Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ስኬታማ አመራር: 8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች
ስኬታማ አመራር: 8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች
ስኬታማ አመራር: 8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች
Ebook377 pages1 hour

ስኬታማ አመራር: 8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች

Rating: 2.5 out of 5 stars

2.5/5

()

Read preview

About this ebook

ስኬታማ አመራር

 

8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች

 

በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ የተገኙት ከአዲሱ መደበኛ ትርጕም ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ ወይም የትኛውንም የመጽሐፉን ክፍል በማንኛውም መልኩ የማባዛት መብትን ጨምሮ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከባሪኔ ኤ. ኪሪሚ በጽሑፍ በተገኘ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የዚህ መጽሐፍ የትኛውም ክፍል በምንም ዓይነት መልኩ ሊባዛና፣ በመደበኛነት ሊገኝ በሚችልበት መልኩ በማናቸውም ስፍራ፤ በመረጃ መረቦች፣ በፎቶ ኮፒ ተባዝቶ ወይም በትረካ መልኩ ሊሰራጭ አይችልም፡፡ ይህንን መጽሐፍ ወይም የዚህን መጽሐፍ የትኛውንም ክፍል በሌላ ቋንቋ ተርጕሞ ለማሳተም የሚሰጥ መብት ከደራሲው ጋር በመዋዋል ብቻ ሊገኝ ይችላል፡፡ ይህ ኅትመት የተነሣውን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ ጠቅለል ያለ መረጃን የያዘ ሲሆን፣ የተዘጋጀውም ቀልብን የሚስብ ምንባብ እንዲሆን ተደርጎ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሲታተም፣ ሲሰራጭና ሲሸጥ አሳታሚውም ሆነ ደራሲው ሃይማኖታዊ፣ ቤተሰብ-ነክ፣ ሕጋዊ፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ የመዋዕለ ንዋይ አጠቃቀም፣ ገንዘብ-ነክ እንዲሁም ማንኛውንም ሙያዊ የምክር አገልግሎት ለመስጠት አስበን እንዳልሆነ ተገንዘቡልን፡፡ እንዲህ ያለው የምክር አገልግሎት የተፈለገ እንደ ሆነ ወደ የባለሙያዎቹ መሄድ ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ ለማስፈር የተቻለንን ጥረት ሁሉ አድርገናል፡፡ ሆኖም፣ አሳታሚውም ሆነ ደራሲው ለአጠቃቀሙ፣ ወይም ሦስተኛ አካል ሊያነሣ ለሚችለው የባለመብትነት ወይም ሌላ የመብት ሕጋዊ ጥሰት ኃላፊነቱን አንወስድም፡፡

ባሪኔ ኤ. ኪሪሚ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

Languageአማርኛ
Release dateApr 13, 2020
ISBN9781393735588
ስኬታማ አመራር: 8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች

Related to ስኬታማ አመራር

Related ebooks

Reviews for ስኬታማ አመራር

Rating: 2.6666666666666665 out of 5 stars
2.5/5

3 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ስኬታማ አመራር - Kirimi Barine

    በመጽሐፉ ከተጠቀሙ ሰዎች የተቸረ አድናቆት

    ኪሪሚ ባሪኔ የስኬታማ አመራር አስፈላጊነት በቅጡ ገብቶታል፡፡ የተማረው ትምህርት ከሕይወት ልምዱ ጋር ተዋህዶ መልእክቱ በየትኛውም የሕይወት አቅጣጫ ለሚተጉ መሪዎች ጠቃሚና ጊዜውን የጠበቀ እንዲሆንላቸው አድርጓል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልእክትን ወደ ንግዱና ወደ ትምህርቱ ዓለም አቅርቧል፡፡ ይህንን መጽሐፍ ለማንበብ የታደሉትን ሁሉ የምንጊዜም የአገልጋይ-መሪነት አርአያ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመራል፡፡

