Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ
ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ
ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ
Ebook114 pages55 minutes

ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ይህ መጽሐፍ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚገኘውን መዳን እንድትረዳ ትልቅ የሆነን መረጃ የሚሰጥ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የኢየሱስን ፍቅር ፣ እንዴት ዳግመኛ መወለድ እንደሚቻል፣ ወደ ገሃነም መውረድን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻልና በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ሰው መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ትችላለህ። ይህንን መጽሐፍ ለማንም ሰው ስጠው ከዚያም በኢየሱስ ክርስቶስ ደም መዳን (መዋጀት) ምን እንደሆነ ይገባዋል።

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954362
ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ

Related ebooks

Reviews for ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ - Dag Heward-Mills

    ዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    HOW TO BE BORN AGAIN AND AVOID HELL

    ትርጉም፡- እስራኤል ጥበቡ

    አርትዖት፡- ያሬድ ስለሺ

    ስለ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ

    በዚህ ኢሜይል ይጻፉ፡- evangelist@daghewardmills.org

    ዌብሳይታቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.

    በፌስቡክ፣ Facebook: Dag Heward-Mills

    በትዊተር፣ Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-61395-436-2

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው፡፡

    ማውጫ

    1. እግዚአብሔር በታላቅ ፍቅር ይወድሃል/ሻል

    2. ዳግም መወለድ ስላለብህ አትደነቅ

    3. አዲሱ ፍጥረት ማለት ምን ማለት ነው

    4. ስትሞት ምን ትሆናለህ?

    5. በሲኦል የሚሆኑ ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው?

    6. በሲኦል እየሆነ ያለው ምንድን ነው?

    7. የኢየሱሰ ክርስቶስ ደም አንተን ከሲኦል የሚያድንበት መንገድ

    ምዕራፍ 1

    እግዚአብሔር በታላቅ ፍቅር ይወድሃል/ሻል

    እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

    ዮሐንስ 15፡12-14

    የእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር ህይወትህን ለዘለዓለም ይለውጠዋል፡፡ ይህ ፍቅር በምድር ካለ ከየትኛውም ነገር ይበልጣል፡፡ አንድ ወንድ ለአንድ ሴት እወድሻለሁ ሲላት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለእርሱ ከምጽፈው የሚበልጥ ፍቅር ጋር ሊነጻጸር አይችልም፡፡ እናትህ ልትወድህ ትችላለች፣ አባትህ ሊወድህ ይችላል፤ ማናቸውም ግን አይሞቱልህም፡፡ የወንድ ጓደኛሽ ሊወድሽ ይችላል የሴት ጓደኛህም ልትወድህ ትችላለች፤ ማናቸውም ግን አይሞቱልህም።

    ይህ መጽሐፍ የሚያወራው ስለእግዚአብሔር የሚበልጥ ፍቅር ነው፡፡ ይህንን ታላቅ ፍቅር ለመቀበል ልብህን ስትከፍት ዳግም ትወለዳለህ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሆነ ለዚህ ታላቅ ፍቅር ልብህን ብትከፍት አዲስ ፍጥረት ትሆናለህ ፈጽሞ የተለየ ህይወትም ትኖራለህ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሆነ ለዚህ ታላቅ ፍቅር ልብህን ብትከፍት ከገሃነም ቅጣትህ ታመልጣለህ፡፡ እኔም ሆንኩ አንተ ወደ ገሃነም መግባት ይገባናል፡፡ ነገር ግን እንዳንጠፋ አንድያ ልጁን በላከው በእግዚአብሔር ፍቅር አማካኝነት ዳግም መወለድ እንችላለን! ሃሌሉያ! አዲስ ፍጥረቶች መሆን እንችላለን! ጨለማና የገሃነምን ስቃይ ማምለጥ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን መጠራት እንዴት ያለ ፍቅር ነው? ከኃጢያታችን ሊያድነን ኢየሱስ ደሙን ማፍሰሱ እንዴት ያለ ታላቅ ድነት ነው የተገለጠልን!

    ልብህን ከፍተህ ክርስቶስ የሚሰጥህን ታላቅ ድነት እንድታጣጥም እፈልጋለሁ፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ድነትን አይረዱም ስል አዝናለሁ፡፡ ይህንን መጽሐፍ የምጽፈው ለዚህ ነው፡፡ አሁን አሁን ስለድነት ከስንት አንዴ ነው የሚሰበከው፡፡ ክርስትና ለዘለዓለም ጸንቶ የሚቆምባቸውን ጽኑ መሰረቶች መልሰን የምናመጣበት ጊዜው አሁን ነው፡፡

