Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

እንዴት መጸለይ አለብን
እንዴት መጸለይ አለብን
እንዴት መጸለይ አለብን
Ebook147 pages1 hour

እንዴት መጸለይ አለብን

Rating: 2.5 out of 5 stars

2.5/5

()

Read preview

About this ebook

““እንዴት መጸለይ አለብኝ? ስለ ምን መጸለይ አለብኝ? ጸሎት እጅግ ምሥጢራዊ የሆነው ለምንድን ነው? ለረጅም ሰዓት እንዴት መጸለይ እችላለሁ? የሚያስፈልገኝን ቀድሞውኑ እግዚአብሔር አያውቅም? ባልጸልይ ምን ይሆናል? ጸሎቶቼ በእውነት ይመለሳሉ?” ይህንን የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ተግባራዊና ወቅታዊ መጽሐፍ ስታነብብ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ታገኛለህ።

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954379
እንዴት መጸለይ አለብን
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to እንዴት መጸለይ አለብን

Related ebooks

Reviews for እንዴት መጸለይ አለብን

Rating: 2.6666666666666665 out of 5 stars
2.5/5

3 ratings2 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

  • Rating: 5 out of 5 stars
    5/5
    መጽሐፉን ወድጄዋለሁ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ቤተክርስቲያናችሁን ገታ ይባርክ በቀሪው በርቱ
    ታፈሰ
  • Rating: 2 out of 5 stars
    2/5
    ሰላም ሰላም . በዚህ መፀሀፍ በኩል በብዙ ተምሬበታለሁ. የፀሎት ህይወቴን ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር በተያያዘ እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ ተምሬበታለሁ. ኣመሰግናለሁ ተባረክ በብዙ!

Book preview

እንዴት መጸለይ አለብን - Dag Heward-Mills

pray

ትርጉም፡-  እስራኤል ጥበቡ

አርትዖት፡- ያሬድ ስለሺ

ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

Email Dag Heward-Mills: 

evangelist@daghewardmills.org 

Find out more about Dag Heward-Mills at: 

www. daghewardmills.org 

www. lighthousechapel.org 

www.healingjesuscrusade.org 

Write to: 

Dag Heward-Mills 

P.o.Box 114 

Korle-Bu 

Accra 

Ghana 

ስልክ + 251912063821 

መ.ሳ ቁጥር 15134 

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

ISBN: 9781613954379  

ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከተለነው፡፡

Table of Contents

ምዕራፍ 1. ለመጸለይ እጅግ ጊዜ ካጣህ ከሚገባው በላይ በሥራ ተጠምደሃል

ምዕራፍ 2. ጸሎት ምሥጢራዊ የሆነበት ምክንያት

ምዕራፍ 3. ሳትጸልይ ስትቀር የሚሆነው ነገር

ምዕራፍ 4. ታላቅን ሰው የምናዋራበት ሥርዓት

ምዕራፍ 5. በልሳን በመጸለይ እንዴት ልትረዳ እንደምትችል

ምዕራፍ 6. ሦስቱ ታላላቅ የጸሎት ርዕሶች

ምዕራፍ 7. ሁሉን ዓይነት ጸሎት እንዴት መጸለይ እንደሚገባ

ምዕራፍ 8. እግዚአብሔር ሁሉንም ጸሎቶቻችንን ይመልሳል?

ምዕራፍ 9. 100% ወደሚመለስ ጸሎት የሚያደርሱ አሥራ ሁለት እርምጃዎች

ምዕራፍ 1

ለመጸለይ እጅግ ጊዜ ካጣህ ከሚገባው በላይ በሥራ ተጠምደሃል

ዳንኤልም ጽሕፈቱ እንደ ተጻፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ በየዕለቱ ሦስት ጊዜ በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም።

