Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የተጠሩ ብዙዎች ናቸው
የተጠሩ ብዙዎች ናቸው
የተጠሩ ብዙዎች ናቸው
Ebook247 pages2 hours

የተጠሩ ብዙዎች ናቸው

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

በእርግጥ እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን ጠርቷል፡፡ በእዚህ ምድር ላይ ያለን ሕይወት እግዚአብሔርን ለማገልገል የተሰጠን ዕድል ሲሆን የእርሱም ዓይኖች ለመንግሥቱ በምንሠራቸው ነገሮች ላይ ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ ሲነበብ ያነቃቃል፡፡ በጸሐፊው የተላለፈውን መልእክት ብትቀበል፣ የሕይወትህን መልካም አጋጣሚዎች በአግባቡ እንድትጠቀምባቸው የሚረዳህን ጥበብ ትቀበላለህ፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954416
የተጠሩ ብዙዎች ናቸው
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የተጠሩ ብዙዎች ናቸው

Related ebooks

Reviews for የተጠሩ ብዙዎች ናቸው

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው - Dag Heward-Mills

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ትርጉም፡- ናታን ደምሴ

    አርትዖት፡- ያሬድ ስለሺ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    Find out more about Dag Heward-Mills 

    Healing Jesus Crusade

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    መታሰቢያነቱ

    ለኬት አሎቴይ

    ለብዙ ዓመታት በእረኝነትና በትርፍ ጊዜ መጋቢነት ስላገለገልሽ ምስጋናዬ ይድረስሽ፡

    ISBN: 978-1-61395-441-6

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው።

    ጫውጫ

    እስካሁን በሕይወት የቆየህበት ምክንያት

    ብዙ ክርስቲያኖች ተጠርተዋል

    የተለያዩ ሰዎች የተጠሩበት መንገድ

    የተጠሩ ሰዎች ባሕሪያት

    ጥሪ ማለት ምን ማለት ነው

    በአንድ ግለሰብ ጥሪ ላይ ያሉ ውስንነቶች

    በልብህ ያለው ምንድን ነው?

    እግዚአብሔር ሥራህን የሚቆጣጠርበት መንገድ

    ሲዖልን ማየት ስለተሳነህ ፍሬ አልባ ሆነሃል

    መንግሥተ ሰማይን ማየት ስለተሳነህ ፍሬ አልባ ሆነሃል

    አርቆ ማየት ስለተሳነህ መካን ሆነሃል

    ከመርሳትህ የተነሳ መካን ሆነሃል

    ፍሬ የማፍራት እንቅፋቶች

    ፍሬ የማፍራት አራት ጥቅሞች

    ሰዎች መክሊታቸውን የማይጠቀሙበት አሥር ምክንያቶች

    ለመንፈሳዊ ሕይወትህ የተቀጠረ ጊዜ

    ዘመንን መዋጀት

    የወንጌል ስርጭት ላይ ያተኮረ ጉልበት ያለው ክርስትና

    ዮሐንስ 3፥16 የማይለወጠው የክርስትና ዓላማ

    ምዕራፍ 1

    እስካሁን በሕይወት የቆየህበት ምክንያት

    እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

    ኤፌሶን 2፥10

    አንድ ጊዜ ወደ መካከለኛው ለንደን ከሚወስደኝ ከአንድ እንግሊዛዊ የታክሲ ሹፌር ጋር እየተጫወትን ስንሄድ ሳለ በእግዚአብሔር ያምን እንደሆነ ጠየቅሁት።

    በእርግጠኝነት ለመናገር፣ በእግዚአብሔር አላምንም። ሲል መለሰልኝ።

    ደግሜ፣ ገሀነም እንዳለ ታምናለህ? ብዬ ጠየቅሁት።

    በስጨት በማለት፣ በእርግጥ አላምንም! ሲል መለሰ።

    ቀጠልሁና፣ መንግሥተ ሰማይ እንዳለ ታምናለህ?

