Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን
ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን
ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን
Ebook190 pages1 hour

ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን

Rating: 1.5 out of 5 stars

1.5/5

()

Read preview

About this ebook

ታማኝነት ለመሪዎች የእግዚአብሔር የቅድሚያ መለኪያ ቢሆንም እንኳን ፣በእዚህ ርዕስ የተጻፉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በዚህ መጽሐፉ፣ የቤተክርስቲያኖች በመጽናት ማደግን አስመልክቶ በጣም አስፈላጊ መመሪያዎችን በግልፅ ይዘረዝርልናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወቅታዊና ተግባራዊ የሆኑ ርዕሶችን ያካተተ ነው ፣ በመሆኑም ለቤተክርስቲያን መሪዎች የሁልግዜ መገልገያ መሳሪያ ይሆናል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954409
ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን

Related ebooks

Reviews for ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን

Rating: 1.5 out of 5 stars
1.5/5

2 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን - Dag Heward-Mills

    ትርጉም፡-  ሬቨረንድ አማኑኤል ቶማስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    Email Dag Heward-Mills:

    evangelist@daghewardmills.org

    Find out more about Dag Heward-Mills at:

    www. daghewardmills.org

    www. lighthousechapel.org

    www.healingjesuscrusade.org

    Write to:

    Dag Heward-Mills

    P.o.Box 114

    Korle-Bu

    Accra

    Ghana

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ISBN: 9781613954409

    ይህንን መፅሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከተለ ነው፡፡

    መታሰቢያነቱ

    ለጓደኛዬና ለረዳቴ ሬቨረንድ ኢ..ቲ፣ ስለ ብዙ ዓመታት ታማኝነትህ አመሰግንሃለሁ፡፡

    Table of Contents

    ምዕራፍ 1. ታማኝነት ለምን?

    ምዕራፍ 2. ታማኝ ያለመሆን ደረጃዎች

    ምዕራፍ 3. የታማኝነት ባህል

    ምዕራፍ 4. የታማኝነት ሰባት ትምህርቶች

    ምዕራፍ 5. ታማኝ ያለመሆን ምልክቶች

    ምዕራፍ 6. ከከዳተኛ ሰዎች አንደበት

    ምዕራፍ 7. ታማኝ ረዳት

    ምዕራፍ 8. ታማኝ ያልሆነ ረዳት

    ምዕራፍ 9. ይሁዳ ለምን ክርስቶስን ካደ

    ምዕራፍ 10. ታማኝ አለመሆንን ማስወገድ

    ምዕራፍ 11. የሰሜን ነፋስ

    ምዕራፍ 12. የታማኝነት መልካም ፍሬዎች

    ምዕራፍ 1

    ታማኝነት ለምን?

    ታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን በሚል ርዕስ ማስተማር ለምን አስፈለገ? ጌታ ይህን ዐብይ ርዕስ በተለያዩ ምክንያቶች በልቤ እንዳስቀመጠ አምናለሁ፡፡  በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ርዕስ በእግዚአብሔር ቃል የተደገፈ መሆኑን ተረድቼአለሁ፡፡  ቅዱሳን መጽሐፍት በታማኝ እና በከዳተኛ ሰዎች ታሪክ የተሞሉ ናቸው፡፡  ከእነኚህ ታሪኮች ደግሞ ብዙ መማር ይቻላል፡፡

    በአገልግሎት ባሳለፍሁባቸው ጥቂት ዓመታት ውስጥ ታማኝ እና ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች ያጋጠሙኝ ሲሆን በቤተክርስቲያንና በአገልግሎት ላይ ያላቸውንም አሉታዊ ተፅዕኖ አስተውያለሁ፡፡  በሚቀጥሉት ገፆች ታማኝነት የሚለው ርዕስ በጣም አስፈላጊ የሆነበትን ጥቂት ምክንያቶች አካፍልሃለሁ፡፡

    ታማኝነት የሚለው ርዕስ አስፈላጊ የሆነበት 7 ምክንያቶች

    1.         ታማኝነት ለሁሉም አገልጋይ ተቀዳሚ መመዘኛ ነው፡፡

    ልምድ የሌለው ሰው ብዙ ስጦታ ባለህ መጠን፣ ለአገልግሎት ይበልጥ ብቁ ትሆናለህ ብሎ ሊያስብ

    ይችላል፡፡  በቤተክርስቲያን ውስጥ እውነተኛ እና ታማኝ የሆኑ ሰዎች ከሁሉም በላይ ብቁ መሪዎች እንደሆኑ ጥቂቷ ልምዴ አሳይታኛለች፡፡

    መልካም አቀራረብና ታይታ!

