Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!
ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!
ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!
Ebook120 pages1 hour

ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

ይህ በጌታ የተሰጠ ማረጋገጫ ለዚህ አዲስ እና ኃይለኛ መጽሐፍ “ሰይመው፣ ይገባኛል በል፣ ውሰድ!” መሰረት ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ አማኙ መንፈሳዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ መጣስ እንዲሆንለት የሚያስችለውን ዋነኛ ቁልፍ ያሳያሉ፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954430
ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!

Related ebooks

Reviews for ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!!

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

2 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደ!!! - Dag Heward-Mills

    ሰይመው! ይገባኛል በል!! ውሰደው!!!

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ትርጉም፡- ብስራት ተክሌ

    አርትዖት፡- ዘላለም ፀጋዬ እና መጋቢ ልዑል ኃይሉ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    Find out more about Dag Heward-Mills 

    Healing Jesus Crusade

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    Write to:

    Dag Heward-Mills

    P.o.Box 114

    Korle-Bu

    Accra

    Ghana

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    ስልክ +251912063821

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባኢትዮጵያ

    ISBN: 978-1-61395-443-0

    ይህንን መፅሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው።

    ማውጫ

    የስኬት ዋነኛ ቁልፍ

    እውነተኛ የሆነ እምነት ማዳበር

    ሰይመው!

    ‘‘የእኔ ነው’’ በል!

    ነኝ! አለኝ! እችላለሁ!

    እንዴት እንደምትወርሰው

    በተግባር ‘‘የእኔ ነው’’ ማለትና አዎንታዊ የስምምነት ቃል!

    ምዕራፍ 1

    የስኬት ዋነኛ ቁልፍ

    ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል . . .

    ዕብራውያን 10፡38

    ‘‘ሰይመው! ይገባኛል በል! ውሰደው!

    ምን ማለት ነው;

    ‘‘ሰይመው፣ የእኔ ነው በል፣ እናም ውሰደው’’ የሚለው አነጋገር በአጭሩ እምነትን ስለመተግበር ይገልጻል። ሁሉም ክርስቲያን እምነት ሊኖረውና ሊለማመደውም ይገባል። እምነት በሕይወታችን የመጣስና የተአምራት ምክንያት ነው። እምነት የጸሎታችን መልስ ምክንያት ነው! በአጠቃላይ እምነት ያላቸው ሰዎች በተቃራኒው እምነት ከሌላቸው የበለጠ ባለጠጎች ናቸው። እኔ በእምነትና ያለ እምነት በሚራመዱ ክርስቲያኖች መካከል ያለውን ልዩነት አይቼአለሁ።

    የእምነት ሰዎችም እንደሌላው ሰው ይበሳጫሉ፣ ይታመማሉ እንዲሁም ሌሎች ነገሮች ያጋጥሟቸዋል። ነገር ግን በአጠቃላይ እነርሱ ላይ ያስተዋልሁት ነገር በረከትን፣ መበልጸግን እንዲሁም ረጅም ዕድሜን ነው።

    ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።

    ዕብራውያን 10፡38

    ከእምነት ወደ ኋላ ብታፈገፍግ እርሱ በአንተ እንደማይደሰት እግዚአብሔር በቃሉ ተናግሯል። እምነት ብዙም ጠቃሚ አይደለም ብለው የሚያስቡ አሉ። እነዚህ ሰዎች ከእምነት ሰዎችና ስለ እምነት ከሚነገረው መልእክት ይሸሻሉ። በክርስትና ሕይወታቸውም የበለጠ ትኩረት መስጠት ያለባቸው ለትዕግሥት፣ መረጋጋትና ቅድስና ለመሳሰሉት እሴቶች እንደሆነ ያስባሉ። በእርግጥ በክርስትና ሕይወታችን ከተጠቀሱት ነገሮች ወደ ኋላ ማለት አለብን ማለት አይደለምልብ የሰውነታችን በጣም ጠቃሚ ክፍል ነው ስንል ኩላሊት አይጠቅምም ማለት አይሆንም፤ ሁለቱም ጠቃሚ ናቸው። ምክንያቱም ሁለቱም ለሰውነታችን የተለያየ ሚና ይጫወታሉ።

    እምነት በእያንዳንዱ ሰው የክርስትና ሕይወት ላይ በጣም ልዩ እና ጠቃሚ ሚና አለው። መጽሐፍ ቅዱስም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት የማይቻል መሆኑን ይነግረናል።

    ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።

    ዕብራውያን 11፡6

    የእግዚአብሔር ቃል ያለ ፍቅር እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም አይልም። ያለ ሰላም እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም ተብሎም አልተጻፈም።

    መጽሐፍ ቅዱስ እውነታውን ግልጽ አድርጎልናል። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም!

    አብርሃም በእግዚያብሔር ላይ የነበረው እምነት ጽድቅ ሆኖ ተቆጥሮለታል። አብርሃም ኤልሻዳይ የሆነው አምላክ በእርጅና ዘመኑ ልጅ እንደሚሰጠው አምኖ ተቀብሏል። አብርሃም የራሱ ድክመቶች ነበሩት። ስለ ሚስቱ ዋሽቷል። እንዲሁም ሚስቱን አማኝ ላልሆኑ ነገሥታት አሳልፎ ሰጥቷል። ምንም እንኳ ቢዋሽም ሆነ ቢያመቻምችም አምላኩ በተናገረው ቃል ላይ እምነት ስለነበረው እግዚአብሔር በእርሱ ተደስቷል።

    ምናልባት በአንተ መመዘኛ አብርሃም ፈተናውን አላለፈ ይሆናል። ይሄኔ በአንተ አስተያየት አብርሃም ጥሩ ሰው አልነበረም። በእግዚአብሔር እይታ ግን አብርሃም ታላቅ ሰው ነበር። ታላቅነቱም የእምነቱ ውጤት ነው።

    ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።

    ሮሜ 4፡21፣ 22

    ውድ ክርስቲያን ወዳጄ፣ እግዚአብሔር ደስተኛ የሚሆነው ስታምነው ነው። እግዚአብሔር ይፈውሰኛል ብለህ ስታምን ደስተኛ ታደርገዋለህ! እግዚአብሔር እንደሚያበለጽግህ ስታምን፣ እግዚአብሔርን ደስተኛ ታደርገዋለህ። ነገሮችህን ጥሰህ የምትወጣው በቅርብ ጊዜ እንደሆነ ስታምን እግዚአብሔር ይደሰታል። ረጅም እድሜ እኖራለሁ ብለህ ስታምን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1