Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ
Ebook293 pages2 hours

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ

Rating: 4 out of 5 stars

4/5

()

Read preview

About this ebook

የብሄር ፌዴራሊዝም ወይስ መልካምድራዊ ፌዴራሊዝም? ህገ መንግሥት ማሻሻል ወይስ መለወጥ፣ የአዲስ አበባ ባለቤትነት፣ የአሰብ ባለቤትነት፣ የክልልነትና የማንነት ጥያቄ፣ ብሄራዊ ቋንቋ፣ አንቀፅ 39፣ ባንዲራ፣ አርማ፣ ዘረኝነት፣ ሙስና፣ ምርጫ … የሀገሪቱን መሠረታዊ ችግሮች ከመፍትሄአቸው ጋር እንመለከታለን፡፡

Languageአማርኛ
PublisherTariku Tefera
Release dateMar 22, 2020
ISBN9781393910688
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ

Related to የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ

Related ebooks

Reviews for የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ

Rating: 4 out of 5 stars
4/5

4 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ - Tariku Tefera

    ማውጫ

    ምህፃረ ቃል(Abbreviations)

    መቅድም 

    1. የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በአጭሩ

    1.1. የአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት

    1.2. የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት

    1.3. የኮሎኔል መንግሥቱ ዘመነ መንግሥት

    1.4. የህወሀት ኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት

    2. የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ

    2.1. የብልፅግና ፓርቲ (የኦዴፓ ኢህአዴግ)

    2.2. ፅንፈኛ የብሄር ፖለቲካ - ጠባብተኝነት

    2.3. ፅንፈኛ የአንድነት ፖለቲካ - ትምክህተኝነት

    2.4. አጋጣሚ እየጠበቀ ያለ ኃይማኖታዊ ፅንፈኝነት

    2.5. አወዛጋቢው የፓርቲዎች ብዛትና ከጀርባቸው ያለው እውነታ

    2.6. 7ቱ የአክቲቪዝም ቡድኖች

    2.7. የፖለቲካ የቴሌቪዥንና የራዲዮ ጣብያዎች

    2.8. ህገ መንግሥት

    2.8.1. የፌዴሬሽን ህገ መንግሥት እየተባለ ሀገር በሚከፋፍል የኮንፌዴሬሽን ፅነሰ ሀሳብ የተሰራ ህገ መንግሥት መሆኑ

    2.8.2. አድሏዊ መሆኑ

    2.8.3. ለወደፊቱ የሠላም ጠንቅ የሆኑ ሀሳቦችን የያዘ መሆኑ

    2.8.4. ሀገርን ባለቤት ዜጎችን ደግሞ የሀገር የባለቤትነት መብት የነፈገ   ህገ መንግሥት መሆኑ

    2.8.5. በባለቤትነት መንፈስ በጥንቃቄ ያልተሰራ ህገመንግሥት መሆኑ

    2.8.6. ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ህወሀታዊ ህገ መንግሥት መሆኑ

    3. ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ እየገሰገሰ ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ

    ––––––––

    4. ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ ችግር ዘላቂ የመፍትሄ አቅጣጫ

    4.1. ህገ መንግሥታዊ የመፍትሄ አቅጣጫ

    4.1.1. ከብሄርና ከመልካምድራዊ ፌዴራሊዝም አንዱን መምረጥ

    4.1.2. የኮንፍዴራል ህገመንግሥቱን የፌዴራል ህገመንግሥት ማድረግ

    4.1.3. ከብሄር ሽኩቻ ገለልተኛ የሆነ ብሄራዊ ቋንቋ መጠቀምና   የፌዴራል መንግሥቱን ከብሄር ፖለቲካ ነፃ ማድረግ

    4.1.4. ሥርአተ መንግሥቱ ላይ ማስተካከያ ማድረግ

    4.1.5. የአዲስ አበባ ከተማን ባለቤትነት ግልፅ ማድረግ

    4.1.6. የአሰብ ባለቤትነት ላይ ግልፅ አቋም መያዝ

    4.1.7. ከአንቀፅ 39ና ከሀገር ሉአላዊነት አንዱን መምረጥ

    4.1.8. ክልሎችን በቋሚነት ማዋቀር

    4.1.9. ሁሉንም የሚያግባባ ሀገራዊ ባንዲራና አርማ መጠቀም

    4.1.10..............................................................ዜግነት ላይ የተጣለውን ገደብ ማንሳት

