Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ
መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ
መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ
Ebook128 pages39 minutes

መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

በዚህ ለየት ያለ ምጽሐፍ ውስጥ በልብ የሚጠኑ ቁልፍ የሆኑ የምጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ታገኛለህ። ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በልቡ ይዞ ነበር፤ እኛም ማድረግ አለብን! የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በልብ ለማጥናት እናልም እንዲሁም መልካም እና የትቀየረ ባህሪይ። የክርስቶስ ተከታዮች ነን!

Languageአማርኛ
Release dateAug 14, 2018
ISBN9781641357111
መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ

Related ebooks

Reviews for መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ - Dag Heward-Mills

    ምዕራፍ 1

    መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ማስታወስ ማለት ምን ማለት ነው?

    መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ማስታወስ ማለት የትልቅ አገልግሎት ትልቅ መሰረት ነው። ዛሬ ብዙ ሰዎች በትልቅ መሰረት ላይ አልቆሙም ስለዚህም በምድር ላይ ታላላቅ የእግዚአብሔር ስራዎችን ማድረግ አይችሉም።

    በከባድ ስራ እንዲሁም በመሰጠት እና በትህትና መንፈስ የእግዚአብሔርን ትልቅ ስጦታ የምትሸከምበት አስፈላጊ ባህሪ ማዳበር ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስን በልብ በማስታወስ አገልግሎትህ ትልቅ ወደሚባለው ከፍታ ይሄዳል።

    መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ማስታወስ ማለት ቁልፍ የሆኑ ጥቅሶችን በልብ አጥንቶ በመያዝ በአስፈላጊ ጊዜ በቃልህ መጥቀስ ነው።

    የኢየሱስ ተከታይ ሁን

    እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

    ማቴዎስ 419

    የዚህ አላማ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልቡ የሚያስታውስ የኢየሱስ ተከታይ እንዲያደርግህ እንደሆነ ልተረዳ ያስፈልጋል።

    በህይወትህ በየቀኑ አንድን የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ በልብህ የምትይዝበት ቀን ነው።

    በህይወትህ እያንዳንዱ ቀን መልካም እና የተሻለ ባህሪ የምታዳብርበት ትልቅ እድል ነው።

    ከሌሎች ሰዎች ጋር የምታደርጋቸው ጭውውቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ ለመያዝ እድል ይሰጥሃል።

    ከሚያምኑ ወንድሞች ጋር የምታደርጋቸው ጭውውቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ ለመያዝ እድል ይሰጥሃል።

    በሚቀጥሉት ገፆች ውስጥ እያንዳንዱ ክርስቲያን በልቡ ሊይዛቸው የሚገቡትን የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶችን ታገኛለህ። እያንዳንዳቸውን ጥቅሶች የመርጥኩተ እኔ ነኝ። ጥቅሶቹ እንዳሉ ለመጥቀስ የታሰቡ አይደሉም። በልብ ለመያዝ የሚጠኑ ናቸው! ብዙ ልታውቃቸው የምትችላቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች አሉ ነገር ግን እነዚህን በልብህ (በቃልህ) ልትናገራቸው የሚገቡ ናቸው!

    ይህንን መጽሐፍ ሁሌ ከአንተ ጋር ያዘው። በማንኛውም ጊዜ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ በተጠየቅህበት ጊዜ ለመመለስ ዝግጁ ሁን። ክርስቲያን በሆንክበት ጥቂት ጊዜያቶች ውስጥ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን በቃልህ መናገር መቻል አለብህ። በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስን በቃሉ መጠቀስ ዪችል የእግዚአብሔር ሰው መሆን አለብህ።

    የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ ለመያዝ ከሚያሰተምረው መጸሐፍ የተነሳ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ እና የአገልግሎት መልካም ምሳሌ እንድትሆን አውጅብሃለሁ!

    ምዕራፍ 2

    የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ መያዝ አስፈላጊነት

    አገልጋይ የእግዚአብሔርን ቃል ተሸካሚ መሆን አለበት። በእግዚአብሔር ቃል እና በክብሩ የተከበበ ሰው መሆን አለበት። ለዚህም ነው የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ ማጥናት ለአገልግሎት እድገት ወሳኝ የሆነው።

    በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ይህም ማለት እግዚአብሔር ለሚሰራቸው ማናቸውም ነገር ሁልጊዜ መሰረቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

    ዛሬም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ ማወቅ አስፈላጊነቱ እንደገና ቦታ የሚሰጥበት ምክንያቱ እግዚአብሔር እየገነባ ያለው ቤተክርስቲያን ክብሩ የሚበልጥ ስለሆነ ነው። አሁን ያለው የቤተክርስቲያን ክብር ከዚህ በፊት የኢየሱስ ክርስቶስን የምስራች ከሰበኩት ቤተክርስቲያኖች ክብር የበለጠ ይሆናል። ይህ ማለትም ደግሞ በመጨረሻው ቀናቶች የሚነሱት አገልጋዮች በኃይል የተቀቡ እና ከበፊቱ በክብር የላቁ ናቸው። የእግዚአብሔር ቃል ያውቃሉ ደግሞም ያለችግር በቃል ይጠቅሱታል!

    እንዴት አድርጎ ነው እነዚህ የከበሩ አገልጋዮች እና የከበሩ ቤተክርስቲያኖች የሚወለዱት እና የሚፈጠሩት? መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ላይ ግልጽ ያለ ነው። አንድ አገልጋይ ለኢሱስ ስራ የሚዳብረው እና የሚዘጋጀው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ነው። ሁሉም በቃሉ እውቀት ነው!

    በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17፤ ለመልካም ስራ የተዘጋጀ መልካም አገልጋይ እንዴት እንደሚፈጠር የሚያሳይ ትልቅ እና ህያው መገለጥ እናገኛለን፤ ቃሉ!

    የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።

    በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብ ማጥኛ መጽሐፍ ልታውቃቸው የሚገቡህን በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ጥቅሶች ይሰጥሃል። ሊታወቁ የሚገባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውድ ስብስብ ነው። እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች በልብህ ስታጠና ለራስህ አገልግሎት ታላቅ መሰረት እየሰጠህ ነው።

    እንደ አዳኛችን እንደ ኢሱስ ሁን! ኢየሱስ ከክርስቶስ በልብ በተጠኑ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች የተሞላ ነበር። በአጠገብህ ላሉት ያጠናሃቸውን ጥቅሶች ለመናገር ተማር። ለሚቀሩት የህይወት ዘመንህ ባጠናሃቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅሶች ትመራለህ። በምድረ በዳ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰይጣን ጠቅሶለታል እንዲሁም በፈተናም እንዳይወድቅ መከላከያውም ነበር።

    ዛሬ የታወቁ በአለም ውስጥ ያሉ የታወቁ ሃይማኖቶች የእነርሱን የተቀደሱ መጽሐፎቻቸውን ጥቅሶች በልብ እንዲያውቁ ግድ ይላሉ። በእነዚህ ሃይማኖቶች ውስጥ ያሉ ወጣት ልጆች በቅዱስ መጽሐፎቻቸው ውሰጥ ያሉትን ቃላቶች በሙሉ በልብ ለመያዝ ለሰዓታት ይቀመጣሉ። የዚህ ዓይነት የተሰጠ ጥናት ለእምነታቸው ለመሞት የተዘጋጁ ሰዎችን አፍርቷል።

    የእኛን ቅዱስ መጽሐፍ በልብ በማጥናት እኛም ለክርስቶስ አክራሪዎች መሆን አለብን። መንገዱ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1