ዳንኤል 6፡10

ለመጸለይ ጊዜ የሌለው ማንኛውም ሰው ከሚገባው በላይ በሥራ ተጠምዷል ማለት ነው፡፡ ማንም ሁን ማንም መጸለይ እስከማትችል ድረስ በሥራ እንድትጠመድ ለራስህ መፍቀድ የለብህም፡፡ ከላይ በተጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ዳንኤል በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ እንደነበር ማየት ትችላለህ፡፡ በክፍሉ ላይ ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ የሚል አንድ ጠቃሚ ሐረግ አለ፡፡ ይህም ማለት ዳንኤል እነኚህን ጸሎቶች ሳያሰልስ ይጸልይ ነበር ማለት ነው፡፡ ዳንኤል በችግር ውስጥ ስላለ ብቻ አልነበረም ይጸልይ የነበረው፤ የጸሎት ልማድ ነበረው፡፡

ብዙ ጊዜ ሰዎች መበልጸግ ሲጀምሩ ወደጸሎት ስብሰባዎች መሄድ ያቆማሉ፤ ብለውም ወደኋላ ይመለሳሉ፡፡ ዳንኤል ግን እንዲህ አልነበረም! የሀገሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነበር፣ በስልጣን ከንጉሱ ብቻ ነበር የሚያንሰው፡፡ ከባርነት ተነስቶ ወደጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ከፍ ያለ ስኬታማ ሰው ነበር፡፡ በሀገሪቱ እጅግ ከሚከበሩና ከሚፈሩ ሰዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡ የጊዜው ዋና ፖለቲከኛ ነበር፡፡ የመንግስት ሰራተኛ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በቀን ሦስት ጊዜ ይጸልይ ነበር፣ በየቀኑ!

እንደዚህ ዓይነት ያልተለመደና ያላሰለሰ የጸሎት ጊዜ እንዲኖረው ዳንኤልን ይመሩት የነበሩት መርሆች የትኞቹ ናቸው? እነኚሁ፣ አንብባቸውና የአንተ መርሆች ይሁኑ፡፡ ዳንኤል የነበረው ስኬት አንተም ሊኖርህ ይችላል፡፡ ዳንኤልን በህይወቱ መርተውታል ብዬ የማስባቸውን የሚከተሉትን መርሆች ፈጽመህ አንብብ፣ አጥና እንዲሁም አጢን፡፡

መርህ ቁጥር 1፡- ጸሎት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

በአንድ ወቅት አንድ ሰው የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ከማግኘት ይልቅ እንዴት እንሚጸለይ ማወቅ የበለጠ ጠቃሚ ነው ብሏል፡፡ በዚህ ህይወት ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ጥሩ ትምህርት ጠቃሚ ነው፡፡ ገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ መልካም ጋብቻ ጠቃሚ ነው፡፡ ጥሩ የጸሎት ህይወት ግን ከምንም በላይ ጠቃሚ ነው! ይህ ወደመንፈስህ ይግባ፤ በማግኘትህ ሁሉ ጸሎትን አግኝ! በተግባሮችህ ሁሉ መካከል ለጸሎት ክፍተት አብጅ!

መርህ ቁጥር 2፡- ጸሎትን እስኪተው ድረስ በስራ የተጠመደ፣ እጅግ የተባረከ ወይም እጅግ ስኬታማ የሆነ ሰው የለም

እጅግ የተጣበበ የህይወት ዘይቤ ሊኖርህ ይችላል፣ እጅግ ጠቃሚ ሰውም ልትሆን ትችላለህ፤ ሆኖም ከዳንኤል ይልቅ በሥራ የተወጠርክ አይመስለኝም፡፡ ዳንኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ነገር፣ ከሀገሪቷ መሪዎች አንዱ ማለት ነው፡፡  ብዙ ሰዎች የሀገር መሪዎችና የመንግስት ሚኒስቴሮች ከሀገር ሀገር እየበረሩ ፈታ ያለና የሚያዝናና ህይወት የሚኖሩ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ እውነት አይደለም! እኔ ራሴ የትልቅ ተቋም መሪ ነኝ፤ እናም በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ ሰዎች ቀላል ህይወት እንደሌላቸውን አውቃለሁ፡፡ ከፍታህ በጨመረ ቁጥር የሚኖርብህ ኃላፊነት እየጨመረ ይመጣል፡፡