    4.1.11..............................................................ለአዲስ ህገመንግሥት ህዝበ ውሳኔ(Referendum) ማድረግ

    4.2. ከህገ መንግሥት ወረድ ብለው ባሉ ህጎችና አሰራሮች ሊፈቱ የሚገቡ   የሀገሪቱ መሠረታዊ ችግሮች

    4.2.1. ጠንካራ የትምህርት ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.2. ጠንካራ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.3. ጠንካራ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.4. ጠንካራ የግብርና ልማት ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.5. ከአድሏዊነት የፀዳ የህዝብ ምጣኔ ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.6. ከአድሏዊነት የፀዳ የፀረ ሙስና ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.7. ከአድሏዊነት የፀዳ የፀረ ዘረኝነት ፖሊሲ መቅረፅ

    4.2.8. ወጣቶችን በመልካም ስነምግባር ማነፅ

    4.2.9. ዜጎችን በሀገር ፍቅር ማነፅ

    4.2.10..............................................................ብሄራዊ ዕርቅና ሀገራዊ ተሀድሶ ማድረግ

    4.2.11................................................................ከፊት ለፊታችን ያለው ምርጫ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ

    5. ማጠቃለያ

    ምህፃረ ቃል(Abbreviations)

    ሀብሊ - የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ

    ህወሀት - ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ

    መአድ - የመላ አማራ ድርጅት

    መኢአድ - የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት

    መኢሶን - የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ

    ሲአን - የሲዳማ አርነት ንቅናቄ

    ቤጉህዴፓ - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

    ብአዴን - የብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

    ትዴት - የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር

    አብን - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ

    አዴፓ - የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

    አፍዴፓ - የአፋር ፍትሀዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

    ኢሀን - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ

    ኢህአዴግ - የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት

    ኢህአፓ - የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ

    ኢሶዴፓ - የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

    ኢዜማ - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ

    ኢዲዩ - የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ዩኒየን

    ኢዴፓ - የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

    ኢጭአት - የኢትዮጵያ ጭቁኖች አብዮታዊ ትግል

    ኦህዴድ - የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት

    ኦብኮ - የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ

    ኦብነግ - የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር

    ኦነግ - የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

    ኦዴፓ - የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

    ኦፌኮ - የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ

    ወብን - የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ

    ወዝሊግ - የወዛደር ሊግ

    ደኢህዴን - የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

    መቅድም

    ኢትዮጵያ መንግሥታዊ አወቃቀርን የምታውቀው ከሺ አመታት በፊት ነው፣ ለዚህም ዘመናዊው ታሪክ፣ ቅዱሳት መፅሀፍትና አፈ ታሪኮች ምስክሮች ናቸው ይሁን እንጂ ዛሬም ሀገሪቱ የምትገኘው በባዶ ዲሞክራሲና በብዙ ስጋቶች ውስጥ ነው፣ ብዙ ሀገራት ከኋላዋ ተነስተው አልፈዋት የሚያስቀና የዲሞክራሲ እድገት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፣ ኢትዮጵያ ግን ያሳለፈችው ታሪክ በአብዛኛው የጠገበውን አምባገነን በተራበው አምባገነን የሚተካካበት የታሪክ ሂደት ነው፣ በዚህም ህዝቦች አልቀዋል፣ ኢኮኖሚው ደቋል፣ የህዝቦችና የሀገር አንድነት ችግር ውስጥ ገብቷል ...

