Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የድል ሚስጢር
የድል ሚስጢር
የድል ሚስጢር
Ebook258 pages1 hour

የድል ሚስጢር

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ለእያንዳዳችን ሀይወት ውጣ ውረድ አልው። በአብዛኛው ጊዜየሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንወጣቸው የሚያስፈልገን ጥበብን በመለማምድ ነው። ጥበብ ችግርን ተቋቁመን ወደ ተአምራታዊ ሀይወት የሚያስገባን የእግዚአብሔር ሚስጥራዊ እርዳታ ነው። እግዚአብሔር ለክብር ጠርቶሃል። ለክብርህና ለውበትህ መንገድ ሆኖ የትዝጋጀው የእግዚአብሔር ሚስጢራዊ አሰራር ድብቅ አሰራሩ ነው። በመጽሐፍ ውስጥ ያለው መገለጥ ለህይወትህ ድል ይስጥህ። ይህ ምጽሐፍ ለከፍታህ እውቀትን ይስጥህ።

Languageአማርኛ
Release dateNov 8, 2018
ISBN9781641357531
የድል ሚስጢር
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የድል ሚስጢር

Related ebooks

Reviews for የድል ሚስጢር

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የድል ሚስጢር - Dag Heward-Mills

    ድል ምሥጢር ቁጥር 1

    የድል ምሥጢር  ምንድን ነው?

    የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን? ወይስ ጥበብን ለብቻህ አድርገሃልን?

    ኢዮብ 15:8

    የድል ምሥጢር አስደናቂ ፍጡር የሚያደርግህ ምሥጢር  ነው! የድል ምሥጢር  የእግዚአብሔር ምሥጢር  ነው!

    የእግዚአብሔርን ምሥጢር  ሰምተሃል? የእግዚአብሔርን ምሥጢር  አንብበሃል? የእግዚአብሔርን ምሥጢር  አውቀሃል? የተሰወረ የእግዚአብሔር  ጥበብ የእግዚአብሔር ምሥጢር  ነው! የእግዚአብሔርን ጥበብ ተቀብለሃል? ከላይ መገለጥ ተቀብለሃል? የእግዚአብሔርን ምሥጢር  ካልሰማህ በእርግጥ የሚያስፈልግህን ነገር አጥተሃል። የእግዚአብሔር ምሥጢር  ለክብርህና እና ለውበትህ የታዘዘልህ የተሰወረ የእግዚአብሔር ጥበብ ነው።

    ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።

    1ኛ ቆሮንቶስ 2:7

    የሚያስፈልግህ ምድራዊ ጥበብ አይደለም። ምድራዊ ጥበበ የምጣኔ ሀብት፣ የህግ፣ የሂሳብ፣ የሳይንስ፣ የሂሳብ አያያዝ ወዘተ ትምህርት ነው። እነዚህ ሁሉ ምድራዊ ጉዳዮች ጥሩ ቢሆኑም ነገር ግን ምድራዊ የሰው ጥበብ ናቸው። ለእነዚህ ነገሮች ሁሉ ቦታ አላቸው። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ግን ቦታ የላቸውም። በቤተ ክርስቲያ ውስጥ ከዚህ እጅግ ከፍ ያለ ነገር አለን  …ቃሌም ስብከቴም … በሚያባብል በ(ሰው) ጥበብ ቃል አልነበረም። (1ኛ ቆሮንቶስ 2:4)። ከዚህ እጅግ የሚበልጥ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ጥበብ አለ። የእግዚአብሔር ጥበብ የእግዚአብሔርን ምሥጢር  ይይዛል። ለህይወትህ የሚያስፈልግህ ይህንን ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን። (1ኛ ቆሮንቶስ 2:7)። ይህ ዓይነቱ ጥበብ ሊያሸበርቅህ እና ወደ ህያው አስደናቂ ፍጡር ሊቀይርህ ታዞልሃል።

    የእግዚአብሔርን ምሥጢር  የማግኘትን አስደናቂ ጥቅሞች እንመልከት

    የእግዚአብሔርን ምሥጢር  ማግኘት ያለብህ ስድስት ምክንያቶች

    1. ህይወት እና ሞት የእግዚአብሔርን ምሥጢር  በማግኘትህ የሚወሰኑ ናቸው:

    ንጉሡ መልሶ። ነገሩ ከእኔ ዘንድ እንደ ራቀ ታውቃላችሁና ጊዜውን እንድታስረዝሙ እኔ አውቃለሁ። ሕልሙንም ባታስታውቁኝ አንድ ፍርድ አለባችሁ፤ ጊዜውን ለማሳለፍ የሐሰትንና የተንኰልን ቃል ልትነግሩኝ አዘጋጅታችኋል፤ ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፥ ፍቺውንም ማሳየት እንድትችሉ አውቃለሁ አለ። ከለዳውያኑም በንጉሡ ፊት መልሰው። የንጉሡን ነገር ያሳይ ዘንድ የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም፤ ከነገሥታትም ታላቅና ኃይለኛ የሆነ እንደዚህ ያለ ነገር የሕልም ተርጓሚንና አስማተኛን ከለዳዊንም አልጠየቀም። ንጉሡም የሚጠይቀው ነገር የቸገረ ነው፤ መኖሪያቸው ከሰው ጋር ካልሆነ ከአማልክት በቀር በንጉሡ ፊት የሚያሳየው ማንም የለም አሉ። ስለዚህም ንጉሡ ተበሳጨ እጅግም ተቈጣ፥ የባቢሎንንም ጠቢባን ሁሉ ያጠፉ ዘንድ አዘዘ። ትእዛዝም ወጣ፥ ጠቢባንንም ይገድሉ ዘንድ ጀመሩ፤ ዳንኤልንና ባልንጀሮቹንም ይገድሉ ዘንድ ፈለጉአቸው።

    ዳንኤልም ገብቶ ፍቺውን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት ጊዜ ይሰጠው ዘንድ ንጉሡን ለመነ። የዚያን ጊዜም ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደ። ዳንኤልም ባልንጀሮቹም ከቀሩት ከባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይሞቱ ስለዚህ ምሥጢር ምሕረትን ከሰማይ አምላክ ይለምኑ ዘንድ ነገሩን ለባልንጀሮቹ ለአናንያና ለሚሳኤል ለአዛርያ አስታወቃቸው። የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት፤ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ። ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ። ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። የጠለቀውንና የተሠወረውን ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፥ ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነው።

    ዳንኤል 2:8-13, 16-22

    ዳንኤል እና ባልንጀሮቹ ህይወታቸውን ሊያሳጣ የሚችል ሁኔታ ውስጥ ገብተው ነበር። ሞትን ፊት ለፊት እያዩት ነበር። አብዛኞቹ ጠቢባን፣ ሕልም ተርጓሚዎች እና አስማተኞች ስህተትን የተሞሉ ግብዞች እንደነበሩ ንጉሱ ያውቅ ነበር። ንጉስ ናቡከደነጾር ቤተ መንግስቱን ከእንደዚህ ካሉ አስመሳዮች ማፅዳት እጅግ ይፈለግ ነበር። ንጉሱም ያዘጋጀው ፈተና እውነተኛ የሆኑ ጠቢባን ብቻ በቤተ መንግስቱ የእርሱ አማካሪዎች ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስችል ነበር። ጥሩ አማካሪ ለመሆን አንዳንድ ምስጢራትን ማወቅ ይኖርብሃል። ከየትኛውም ታላቅ ስራ እና ታላቅ ሰው ጀርባ ምስጢራት አሉ።

