Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ
እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ
እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ
Ebook133 pages59 minutes

እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

ዕድሜው ለሴቶች ብዙ እድሎች ፈጣሪ ሆኗል. በጣም ጥሩውን ሽያጭ "ታማኝነት እና ታማኝነትን" ያካትታሉ. ከሰባት የወር ሴቶችን ከሁለት ሳምንት ያነሱ ናቸው. እነዚህ መብራቶች የብርሃን የቤት አዳራሽ ዓለም አቀፍ ተብሎ ይጠራሉ.
በተመሳሳይ ጊዜ አዛዡ, ታማኙ ሰው እና ዓለም አቀፍ ዱህንግ ዢ በ Cooper FC ውስጥ እያገለገሉ ነው. ለተጨማሪ መረጃ www.daghewardmills.org

Languageአማርኛ
Release dateJun 1, 2018
ISBN9781641348065
እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ

Related ebooks

Reviews for እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating1 review

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

  • Rating: 5 out of 5 stars
    5/5
    this book best book tanks to our lord Jesus krist

Book preview

እንዴት ብርቱ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለህ - Dag Heward-Mills

በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።

ኤፌሶን 6፣10

ጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ ክርስቲያኖች እንዲበረቱ ይመክራል።  በርታ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ሥፍራ ይገኛል።  ብዙ ክርስቲያኖች በአካላቸው በፖለቲካ ከትምህርት፣ በንግድ፣ ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ብርቱዎች ናቸው፤ በጌታ ግን አይደሉም።  እግዚአብሔር ግን በጌታ እንድትበረታ በፅኑ ይፈልጋል።

በጌታ መበርታት ብርቱ ክርስቲያን መሆን ማለት ነው።  ብዙዎች ጌታን ያውቃሉ በጌታ አይበረቱም።  ቀሪውን ዘመናቸውን በመፈሳዊ ሕይወታቸው ደካማ እንደሆኑ ይጨርሳሉ።  ይ¬ህ መጽሐፍ ጥሩ ብርቱ ክርስቲያን እንዴት ልትሆን እንደምትችል ያስተምርሃል። አንድን ጥሩ ብርቱ ክርስቲያን ለመሆን ከፈለግህ እነዚህን ባህሪያት ልታዳብር ይገባል።  ብርቱ ክርስቲያን ለመሆን መንፈሳዊነትን፣ መንፈሳዊ ቅናትን፣ ብስለትን፣ ቅድስናን እና ፅናትን በጌታ ማጐልበት ይኖርብሃል። 

ብርቱ ክርስቲያን ለመባል በሕይወትህ ማደግ ያለባቸወ የተለያዩ ነገሮች አሉ።  ይህም መጽሐፍ አንተን ወደ ብርቱ ክርስቲያን ለመለወጥ እነዚህ የሕይወት አቅጣጫዎች የሚያሳድግ ነው።  በጌታ ለመበርታት የምትፈልግ ከሆነ ዘጠኙ የትኩረት አቅጣጫዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

1. ብርቱ ክርስቲያን ለመሆን ጥልቅ የክርስትና ሕይወትን ማጐልበት ይጠይቃል።

በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።

መዝሙር 42፣7

2. ብርቱu ክርስቲያን መሆን መፅናት ነው።

ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፣58

3. ብርቱ ክርስቲያን መሆን የማይነቃነቅ ሰው መሆን ማለት ነው።

ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።

1ኛ ቆሮንቶስ 15፣58

4. ብርቱ ክርስቲያን መሆን መንፈሳዊ መሆን ነው።

እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።

1ኛ ቆሮንቶስ 3፣1

5. ብርቱ ክርስቲያን መሆን መቀደስ ነው።

ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።

ዕብራውያን 12፣14

6. ብርቱ ክርስቲያን መሆን በሳል መሆን ነው።

እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥

ኤፌሶን 4፣14

7. ብርቱ ክርስቲያን መሆን ለበጐ ነገር ሁልጊዜም የተነቃቃ ነው።  በጌታ መበርታት ማለት የነቃ መንፈስ ባለቤት መሆን ነው።

ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው።

ገላትያ 4፣18

8. ብርቱ ክርስቲያን መሆን ፍሬያማ መሆን ነው።

እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።

ያዕቆብ 15፡16

9. ብርቱ ክርስቲያን መሆን በማንኛውም ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት የተዘጋጀ ሕይወት ነው።

ስለዚህ፥ እስራኤል ሆይ፥ እንደዚህ አደርግብሃለሁ እስራኤልም ሆይ፥ እንደዚህ ስለማደርግብህ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ።

አሞፅ 4፣12

ራስህን እንድታበረታ የሚያስፈልግበት ስድስት ምክንያቶች

1. ክፉውን ድል መንሳት እንድትችል ራስህን አበርታ

አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።

1ኛ ዮሐንስ 2፣14

ክፉው እየደከመ አይመጣም። ክፉውን ድል መንሳት የምትቸለው ስትበረታ ብቻ ነው።  ከጠላት ጋር የምትቀልድ ከሆነ ተጠያቂ የምትሆነው እራስህ ነህ።  ከሰይጣን ጋር መዋጋት ማለት የብዙ ዓመት ልማድ ካለው ተዋጊ ጋር መዋጋት ነው።  ዲያቢሎስም ለብዙ ዓመታት ብዙ ክርስቲያኖችን ይዋጋ ነበረ። ክርስቲያኖችን በመፈተን እና በማጣል ልምድ ያለው ነው። እርሱ አዲስ አይደለም፣ አንተ ግን ነህ! ክፉውን ለማሸነፍ ትችል ዘንድ ተነሳና ብርቱ ሁን። 

በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሳለሁ ታላላቆቼ ያንገላቱኝ ነበር።  አንድ ዓመት ብቻ ከበላዬ በሆኑ ልጆች አማካኝነት ብዙ ስቃይ እና ቅጣት ደርሶብኛል። በዚህ ወቅት በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ያለውን የክፋት ጥልቀት ለመረዳት ቻልኩ።  እነዚህ እድሜያቸው አስራ ሶስት እና አስራ አራት ዓመት የሆነ ልጆች አንድ ዓመት ብቻ ከእኔ በመብለጣቸው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉኝ።

አንዳንድ ጊዜ እንደ ዝንጀሮ ደንስ ይሉኛል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እጆቼን አዘርግተው በአንድ እግሬ እያስቆሙ ይቀጡኛል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እስከ ሌሊቱ ዘጠኝ ስዓት ድረስ ሽንት ቤት ያሳጥቡኛል።  አንዳንዱ በርካታ ባልዲ ሙሉ የከብት እበት ለአምስት ኪሎ ሜትር ያህል ያሸክሙኛል።  አንዳንዴ ደግሞ አልጋቸው ጐን "ቆሜ ቢንቢ ሲመጣ የመግደል ሥራ ይሰጡኛል።  አንዳንዴ ደግሞ። ጋሪ የሚባል ምግብ እና የተፈጨ መራራ ነገር እንድበላ ያስገድዱኛል።  ለብዙ ወራት በእነዚህ ክፉ ታላቆቼ እጅ ተሰቃየሁ።  አንድ ቀን ከክፍል ጓደኞቼ መካከል አንዱን ፈፅሞ እንደማይጠራ የትም እንደማይላክ ማንም እንደማያንገላታውና እንደማይቀጣው አስተዋልኩት ነገር ግን ለምን እንደሆነም ገባኝ በክፍል ውስጥ ከነበሩት ታማሪዎች ይልቅ የእርሱ ሰውነት ይተልቃል፣ ይጠነክራልም። ይሄኛው የክፍል ባልደረባዬ ከሌሎቹ የክፍል ባልደረቦቼ ይልቅ ሰውነቱ ትልቅ ጠንካራ በዕድሜውም ይበልጠን ነበር፤ ከእኛ በክፍል የሚበልጡን ሁሉ በእርግጥ ይፈሩት ነበር። አንዳቸውም በፊቱ ሊቆሙ አይችሉም።

ከበላዮቻችን አንዱ ድንገት አንድ ትንሽ ልጅ! ብሎ ይጣራል፤ ይህንን ስንሰማ ከበታች ያለን ሁላችንም እንሮጣለን ተለቅ የሚለው ልጅ ግን ለበላዮቼ ጥሪ ምላሽ አይሰጥም ዝም ብሎ ስራውን ይቀጥላል።  ማንም ደፍሮ አይጠይቀውም እርሱ በጣም ጠንካራ ስለነበረ ይፈሩታል! እኔ ግን ጠንካራ አልነበርኩም።  እኔ ደካማ ተደብዳቢ እና ተቀጪ ነበርኩ።  እንደዚያ እንደ ትልቁ እና እንደጡንቻሙ የክፍል ጓደኛዬ በሆንኩ!

የጥንካሬን አስፈላጊነቱን የተማርኩት እዚህ ነው። ጠንካራ ስትሆን ከፉዎቹ ሳይወዱ በግድ ይተውሃል። ክፉዎቹ እንደሚሸነፉ ያውቃሉ።  ሰይጣን መጨረሻው እንደማይሰምርለት ስለሚያውቅ ለመተንኮስ እንኳን አይደፍርም።  ከአንተ የበረታ ከተነሳብህ ስለሚረታህ አንተ ጠንካራ መሆን አለብህ።

ኃይለኛ ሰው ጋሻና ጦር ይዞ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ገንዘቡ በሰላም ይሆናል፤ ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ መጥቶ ሲያሸንፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን ጋሻና ጦር ይወስድበታል ምርኮውንም ያካፍላል።

ሉቃስ 11፣21-22 

እራስህን ለማበርታት ይህ ትልቅ ተነሳሽነትን ሊሰጥህ ይገባል!  እየበረታህ ስትመጣ ክፉው አንተን ላለመንካት ይገደዳል ምክንያቱ የተለያዩ ፈተናዎቹ በአንተ ላይ እንደማይሰሩ ያውቃል። በጌታ በርታ!

2. ጠላት እንደገና ሊያጠቃህ እያቀደ ነውና ራስህን በጌታ አበርታ።

ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፥ ሶርያውያንም ሸሹ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር በፈረሱ አመለጠ።

የእስራኤል ንጉሥም ወጥቶ ፈረሶቹንና ሰረገሎቹን ያዘ፥ ሶርያውያንንም በታላቅ ውጊት ገደላቸው።

ነቢዩም ወደ እስራኤል ንጉሥ ቀርቦ። የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው ዓመት ይመጣብሃልና ሂድ፥ በርታ፥ የምታደርገውንም ተመልከትና እወቅ አለው።

1ኛ ነገስት 20፣20-22

ጠላትህ ሊያጠቃህ እያቀደ ነው።  ወደድክም ጠላህም ትጠቃለህ።  ጠላትህ አይቶሃል፤ ኢላማው ውስጥ አስገብቶሃል።  ጊዜው ሲመጣለት አንተ ሳትነካው እርሱ ይሰነዝርብሀል።  ኢየሱስ በዘመኑ

Enjoying the preview?
Page 1 of 1