    የሚያሳዝነው ደግሞ ህዝቡ ለውጥ እንዲመጣ በየዘመናቱ እነዚህን አምባገነን መንግሥታትን በመቃወም ከሠላማዊ ሰልፍ አንስቶ እስከ ትጥቅ ትግል ድረስ የተለያዩ ጥረቶችን አድርጎ፣ ለውጥም ተደርጎ፣ ነገሮች በመልካም ሁኔታ ተጀምረው በሂደት ወደ ዜሮ የሚመለስበት የታሪክ ሂደት ነው፡፡

    ከሁሉ አምባገነን መሪዎች ደግሞ በተለየ የህወሀት-ኢህአዴግ ሀገሪቱን በእጅጉ ጎድቷታል፣ ህወሀት በመገንጠል ፖለቲካ የተመሠረተ በመሆኑ፣ ብዙ ጥንቃቄ የሚጠይቀውን የብሄር ፌዴራሊዝምን በዘረኝነት የከፋፍለህ ግዛ ሴራ በመተግበሩ ለሀገሪቱ የ27 አመታት የምጥ ጊዜ ፈጥሮ፣ ሉአላዊነቷንም አስጊ ሁኔታ ውስጥ አስገብቶ፣ እራሱም እጅግ የሚሰቀጥጡ ድርጊቶችን በዜጎችና በሀገር ላይ ሲፈፅም ቆይቷል፡፡

    ዛሬ ስልጣን የያዘው ቡድንም ሁሉንም አካላት አሳትፎ፣ የሽግግር ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ፣ የሀገሪቱን መሠረታዊ ችግር በመፍታት ሀገሪቱን ከማሸጋገር ይልቅ አትኩሮት ያደረገው የፓርቲውን ወንበር በማመቻቸት ላይ ነው፣ አብዛኞቹ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከልም ያለው ችግር ዘርፈ ብዙ ነው፣ ዛሬ ሀገራችን ውስጥ፣ በሁለት፣ ይህም በብሄርና ሀገራዊ አደረጃጀት የሚከፈሉ፣ ከ107 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፣ ይህ ሁሉ ልዩነትም የመጣው የሀገሪቱ ፖለቲካ እጅግ ታፍኖ የቆየ በመሆኑና ህወሀት በዘራው የዘረኝነት ከፋፍለህ ግዛ ሴራ እርስ በርስ መተማመን በመጥፋቱ ምክንያት ነው፡፡

    ከሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ የሀገሪቱ ፖለቲካ ችግር የፓርቲ ርዕዮተ ዓለም/ፕሮግራም ጋር ሳይደርስ ከወዲሁ ብዙ የቤት ስራዎች ያሉበት መሆኑ ነው፣ ፖለቲካው የርዕዮተ ዓለም(ሊበራል ዲሞክራሲ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ልማታዊ ዲሞክራሲ፣ ሶሻል ዲሞክራሲ ...) ክርክሮች ጋር መድረስ ይቅርና ገና ከህገ መንግሥት ጉዳይ ያልወጣ ፖለቲካ ነው፡፡

    በዚህም ነው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የርዕዮተ ዓለም ክርክር የማንመለከተው፣ የአብዛኞቹን ታዋቂ ፓርቲዎች ርዕዮተ ዓለም እንኳን የማናውቀው፣ እነሱም ርዕዮተ ዓለማቸውን አይናገሩም ቢናገሩም የሚያዳምጣቸው ሰው የለም፣ የህዝቡና የፖለቲካ ፓርቲዎች አትኩሮት ህገ መንግሥቱ ላይ ባለው፣ የብሄር ፌዴራሊዝም ወይስ የጂኦግራፊ፣ የብሄራዊ ቋንቋ ጉዳይ፣ የአዲስ አበባ ባለቤት ጉዳይ ... ላይ ነው፡፡

