የአገልግሎት ሥነ ምግባር
4/5
()
About this ebook
ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በጊዜው አገልግሎት ውስጥ ያለውን የእውነተኛ ህይወት ገጠመኞች በዚህ ድንቅ ስራው ይገመግማል፡፡ ገንዘብ፣ፖለቲካ፣ከተቃራኒ ፆታ ጋር ስለሚኖረን ግንኙነቶችና አገልግሎታዊ ተጽዕኖችን የመሳሰሉትን ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን ያሳየናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ለእያንዳዱ መሪ ሊኖረው የሚገባ፣ ለጥሪህ መሰረታው የሆኑ ልምምዶችን በቀላሉ የሚያስረዳ መመሪያ ነው፡፡ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚሰሩ እንዲኖራቸው በከፍተኛው የሚመከር ነው።
Dag Heward-Mills
Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.
Related to የአገልግሎት ሥነ ምግባር
Related ebooks
የትህትና ቀመር Rating: 5 out of 5 stars5/5እረኛ መሆን ምን ማለት ነው Rating: 5 out of 5 stars5/5ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን Rating: 2 out of 5 stars2/5ትተውህ የሚሄዱ ሰዎች Rating: 2 out of 5 stars2/5የተቀባው ሰው እና ቅባቱ Rating: 5 out of 5 stars5/5መጽሐፍ ቅዱስህን አንብብ በየቀኑ ጸልይ Rating: 5 out of 5 stars5/5ወደኋላ ማፈግፈግ Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsቅባቱን ያዝ Rating: 5 out of 5 stars5/5አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል Rating: 5 out of 5 stars5/5የአገልግሎትህን እስከ መጨረሻው እንዴት ማድረስ ትችላለህ Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsዳግም መወለድ ብሎም ገሃነምን ማስወገድ Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsጣፋጭ የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች Rating: 4 out of 5 stars4/5ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድብትል Rating: 5 out of 5 stars5/5የመከተል ጥበብ Rating: 5 out of 5 stars5/5ልጄ ሆይ ትችያለሽ Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsዛፉ እና አገልግሎትህ Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsመጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት Rating: 5 out of 5 stars5/5የመጋቢነት አገልግሎትህን ወደ ላቀ ደረጃ አሳድግ Rating: 5 out of 5 stars5/5የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል Rating: 4 out of 5 stars4/5መጽሐፍ ቅዱስን በልብ ለማስታወስ ማጥኛ መጽሐፍ Rating: 5 out of 5 stars5/5እንዴት መጸለይ አለብን Rating: 3 out of 5 stars3/5የሚከሱህ ሰዎች Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsእግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው Rating: 4 out of 5 stars4/5ወደ ቅባቱ የሚያደርሱ እርምጃዎች Rating: 5 out of 5 stars5/5ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!! Rating: 5 out of 5 stars5/5ስኬታማ አመራር: 8 ማወቅ የሚኖርብዎት አስፈላጊ መርኆች Rating: 3 out of 5 stars3/5ቤተ ክርስቲያን ትከል Rating: 0 out of 5 stars0 ratingsየመሪነት ጥበብ Rating: 4 out of 5 stars4/5እንደ እባብ ብልህ መሆን ማለት ምን ማለት ነው Rating: 5 out of 5 stars5/5በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል Rating: 0 out of 5 stars0 ratings
Reviews for የአገልግሎት ሥነ ምግባር
3 ratings0 reviews