    ሲ. ጄን ዊልክስ፥ ፒ. ኤች. ዲ የጂሰስ ኦን ሊደርሺፕ ደራሲ ዩ. ኤስ. ኤ

    መንፈሳዊ ባሕርይን የተላበሱ እና የእግዚአብሔር ብርቱ ክንድ በማንነታቸው የሚገለጥባቸው ኃይልን የተሞሉ ቆራጥ መሪዎች ለመሆን ትፈልጋላችሁ? እግዚአብሔር በሕይወታችሁ ያስቀመጠውን የመሪነት ጥሪ ለማከናወን ዕምቅ መሻት አላችሁ? እንዲያ ከሆነ፣ ይህንን መጽሐፍ እንደምትገዙት ርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህ ስኬታማ አመራር፡- 8 ማወቅ የሚኖርባችሁ አስፈላጊ መርኆች የሚለው የኪሪሚ ባሪኔ መጽሐፍ አመራርን በተመለከተ አዲስ ዕይታን የሚያቀርብላችሁ ሲሆን፣ አመራርን በተመለከተ ያላችሁን አስተሳሰብ አዎንታዊ በሆነ መልኩ የሚያዳብሩ ጠቃሚ መርኆችንም ያካፍላችኋል፡፡ ባሪኔ እንደሚያሳየን፣ አመራር በአንድ ሰሞን የሚጠናቀቅ ቀላል ግብ ሳይሆን፣ ጊዜን የሚጠይቅ ሂደት ነው፡፡ ውጤታማ መሪ መሆን ካለባችሁ እንዴት መምራት እንዳለባችሁ ለመረዳት ሁልጊዜም ለመማር የተዘጋጃችሁ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡

    ሪቻርድ ብሮት ኤግዝኪውቲቭ ዳይሬክተር፣

    ሲቲ ክርስቲያን ፐብሊሺንግ፣ ኦሬገን

    ዩ. ኤስ. ኤ

    የዚህ መጽሐፍ ይዘት አመራርን በተመለከተ ያለኝን አስተሳሰብና ልምምድ በአጠቃላይ ቀይሮታል፡፡ ስኬታማ አመራር የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በአመራር እሳቤዎች ላይ ቀመር እና መላምቶችን አይደረድርላችሁም፡፡ በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በጠቅላላው ማኅበረሰብ ውስጥ የአሁኑና የወደ ፊቱ አመራር ላይ አብዮት የማስነሣት አቅም ያላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊና ተግባራዊ መርኆች አካትቶልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረቱ ተጨባጭ ተግባራዊ ሁኔታዎችን ያካተተ በመሆኑ በሚያነብበው በማንኛውም ሰው ውስጥ የተደበቀውን የመሪነት ብቃት የሚገልጥና ገበያ ላይ ከሚገኙት በጣት የሚቆጠሩ መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ስለ አመራር ጥርት ያለ እና በቅጡ የተብራራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አተያይ እንዲኖረው የሚናፍቅ መሪ ሁሉ ሊያነብበው የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡

    ቄስ ስቴፈን ኬ. ባሪኔ አፍሪካን ሚኒስትሪ ፓስተር፣

    ክሮስሮድስ ፌሎሺፕ ቸርች፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ዩ. ኤስ. ኤ

    በእያንዳንዱ ሳይንሳዊ ሙከራ ሂደት ወደ አንድ የታመነ ማጠቃለያ መድረስ የሚቻለው አንድ ጊዜ የተመዘገበው ውጤት ተደጋግሞ የተገኘ እንደ ሆነ ነው፡፡ ባሪኔ በገዛ ሕይወቱ ውስጥ ካለፈበት የመሪነት ተሞክሮ በመነሣት ሁሉም መሪዎች ሌሎችን በሚመሩ ጊዜ ሁሉ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሞላበት የአገልጋይ-መሪነት አርአያ የመሆን ግዴታ እንዳለባቸው ደምድሟል፡፡ የስኬታማ አመራር አንባቢዎች ሁሉ የዚህ ሙከራ መገለጫዎች ሆነው የድምዳሜውን መርኆች እውን እንደሚያደርጓቸው ተስፋዬ ነው፤ እንዲያም እንዲሆን እጠብቃለሁ፡፡