    በዚህም የሀገሪቱ ፖለቲካ ገና ህገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ያለ ጥሬ ፖለቲካ ነው፣ በዚህም የሀገሪቱ ፖለቲካ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት የሚችለው ከመሠረቱ ህገ መንግሥታዊ ችግሮችን በመፍታት ነው፡፡

    ይህቺ መፅሀፍም እንድትዘጋጅ ምክንያት የሆነው፣ ለዚህ የሀገሪቱ መሠረታዊ ችግር አስፈላጊው መሠረታዊ የመፍትሄ አቅጣጫ መሆኑን በመገንዘብ ነው፤ መሠረታዊ ነገር ለማስቀመጥም ከፖለቲካ ወገንተኝነት ገለልተኛ መሆን አስፈላጊ በመሆኑም መፅሀፏ የተዘጋጀችው ለሁሉም አማካይ በሆነ መንገድ ነው፣ በዚህም መፅሀፏ ለጊዜው በሁለቱም ፅንፈኞችና መሠረታዊ ለውጥ በማይፈልጉት ፖለቲከኞች ተወዳጅ የማትሆን ቢሆንም፣ እነዚህ ቡድኖች ግን መሸናነፍ እንደማይችሉ ቢሸናነፉ እንኳን መሸናነፍ የሚችሉት ከብዙ እልቂት ቦሃላ መሆኑ በጊዜ ሂደት የሚረዱት እውነታ በመሆኑ ሁሉንም የሚያማክል አስታራቂ ሀሳብ በጊዜ ማስቀመጡ አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡

    መፅሀፏ መሠረታዊውን የህገ መንግሥቱንና ከህገ መንግሥቱ ወረድ ብለው በፓርቲዎች ፖሊሲና ፕሮግራም መፈታት ያለባቸውን ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ ከመመልከቷ በፊት፣ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የፖለቲካ ባለድርሻዎችን ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ሴረኝነትና ሽኩቻ ተመልክታለች፣ ይህንን መመልከት ያስፈለገው ለክፋት ሳይሆን ሁሉም ያለበትን ድክመት፣ ጠንካሬና ሽኩቻ እንዲያስተውልና ሴረኝነቱንም ህዝብ የሚያውቀው መሆኑን ተረድቶ ከሴረኝነት በመመለስ አሁን ሀገሪቱ ላለችበት ችግርና ስጋት በመፍትሄ እንዲንቀሳቀስ በማሰብ ብቻ ነው፡፡

    በመቀጠልም መፅሀፏ የሀገሪቱ መሠረታዊ ችግር የሆነውን የዋናውን የህገ መንግሥቱን ችግሮችንና ሌሎች ከህገ መንግሥቱ ወረድ ብለው ባሉት የፓርቲዎች ፖሊሲ፣ ፕሮግራም፣ እስትራቴጂ ... መቀረፍ የሚገባቸውን ችግሮች ከነመፍትሄ አቅጣጫዎቻቸው ጋር በስፋት ተመልክታለች፤ ከሁሉም በፊት ግን ታሪኩን የማያውቅ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም እንደሚባለው መፅሀፏ ለዛሬ ችግራችን ትምህርት የሚሆኑንን የሀገሪቱን የፖለቲካ ታሪኮች አጠር አጠር አድርጋ ተመልክታለች፡፡

    በዚህም መፅሀፏ በሀገሪቱ ላይ ዘላቂ ሠላምና የህግ የበላይነት ማስፈን የሚቻልበትን፣ አስተማማኝ የዲሞክራሲና የኢኮኖሚ እድገት መሠረት መጣል የሚቻልበትን፣ ፖለቲካ ፓርቲዎችም ከህገ መንግሥታዊ ጉዳይ ወጥተው ወደ ርዕዮተ ዓለማዊ ጉዳይ ማለፍ የሚችሉበትን መንገድ ተመልክታለች፡፡

    መልካም ንባብ !!