    በእንደዚህ ዓይነቱ ነገር ምንም አላምንም።

    የታክሲ ሹፌሩ በተራው፣"እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" አለኝ።

    እኔም፣ እንዴታ፣ የምትፈልገውን ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ነፃ ሁን። ስል መለስሁለት።

    መንግሥተ ሰማይ እንዳለ ታምናለህ? ሲል ጠየቀኝ።

    በደንብ አድርጌ አምናለሁ እንጂ። ስል መለስሁለት።እስቲ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ። አለኝና መንግሥተ ሰማይ እገባለሁ ብለህ የምታምን ከሆነ ለምን ራስህን አጥፍተህ አሁን ወደ መንግሥተ ሰማይ አትሄድም። እንዲህ ብታደርግ፤ ከብዙ ዓይነት ወጪዎች፣ ዕዳዎችና ችግሮች ትገላገል ነበር። አለኝ።

    በጣም ደነገጥሁ፤ ምክንያቱም እንደዚህ ያለ ጥያቄ አልጠበቅሁም ነበር። ይሁንና ጥያቄው ትርጉም የሚሰጥ ነበር። መንግሥተ ሰማይ እንደዚያ እጅግ የሚያስደስት ስፍራ ከሆነ፣ እስካሁን በምድር ሆኜ መሥራቴ ምን ያደርጋል? ለምን አሁን እራሴን ገድዬ ከዚህ ዓለም ጣጣ አልገላገልም?

    ለራሴ ይህ ጥሩ ጥያቄ ነው። ብዬ አሰብሁ። ይሁንና ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ የምመልስበትን ዕድል ሳላገኝ መድረሻችን ደረስን።

    ከዛ የታክሲ ሹፌር ጋር ካደረግሁት የጭውውት ጊዜ ጀምሮ ይሄንን ጥያቄ በተለያዩ ጉባኤዎች ላይ መልሼዋለሁ። እንደዳንን ወዲያውኑ ወደ መንግሥተ ሰማይ ያልሄድነው ለምንድን ነው?

    ምንም እንኳ እግዚአብሔር ሕይወታችንን ቢለውጥና መንግሥተ ሰማይን የመውረስ ተስፋ ቢሰጠንም፣ በዚህ በምድር የሚሠራ ሥራ እስካሁን አለ። ለእግዚአብሔር የሚከናወኑ ተግባራት ይኖራሉ። ራሳችንን ለእርሱ ሥራ በመስጠት ለታላቅ ፍቅሩ ምላሽ እንድንሰጥ እግዚአብሔር ይጠብቅብናል።

    ወደ ኢየሱስ በመጣን ጊዜ፣ የተጫነንን የኃጢአት ሸክምና ጨለማ ከላያችን ላይ በማንሳት የራሱን ሸክም ሰጥቶናል። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴዎስ 11፥28-29) የክርስቶስ ሸክም ምንድን ነው? በዚህ ዓለም ያሉ የጠፉ ነፍሳት ሸክም ነው።

    በርካታ ክርስቲያኖች በሕይወት የመሰንበታቸውን ምክንያት አውቀው ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው ሳያውቁ ዝም ብለው መኖራቸው የሚያስገርም ነው። በሕይወት የሚኖሩበት ምክንያት ቤቶችን ሊሠሩና የዚህን ዓለም መልካም ነገሮች ለማጋበስ አይደለም። ብዙ ገንዘብ ለማግኘትና በዚህ ዓለም ላይ ሀብትን ለማካበትም አይደለም። የመኖራችን ዋና ዓላማ አንድ ብቻ ነው፤ያም ሁሉን ነገር የሰጠንን አዳኝ ማገልገል ነው። በክርስቶስ አካል ውስጥ የሚሰጠው አብዛኛው አስተምህሮ ግን ክርስቲያኖችን ከትክክለኛው የሕይወት ዓላማቸው የሚለይ መሆኑ አሳዛኝ እውነታ ነው።

    "ስለ አምላካችን እናስብ፣

    ስለአዳኛችንና ስለንጉሣችን

    ሁሉን ስለሰጠው…

    የእርሱ ወዳጆች እንሆን ዘንድ ሁሉን ተወ"¹

    ብዙውን ጊዜ ስለ አዳኛችንና ንጉሣችን እንደማናስብ አውቃለሁ። ብዙውን ጊዜ ሁሉን የሰጠንን እርሱን አናስብም። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ያለንን ሁሉ የማንሰጠው። ለዚህም ነው በመንግሥቱ ውስጥ መካንና ፍሬ አልባ የሆንነው።