    ትሬቮር ቡሎር፣ ካናዳ

    እያንዳንዱ መሪ የሚገጥመው ፈተና አመራር ምን እንደ ሆነ መረዳት ነው፡፡ አፍሪካ ለዚህ ፈተና የሚሰጠው ምላሽ የተዛባ እንዲሆን ያደረጉ አያሌ መሪዎች አሏት፡፡ ይህንን የአፍሪካውያን ችግር በጥልቁ የተገነዘበው ባሪኔ በአመራራችን ውጤታማ እንድንሆን የሚያግዙንን ወሳኝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርኆች ነቅሶ አውጥቶልናል፡፡ ይህ የግሉን የአመራር ጕዞ እና መረዳት ሰውኛን በተላበሰ ሁኔታ የሚያቀርብልን አፍሪካዊ ደራሲ ልብን የሚያነሣሣ ሥራ ነው፡፡

    ዴቪድ ካዳሊ፣

    የሊደርስ ሪሶርስ ኪት ደራሲ

    ዩዝ ፎር ክራይስት ሪጅናል ዳይሬክተር፣ ኢስት ኢንዲያን አይላንድ ኔሽንስ፣

    ሳውዝ አፍሪካ

    ይህንን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ እንዲህ ያለ ልዩ መረጃ ሊያዘጋጅልን የቻለ ሰው በአመራር የካበተ ልምድ እንዳለው አያጠራጥርም፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ባሪኔ የመሪነትን ነባራዊ ሁኔታ፡- ጥሪውን፣ ፈተናዎቹን፣ ግጭቶቹን፣ የዝግጁነትን አስፈላጊነት፣ እሴቶቹን፣ መርኆቹን እንዲሁም ዋነኛ ቁልፍ የሆነውን በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን በጠራ ሁኔታ የምንረዳበት መንገድ አኑሮልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ በዓለም ዙሪያ የምናገኛቸውን እጅግ ጠቃሚ የመሪነት መርኆች ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌዎች ጋር በማዛመድ የመሪነት ልምምዳችን የላቀ እንዲሆን ያግዘናል እንዲህ ያለውን ልዩ ስጦታ ሊያበረክትልን የሚችለው እነዚህን እሴቶች በዕለት ተዕለት የአመራር ሕይወቱ ውስጥ የሚተገብራቸው፣ እና ለሚወስናቸው ውሳኔዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈልግ ሰው ብቻ ነው፡፡

    ፓስተር ዴቪድሰን ፍሬይታስ፣ ብራዚል

    ይህ መጽሐፍ አመራርን በተመለከተ የፈጠጡ እውነታዎችን ያከማቸ

    ‹ቤተ መዛግብት› ነው፡፡ ብቅ ብቅ እያሉ የሚገኙ መሪዎችም ሆኑ አንቱ የሚባሉት ቢያነቡት ሰፊ ጥቅም ያገኙበታል፡፡ ለአዕምሯችን ከመናገር አልፎ፣ የልብ እና የነፍሳችንን ጥልቀትም ጭምር ይዘልቃል፡፡

    ቄስ ኒክ ምባይ፣

    ፓስተር፣ ቲካ ሮድ ባፕቲስት ቸርች፣ ናይሮቢ፣ ኬንያ

    ‹‹ስኬታማ አመራር እንዲያው ስለ መሪነት በማውራት ብቻ አይገታም፡፡ ጠለቅ ብሎ ስለ አመራር መሠረታውያን ያወያየናል፡፡ ይህ መጽሐፍ የመሪነት ኃላፊነት ላለበት ሰው ሁሉ ይጠቅማል፡፡››

    ዳንኤል ደብሊው. ዋባላ

    የሪዲስከቨሪንግ ዘ ፐርል ኦፍ ሰርቫንትሁድ ደራሲ ናይሮቢ፣ ኬንያ

    ወዳጄ ባሪኔ በዚህ መጽሐፉ ውስጥ፡- ‹በዓለማችን ውስጥ ያለው ቀውስ ከአመራር እጥረት የመነጨ ይሆንን?› የሚል መሠረታዊ ጥያቄን ያነሣል፡፡ ይህ ነገር ለዓለማችን ብቻ ሳይሆን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው መሪዎች ላጠሯት ቤተ ክርስቲያንም ጭምር እውነትነት አለው ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህን ጥሩ መጽሐፍ መሪዎች እና ተመሪዎች ሁሉ እንዲያነብቡት እጋብዛለሁ፡፡