    ምዕራፍ አንድ

    1.  የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በአጭሩ

    የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከእስልምናው ቁርአንና ከክርስትናው አዲስ ኪዳን በፊት በነበሩት ከአይሁድ ቅዱሳት መፅሀፍት (ብሉይ ኪዳን/ቶራ/ተውራት)  ጀምሮ ሲዘገብ የነበረ ታሪክ ነው፣ በነዚህ የኃይማኖት መፅሀፍት ውስጥ የተጠቀሱትን የኢትዮጵያውያን ታሪኮችን ስንመለከት ህዝቡ በጋርዮሽ ዘመን ውስጥ ሆኖ ነገር ግን በከፍተኛ ንቃተ ህሊና፣ ፍልስፍና፣ ስርአተ መንግሥት ... ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው፡፡

    ከመፅሀፍ ቅዱሱ ብንነሳ፣ የሙሴ አማት ኢትዮጵያዊው ካህን(ዮቶር)፣ ሙሴን ያስተማረው የመዋቅራዊ አስተዳደር ፍልስፍና ዛሬም ድረስ የዘመናዊው አመራር ሳይንስ ዘመናዊ ፍልስፍና ነው፣ የሳባ ንግሥት ይህንን ሁሉ ሀገር አቋርጣ ሰለሞን ጋር የሄደችው ለጥበብ በነበራት ጉጉት ነው፣ አሳ የተባለውን የእስራኤል ንጉሥ ሊገጥም አንድ ሚሊየን ጦር አደራጅቶ የዘመተው የኢትዮጵያ ንጉሥ  ምን ያህል ኃያል እንደነበረ እንመለከታለን፣ ነብዩ መሐመድ በዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት ፍልስፍናው ምጡቅነት የመሰከሩለት አልነጃሺ በተግባርም እንደዚያው ሆኖ ነው ያገኙት እንደዚሁ የኦሮሞን የገዳ አስተዳደራዊ ፍልስፍና ስንመለከት ቀድሞ የነበረው ትውልድ ምንም እንኳን እንደኛ አስራ ምናምን አመታት ባይማርም በከፍተኛ የዘመናዊነት ስነ ልቦና ውስጥ እንደነበረ ያሳያል፡፡

    የሚገርመው ደግሞ በዚያን ወቅት አብዛኛው ዓለም በጋርዮሽ ህይወት ውስጥ የነበረ መሆኑ ነው፣ የኛዎቹ ግን በወቅቱ በጋርዮሽነት ውስጥ አልነበሩም፣ የረቀቀ የኃይማኖት፣ የስነ ጥበብ፣ የሰብአዊ መብት፣ የዲሞክራሲ፣ የዲፕሎማሲ ... ፍልስፍናን ሲያራምዱ ነበሩ፡፡

    ይሁን እንጂ ይህ መንፈስ ከሆነ ትውልድ ቦሃላ ከሀገሪቱ ላይ ተሰልቧል፣ በቅዱሳት መፅሀፍትና በታሪክ መፅሀፍት ስለ ኢትዮጵያ የምንመለከተውን እውነታ ከዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ጋር ስናነፃፅር ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፣ መጨመር ይቅርና የነበረውን እንኳን ይዞ ማስቀጠል አልተቻለም፣  የሚያሳዝነው ደግሞ ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ከፊት ለፊታችን ልባችን የሚያሳርፍ ተስፋ መጥፋቱና በእንጥልጥል ምን ይመጣ ይሆን በሚል ግራ በተጋባ ፖለቲካ ውስጥ መኖራችን ነው፣ በዚህም አሁን ሀገሪቱ ቆም ብሎ የሚያስብ ትውልድ የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡

    ሀገሪቱ አሁን ላለችበት አስጊ ሁኔታ የመፍትሄ አቅጣጫ ከመመልከታችን በፊት ለዚህ ችግር ምክንያት የሆኑትን ታሪካዊ ዳራዎች በቅድሚያ መመልከቱ አስፈላጊ ነው፣ በዚህም ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ ያሉትን ተያያዥ ታሪካዊ ጉዳዮች በቅድሚያ እንመለከታለን፣ እዚህ ጋር የህወሀት ቀጥተኛ አስተዳደር ታሪክ ቢሆንም ድርጅቱ ግን ዛሬም በህይወት ያለና አገግሞም ተፅዕኖ መፍጠር የሚችልበት አቅም ስላለው የድርጅቱን ታሪክና የሴራ ፖለቲካ ከሌሎቹ በተለየ ሰፋ አድርገን እንመለከታለን፣

    1.1.  የአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት

    ኢትዮጵያ ቀደምት ሀገር ብትሆንም ሀገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜ ሂደት ውስጥ ቅርጿና መጠኗ ሲቀያየር ቆይቷል፣ ይህ ደግሞ መፅሀፍ ቅዱሱ ላይ ከተገለፀው፣ ከዩጋንዳ ተነስቶ ግብፅ ድረስ የሚዘረጋው ናይል ወንዝ  እኩል ከሚረዝም ግዛት አንስቶ እስከ ቅድመ ዳግማዊ ሚኒሊክ የተገነጣጠለች ኢትዮጵያ ድረስ ሲቀያየር የነበረ ግዛት ነው፡፡

    ይሁን እንጂ ከ1881-1905 የነገሡት አፄ ሚኒሊክ በመፅሀፍ ቅዱሱ ላይ የተገለፅውን የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ለማስመለስ ቢነሱም በአቅም ውሱንነትና በወቅቱ ከቅኝ ግዛት ጋር በነበሩ ውስብስብ ችግሮች ምክንያት ዛሬ ከምንመለከተው ኢትዮጵያ ቅርፅና መጠን በላይ ሄደው ነባሩን ከናይል ወንዝ ወዲህ የተባለውን የሀገሪቱን ወሰን ማስከበር አልቻሉም፣ በዚህም ብሄሮች ወደ ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት ተቆራርጠው ቀርተዋል፡፡

    ይሁን እንጂ ንጉሡ በዘመኑ ከብሄር እንኳን ወረድ ብላ ተገነጣጥላ የነበረችውን ኢትዮጵያ ወደ አንድ ሀገርነት ሊመልሱ ችለዋል፣ ለምሳሌ አፄው ወደ ኦሮሞ ምድር ሲመጡ ኦሮሚያ ዛሬ እንደምንመለከታት አንድ መሪ የሚያስተዳድራት ሀገር አልነበረችም፣ ከዚያ በወረደ የተበታተነ አመራር የአባ ጅፋር፣ የኩምሳ ሞሮዳ፣ የጆቴ ቱሉ ... በሚባሉ የየአካባቢ መሪዎች ሲትተዳደር ነበረ፣ ሌሎቹም ብሄሮች ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ነበረ፣ በዚህም አፄው የዛሬዪቱ ኢትዮጵያን አንድነት የሰሩ መሀንዲስ መሆናቸውን የማታበይ ሀቅ ነው፡፡

    አፄ ሚኒሊክ ከሌሎቹ ቀደምት ነገሥታት ይልቅ ሰፋ ያለ ራዕይ የነበራቸው በመሆኑም ከዚህ የሀገር አንድነት መልሶ ማቆም ስራ በተጨማሪ ዘመናዊውን ቴክኖሎጂ በማስፋፋትና ዘመናዊ ዲፕሎማሲን በመከተል ለሀገሪቱ ፈር ቀዳጅ ስራዎችን ሰርተዋል፣ ንጉሡ በወራሪው የኢጣልያን ጦር ላይ የፈፀሙት ጀብዱ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም እንድትታወቅና የኢትዮጵያን ጀግንነት በዓለም እንዲናኝ አድርገዋል፡፡