    ልምድ የሌለው ሰው ጥሩ አቀራረብ ያለው ሰው ጥሩ መጋቢ እንዲሁም ጥሩ የንግግር ችሎታ ያለው ሰው ደግሞ የተዋጣለት ሰባኪ መሆን እንደማያቅተው ሊያስብ ይችላል፡፡  አትሳት!  መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን የመሪነት ዋነኛ መመዘኛ ታማኝነት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡

    … እንደዚህ ሲሆን፣ በመጋቢዎች ዘንድ የታማነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል፡፡

    1ኛ ቆሮንቶስ 4፡2

    ብዙ አብረውኝ የሚሠሩ ግሩም መጋቢዎች አሉኝ፡፡  አብዛኞቹ ቀልጣፎች፣ የሚማርኩ ወይም ልዩ ስጦታ ያላቸው ሣይሆኑ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንና ለእኔ የሰጣቸው ውድ ስጦታዎች እንደሆኑ ጊዜ አሳይቶኛል፡፡

    2.         5ኛ ረድፍን ለመዋጋት

    ገና አገልግሎት እንደጀመርኩ ሰይጣን ቤተክርስቲያንን ከውስጥ በማፍረስ የረቀቀ መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፡፡  የእግዚአብሔር ጥሪ ያለህና ትክክለኛውን ነገር የምታደርግ መልካም አገልጋይ ከሆንህ፣ ሰይጣን ከውጭ ሊዋጋህ የሚችልበት እድል በጣመ የጠበበ ነው፡፡  ኢየሱስ እንዳለው፣

    … የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፡፡

    ዮሐንስ 14፡3ዐ

    ከዚህ የጌታ አባባል፣ ሰይጣን አብዛኛውን ጊዜ ከውጭ ሆኖ አደገኛ ጥቃት ሊያደርስብህ የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ትገነዘባለህ፡፡  ኢየሱስም የተናገረው፣ ምንም እንኳ ቢመጣ ሊያጠፋው የሚችልበት አንዳች መሠረት እንደሌለው ነው፡፡  ከዚህ የሚመደቡ ብዙ የተቀቡ ሰባ ሰባኪዎች አሉ፡፡  በመሆኑም ሰይጣን እነርሱን ለማሸነፍ አንዳችም መሠረት ስለሌው የውስጥ ሰው መጠቀም ግድ ይሆንበታል፡፡  የኢየሱስን ሁኔታ ስንመለከት ሰይጣን የተጠቀመበት ከኃዲው ይሁዳን ነበር፡፡

    ትልቅ ከተማን ለመቆጣጠር ከበባ ስለአካሄደ አንድ የጦር ጄኔራል ያነበብኩትን አስታውሳለሁ፡፡  ይህ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ ትልቅና አስቸጋሪ በሆነ ቅጥር እና በር የተመሸገ ነበር፡፡  የጦር ጄኔራሉ ከተማውን በመክበብ ለማጥቃት ተዘጋጅቶ ሳለ አንድ የጄኔራሉ ጓደኛ መጣና እንዲህ ሲል ጠየቀው፤

    ጌታው እንዴት የዚህን ከተማ መከላከያ አሸንፋለሁ ብለህ ታስባለህ? በታሪክ ውስጥ እስካሁን ማንም ይህን ታላቅ ከተማ ተቆጣጥሮ አያውቅም፡፡ የጦር ጄኔራሉም ብሎ ይህን ጨዋታ ለመጫወት የሚችልና የምተማመንበት አምስተኛ ረድፍ አለኝ፡፡  ሲል መለሰለት፡፡

