Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች
አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች
አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች
Ebook262 pages3 hours

አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

መለኮታዊ ኃይል ዛሬም አለን ? በመለኮታው ኃይል ውስጥ ሆኜ ማገልገል እችላለሁን ? እግዚአብሔር አሁንም ሰዎችን እየፈወሰ ከሆን ፣ለምን ሁሉንም አይፈውስም ? የፈውስን ቅባት እንዴት ልቀበል እችላለሁ ? በዚህ ድንቅ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሐፍ የተለያዩ ገፆች ውስጥ ለእነዚህና ለሌላም ብዙ ጠያቄዎችህ መልሶቹን ድረስባቸው።

Languageአማርኛ
Release dateFeb 28, 2011
ISBN9781613954256
አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች

Related ebooks

Reviews for አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    አገልግሎትህን አጉላው በመንፈስ ቅዱስ በሚደረግ ተዓምራትና መገለጦች - Dag Heward-Mills

    በመንፈስ ቅዱስ የሚደረጉ ተዓምራትና መገለጦች አገልግሎትህን ለምን እንደሚያጎሉት

    ዓለምን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመድረስ ተዓምራት እና መገለጦች ብቸኛ እድሎቻችን ናቸው። የምድርን ወገኖች እና አህዛብን ለመንግስቱ ለማብቃት ብቸኛ እድሎቻችን ናቸው። የእግዚአብሔር አገልጋዮች የተጠሩበትን ተግባር እንዲከውኑ የሚረዷቸው እድሎቻቸው ናቸው። ኢየሱስ ለጠራቸው አስራ ሁለት ደቀመዛሙርትም ሆነ ሰባዎቹ የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራቶች እና መገለጦች ነበሯቸው። ለታላቁ ተልዕኮም አገልግሎት ሲባል ለእኛ ተሰጥተውናል። እግዚአብሔር የሰጠንን ብናውቅ እና ብናስተውል፣ ይህ ሁሉ ለእኛ ተሰጥተውናል።

    2. በመንፈስ ቅዱስ የሆኑ ተዓምራት እና መገለጦች ዓለምን በክርስቶስ ለመድረስ ይረዳሃል።

    አንድ ወቅት ከተለያዩ የአገሬ ግዛት የምርጫ ውጤት መግለጫ ሲሰጥ፣ በርካታ ሚሊዮን ነፍሳት በገጠሩ ክፍል እንደሚኖሩ ተገነዘብሁ። የእግዚአብሔር ልብ ስለሚጠፉ ነፍሳት ይደማል። ለህዝባችን የማህበራዊ አገልግሎት ለመስጠት ለፖለቲካዊ ጫና ጎንበስ ማለት የለብንም። የማህበራዊ አገልግሎቶች ማለትም ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች መስጠታችን በዋነኛነት ለህዝባችን ጠቃሚዎች አያደርጉንም። ቤተክርስቲያን ልዩ ኃይል እና ቅባት የታደለች በእግዚአብሔር የተቀባች ልዩ ተቋም ነች። በዚያም ኃይል እና ቅባት አማካኝነት፣ እግዚአብሔር እንድንሰራ የሰጠንን ማከናወን እንችላለን። የጠፋውን የሰው ልጅ ለማዳን ስብከትን፣ ማስተማርን እንዲሁም ፈውስን መንገድ አድርጎ መርጥዋል።

    3. በመንፈስ ቅዱስ የሆኑ ተዓምራቶች እና መገለጦች ከተሸሸግህበት ያወጡሃል።

    ከተሸሸግህበት ልትወጣ ይገባሃል! አገልግሎትህ በዓለም ሊታይ እና ሊሰማ ያስፈልጋል! ጥበብ ካልተሰማ እና ካልታየ ጥቅሙ ምንድር ነው? ኢየሱስ ይህ ነው በማይባል የአናጺ ቤት ቢያድግም እንኳ እግዚአብሔር ግን ለየት ያለ ነገር ሰጥቶት ነበር። ኢየሱስን ከተደበቀበት ያወጣው ነገር ምን ነበር? መልዕክቱ እንዲደመጥ ያደረገው ምን ነበር? ኢየሱስ ያለ ዘመናዊ ማስታወቂያ ምን ማድረግ ይችል ነበር? ኢየሱስን ከተሸሸገበት ያወጡት ነገሮች ተዓምራቶች እና መገለጦች ናቸው። አንተንም ተዓምራቶች እና መገለጦች ከተሸሸግህበት ሊያወጡህ የሚችሉ እድሎችህ ናቸው። ኢየሱስ መጽሐፍ አልጻፈም፣ መኪና አልነዳም፣ በባቡር አልተጓዘም፣ በአውሮፕላን አልበረረም ሆኖም ግን ስመ ጥር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዝናው ሁሉ በዙሪያው ወጣ፣ . . . ከተማይቱም ሁሉ በደጅ ተሰባስባ ነበር (ማር. 1፡28-33) ይላል። የዚህ ዓለም ከተሞች በጀማ ስብከቶቻችን ደጅ ላይ ይገኙ ዘንድ የፈውስ ቅባት ያስፈልገናል። የዚህ ዓለም ከተሞች በቤተክርስቲያኖቻችን ይገኙ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራቶችና መገለጦች ቁልፍ ናቸው። የፈውስ ቅባት ከተማው ሁሉ በደጅህ እንዲከማቹ ስለሚያደርግ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትነግራቸው ያስችልሃል።