    ስለሚበልጥ ፍቅር ማወቅ ያለብህ ሰባት ነገሮች

    1. የተለያዩ የፍቅር ዓይነቶች አሉ፤ የኢየሱስ ፍቅር ግን ከሁሉም ታላቅ ነው፡፡

    እግዚአብሔር በዓለም ካሉ የፍቅር ዓይነቶች ሁሉ ታላቅ የሆነ የፍቅር ዓይነት አለው፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚገልጹትን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ብቻ ተመልከት፡፡ ይህ እንዴት ዓይነት ፍቅር ነው? የእግዚአብሔር ፍቅር ትልቅ ፍቅር ነው፣ የዘላለም ፍቅር ነው፣ እንዲሁም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

    የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።

    1ኛ ዮሐንስ 3፡1

    ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥

    ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

    ኤፌሶን 2፡4-5

    እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።

    በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።

    1ኛ ዮሐንስ 4፡16-17

    እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።

    ኤርምያስ 31፡3

    ተወዳጁና የሚበልጠው ፍቅር

    በአንድ ወቅት ውዳጅ የነበራት ወጣት ሴት አውቅ ነበር፡፡ ይህ የተወደደ ወጣት ሰው ይህችን ወጣት ሴት ሊያገባት ቢፈልግም በሚገባ አይንከባከባትም ነበር፡፡ በወዳጇ እና በሌሎች ሴቶች መካከል ልቡ የተከፈለ ይመስላል፡፡ ያለማጋነን ግንኙነታቸው የጋለ ነበር፡፡ አንድ ቀን ይህች ሴት በመጨረሻ ወደቤት ተመልሳ አክትሟል አለች፡፡ በተሰበረው ግንኙነት ልቧ ስለተሰበረ እያነባች ነበር፡፡ እኔ ግን አጽናናኋትና እግዚአብሔር ሌላ ሰው፣ የተሻለ ወዳጅ እንደሚሰጣት ነገርኳት፡፡

    ከወራት በኋላ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ አንድ መልካም ከየት መጣ ሳይባል ከእርሷ ጋር በፍቅር ይወድቃል፡፡ ግንኙነታቸውን እያጣጣሙት እንዳሉ ያስታውቁ ነበር፤ አንድም ቀን ይህችን ወጣት ሴት አዲሱ ግንኙነትሽ እንዴት ነው? ብዬ ጠየቅኋት፡፡

    በፈገግታ ከመጀመሪያው ግንኙነት እጅግ የሚበልጥ ነው፤ እግዚአብሔር መልካም ሆኖልኛል፡፡ አለች፡፡

    በሌላ ቋንቋ የሚበልጥ ፍቅርና የተሻለ ግንኙነት እየተለማመደች ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ብየ ጠየቅኋት ይህ ግንኙነት ለምንድን ነው የሚሻለው?

    እንዲህ አለች ይህን ያህል ልደሰት እችል እንደነበር እንኳን አላውቅም፡፡ ልለማመደው የምችለው እጅግ የሚበልጥ ፍቅር እንዳለ አላወቅሁም ነበር፡፡

    በእርግጥም ይህች ወጣት ሴት የሚበልጥ ዓይነት ፍቅር ተለማምዳለች፡፡ የእግዚአብሔርም ፍቅር እንዲሁ ነው፡፡ እጅግ የሚበልጥ የፍቅር ዓይነት ነው፡፡ ይህ እንዴት ያለ ፍቅር ነው?

    2. የኢየሱስ ፍቅር ከ ወንድሞች ፍቅር ይበልጣል፡፡

    ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

    1ኛ ጴጥሮስ 1፡22

    በርካታ ቤተሰቦቸች ቢዛመዱም እንኳን ተበታትነዋል፡፡ ደግመው ደጋግመው እርስ በእርስ ይለያያሉ ይጣላሉ፡፡ የኢየሱስ ፍቅር በወንድማማቾች መካከል ካለ ፍቅር እጅግ የሚበልጥ መሆን አለበት፡፡

    የኩላሊት ልገሳው

    አንድ ቀን የኩላሊት ልገሳ ለሚያስፈልገው ለአንድ ወንድም ጸሎቶች የሚደረጉበት የጸሎት ስብሰባ ነበር፡፡ ለዚህ ወንድም ያላቸውን ፍቅር ይገልጹ ነበር፤ ከኩላሊት ልገሳውም በኋላ ሲኖር ለማየት ይፈልጉ ነበር፡፡

    ይሁንና የጸሎት ስብሰባው እየተደረገ ሳለ የሚጸልዩት ስለእርሱ ቢሆንም ማናቸውም ኩላሊቱን ለመለገስ ዝግጁ እንዳልሆነ አስተዋሉ፡፡ በመጨረሻ የጸሎት ስብሰቢው መሪ የማን ኩላሊት መለገስ እንዳለበት እግዚአብሔር እንዲመርጥ ለመፍቀድ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1