Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል
በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል
በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል
Ebook87 pages38 minutes

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ከክርስቲያን መሪዎች ውስጥ ታዋቂ የሆነው ዶ/ር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከሚስጢሮቹ አንዱን እንዲህ በማለት ይናገራል « ማንም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገው ህብረት ውስጥ ትልቁ ሚስጢር ምንድ ነው ብሎ ቢጠይቀኝ ፣ካለምንም ጥርጥር የምመልስለት በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የማደርገው የጥሞና ጊዜ ኃይል ነው እላለሁ »። ይህን መጽሐፍ ለመጻፍ የወሰነው ፣ አንተም የጥሞናን ጊዜን ኃይል ትርፉን እንድታገኝ በማሰብ ነው።

Languageአማርኛ
Release dateJun 1, 2018
ISBN9781641356596
በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል

Related ebooks

Reviews for በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ የጥሞና ጊዜ ሊኖርህ ይችላል - Dag Heward-Mills

    ምዕራፍ 1

    የጥሞና ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ልማድ 

    የሰው ሕይወት ሁለተኛው አጋማሽ የተገነባው፣ በመጀመሪያው አጋማሽ ከተገኘው ልማድ ነው፡፡ 

    ዶስቶይቪስካይ

    የሰው ልጅ የምግባረ ሰናይ ጥንካሬ የሚገነባው ከልማዳዊ ድርጊቶቹ ነው፡፡ 

    ፓስካል

    ልማድ፣ ላድርገው ብለህ ሳታስብበትና ሳታስተውል የምታደርገው ድርጊት ነው፡፡ እያንዳንዱ መልካም ክርስቲያን ብዙ መልካም ልማዶች አሉት፡፡ እነኚህ መልካም ልማዶቹ ናቸው እርሱነቱን የገነቡት፡፡

    ታላላቅ ሰዎች ሁሉ እነርሱን ታላቅ ያደረጓቸው ልማዶች አሏቸው፡፡ ጌታችን ኢየሱስንም ታላቅ ያደረጉት ልማዶች ነበሩት።

    ኢየሱስ ክርስቶስ

    ወደቤተክርስቲያንያለማቋረጥመሄድ

    ኢየሱስ መልካም ልማዶች እንደነበሩት ታውቃለህ? መጽሐፍ ቅዱስ እርሱ በሰንበት ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመሄድ ልማድ እንደነበረው ያስተምረናል።

    ወዳደገበቱም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።

    ሉቃስ 4፡16

    2. ወደ ጸሎት መስክ መሄድ

    ኢየሱስ ለጸሎት ወደ አንድ የአትክልት ስፍራ የመሄድ ልማድ ነበረው፤ ይህ ስፍራ አዘውትሮ የሚሄድበት ስፍራ ነበር፡፡ እናም በዚህ የአትክልት ስፍራ የመጸለይ ልማድ እንዳለው ሁሉም ሰው ያውቃል፡፡

    ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ። ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ጊዜ ወደዚያ ስለ ተሰበሰቡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ደግሞ ስፍራውን ያውቅ ነበር።

    ዮሐንስ 18፡1፣2

    ዳንኤል

    ዳንኤል በየቀኑ የሚጸልይባቸው የተወሰኑ ሰዓቶች ነበሩት፡፡ ይህን ማድረግ ልማዱ ነበር፡፡ ይህ አንዱ የእርሱ ሕይወት ታላቅ ምስጢር ነበር፡፡

    ዳንኤልም ጽሕፈቱ እንደ ተጻፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ በየዕለቱ ሦስት ጊዜ በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም።

    ዳንኤል 6፡10

    እያንዳንዱ ክርስቲያን ስለ ልማድ ሊያውቃቸው የሚገቡ አሥር ነገሮች

    ልማድሳይታሰብናሳይታቀድበቀላሉበመደጋገምየሚፈጸምድርጊትነው፡፡

    ልማድአውቀኸውምሆነሳታውቀውልምድህሆኖየምትፈጽመውድርጊትነው፡፡

    ልማድአብዛኛውንጊዜየወደፊትሕይወትህላይተፅእኖያመጣልብለህየማትገምተውጉልህያልሆነድርጊትነው፡፡ከዚህምየተነሣነውብዙሰዎችየመልካምልማድጽንስሀሳብንኃይለኛመሣሪያትናበወደፊቱሕይወታቸውስኬትላይተፅዕኖአምጪመሆኑንልብየማይሉት፡፡

    ልማድመልካምወይምክፉ፣ተፈጥሮአዊወይምመንፈሳዊሊሆንይችላል፡፡መንፈሳዊልማድከምንላቸውውስጥእንደማለዳጸሎት፣የየዕለቱየጥሞናጊዜይገኙበታል፡፡ተፈጥሯዊልማዶችከምንላቸውምዘወትርጥርስንመቦረሽናበየቀኑገላንመታጠብየመሳሰሉናቸው፡፡