Book preview
የአገልግሎት ሥነ ምግባር - Dag Heward-Mills
ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።
Find out more about Dag Heward-Mills
Healing Jesus Crusade
Write to: evangelist@daghewardmills.org
Website: www. daghewardmills.org
Facebook: Dag Heward-Mills
Twitter: @EvangelistDag
ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል
መ.ሳ ቁጥር 15134
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
መታሰቢያነቱ
ለባለቤቴ አባት ለሞይስ ክዌኩ ቤደን
ከእርስዎ ከተማርኩት ብዙና ውድ ነገሮች አመሰግኖታለሁ። ለኔ እንደ ሁለተኛ አባቴ ሆነውልኛል።
ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው፡
Table of Contents
ምዕራፍ 1. ስነ ምግባር ለምን አስፈለገ
ምዕራፍ 2. ስነ ምግባር ለመሪ
ምዕራፍ 3. ሥነ ምግባር ለረዳቶች
ምዕራፍ 4. ከአገልግሎት ለመልቀቅና ወደሌላ ለመሄድ የሚያስፈልግ ስነምግባር
ምዕራፍ 5. ለቤተክርስቲያን ኘሮግራም ስነምግባር
ምዕራፍ 6. ከቤተክርስቲያን አባላት ጋር ስለሚኖርህ ግንኙነት ስነምግባር
ምዕራፍ 7. ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለሚኖር ግንኙነት ስነምግባር
ምዕራፍ 8. ስነምግባር - ከውጭ አገልጋዮች ጋር ባለ ግንኙነት
ምዕራፍ 9. ስነምግባር - ስለተጋባዥ አገልጋዮች
ምዕራፍ 10. ለተጓዥ አገልጋዮች የሚገባ ስነምግባር
ምዕራፍ 11. ስለ ገንዘብ ማወቅ የሚገባን ስነምግባር
ምዕራፍ 12. ስጦታን ስለመቀበል የሚገባ ስነምግባር
ምዕራፍ 13. የግል ሕይወትን ምስጢራዊነት ስለማክበር የሚገባ ስነምግባር
ምዕራፍ 14. በአደባባይ ስለመታየት የሚገባ ስነምግባር
ምዕራፍ 15, ስነምግባር ከውጪ ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት
ምዕራፍ 1
ስነ ምግባር ለምን አስፈለገ
ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
1 ጢሞሲዎስ 3፡15
አገልጋዮች ብዙ ጫና አለባቸው፡፡ የገንዘብ ጫና፣ የቤተሰብ ጫና፣ ሰው ከእነርሱ የሚጠብቅባቸው ነገር እነዚህ በአገልግሎት ከሚገጥሙ ጫናቸዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በጌታ አገልግሎት ውስጥ ከሚገጥሙ ከነዚህ ጫናዎች የተነሳ ብዙ ጊዜ የመጋቢዎች ፀባይ ከመስመር የለቀቀ ይሆናል፡፡
በአገልግሎት ውስጥ ያለ ሰው የሚያሳየው ከመስመር የወጣ ባህሪ የአገልግሎታችንን አላማ በሕይወት እንዳንገልጠው ያደርገናል፡፡ በክርስትና ታሪክ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በአሁኑ ጊዜ አለም የአገልጋዮችን አኳኋንና የሕይወት ዘይቤ በጥንቃቄ እየተከታተለች ነው፡፡ እኛ ወደ አገልግሎት የተጠራንው ከፍ ባለ የሕይወት ደረጃ ለመገኘት መታገል አለብን፡፡
አለም እኛን ለማሳደድ እንድትችል ከእኛ ዘንድ አንዳች ግድፈት ለማግኘት እየተከታተለችን ነው፡፡ ለዚህ ነው በማያምኑት ዘንድ እንኳን አገልጋዩች በመልካም የተመሰከረላቸው መሆን እንዳለባቸው ጰውሎስ የሚመሰክረው ፡፡
በዲያብሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።
1 ጢሞቲዎስ 3፡7
እግዚአብሔር ሰውን ሲጠራ አስቀድሞ የሚጠራው እንዲከተለው ሲሆን፣ ቀጥሎ ደግሞ ከእርሱ እንዲማር ነው፡፡ መማርን ፈጽሞ አናቆምም፡፡ አገልግሎት የማያቋርጥ ትምህርት ያለው ረጅም ጉዞ ነው፡፡ ጳውሎስ እንድንማር ከጠየቀን አንዱ ጉዳይ የአኗኗር ዘይቤውን ነው፡፡ በሌላ አባባል እንደ አገልጋይ፣ የእርሱን አልባሌ ባህሪ የገሩትን የስነምግባር መርሆዎች ልንከተል ይገባል፡፡
እነዚህም ደግሞ አስቀድሞ ይፈተኑ፥ ከዚያም በኋላ ያለ ነቀፋ ቢሆኑ በዲቁና ሥራ ያገልግሉ።
2 ጢሞቲዎስ 3፡10
እንግዲያው የአገልግሎት ስነ ምግባሮች ምንድን ናቸው? እነዚህ በአገልግሎታችን ልንከተላቸው የሚገባን መለኪያዎች፣መርሆዎች እና መመሪያዎች ናቸው፡፡ የስነ-ምግባር መርሆዎች ቅን፣ ለአእምሮ የሚመቹ፣ክብርን የተላበሱ፣ ግብረገባዊ፣ ሕጋዊ፣ ከነቀፌታ በላይና ሀቅን የተመሉ ናቸው፡፡
ከስነ ምግባር ውጪ የሆነ ባህሪ ግን በሌላ መልኩ ነውረኛ፣ ሚዛናዊ ያልኀሆነ፣ አግባብ ያልሆነ፣ አሳፋሪ፣ አጠራጣሪ፣ ይሉኝታ የሌለውና ጠማማ ምናልባትም አንካሳ ነው፡፡