    የጄኔራሉም ጓደኛ በአግራሞትና በጉጉት እንዲህ ሲል ጠየቀው ይህ 5ኛ ረድፍ የምትለው ምንድነው?  እኔ የማስበው አራት ክፍለ ጦር ብቻ እንዳለህ ነበር፡፡  የጦር ጄኔራሉም ሲመልስ፣ 5ኛ ረድፍ አለኝ አለ፡፡  ጓደኛውም "ኦ!  ገባኝ ልዩ የኮማንዶ ክፍለ ጦር ወይስ አየር ወለድ?  ሲል ጠየቀ፡፡

    የምዋጋው ከውስጥ ነው

    ጄነራሉመ ሳቀና፣ አይደለም አልደረስክበትም፣ አምስተኛ ረድፌ ሰላዮቼን፣ ወኪሎቼን፣ ጓደኞቼንና ደጋፊዎቼን የሚያካትት ሲሆን እነርሱም ያሉት በከተማው ውስጥ ነው፡፡  ታገስ ብቻ እነርሱ እነዚያን ትላልቅ በሮች ከውስጥ ሲከፍቱ ሠራዊቴ በፍጥነት ወደ ውስጥ ይዘልቃል አለ፡፡

    ጠላት በመልካም ሥራ ላይ የተሰማራ፣ ውጤታማና ኃይለኛ አገልግሎትን ማጥፋት የሚችልበት ብቸኛ መንገድ ይህ ብቻ ነው፡፡  ከውስጥ መምጣት አለበት፡፡ 5ኛው ረድፍ የሚያካትተው በየአገልግሎቱ ውስጥ ያሉትን ታማኝ ያልሆኑ፣ ሁለት መልክ እና ምላስ ያላቸውንና በቅሬታ የተሞሉ ሰዎችን ነው፡፡  እነኚህ ሰዎች እድሉን ካገኙ፣ ቤተክርስቲያንን ከማፈራረስ አልፈው እስከ ማጥፋት ሊደርሱ ይችላሉ፡፡

    ታማኝ ያልሆነ ረዳት አገልጋይ ነበረኝ

    አስታውሳለሁ፣ ከዓመታት በፊት አገልግሎት ስጀምር ታማኝ ያልሆነ ረዳት አገልጋይ የሚያስከትለውን መዘዝ አይቼአለሁ፡፡  ይህ ሰው ምንም እንኳ በአደባባይ ከጐኔ የቆመ ቢመስልም፣ ፈጽሞ በእኔ የማያምንና ሁሌ በእኔ ላይ የሚያጉረመርም ሰው የእርሱ ቤት በቤተክርስቲያን ውስጥ ቅሬታ ያለባቸው ሰዎች መሰብሰቢያ ሥፍራ በመሆኑ በተሰበሰቡ ጊዜ ሁሉ፣ ስለ እኔ ይወያዩ እና ይተቹኝ ነበር፡፡  አንዴ፣ ስለ አሰባበኬ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ በስብከት መሀል እንዴት ውሃ እንደምጐነጭ፣ እንደገና ደግሞ አንዳንዶቹ በደንብ አይቀርበንም በሚል ስሜት ይተቹኛል፡፡  ነገር ግን ጌታ ይህን ሁሉ ገለጠልኝ፡፡  እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ ጸለይኩና ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ጌታን ጠየቅኩት፡፡

    እግዚአብሔርም፣ ይህን ሰው አስወግደው አለኝ፡፡  እኔም፣ ጌታ ሆይ ቤተክርስቲያን መልቀቅ አለበት ማለት ነው? ብዬ ጠየቅኩት፡፡  ጌታም በእርግጥ ያን ማለቴ ነው! ካላስወገድከው በቀል መቼም ቢሆን ሰላም ልታገኝና ቤተክርስቲያንህም በፍጹም ልታድግ አትችልም! አለኝ፡፡

    ስለዚህም የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን ስብሰባ ጠራሁ፡፡  በስብሰባውም ላይ ወንድም እገሌ ደጋፊዬ እንዳልሆነ ተረድቼአለሁ፡፡  በማያቋርጥ ሁኔታ በምሬትና በትችት ተሞልቷል፡፡  ካልኳቸው በኋላ ለዚያም ወንድም እንዲህ አልኩት፣ በእኔ አመራር እንደማታምን ተረድቼአለሁ፤ አሰልጥኜሃለሁ፣ አሳድጌሃለሁ ዛሬ ግን በእኔ ሥልጣን ሥር ለመሆን የማትችል እጅግ ትልቅ ሆነሃል፡፡

    በመቀጠልም እንዲህ ስል ጠየቅሁት ምን ብናደርግ የሚሻል ይመስልሃል?