    መልካምልማዶችእንደክፉልማዶችሁሉበየቀኑበቀላሉይፈጸማሉ፡፡

    መጥፎልማዶችሰውየውምንእየሆነበትእንደሆነሳይገነዘብወደማያቋርጥውድቀትናሽንፈትያመራሉ፡፡

    መልካምልማዶችሰውየውምንእንዳደረገምሳያስተውልወደማያቋርጥስኬታማነትናድልያመራሉ፡፡

    መጥፎልማዶችበቀላሉይለመዳሉ፣ነገርግንበቀላሉመላቀቅአይቻልም፡፡መልካምልማዶችንበቀላሉመገንባትአይቻልም፣ሆኖምበቀላሉአብሮመኖርይቻላል፡፡

    እያንዳንዱስኬታማክርስቲያንወደስኬትያመጡትበርካታመልካምልማዶችአሉት፡፡ከረዥምዓመታትበፊትአንዲትጓደኞዬበየቀኑጠዋትእንዴትከእግዚአብሔርጋርየጥሞናጊዜእንደሚኖረኝአስተማረችኝ፡፡እኔምየግልልማዴአድርጌአሳደግሁት፣እናምእንደክርስቲያንናእንደአገልጋይምየሕይወቴትልቅምስጢርይህሆነ፡፡የምሰብካቸውመልእክቶቼሁሉየዚህመልካምልማድውጤትናቸውማለትይቻላል፡፡

    ልማዶችለክርስቲያኖችየዋስትናምንጭናቸው፡፡ይህየሚሆንበትምክንያትአንድመሪበውጥረትውስጥበሚሆንበትሰዓትእንኳበልማድ፣በተፈጥሮእናበቀላሉየሚያደርጋቸውአንዳንድመልካምነገሮችአሉ፡፡መሪበውጥረትውስጥሲሆንምንማድረግእንዳለበትእናምንዓይነትእርምጃመውሰድእንዳለበትለማሰብምጊዜላይኖረውይችላል፡፡ከዚያችግርውስጥለመውጣትየሚያስችለውየጸሎትወይምየጥሞናጊዜመልካምልማድሊሆንይችላል፡፡ልክእንደኢየሱስ፣እኔአብዛኛውንጊዜለጸሎትየምሄድበትቦታአለኝ፡፡አብዛኛውንጊዜበስሬካሉመጋቢዎቼጋርምአብረንወደዚያእንሄዳለን፡፡ይህልማድአንዳንዴየሚያጋጥመኝአደጋምንእንደሆነበማላውቅበትጊዜእንኳበመንፈስየተጠበቅሁሊያደርገኝይችላል፡፡

    ምዕራፍ 2

    የጥሞና ጊዜ - የታላላቅ ሰዎች ምስጢር

    ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር የጥሞና ጊዜ ነበረው

    እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። ነገም የተዘጋጀህ ሁን፥ በማለዳም ወደ ሲና ተራራ ወጥተህ በዚያ በተራራው ራስ ላይ በፊቴ ቁም።

    ከአንተም ጋር ማንም ሰው አይውጣ፥ በተራራውም ሁሉ ማንም አይታይ መንጎችና ከብቶችም በዚያ ተራራ ፊት አይሰማሩ። ሙሴም እንደ ፊተኞቹ አድርጎ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረበ በነጋውም ማልዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወደ ሲና ተራራ ወጣ፥ ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች በእጁ ወሰደ፥ እግዚአብሔርም በደመናው ውስጥ ወረደ፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆመ፥ የእግዚአብሔርንም ስም አወጀ። እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፣

    እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ። ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጐነበሰና ሰገደ።

    አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነውና ጌታዬ በመካከላችን ይሂድ ጠማማነታችንንና ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ ለርስትህም ተቀበለን አለ። እርሱም አለው፦ እነሆ እኔ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ በምድር ሁሉ፥

    በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እንደ እርሱ ያለ ከቶ ያልተደረገውን ተአምራት በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ እኔም በአንተ ዘንድ የምሠራው ነገር የሚያስፈራ ነውና አንተ ያለህበት ይህ ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን ሥራ ያያል።

    ዘጸአት 34፡1-10

    እግዚአብሔር ለኢያሱ በየቀኑ የጥሞና ጊዜ እንዲኖረው አዞታል፡፡

    የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።

    ኢያሱ 1፡8

    አዳም እስከ ወደቀበት ጊዜ ድረስ የጥሞና ጊዜ ነበረው፡፡

    እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ፦ ወዴት ነህ? አለው። እርሱም አለ፦ በገነት ድምፅህን ሰማሁ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1