    ብዙ ጊዜ አንድን ሰው ታላቅ ስላደረገው ነገር የተሳሳተ ግምት አለን። አብዛኛውን ጊዜ የአንድን ሰው የታላቅነት ምሥጢር አናውቅም። አንዳንድ ምስጢራትን ማወቅ ከመጥፋት ይጠብቅሃል። የእውቀት መንፈስም የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ጠላት እንደ ጎርፍ በሚመጣበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በውጊያ ያዋርደዋል ኢሳይያስ 59፡19(አ.መ.ት.) ጠላት ሊገድልህ ሲመጣ የእግዚአብሔር መንፈስ እርሱን ተቃውሞ ይነሳል። ‘በውጊያ ያዋርደዋል’ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ኑስ ሲሆን ትርጓሜውም ያጠፋዋል ማለት ነው። በእውቀት አንዳንድ ነገሮች እንዲጠፉ ይደረጋሉ። ከብዙ ዓመታት በፊት የወባ በሽታ፣ አስም፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም የስኳር በሽታ የያዘው ሰው በሙሉ ይሞት ነበር። አሁን ግን በእውቀት እነዚህ በሽታዎች ‘እንዲጠፉ’ እና ብዙ ሰው እንዳይገድሉ ተደርጓል።

    ህይወት እና ሞት አንዳንድ ምስጢራትን በማወቅህ የሚወሰኑ ናቸው። ለህይወትህ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ምስጢራት አሉ። የእግዚአብሔርን ምሥጢራት በማግኘት የተባረከ ማንኛውም ሰው ህይወት እና ሞት የሆነ ምስጢራትን በማወቃቸው ልክ የሚወሰኑ እንደሆነ ያውቃል። ለዚህ ነው ከእግዚአብሔር መገለጥን ልትፈልግ የሚገባው። ምሥጢርን ማወቅ የበላይ እንድትሆን ያደርግሃል። በሳይንስ፣ በህክምና፣ በህዋ ሳይንስ፣ በግብርና፣ በሜካኒክስ እና ፊዚክስ የመጡ አዳዲስ ግኝቶች በሙሉ አንዳንድ ምስጢራትን በማወቅ የተገኙ ናቸው። እነዚህ ምስጢራት ለብዙ ሺህ አመታት የነበሩ እውነታዎች ናቸው። አዲስን ነገር የሚፈጥሩ ሰዎች ምስጢራትን ፈልገው ያገኙ ሰዎች ናቸው። E ሁልጊዜም ከ mc² ጋር እኩል ነበር። አንስታይን ለብዙ ሺህ አመታት የነበረውን ምሥጢር  ነው ፈልጎ ያገኘው።

    የድል ምሥጢር  ድልን የሚያመጣልህ መገለጥ ነው። የድል ምሥጢር  በህይወትህ፣ በስራህ እና በአገልግሎትህ ለውጥን የሚያመጣ ከመንፈስ ቅዱስ የምትቀበለው መገለጦች ነው። ብዙ ጊዜ በህይወት እና በሞት መካከል ያለው ልዩነት ትንሽ እውቀት ነው። ዛሬ እግዚአብሔር እውቀትን ሊሰጥህ ይችላል! እግዚአብሔር ህይወትህን እና አገልግሎትህን ሙሉ ለሙሉ የሚለውጥ ትንሽን እውቀት እንድታውቅ ሊያደርግ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች እነዚህ ወሳኝ ትናንሽ እውቀቶች ‘መገለጥ’ ብለው ይጠሯቸዋል። ምንም ብለህ ብትጠራቸው እነዚህ የድል ምስጢራት ወደ ታላቅ ድል መንሳት እና ማሸነፍ ይመሩሃል።

    በታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ብዙ የድል ምስጢራት ውጤት ጥሩ ምሳሌዎችን እናገኛለን። በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን አንድ ወረርሺኝ በሽታ ወደ ዓለም ገብቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሎ ነበር። ብዙ ሰዎች ሞቱ፤ አንድ አካባቢ ላይ የሚኖሩ ህዝቦች ሙሉ አለቁ። ይህ ወረርሺኝ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተደጋጋሚ እየመጣ፣ ህዝብን እያሸበረ እና ብዙ ሰዎችን በሞት እየጨረሰ ስለቀጠለ የዚህ በሽታ ፍርሃት ለብዙ ዓመታት ቀጠለ።