    ከዚያም ያ ወንድም ነገሮችን እንፍታ አለ፡፡  ነገር ግን ጌታ ያሳየኝ ጥቅስ እየተንሳፈፈ ወደ አእምሮዬ መጣ

    ፌዘኛን አስወጣው፣ ጠብ ይወገዳል፤ ጥልና ስድብም ያከትማል፡፡

    ምሳሌ 22፡1ዐ

    (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

    ወደ ረዳቴ በመጠቆም እንዲህ ስል ተናገርኩ፤ ይህ ሊሠራ እንደማይችል አንተም ታውቃለህ እኔም አውቃለሁ፡፡  ከዚህ በኋላ በፍጹም በእኔ አታምንም፡፡

    በመቀጠልም፣ ከዛሬ ጀምሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉህ ኃላፊነቶች በሙሉ አንስቼሃለሁ፡፡ አልኩት፡፡

    በመደናገጥ ምን! ካለ በኋላ፣ እነኚህ ኃላፊነቶች ባይኖሩኝም ቤተክርስቲያን መምጣት እቀጥላለሁ አለ፡፡

    አሁን ይህን ቤተክርስቲያን መልቀቅ አለብህ!

    እኔ ግን እንዲህ አልኩት አይሆንም መልቀቅ አለብህ! አንተ የእኛ አካል አይደለህም፡፡  ያንተ በቤተክርስቲያን ውስጥ መገኘት ትርፉ ጥፋት ነው፡፡ እውነት እልሃለሁ፣ የብዙ ዓመት ጓደኛና ረዳትን ማስወገድ ቀላል ባይሆንም መሆን ነበረበት፡፡  መጽሐፍ ቅዱስ አብርሃም ከሎጥ ጋር ግጭት ሲፈጥር ሎጥን ወደ ሌላ ሥፍራ እንዲሄድ እንደመራው ይናገራል!  አብርሃም ያለው እንዲህ ነበር፣

    እኛ ብንለያይ ሰላም ይኖራል የእግዚአብሔርም ሥራ ይቀጥላል፡፡

    ታማኝ ያልሆነ ሰው ሁከት፣ ጥላቻ እና ማጉረምረም ያስከትላል፡፡  እነኚህ ታማኝ ያለመሆን ስሜቶች ደግሞ ልክ ቤትን እንደሚያፍን ጭስ ናቸው፡፡  ጭስን የማስወገድ ብቸኛ መንገድ እሳቱን ከቤት ማውጣት ነው፡፡

    ትልቅ ቤተክርስቲያን እንዲኖረን ከፈለግን፣ በፍቅር እና በአንድነት ማገልገል ይገባናል፡፡  አንድ መሆን ካልቻልን ማስመሰል እናቁምና እንለያይ፡፡  ሰዎች ልባቸው ከእኔ ጋር ካልሆነ ከቤተክርስቲያኔ ለቀው እንዲወጡ አበረታታለሁ፡፡

    ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል…

    ማቴዎስ 12፡3ዐ

    ማድረግ ካለብኝ፣ እንድትለቅ እለምንሃለሁ፡፡  በዚህ ጉዳይ ቁርጠኛ ነኝ፡፡  እንዲያውም ቢያስፈልግ ስትለቅ ለትራንስፖርትና ለምግብ የሚያስፈልግህን ገንዘብ እሰጥሃለሁ!  እንዲህ ከሆነ፣ እርስ በእርሳችን የምንዋደድ እና የምንተማመን ሰዎች አብረን መቆየትና ሥራ መቀጠል እንችላለን፡፡

    አስመሳዮችን አስወግድ!