    4. የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራቶች እና መገለጦች ልባቸው የተሰበሩ በርካቶችን ወደ አገልግሎትህ ይስባል።

    ኢየሱስ ልባቸው የተሰበረውን ይጠግን ዘንድ እንደተቀባ ተናግሯል። የልብ መሰበር ከእጮኛ ጋር ከመለያየት የበለጠ ነገር ነው። የተሰበሩ ልቦች በአጠቃላይ መነሾዋቸው ሐዘን ነው። ብዙዎች በህይወት በሚገጥማቸው ነገሮች ግራ ይጋባሉ። ሰዎች ሁሉም ነገር መልካም እንደሆነላቸው መስለው ይኖራሉ ነገር ግን ውስጣቸው እየደማ፣ እያዘነ እና እየተጎዳ ነው።

    አብዛኛው የሰዎች ችግር በመድሐኒት፣ በስነልቦና ባለሙያ ወይንም በስነ አዕምሮ ሐኪም አይፈውሰውም። ብዙ ሰዎች ተስፋ ያገኙ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲነካቸው ያሻል። እግዚአብሔርም ወደ ህዝቡ ልብ በመምጣት የተሰበረ ልባቸውን መፈወስ ተያይዟል።

    ብዙ ፖለቲከኞች ሰዎች ሁልጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን መምጣታቸው ያስደንቃቸዋል ምክንያቱም መጋቢዎቻቸው ገንዘቦቻቸውን እየዘረፏቸው እንዳሉ ስለሚያስቡ ነው። ይህንን መታለል የሚመስለውን ህዝቡ አንዴት ሊገነዘቡት እንዳልቻሉ ያስገርማቸዋል። አየህ፣ የተለያዩ ችግሮችን የተሸከሙ ሰዎች አያስታውቁም። ሰዎች በውጪያዊው ገጽታቸው ፈገግ ይላሉ፤ ውስጣቸው ግን ያለቅሳል። ቤተክርስቲያንን የሚተቹ ሰዎች የማያውቁት ነገር ቤተክርስቲያን ለሰዎች የምታደርገውን ነገር ስለማያውቁ ነው።

    አንድ ጊዜ አስታውሳለሁ በቴሌቪዝን አንድ ስመጥር የፈውስ አገልጋይ ወንጌላዊ፣ ቃለ መጠይቅ እየተደረገለት ነበር። ስለ ደመወዙ፣ቤቶቹ እና መኪኖቹ ተጠየቀ። ቃለመጠይቁ አላዋቂነቱን ለማሳየት የታቀደ ነበር።

    ኋላ ላይ ግን ለጸሎት የስልክ መስመሮች ክፍት ተደረጉለትና አንድ ሰው የጸሎት ጥያቄ አቀረበ። ወዲያውኑ የአየሩ ድባብ ተለወጠ። ደዋዩ ወደ ሞት እያዘገመ ያለ የካንሰር ታማሚ ነበር። ወንጌላዊው እንዲጸልይለት ፈለገ። አሁን ቃለ መጠይቅ አቅራቢው የሰነዘራቸው አይረቤ ጥያቄዎቹ ሁሉ እንደምናምን ሆኑ። ቃለ መጠይቅ አቅራቢው አስቸኳይ እገዛ ከሚሻ ለቅሶ ከሚተናነቀው የከፋ ሁኔታ ላይ ከሚገኝ ደዋይ ጋር ተፋጠጠ። ይህንን እገዛና አገልግሎት ደግሞ ሊያበረክት የሚችል ይህ ወንጌላዊ ብቻ ነበር። የወንጌላዊው አገልግሎት አስፈላጊነት ለሁሉም የታወቀ ነበር። በርካታ ሰዎች ለከፉ ነገሮቻቸው እና ተስፋ ለታጣበት ሁኔታዎቻቸው የጸሎት ጥያቄ ለማቅረብ መደወላቸውን ቀጠሉ። ሰዎች የተለያዩ መሻቶች አሏቸው፤ ለነዚያ ፍላጎታቸው ታዲያ የፈውስ ቅባት መፍትሔ ይሰጣቸዋል። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተዓምራት እና የመገለጥ የእግዚአብሔር ኃይል በህይወትህ ሲኖር ፣ ልባቸው የተሰበሩ ሰዎች ወዳንተ መጉረፍ ይጀምራሉ።