    በ1347እ.ኤ.አ. ይህ ወረርሺኝ አውሮፓን ሲመታ በእርግጥ በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አስከፊ የሆነ የሰዎች እልቂት ደርሶ ነበር። ይህ እባጭን የሚያመጣ ወረርሺኝ የአውሮፓን ህዝብ ሲሶውን ጨረሰ። አስባችሁታል፥ አንድ በሽታ እጅግ ከመሰራጨቱ የተነሳ የአንድን አህጉር ሲሶ ህዝብ ሲጨርስ? በቅርብ ዘመን እንኳን የኢቦላ ቫይረስ በሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ እና ጊኒ በተሰራጨ ጊዜ አስር ሺህ ሰዎች ብቻ ናቸው የሞቱት። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መጨረስ እና ሁሉ አህጉራትን ባዶ ማድረግ የሚችል በሽታ እንዴት አስከፊ ሊሆን እንደሚችል አስቡ።

    በዚህ ወረርሺኝ የተጠቁ ሰዎች የመትረፍ እድላቸው በጣል ትንሽ ነበር ምክንያቱም የበሽታው ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳት እና በሰውነት ውስጥ የደም መፍሰስ ነበር፥ ይህም ጥቋቁር ነጠብጣብ እና እባጮች እንዲወጡባቸው ያደርግ ነበር። ይህን በሽታ የያዘው የትኛውም ሰው ከሶስት እስከ አምስት በሚሆኑ ቀናት ውስጥ ይሞት ነበር።

    በዚያ ዘመን የነበሩት ዶክተሮች ይህ ወረርሺኝ የመጣው እርጥበት ባለው የተበከለ አየር፣ ሳይቀበሩ እየበሰበሱ ባሉ በድኖች እና ንጽህና ከማጣት እንደሆነ አስበው ነበር። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ወረርሺኙ እየተሰራጨ ያለው በአይሁዶች እንደሆነ አስበው ነበር። የአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ዶክተሮች ወረርሺኙ የሚመጣው በቅማሎች እና በአይጦች በሚመጣ ቀላል ባክቴሪያ እንደሆነ አላወቁም ነበር። የህክምናው ዓለም ስለ ቀላል ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች አያውቅም ነበር። ስለዚህ ወረርሺኙን መዋጋት የሚችሉበት ምንም መንገድ አልነበራቸውም። ስለ ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ምሥጢር  እውቀት ቢኖር ኖሮ ብዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት በዳኑ ነበር።

    በ1877እ.ኤ.አ. ሊውስ ፓስቸር እና ሮበርት ኮች አንድ አየር ወለድ የሆነ ባኪዩሊስ (bacillus) የሌላን ባክቴሪያ፥ ባኪዩሊስ አንትራሲስ (bacillus anthracis) እድገት መግታት እንደሚችል አዩ። ይህ በፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች የታየው ሁኔታ አንቲባዮሲስ(antibiosis) ተብሎ ይጠራ ጀመር። በ1942እ.ኤ.አ. መድሃኒቶች እንደዚህ ዓይነት ባህርይ ሲያሳዩ በአሜሪካዊው ማይክሮ ባዮሎጂስት፤ ሰይማን ዋክስማን አንቲባዮቲክስ ወይም ፀረ ባክቴሪያ ተብለው መጠራት የጀመሩት።

    ይህ የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ምሥጢር  በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ያልነበረው! ይህ ምሥጢር ነው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን በወረርሺን እንዳይሞቱ መከላከል ይችል ነበር። ቀላይ የሆኑ እንደ ስትሬፕቶማይሲን (streptomycin)፣ ጀንታሚሲን (gentamicin) እና ሲፕሮፍሎክሲን (ciprofloxacin) ያሉ መድሃኒቶች በሽታውን ማስቆም ይችሉ ነበር። ዛሬ በእንደዚህ ዓይነት ወረርሺኝ የመሞት እድላችሁ በጣም ትንሽ ነው።

    የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ምሥጢር  ታውቆ ቢሆን ኖሮ አንድም ሰው በወረርሺኙ ባልሞተ ነበር። የድል ምሥጢር  ህይወትህን ሙሉ ለሙሉ ይለውጣል። የድል ምሥጢር  ብዙ ህይወቶችን ያድናል። የድል ምሥጢር  ሁሉን ነገር ይቀይራል።