    ፓስተር አያድ ቤባዌ፣ ግብጽ

    ኪሪሚ ባሪኔ በጻፈው መልኩ በአመራር ላይ ጥልቅ እና ተግባራዊ መንገዶችን የከተቡ ብዙ ጸሐፊዎች የሉንም፡፡ መጽሐፉ ለአመራር ያለውን ልብ እና እምቅ መሻት ያሳያል፡፡ ይህንን መጽሐፍ ብታነብቡት አመራራችሁ ፈጽሞ እንደ ነበረው እንደማይቀጥል ስለ ማውቅ እንድታነብቡት አበረታታችኋለሁ፡፡

    ኩስናዲ ኩናዊ

    የሜታኖያ ፐብሊሺንግና ቡክ ስቶርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ

    ጃካርታ፣ ኢንዶኔዥያ

    ጌታችን በየጊዜው ሰዎችን፣ ሁኔታዎችን ወይም . . . አንድን መጽሐፍ ትኩረታችንን ወደ እርሱ እንድንመልስ ለማድረግ ይጠቀምባቸዋል፡፡ በባሪኔ ኪሪሚ የተጻፈውን ስኬታማ አመራር፡- 8 ማወቅ የሚኖርባችሁ አስፈላጊ መርኆች ባነበብሁ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ መጽሐፉን በመጠቀም በሕይወቴ ወዳስቀመጠው ጥሪ ሲመልሰኝ አስተውያለሁ፡፡ የሥርዓት አጥባቂነትን፣ የመሀል ሰፋሪነትንና በራስ ማስተዋል ብቻ የመደገፍን እግረ-ሙቅ አውልቄ ጥዬ ወደ ጠራኝና ወደሚያስታጥቀኝ ጌታ ዘወር ብያለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ መንፈሳዊ ጤናዬ ወደ መስመር እንዲመለስ በሐኪም የታዘዘ ኪኒን ያህል የማንቂያ ደወል ሆኖ አገልግሎኛል፡፡

    ዳንኤል ስኮት ሜይስ አውስትራሊያ

    መታሰቢያነቱ፡-

    በዚህ መጽሐፍ ያካፈልኋችሁን መርኆች በቀዳሚነት ሲተገብር ላየሁበት ወደ ጌታ ለተሰበሰበው  ለአባቴ ቄስ ፊንሀስ ባሪኔ፡፡ በጌታ የምደክመው ድካም ከንቱ እንዳልሆነ እንዳደንቅ አድርጎኛል፡፡

    Successful Leadership

    8 Essential Principles You Must Know

    © Copyright 2007 by BARINE A. KIRIMI

    በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሙሉ የተገኙት ከአዲሱ መደበኛ ትርጕም ነው፡፡

    ይህንን መጽሐፍ ወይም የትኛውንም የመጽሐፉን ክፍል በማንኛውም መልኩ የማባዛት መብትን ጨምሮ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከባሪኔ ኤ. ኪሪሚ በጽሑፍ በተገኘ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የዚህ መጽሐፍ የትኛውም ክፍል በምንም ዓይነት መልኩ ሊባዛና፣ በመደበኛነት ሊገኝ በሚችልበት መልኩ በማናቸውም ስፍራ፤ በመረጃ መረቦች፣ በፎቶ ኮፒ ተባዝቶ ወይም በትረካ መልኩ ሊሰራጭ አይችልም፡፡ ይህንን መጽሐፍ ወይም የዚህን መጽሐፍ የትኛውንም ክፍል በሌላ ቋንቋ ተርጕሞ ለማሳተም የሚሰጥ መብት ከደራሲው ጋር በመዋዋል ብቻ ሊገኝ ይችላል፡፡

