብልጽግና የሚያወሩ መጻሕፍት ምንም ችግር የለባቸውም፡፡ በብልጽግና አምናሁ፡፡ ነገር ግን ይህ መጽሐፍ ከዚህ እርቆ ሄዶ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የሚሉትን የኢየሱስ ምሥጢራዊ ቃላት ለመረዳት ይሞክራል፡፡ የዚህን መጽሐፍ መርሆች ከተገበርህ ያለው ትሆናለህ፡፡

    በሚገርም መልኩ በአለማዊ ተመራማሪዎች የተደረጉ ጥናቶች የኢየሱስን ቃላት እውነተኛነት ያረጋግጣሉ፡፡ ዓለማዊ ሰዎች የደረሱባቸውን ግኝቶች በቅርበት መመልከት ያለው ለምን ተጨማሪ እንደሚቀበል እና የሌለው ያለውን እንኳ ለምን እንደሚያጣ ለመረዳት በጣም ያግዛል፡፡

    የኢየሱስ ቃላት ፍፁም ጥልቅ ናቸው፡፡ ምንም ጥናት ባይደረግ እንኳ በዚህ ዓለም ላይ ያላቸው እና የሌላቸው እንዴት እንደተፈጠሩ የሚያስረዱት ቃላት የኢየሱስ ቃላት ናቸው፡፡

    በዚህ መጽሐፍ የተገለጠውን ዕውቀትና ጥበብ አትናቅ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ የዕውቀት መንፈስ ስለሆነ ቁም ነገር አድርገህ ውሰደው፡፡

    በእርግጥ እንደ ኢየሱስ ጥበብ ያለ ጥበብ የለም፤ እንደ ኢየሱስ ቃላት ያሉ ቃላትም የሉም፡፡ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤አንተ ግን ያላቸው ተጨማሪ እንደሚያገኙ እና የሌላቸው ያላቸውን ጥቂቱን እንኳ እንደሚያጡ ትደርስበታለህ፡፡

    ምዕራፍ 2

    ያለው መልካም ባሕርያትና አመለካከቶች ስላሉት ተጨማሪ ያገኛል

    ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤

    2ኛ ጴጥሮስ 1፡5-8

    ከላይ የተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንዳንድ ነገሮች ካሉህ ሥራ ፈትፍሬ ቢስ እና ምርት አልባ እንደማትሆን ያሳየናል፡፡ ጴጥሮስ የሚጠቅሳቸው ነገሮች እንደ ትጋት፣ እምነት፣ ራስን መግዛት፣ ወዘተ… የመሳሰሉ መልካም ባህርያትናቸው፡፡ እነዚህ በሰው ውስጥ የሚገኙ መልካም ባህርያት ናቸው ለፍሬአማነትና ለምርታማነት የሚያበቁት፡፡

    በአንድ ሰው ማንነት ውስጥ ያሉ መልካም ባህርያት ናቸው ከፍሬ ቢስ፣ ምርት አልባ እና ከማያበለጽጉ ክልሎች ሰብሮ እንዲወጣ የሚያደርጉት፡፡ ሥራ ፈትነት ጥቂት ምርታማነት ስላለው ደረቅ ገፀ ምድር የሚያወራ ነው፡፡ የሌለው ደረቅ እና ሥራ ፈት መስክ በአንድ ሰው ውስጥ አንዳንድ መልካም ባህርያት ላለመኖራቸው ምስክር ነው፡፡ በአንድ ሰው ውስጥ ያለው የሚያደርጉት መልካም ባህርያት ምን ምን ናቸው? ይህ ምዕራፍ ስለዚህ ነው የሚያወራው፡፡ ከፍሬአማነት፣ ምርታማነት እና መትረፍረፍ ጋር የተያያዙ ዘጠኝ ጠቃሚ መልካም ባህርያት አሉ፡፡

    እነዚህ መልካም ባህርያት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እና ከላይ በተመለከተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡ ማንንም ሀብታም የሚያደርጉ የግል ባህርያት ናቸው፡፡ ያለው መሆን እንድትችል እነዚህ የግል ባህርያት ሊለዩ፣ ሊበረታቱና ሊዳብሩ ይገባል፡፡ አንዴ እነዚህ መልካም ባህርያት ከተገኙ ፍሬ ቢስነት፣ ሥራ ፈትነት ወይም ድህነት እንደማይኖር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

    መልካም ባህርያቱ ትጋት፣ እምነት፣ በጎነት፣ እውቀት፣ ራስን መግዛት፣ መጽናት፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ የወንድማማች መዋደድ እና ፍቅር ናቸው፡፡ እነዚህ ባህርያት እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ስለእያንዳንዳንዳቸው ጥቂት ነገሮችን ማወቅ እንዲሁም እንዴት እንደሚተገበሩ መረዳት አለብህ፡፡

    መልካም ባህርይ፡- ትጋት

    የትጋት ትርጓሜ፡- ትጋት አንድ ሰው የሆነን ችግር ለመፍታት፣ ችግሮችን ለማሸነፍና ታላላቅ ነገሮችን ለማሳካት የሚያደርገው ያላሰለሰ እና ፋታ የለሽ ጥረት ነው፡፡

    ስለትጋት ልታውቃቸው የሚገቡ አራት ነገሮች

    1. ትጋት አንድን ሰው ሀብታም የሚያደርግ የግል ባህርይ ነው፡፡

    ሀብታም ሰው ሁሉ ማለት ይቻላል፣ ትጉህ ሰው ነው፡፡

    የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች።

    ምሳሌ 10፡4

    2. ትጋት አንድን ሰው መሪ የሚያደርግ የግል ባህርይ ነው፡፡ አብዛኞቹ መሪዎች ሀብታምና ባለጠጋ የሆኑት ከሚመሩት ሰው ሁሉ ቀድመው ስለሚገኙ ነው፡፡

    የትጉ እጅ ትገዛለች የታካች እጅ ግን ትገብራለች።

    ምሳሌ 12፡24

    3. ትጋት አንድን ሰው ወደ መትረፍረፍና ባለጠግነት የሚያደርሱ አሳቦች እንዲኖሩት የሚያደርግ የግል ባህርይ ነው፡፡

    የትጉህ አሳብ ወደ ጥጋብ ያደርሳል ችኵል ሰው ሁሉ ግን ለመጕደል ይቸኩላል።

    ምሳሌ 21፡5

    4. ትጋት ለሹመት የሚያበቃ የግል ባህርይ ነው፡፡

    በሥራው የቀጠፈ ሰውን አይተሃልን? በነገሥታት ፊት ይቆማል በተዋረዱም ሰዎች ፊት አይቆምም።

    ምሳሌ 22፡29

    በታሪክ ውስጥ ባለጠጋ እና ስኬታማ ሰዎችን የፈጠረው ትጋት ነው፡፡ መሪዎችን፣ ሚሊዮነሮችን እና መትረፍረፍ የሆነላቸውን ሰዎች ጠጋ ብለህ ብትመለከት ብዙ ትጋት እና ከባድ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1