በህይወትና በአገልግሎት ግንባር ላይ ፊት አውራሪ ሆኖ መቆየት እጅግ ብዙ ከባድ ሥራን የሚጠይቅ ነገር ነው፡፡ እንደ ዳንኤል ያሉ ስኬታማ ስራ አስፈጻሚዎች እንደ የጨጓራ ህመምና የልብ ድካም ለመሳሰሉ በሽታዎች እስኪጋለጡ ድረስ እጅግ እንደሚጨናነቁ ታውቃለህ? እነዚህ የጤና ችግሮች በሚሰሩት ከባድ ሥራ ምክንያት እጅግ በስራ በተጠመዱ ሰዎች ላይ በይበልጥ ይስተዋላሉ፡፡

ዳንኤል እንዲህ ያለ ሰው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነበር፤ ይሁንና በቀን ሦስት ጊዜ ለመጸለይ እስከማይችል ድረስ እጅግ በሥራ የተጠመደ እንደሆነ አይሰማውም ነበር፡፡ ለመጸለይ እስከማትችል በሥራ እንደተጠመድክ የምታስብ ከሆነ ራስህን እያሳትክ ነው፡፡ የማትጸልይ ከሆነ መጸለይ ስለማትፈልግ ነው፡፡ ጸሎት አሁን አስፈላጊ እንደሆነ ስለማታስብ ነው! ዳንኤል ስኬታማ ነበር፤ ግን ይጸልይ ነበር፡፡ ለምን በቀን ሦስት ጊዜ መጸለይ ቻለ?!

ሰዎች ከድህነት ወጥተው ወደ ብልጽግና አድገዋል፡፡ ድሆች ሳሉ የጸሎት ስብሰባዎችን ለመካፈል ብዙ ጊዜ ነበራቸው፡፡ ሲባረኩ ግን ሁሉም ነገር የተስተካከለ እንደሆነ ተሰማቸው፡፡ በፍፁም! ሁሉም ነገር ትክክል አይደለም! በልጽግናህ ጸሎት ማቆም እንዳለብህ የሚናገር ምልክት አይደለም፡፡

መርህ ቁጥር 3፡- ጸሎት የኃይላችንና የጥበቃችን ምንጭ ነው፡፡

የእግዚአብሔርን ኃይል ለእኛ የሚለቅልን ጸሎት መሆኑን ማስተዋል አለብህ፡፡ ኢየሱስ የጸሎትን ኃይል ያውቅ ነበር፡፡ በጸሎት ረጅም ሰዓት ያሳልፍ የነበረውም በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ ምናልባት ስኬታማ ነጋዴ ልትሆን ትችላለህ፤ እንደዚህ ዓይነት መንፈሳዊ ነገር እንደሚያስፈልግህም ላታስብ ትችላለህ፡፡ አልያም ፖለቲከኛ ልትሆን ትችላለህ፤ እናም  ጥበቃህ ከጣዖት ወይም ምትሀታዊ ኃይሎች ዘንድ መሆን እንዳለበት ታስብ ይሆናል፡፡