    ይህ ኅትመት የተነሣውን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ ጠቅለል ያለ መረጃን የያዘ ሲሆን፣ የተዘጋጀውም ቀልብን የሚስብ ምንባብ እንዲሆን ተደርጎ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሲታተም፣ ሲሰራጭና ሲሸጥ አሳታሚውም ሆነ ደራሲው ሃይማኖታዊ፣ ቤተሰብ-ነክ፣ ሕጋዊ፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ የመዋዕለ ንዋይ አጠቃቀም፣ ገንዘብ-ነክ እንዲሁም ማንኛውንም ሙያዊ የምክር አገልግሎት ለመስጠት አስበን እንዳልሆነ ተገንዘቡልን፡፡ እንዲህ ያለው የምክር አገልግሎት የተፈለገ እንደ ሆነ ወደ የባለሙያዎቹ መሄድ ተገቢነት ይኖረዋል፡፡

    የተሟላና ትክክለኛ መረጃ ለማስፈር የተቻለንን ጥረት ሁሉ አድርገናል፡፡ ሆኖም፣ አሳታሚውም ሆነ ደራሲው ለአጠቃቀሙ፣ ወይም ሦስተኛ አካል ሊያነሣ ለሚችለው የባለመብትነት ወይም ሌላ የመብት ሕጋዊ ጥሰት ኃላፊነቱን አንወስድም፡፡

    ባሪኔ ኤ. ኪሪሚ

    መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

    ምስጋና

    ልዩ ምስጋናዬን ለሚከተሉት አቀርባለሁ፡-

    አመራሬን ለታገሣችሁ ለባለቤቴ ጆይስና ልጆቻችን አልቪንና አድሪያን፡፡ ስሕተቶቼን እና ድክመቶቼን በመቀበል እና ስኬቴን በመጋራት በእጅጉ ባለውለታዎቼ ናችሁ፡፡ በዘመን መጨረሻ ያላችሁኝ ቀሪ ሀብቶቼ እናንተው ናችሁ፡፡

    የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን እግዚአብሔርን መፍራት ላስተማራችሁኝ ለወላጆቼ፡፡

    የደቀ መዝሙርነት እና የአመራር ሥልጠናን በምወስድበት ወቅት ሕይወቷን ላካፈለችኝ ለጂል ብራንየን፡፡ ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር አትረፍርፎ ይባርክሽ፡፡

    ለጌታ ያላችሁ መሰጠት እና አገልግሎት ለልቤ ብርቱ መነሣሣት

    ላደረገለት ለስቴፈን እና ሜሪ ባሪኔ፡፡

    ለእናንተና ከእናንተ ጋር በነበረኝ የመሪነት አገልግሎት ውስጥ ብዙ ትምህርት እንደምቀስም ያመናችሁብኝ ቄስ ኒክ ምባይና ታላቁ የካህዋ ሱካሪ ባፕቲስት ቸርች ቤተሰብ በአንድ ወቅት የመሪነት ብቃቴን በየትኛውም ሁኔታ ፈትናችሁ ባታውቁም፣ እንድመራችሁ ስለ ፈቀዳችሁልኝ አመሰግናችኋለሁ፡፡

    በፒ.ኤ.ሲ.ሲ ውስጥ የመሪነት ኃላፊነትን እንድወስድ ለገፋፋችሁኝ ለከርክ ካውፌልት እና ቄስ ዊልፍ ሂልዴብራንት፤ እዛ በነበርኩ ጊዜ ሳለሁ በጥልቅ የማደግን ዕድል አግኝቻለሁ፡፡

    በወረቀት ያሰፈርሁት ጽሑፍ ለአሳታሚ ድርጅት ለማቅረብ የሚበቃ ረቂቅ እንዲሆን ላገዝሽኝ ኤስተር ኒያጋ፡፡

    በጥሬው ረቂቅ ላይ ለደከማችሁት ለዊልሰን ማካሪያና ለካትሪን ኒያጋ፡፡ ለዕድገቴ ስፍራ በመስጠት ባጋጠሙኝ ፈተናዎች ውስጥ የመሪነት ብቃቴን