    በህይወትህ መጸለይ ያለብህ አንዱ በጣም አስፈላጊ ጸሎት የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጥህ ነው። የድል ምስጢራትን ታገኝ ዘንድ ጸልይ! ይህ የጊዜውን መገለጥ እና እውቀት ለማግኘት የምትጸልየው ጸሎት በህይወትህ ትልቅ ልዩነትን ያመጣል።

    2. ብልጽግናህ የሚወሰነው የእግዚአብሔርን ምሥጢር  በማግኘትህ ነው

    እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል። በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤ በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።

    ኢሳይያስ 45:1-3

    የድል ምሥጢር  ወደ ብልጽግና ይመራሃል። ብዙ ሐብቶች ከዓይን የተሰወሩ ናቸው። ብዙ እውነተኛ ሀብት ከእይታ የተሰወረ ነው። ለዚህ ነው በስውር የተደበቀ ሀብት የተባለው። በዓለም ላይ አብዛኞቹ ሀብቶች በምስጢራዊ ስፍራ የተሰወሩ ናቸው። እነዚህ የምድር ሀብቶች ለማግኘት እንዴት ማግኘት እንደምትችል ሊገለጥልህ ይገባል። ያ ሀብት የተሰወረበትን ምስጢራዊ ስፍራ ልታገኝ ይገባል።

    አንዳንድ ሰዎች ሀብታም እንደሆኑ ለብዙ ሰዎች እንቆቅልሽ ነው አሁንም። ሰዎች ለመበልጸግ ብዙ ነገር ያደርጋሉ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው የብልጽግና ምሥጢር  የሚሰጣቸው። ገንዘብ የተሸሸገው ምስጢራዊ በሆነ ቦታ ነው። አንዳንድ ምስጢራትን እስካላወቅህ ድረስ እድሜ ልክህን በሙሉ በድህነት ትኖራለህ። የብልጽግናን እና የስኬትን ምሥጢር  እንዲሰጥህ የመገለጥ መንፈስ ያስፈልግሃል። የቤተ ክርስቲያን እድገትም የሚለቀቀው አንዳንድ ምስጢራትን በማወቅ ነው። ከእውነተኛ ስኬት ጀርባ ያለውን ምሥጢር  ብንረዳ ያቃቱን ነገሮቻችን ሁሉ ወዲያው ያቆማሉ።

    ምስጢራትን ልታገኛቸው(ልትደርስባቸው) ያስፈልግሃል ምክንያቱም ታላቅነት እና ብልጽግና አስፈላጊ የሆኑ ምስጢራትን በማግኘት የሚመጡ ናቸው። መኪኖችን፣ አውሮፕላኖችን፣ በእጅ የሚያዙ ኮምቲዩተሮችን (እንደ አይፓድ)፣ ስልኮችን እና ቴሌቪዥኖችን የፈጠሩ ሰዎች የዓለማችን ሚሊየነሮች ናቸው። ብዙ ሀገራት እነዚህን ነገሮች መስራት የሚያስችል ምስጢራትን አያውቁም። እነዚህን ምስጢራት ያገኙ ሰዎች ግን የዓለማችን እጅግ ሀብታም ሰዎች ሆነዋል። የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ምሥጢር  ባገኙ ሰዎች እና ቲማቲምና ብርቱካን በሚሰበስቡ ሰዎች መካከል ያለውን ትልቅ ልዩነት አስብ። ቲማቲምና ቃሪያን ለመሰብሰብ ምንም ልዩ ምሥጢር  አያስፈልግም። ነገር ግን ቴሌቪዥን ለመስራት መታወቅ ያለባቸው ምስጢራት አሉ። ምስጢራትን ማወቅ ሰዎች ትልቅ ዋጋ እንዲኖራቸው ያደርጋል። ዳንኤል መገደሉ ብቻ ሳይሆን የቀረው ነገር ግን በከተማው ሶስተኛው እጅግ ኃያል ሰው እንዲሆን እና በአንገቱ ዙሪያ ላይ በተደረገ የወርቅ ሰንሰለት ምልክት ብልጽግናንም እንዲቀበል ተደረገ። አንተም በመገለጥ መንፈስ የእግዚአብሔርን ምሥጢር  ስታገኝ እጅግ ተፈላጊ ሰው ትሆናለህ። በመገለጥ መንፈስ በወርቅ ትሸፈናለህ።