    ምዕራፍ 2

    ብዙ ክርስቲያኖች ተጠርተዋል

    አንተ እግዚአብሔርን ብትሆንና የምታድናቸው ስድስት ቢሊዮን ሕዝብ ቢኖሩህ ምን ልታደርግ ትችል ነበር? አንድ ወይም ሁለት ሰዎችን በመላክ ልታድናቸው ትሞክራለህ ወይስ ብዙ ሰዎችን ትልካለህ? በእርግጥም ብዙ ሰዎችን ወደ መከሩ ትልካለህ፤ ያ እንግዲህ እግዚአብሔር በትክክል እያደረገ ያለው ነገር ነው። እርሱ ብዙ ሰዎችን ጠርቷል! በቤተ ክርስቲያን ፊተኛ ወንበር ላይ የሚቀመጡትን ጥቂት መጋቢዎች በማየት አትታለል። ይህ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ጥቂት ሰዎች እንደተጠሩና በጉባኤው ውስጥ አብዛኛዎቹ ሰዎች እንዳልተጠሩ ሊያስመስል ይችላል። እውነታው ግን የዚህ ተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን። ምክንያቱም ዓለምን ለማዳን ሥራ ጥቂት መጋቢዎች ብቻ ሳይሆኑ ብዙዎች ተጠርተዋል።

    ስለ እግዚአብሔር ጥሪ አምስት እውነታዎች

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው

    የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

    ማቴዎስ 22፥14

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው። ማለት ምን ማለት ነው?

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት በቁጥር የበዛ ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት ብዙሃኑ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት ቁጥሩ የትየለሌ የሆነ ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት አያሌው ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት ከቁጥር ያለፈ ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት ብዙ ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት ብዙሃኑ ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የተጠሩ ብዙዎች ናቸው ማለት አብዛኛው ሕዝብ ተጠርቷል ማለት ነው።

    የሚያሳዝነው ብዙ መጋቢዎች ጉባኤያቸውን የሚያዩት ጥሪ እንደሌላቸው ሰዎች አድርገው ነው። ለእግዚአብሔር ብዙ ማድረግ እንደማይችሉ አድርገው ይቆጥሯቸዋል። በርካታ መጋቢያን ጉባኤያቸውን እንዴት የተሻለ ሕይወት መኖር እንደሚችሉ ያስተምሯቸዋል። ስለሆነም አብዛኛው ስብከት ስለ ራሳችን፣ ስለ ሕይወታችን፣ ስለ ትዳራችን፣ ስለ ቤታችን፣ ስለ ገንዘባችን ወ.ዘ.ተ. ነው። እንግዲህ እንደዚህ ዓይነቱ ስብከት ነው ዛሬ በርከት ያለ፣ ራስ ወዳድና ፍሬ አልባ የሆኑ ጉባኤዎችን የሚፈጥረው።

    መጋቢያን፣ ሐዋርያት፣ ወንጌላውያንና አስተማሪዎች ቅዱሳንን ወደ ፍፁምነት በማድረስ ቅዱሳን አግልግሎትን እንዲሠሩ ማድረግ ነበረባቸው። የነፍሳትን ምርኮ መሰብሰብ የሚጠበቅበት ወንጌላዊ እንኳን ዋና ሥራው ቅዱሳን አገልግሎትን እንዲሠሩ ወደ ፍፁምነት ማድረስ ነው። እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። (ኤፌሶን 4፥11-13)

    ጥሪው ለፍሬያማነት ነው

    ቀድሞውንም የተጠራህ ነህ፤ ጥሪን እስክስትሰማ መጠበቅ የለብህም

    ኬት ግሪን

    ምን እንድንሠራ ነው የተጠራነው? የተጠራነው ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ወንጌላውያንና አስተማሪዎች እንድንሆን ነው? መልሱ ባጭሩ አይደለም። ምክንያቱም አብዛኛዎቻችን እንደነዚህ ዓይነት ለየት ያለና ከፍ ያለ ጥሪ የለንም። ባጭሩ ሁላችንም ፍሬያማ እንድንሆን ተጠርተናል።

    እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።

    ዮሐንስ 15፥16

    ክርስቲያናዊ አስተምህሮዎቻችንን በአግባቡ እስከመጨረሻው ተከትለን ቢሆን ኖሮ፣ ብዙ ክርስቲያኖች ዋጋ የሚከፍሉና ለእግዚአብሔር አንድ ነገር የሚያደርጉ በሆኑ ነበር። ዛሬ የሚያሳዝነውና ምናልባትም አስቀያሚ የሆነው የብዙ ክርስቲያኖች ገፅታ ለክርስቶስ የምናደርገው ትንሽ መሆኑ ነው። በሚያስደንቅ ፍቅርና ጸጋ ድነትን ያገኘን ብንሆንም ሌሎችን ለማዳን አንድን ነገር ለመተው ዝግጁነት የለንም። ክርስቲያኖች ሕይወታቸውን እንዲህ እያባከኑና ለጌታ አንዳች ሳያደርጉ መታየታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው።