    አጥርታችሁ ለፈተናችሁ የኤቫንጄል ቤተሰብና አጠቃላይ የፒ.ኤ.ሲ.ሲ ማኅበረሰብ በአጠቃላይ፡፡

    የሆሊዴይ ባይብል ክለብስ እና አፍሌም ኢንተርናሽናል አብሮ ሠራተኞች፣ ወዳጆችና ባልደረቦች ሁሉ፤ እንደ መሪ እንዳገለግላችሁና በዚያ ውስጥ አመራርን በተመለከተ በሌላኛው የባሕሩ ጫፍ ያሉ ጠቃሚ ትምህርቶችን እንድመለከት ዕድልን ሰጥታችሁኛል፡፡

    የረቂቁን ክፍሎች አንብባችሁ መጽሐፉ አሁን ላለበት ሁኔታ እንዲበቃ ጠቃሚ አስተያየቶቻችሁን ለሰጣችሁኝ ወዳጆቼ፡፡ ስማችሁን በተናጠል ያልጠቀስሁ እንደ ሆነ አስቤበት እና አቅጄበት እንዳልሆነ ተረዱልኝ፡፡

    የሁላችሁም ውለታ አለብኝ፡፡

    ማውጫ

    በመጽሐፉ ከተጠቀሙ ሰዎች የተቸረ አድናቆት..................................ii

    ምስጋና...............................................................................ix

    መቅድም...............................................................................xii

    መግቢያ...............................................................xviii

    ክፍል አንድ፡- መሠረታውያኑ

    1. የመሪነት ተግዳሮት............................................................20

    2. አመራርን መረዳት..............................................................33

    ክፍል ሁለት፡- መርኆቹ

    1. አመራር ጥሪ ነው.............................................................49

    2. አመራር ዝግጅትን ይፈልጋል................................................68

    3. ውጤታማ መሪዎች በእግዚአብሔር ይተማመናሉ............................80

    4. አመራር ለፈሪዎች አይሆንም...............................................92

    5. መሪዎች ግጭት ይገጥማቸዋል..............................................109

    6. አመራር ባሕርይ ነው......................................................121

    7. የእርስ በርስ ግንኙነት፡- የውጤታማ አመራር ቁልፍ................135

    8. ዕድሜ ቊጥር ብቻ ነው .........................................................144

    ክፍል ሦስት፡- ከዚያ በኋላስ?

    አመራር፡- የእናንተ ኃላፊነት.............................................150

    ድኅረ ታሪክ፡- አመራራችሁን ምሉዕ አድርጉት ................................158

    ማጣቀሻ ምንባብ ....................................................................165

    ተቀጥላዎች......................................................................172

    መቅድም

    ሪዎች የዘወትር ተማሪ ሊሆኑ ይገባል፤ አለዚያ ዛሬ መማር ሲያቆሙ፣ ነገ በውጤታማነት መምራት እንዳይችሉ ይሆናሉ፡፡

    መሪዎች መቼም ሆነ መቼ ትምህርታቸውን ስለማያጠናቅቁ፣ ‹የምረቃ በዓል› አይኖራቸውም፡፡ እንዴት መምራት እንዳለባቸው ተጨማሪ ዕውቀት ለማግኘት የማያቋርጥ ጥማት በውስጣቸው አለ፡፡ መረዳታቸውን በተመለከተ ያለውን ክፍተት በተጨማሪ ዕውቀት፣ ክህሎትን በማዳበርና በትግበራ ሊሞሉ ይገባል፡፡ ያ ክፍተት በሚሞላበት ጊዜም እንኳ የነባራዊ ሁኔታዎችን ለውጥ እና የተለያየ ማንነት ካላቸው ሰዎች ጋር የመሥራትን ፈተና ያማከለ ሊሆን ይገባል፡፡ ወደ ውጤታማ መሪነት የሚወስደው መንገድ አብዛኛውን ጊዜ አደገኛ ፈንጂዎች፣ የእሳተ ገሞራ ጉድጓዶች የሞሉበትና ግድየለሽ፣ ቸልተኛ ወይም ተንኮለኛ ሰዎች የተቀያሪ መንገድ ምልክት ማደናገሪያ እንዲሆን ያስቀመጡበት ይሆናል፡፡ አንዳንዶች ሲደሰቱ ሌሎቹ ለምን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1