አሁኑኑ ልንገርህ፤ በጸሎት ውስጥ ኃይል አለ፡፡ የጸሎት ኃይል እያለልን ሌላ ምንም ዓይነት ኃይል አያስፈልገንም፡፡ ስንጸልይ ጥበቃ አለን፡፡ የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ የመጨረሻው ክፍል ጸሎት ነው (ኤፌሶን 6፡18) ፡፡ በሌላ ቋንቋ ጸሎት የመንፈሳዊ መከላከያህ ጠቃሚ ክፍል ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ሲበለጽጉ ይፈራሉ፡፡ እዮብ ሲበለጽግ በፍርሃት ተሞልቶ   ነበር፡፡ እናም የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና አለ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች አንድ ሰው እነርሱን ለመግደል ልዕለ-ተፈጥሮአዊ ኃይል ሊጠቀም እንደሚችል ይሰማቸዋል፡፡ እንደ ዳንኤል የጸሎት ሰው ስትሆን ምንም የምትፈራው ነገር የለም፡፡ ብዙ ሰዎች ዳንኤልን ለመግደል ፈልገው   ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ዳንኤልን ለመግደል ማሰብ ብቻ ሳይሆን በእርግጥ ሊያጠፉት ሞክረዋል፡፡ በጸሎት ኃይል ዳንኤል ከአንበሶቹ ተጠብቆ ነበር፡፡

በህይወትህ ያሉት አንበሶች በሙሉ በፍርሃት ሲበታተኑ ይታየኛል! የጸሎት ኃይልህ ሲጨምር ይታየኛል! አዲስ በተገኘ የጸሎት ህይወት አማካኝነት ወደፊት ስትሄድ ትታየኛለህ!

... ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥

ሉቃስ 3፡21

ሰማያት በህይወትህ ላይ ሲከፈቱ አያለሁ! ይህንን መቼም እንዳትረሳ! ኢየሱስ ሲጸልይ ሰማይ ተከፈተ፡፡ የጸሎት ሰው ስትሆን ቁሳዊም ሆኑ መንፈሳዊ በረከቶች በአንተ ላይ ይዘንባሉ፡፡

መርህ ቁጥር 4፡- ጸሎት የእግዚአብሔርን በረከቶች ለማግኘትና ለማቆየት ይጠቅማል

የምትኮራበት ነገር አለህ? በዚህ ህይወት ያሳካኸው ነገር አለ? ይህ በእግዚአብሔር ጸጋ እንደሆነ ልንገርህ፡፡ በጸሎት ኃይል የበለጡ ነገሮችን እንኳን ታሳካለህ፡፡ እግዚአብሔር በእጆችህ ያስቀመጠውን የምታቆየው በጸሎት ነው፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን በሥጦታ የተቀበሉ ሰዎች አሉ፡፡ ዛሬ ያ ገንዘብ በኖ ጠፍቷል፡፡ እግዚአግሔር የሆነ ነገር ሊሰጥህ ይችላል፤ ያንን በረከት ለማቆየት ግን የእርሱ ጸጋ ጭምር ያስፈልጋል፡፡ የታላቅ አገልግሎት ፓስተር ነህ? ልንገርህ፣ አንተን በአገልግሎት ውስጥ ለማቆየት ጸሎት ያስፈልጋል፡፡ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለጸሎት የሚሮጠው ልምን ይመስልሃል?

በዚህች ምድር ላይ የማርጀት ህግ ይሰራል፡፡ ሁሉም ነገር እየበሰበሰ    ነው፡፡ ንግድህ እየበሰበሰ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንህ እየበሰበሰች ነው፡፡ ህይወትህ ራሱ እየበሰበሰ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠህን ነገር ሁሉ ለማቆየት በጸሎት ውስጥ የእግዚአብሔር ኃይል ያስፈልጋል፡፡

መርህ ቁጥር 5፡- ጸሎት ውጤታማ እንዲሆን ልማድ መሆን አለበት

ዶስቶዬቭስኪ የሚባል አንድ ሰው የሰው ህይወት ሁለተኛው አጋማሽ በመጀመሪያው አጋማሽ ከተገኙ ልማዶች የተዋቀረ ነው ብሏል፡፡

ፓስካል እንዲህ ብሏል የሰው ብርታት ከልማዳዊ ድርጊቶቹ የተዋቀረ ነው

በህይወትህ ታላቅ ሰው መሆን የምትፈልግ ከሆነ መልካም

Enjoying the preview?
Page 1 of 1