    አንዳንድ ሰዎች በሚያስደንቅ መንገድ ተጠርተዋል

    ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፣ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። እየተንቀጠቀጠ እየተደነቀ፣ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው።

    ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።

    የሐዋርያት ሥራ 9፥3-6

    ሐዋርያው ጳውሎስ ትዕይንታዊ በሆነና በሚያስገርም መልኩ ነበር የተጠራው። የሚያንፀባርቅ ብርሀን ከሰማይ ሲወርድ አየ፤ በፊቱ ላይ ብርሃን አንፀባረቀ ደግሞም የሚያነጋግረውን ድምፅ ሰማ። በመሬት ላይ ወደቀ፤ ለበርካታ ቀናትም ዓይኖቹ ታወሩ። እንዳለመታደል ሆኖ አንድ ሰው የራሱን ልምምድ ለሌሎች ሲያካፍል ሁሉም ሰው ያንኑ ዓይነት ልምምድ እንዲኖረው ይፈልጋል። እያንዳንዱ ሰው ብርሃን ማየትና ድምፅ መስማት ይፈልጋል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንደተጠሩ አያምኑም። ይሁንና እግዚአብሔር ሊወሰን እንዲሁም ተመሳሳይ በሆነና ሊገመት በሚችል መንገድ ራሱን ደጋግሞ እንዲገልጥ ሊጠበቅ አይችልም። በአንድ ጊዜ የሠራበትን መንገድ በየጊዜው ምን ሊያደርግ እንደሆነ በሚገመት መልኩ በየጊዜው እየደገመ እንዲያደርግ የሚጠበቅ አምላክ አይደለም።

    በአንድ ወቅት ኬኔት ሔገን ከልብ ሕመም በሽታ እንዴት እንደተፈወሱና ሞታቸውን ከሚጠባበቁበት አልጋቸው ላይ እንዴት እንደተነሱ ማንበቤን አስታውሳለሁ። አንድ ቀን ታመምሁና እኔም ያንን ልምምድ ለመተግበር ሞከርሁ። ወዳጄ ሆይ እውነቴን ነው የምነግርህ ኬኔት ሔገን የተለማመዱትን ነገር ለመለማመድ ስሞክር ሕይወቴን ላጣ ነበር። እመነኝ እግዚአብሔር ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚሠራበት የተለያየ መንገድ አለው።

    አንዳንድ ሰዎች በተለመደ መንገድ ተጠርተዋል

    "እርሱም፦ ውጣ፥ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ

    የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ።" (1ኛ ነገሥት 19:11-12)

    ትዕይንታዊ በሆነ መልኩ የእግዚአብሔርን ጥሪ ማየት ትልቅ ነገር ነው። ሁላችን እንደዚህ ዓይነት አስደናቂ ልምምድ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲኖረን እንናፍቃለን። እንደ አንድ ሰባኪ የተለማመድሁትን ለጉባኤ ለማካፈል እንደዚህ ዓይነት አስደናቂ ልምምድ እንዲኖረኝ እናፍቅ ነበር። ይህም ሁል ጊዜ፣ የበለጠ ኃይለኛ እንደሚያስመስለኝ ይሰማኝ ነበር። ምህረት!

    በእኔ ግምት ብዙዎች የተጠሩት በተለመደ መንገድ ነው። ይህም ጥሪያቸውን ቸል እንዲሉ ያደርጋቸዋል። ስለ ሰዎች መጠራት በምሰብክበት ጊዜ በውስጣቸው ያለ አንዳች ኃይል እንደሚነሳሳ አስተውያለሁ። ብዙ ሰዎች ተጠርተዋል ነገር ግን ይህንን መጠራታቸውን አያውቁም። በአስገራሚ መንገድ እንዲጠሩ ይጠብቃሉ። ይሁንና ብዙውን ጊዜ ጥሪው የሚመጣው በተለመደውና ተራ በሆነ መንገድ ነው። እንደ ኤሊያስ ያሉ አንጋፋ ነቢያት የእግዚአብሔርን ጥሪ በሚያስደምምና በሚገርም መልኩ በመጠባበቅ ተሳስተዋል። አንተም በእዚያ መንገድ የእግዚአብሔርን ጥሪ የምትጠባበቅ ከሆነ ከበረከትህ ጋር ትተላለፋለህ። እርሱም፦ ውጣ፥ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፈነ፥ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ። እነሆ፣ ኤልያስ ሆይ፥ በዚህ ምን ታደርጋለህ? የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ። (1ኛ ነገሥት 19፥11-13)

    አንዳንዶች አገልግሎትን ሲመኙ ተጠርተዋል

    ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1