    የዚያን ጊዜም ብልጣሶር ለዳንኤል ሐምራዊ ግምጃ እንዲያለብሱት፥ የወርቅ ማርዳም በአንገቱ ዙሪያ እንዲያደርጉለት አዘዘ፤ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዥ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ።

    ዳንኤል 5:29

    3. የእግዚአብሔር ምሥጢር  ለጻድቃን እና ለእርሱ ነቢያቶች የሚሰጥ ነው፡

    ጠማማ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ርኩስ ነውና፤ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው።

    ምሳሌ 3:32

    ምሥጢርህን ለሁሉም ሰው አትነግርም። እግዚአብሔርም ሚስጥሩን ለእያንዳዱ ሰው ይነግራል ብለህ ለምን ትጠብቃለህ? እግዚአብሔር ሚስጥሩን የሰጣቸው ሰዎች እርሱ ጻድቅ ብሎ ለሚያያቸው ነው። እግዚአብሔር የእርሱን መገለጥ  ክፉ ከሆኑ ሰዎች ይሰውራል እና ለጻድቃን ይሰጣል።

    ባሪያዎች ለጌቶቻቸው ቅርብ ናቸው፤ አጠገባቸውም ሆነው ይሰራሉ። ስለዚህ በውጭ ያሉ ሰዎች የማያውቋቸውን ብዙ ምስጢራት ባሪያዎች ማወቃቸው እንግዳ ነገር አይደለም። የእግዚአብሔር ባሪያ ለመሆን ጥረት አድርግ እና የእርሱ ነብይ ለመሆን ጥረት አድርግ፤ ያኔ አስደናቂ ምስጢራትን በመትረፍረፍ ለማግኘትህ እርግጠኛ ትሆናለህ።

    በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።

    አሞጽ  3:7

    4. የእግዚአብሔር ምሥጢር  በህይወትህ በተለየ ወቅት የሚሰጥ ነው።

    እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደ ነበረው ጊዜ፥ እንደ ፊተኛው ወራት ምነው በሆንሁ! በራሴ ላይ መብራቱ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለማውን አልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥ በሙሉ ሰውነቴ እንደ ነበርሁ ጊዜ፥

    እግዚአብሔር ድንኳኔን በጋረደ ጊዜ (የእግዚአብሔር ምሥጢር በድንኳኔ በነበረ ጊዜ)

    ኢዮብ 292-4

    ኢዮብ በህይወቱ በአንድ ወቅት እነዚህን ምስጢራትን በማወቁ ይደሰት ነበር። እግዚአብሔር ምስጢራትን እና መገለጥን ይሰጠው ስለ ነበረበትን ዘመን በጥልቅ ስሜት ተናግሯል። እግዚአብሔር አንዳንድ መገለጦችን የሰጠህን ጊዜያት ሁልጊዜም ታስታውሳቸዋለህ።

    ኢዮብ እነዚያን የመገለጥ ዘመናት ድጋሚ ለመለማመድ በጣም ፈልጎ ነበር። እውነተኛ ነብያት መገለጥ ሲኖራቸውም ይነግሩሃል፤ ሳይኖራቸውም እንደሌላቸው ይነግሩሃል። በእውነቱ፥ መገለጥ ሁልጊዜም አይመጣም። ኢዮብ የእግዚአብሔር ምስጢራት ይገለጡለት እንደነበረው ዘመን ድጋሚ ወጣት በሆንኩ እያለ ነው (ኢዮብ 29፡4)።

    ኬኔት ሄገን ከ1950-1958እ.ኤ.አ. ባሉት አመታት ውስጥ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን በራእይ ስምንት ጊዜ እንዲያይ እንዴት እንደባረከው ይናገራል። ከ1958እ.ኤ.አ. በኋላ እንዴት ጌታ በእንደዚያ ዓይነት ራእይ እንዳልተገለጥም ይናገራል። ኬኔት ሄገን ጌታ ሲገለጥለት ገና የሠላሳ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1