    አፄው ከነዚህ ተራማጅ አሰራሮቻቸው በተቃረኒ ደግሞ በወቅቱ አልገዛላቸው ያለው ህዝብ ላይ የተጠቀሙት አሰቃቂ እርምጃ ዛሬም ድረስ ሲያስወቅሳቸው ይታያል፡፡

    አፄ ሚኒሊክ እነዚህን ሁለቱን ገፅታዎች ይኑራቸው እንጂ ዛሬ ላይ በሁለቱ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ስለ አፄው የሚነገረው አንደኛው ገፅታቸው ብቻ ነው፣ ፅንፈኛ የአንድነት ቡድኖች የአፄውን መልካም ስራ እንጂ መጥፎ ስራቸውን አይቀበሉም፣ ፅንፈኛ ብሄርተኞች ደግሞ የአፄውን ጥፋት እንጂ በጎ ስራቸውን አይቀበሉም፣ የፅንፈኝነት ፖለቲካ አንድ አይኑ የታወረ ፖለቲካ በመሆኑ ሁለቱም ቡድኖች ላይ መፍረድ አይቻልም፣ አፄው ግን ሁለቱንም ገፅታ የነበራቸው ሰው ናቸው፡፡

    የሚገርመው ደግሞ አፄው በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍልም የተለያዩ ሰው ናቸው፣ በአንድ ብሄር ውስጥ እንኳን ቢሆን ስለ አፄው የተለያየ ግንዛቤ ነው የምንመለከተው፣ ለምሳሌ ኦሮሚያ ላይ የአርሲ፣ ባሌና የሐረር ኦሮሞዎች ከአፄው ጦር ጋር እጅግ የተቋሰሉ በመሆናቸው፣ አፄውን የሚመለከቱት በአውሬነት ነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሸዋ፣ የወለጋና የጂማ ኦሮሞዎች አፄውን ከሌሎቹ አምባገነን ነገሥታት የተለየ ንጉሥ አድርገው አይመለከቱም፣ አንዳንዶቹ እንደውም በወቅቱ ከነበረው የእስልምና መስፋፋት በተቃራኒ ለኃይማኖታቸው(ለክርስትና) ቁልፍ ስራ ሲሰሩ የነበሩ ሰው በመሆናቸው አፄውን በበጎ ጎንም የሚያነሷቸው አሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በወቅቱ ከሚኒሊክ ጎን ተሰልፈው አርሲዎችን ሲዋጉ የነበሩት የጦር አበጋዞች የነሱ አካባቢ ሰዎች በመሆናቸው ያንን የግፍ ታሪክ አይቀበሉትም፣ ይህንን እውነታም ለምሳሌ ያህል በአምቦው የኦሮማራ ስብሰባ ላይ የኦሮሚያው ፕሬዚዳንት ራስ ጎበናን የደገፉበትና ተመልሰው ደግሞ በአዲስ አበባው ኢሬቻ በዓል ላይ ሚኒሊክን በወቀሱበት ንግግሮች ውስጥ እንመለከታለን፣ ይሁን እንጂ ሚኒሊክን አርክሰን ጎበናን የምንቀድስበት አሰራር ሊኖር አይችልም፡፡

    ሚኒሊክ መራሹ ጦር በአርሲ ህዝብ ላይ ለሰራው ጭፍጨፋና የመሬት ወረራ ተጠያቂዎቹ በወቅቱ የነበሩት የሁለቱም የአማራና የኦሮሞ ነፍጠኞች ናቸው፣ ይህንንም እውነታ ዛሬም በአርሲ ህዝብ ስብጥር ውስጥ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ሊስተዋል የሚገባው ነገር አፄው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሲፈፅሙ የነበሩት ግፍ በኃ/ስላሴም ሆነ በደርጉ ዘመን ይባሱኑም በ21ኛው ክፍለ ዘመንም በህወሀት ሲፈፀም የቆየ መሆኑ ነው፣ በዚህ ላይ ደግሞ በየትኛውም ሀገር ምሥረታ ታሪክ ውስጥ ህዝብ ተሰብስቦ፣ መክሮበት በምርጫ የመሠረታት ሀገር የሌለች መሆኑና የ19ኛውን ክፍለ ዘመን አሰራር በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት፣ የዲሞክራሲና የህግ የበላይነት መስፈርት መመዘን የማይቻል መሆኑን ነው፡፡