    ማስመሰል አልችልበትም፤እንዴት ላደርገው እንደምችል አላውቅም፡፡  ነገር ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ አስመሳዮች አሉ፡፡  እነዚህ ሰዎች በልባቸው እየናቁህ የሚወዱህ እና የሚደግፉህ ይመስላሉ፡፡

    3.         የእግዚአብሔር ፍቅር ቤተክርስቲያንን እንዲሞላ

    አገልግሎት በፍቅር፣ በአንድነት እና በሕብረት ሥራ ኃይል ሊንቀሳቀስ ይገባዋል፡፡

    እርስ በእርሳቸው ፍቅር ቢኖራችሁ፣ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚያ ያውቃሉ፡፡

    ዮሐንስ 13፡35

    አንተም ውጤታማ መሪ ለመሆን ኢየሱስ የተናገረውን ዓይነት ፍቅር ማሳየት አለብህ፡፡  ሰዎች በፍቅር ይሳባሉ፡፡  ሰዎች፣ መሪዎቻቸው እውነተኛ በሆነ ፍቅር አብረው ሲጓዙ ካዩ ይማረካሉ፡፡  የቤተክርስቲያን አባላት እውሮች ወይም ደንቆሮዎች እንዳልሆኑ መዘንጋት የለብህም፡፡  አንድነትና ስምምነት ሲጠፋም ያያሉ፣ ይገነዘባሉ፡፡

    በጎች የሚጠጡት ከጠራ ውሃ ብቻ ነው

    እያንዳንዱ መጋቢ ስለ በጎች ሊረዳ የሚገባው ነገር፣ በጎች የሚጠጡት ከጠራ ውሃ ብቻ እንደሆነ ነው፡፡  ውሃው የጠቆረና የደፈረሰ ከሆነ ይርቁታል፡፡  አየህ፡-  በውሃ ውስጥ ዓዞ ይኑር አይኑር አያውቁም! 

    … በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤

    መዝሙር 23፡2

    ክህደትና አለመተማመን በሚኖርበት ሁሉ የቤተክርስቲያንህ አባላት ይፈራሉ፣ ይሰጋሉ ደግሞም ይርቃሉ፡፡

    4.         ትልቅና ስኬታማ የአገልግሎት ቡድን እንዲኖር

    አንድ ሰው ሊሠራ የሚችለው ነገር ውስን ነው፡፡  አንድ መጋቢ በአንድ ጊዜ ሊገኝ የሚችለው በአንድ ሥፍራ ብቻ ሲሆን ማገልገልም የሚችለው (ውስን) አቅሙ እስከፈቀደ ብቻ ነው፡፡

    በዚህ ምክንያት፣ ማንኛውም አገልግሎቱ እንዲሠፋና ብዙ ፍሬ ለማፍራት የሚፈልግ ሰው ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር መሥራትን መማር ይገባዋል፡፡  የአገልግሎት ቡድን የምለው እነዚህን ሰዎች ነው፡፡  ይሁን እንጂ፣ ታማኝ ካልሆነ፣ በቅሬታ ከተሞላ፣ እና አንድነት ከሌለው ቡድን ጋር ከመሥራት ለብቻ መሥራት ይሻላል፡፡  በእርግጥ እንደዚህ ካሉ ሰዎች ጋር ውጤታማ የሆነ ቡድን ሊኖር አይችልም፡፡  ይህን ያህል ልሠራ የቻልኩት አብሬው ከምሠራው ቡድን ጋር በመሥራቴ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

    5.         ታላቅ ቤተክርስቲያን እንዲኖር

    በአሁኑ ወቅት ላይትሃውስ ቤተክርስቲያን በመላው ዓለም ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል፣ በጋና፣ በደቡብ አፍሪካ፣ ኒውዮርክ፣ እና በስዊዘርላንድ ትገኛለች፡፡

    እነኚህ አጥቢያ ቤተክርስቲያኖች በጋና ለሚገኘው የቤተክርስቲያኒቱ ዋና ጽሕፈት ቤት ታማኝ የሆኑ የመረቡ አካል ናቸው፡፡  ብዙ ጊዜ ሰዎች፣ "እንዴት በእነኚህ የተለያዩ ሥፍራዎች ሁሉ ቤተክርስቲያንን ልታጸና

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1