    በዚህም የሰውን አካል በመቁረጥ ወንጀል ህወሀትን፣ ደርግንና ኃ/ስላሴን ዘሎ አፄውን ብቻ ለይቶ ተጠያቂ ማድረጉ አግባብ አለመሆኑና ይባሱኑ የሌላ ችግር ምልክት መሆኑን እንመለከታለን፣ ይህ ችግር ደግሞ አፄው ከሌሎቹ ነገሥታት በተለየ የሰሩት ስራ ተቃርኖ፣ ይህም የኢትዮጵያ አንድነት መሀንዲስነታቸውና የክርስትና አስፋፊነታቸው ነው፣ በዚህም አፄው ከሌሎች አምባገነን ነገሥታት ተለይተው እንዲወገዙ እየተደረጉ ያሉት ከመገንጠል ፖለቲካና ከኃይማኖት ጋር በተያያዘ መሆኑን እንመለከታለን፡፡

    1.2.  የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት

    በአፄ ሚኒሊክ ሞት ምክንያት እቴጌ ጣይቱና ልጅ ኢያሱ የተወሰኑ ጊዜያትን ሀገር ቢያስተዳድሩም፣ ከቆይታቸው እንደዚሁ ከተከተሉት ስርአት አንፃር ሀገሪቱ ላይ ያን ያህል የተለየ ነገር የሰሩ ወይንም ተፅዕኖ የፈጠሩ መሪዎች ስላልነበሩ ከሚኒሊክ በመቀጠል የኃ/ሥላሴን አመራር እንመለከታለን፡፡

    አፄ ኃ/ሥላሴ ከ1922 እስከ 1966 ድረስ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ ነበሩ፣ ንጉሡ በወቅቱ ለሀገሪቱ የፈጠሩት ጠንካራ ኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ ኢትዮጵያ በኢጣሊያን በተወረረችበት ጊዜ ለሀገሪቱ ነፃነት ብሎም ለጥቁሮች አንድነት ያደረጉት የዲፕሎማሲ ዘመቻ፣ የአፍሪካ ሀገራት ከቀኝ አገዛዝ ነፃ እንዲወጡ ያደረጉት ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ብዙ ያስመሰግናቸዋል፡፡

    ይሁን እንጂ ንጉሡ በዚህ የንግሥና ዘመናቸው በሀገሪቱ አመራር ስርአት ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሳያመጡ ከቀደምት አፄዎች የመጣውን የመደብ ችግር፣ ይህም ህዝብ ባላባትና ጭሰኛ ተብሎ የሚከፈልበትን አሰራርን ባለማስቀረታቸው፣ የወሎን ረሀብ ችላ በማለታቸውና ህዝቡ በተለያዩ ጊዜያት ሲያነሳባቸው የነበረውን ጥያቄ በአግባብ መመለስ ባለመቻላቸው የራሳቸውም ሆነ አጠቃላይ የአፄው ስርወ መንግሥት(Solomon Dynasty) ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያበቃ ምክንያት ሆነዋል፡፡

    1.3.  የኮሎኔል መንግሥቱ ዘመነ መንግሥት

    አፄ ኃ/ሥላሴ የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ባለመቻላቸው፣ በወቅቱ ብዙ ወጣት ውጪ ሀገር ተምሮ የውጪ ሀገራትን ዲሞክራሲ ተመልክቶ በመመለሱና

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1