    5. የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራቶች እና መገለጦች አገልግሎትህን ለማህበረሰቡ አስፈላጊ ያደርገዋል።

    አስፈላጊ መሆን ስንል ጠቃሚ መሆን ማለት ነው። ለዓለም አስፈላጊ የምንሆነው የፈውስ ቅባት በእኛ መስራት ሲጀምር ነው ። አስፈላጊዎች ሆንን የሚባለው የተሰበሩ ልባቸው ሲጠገን እና ለድሆችም ወንጌል ሲሰበክ ነው። ክፉ መናፍስቶች በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ህይወታቸውን በፍርሃት ይሞሉታል። የፈውስ አገልግሎት ታዲያ ሰዎችን ከክፉ መናፍስቶች ነጻ ያወጣቸዋል።

    በርካታ ህዝቦች በባዕድ አምልኮ ፍርሃት ተገዢ ሆነዋል። በመንፈስ ቅዱስ የተዓምራት እና የመገለጥ አገልግሎት ግን ርግማን ይሰበራል፣ ፈውስም ይመጣል። ብዙዎች መለኮታዊ ኃይልን ይረዳሉ ። የፈውስ ቅባት ካለብህ በየአገሬው ህዝብ ፊት ቆመህ የሚያውካቸውን ክፉ ኃይል ልትቋቋም ትችላለህ! ሆኖም ግን አነስተኛ የሆነች የሰንበት ስብከት ይዘህ በዘመናችን ያለውን ጥንቆላ እና ሟርት ለመገዳደር አቅም አይኖርህም ።

    በዓለማችን እጅግ ብዙ ዓይነት ባዕድ አምልኮ አለ። አሳ ማጥመድ የማይፈቀድባቸው ወንዞች አሉ! አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከእነዚህ ወንዞች ውሃ መቅዳት ይከለከላሉ ። ከባእድ አምልኮ የተነሳ ሊገነቡ የማይቻሉ ግድቦች አሉ። ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ይፈራሉ። ከባዕድ አምልኮ የተነሳ አንዳንድ ጊዜ እና ወቅቶች ላይ መልበስ የምንፈራቸው ልብሶች አሉ። የመንገድ መብራቶችን በአንዳንድ መንገዶች ላይ ማብራት አይቻልም ምክንያቱም እነዚህን መንገዶች እነዚህ አማልክቶች ይኖሩባቸዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ሰዎች አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ መንገዶችን አንዳንድ ጊዜ መጠቀም ይፈራሉ። አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ በአርብ መጓዝ ይፈራሉ። በየትኛውም ወር በ13ኛው ቀን መጓዝ የሚፈሩም አሉ። 13ኛው ቀን ደግሞ አርብ ላይ ከወደቀ ፍርሃቱን ያባብሰዋል። የአየር መንገድ ሰራተኞች እንኳ ይህ ጉዳይ ያሳስባቸዋል። በብዙ አወሮፕላኖች ላይ 13ኛ መቀመጫ የለም። ብዙ ህንጻዎች 13ኛ ፎቅ የሚባል የላቸውም።

    አንድ ጊዜ በአውሮፕላን እየበረርኩ ነበር። ስናርፍ ታዲያ መንገጫገጭ የበዛበት ምቾት የሚነሳ ዓይነት ነበር፤ ለዚህ ታዲያ ካፒቴኑ ይቅርታ ከጠየቀን በኋላ ምክንያቱን ሲያብራራ ቀኑ አርብ 13ኛ ቀን በመሆኑ እንደሆን ገለጸ።

    ምህረት! ብዙ ሰዎች በፍርሃት ውስጥ እየኖሩ ነው።

    ቤተክርስቲያን ልታበረክተው ያለ የሆነ ነገር ሲኖራት አስፈላጊነቷ ይጎላል። ለሰዎች ትክክለኛ ፍላጎት ምላሽ ሲኖረን አስፈላጊዎች እንሆናለን። ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ልታበረክተው የምትችለውን አስተዋጽዖ የትኛውም ምድራዊ መንግስት ማቅረብ አይችልም። ቤተክርስቲያን ልትሰጥ የምትችለውን የትኛውም ፖለቲከኛ መስጠት አይችልም። የትኛውም መምህር ወይም የህክምና ዶክተር ቤተክርስቲያን ልትሰጥ የምትችለውን መስጠት አይችልም ። እግዚአብሔር ብቻ ልባቸው የተሰበረውን መጠገን እና ህዝቡን ማዳን ይችላል። እያንዳንዱ የዓለም ክፍል የመንፈስ ቅዱስን ተዓምራት እና መገለጥ ይስፈልገዎል ።

    እንደ ቤተክርስቲያን አስፈላጊነታችን ትምህርት ቤቶችን እና ዩኒቨርስቲዎችን በመክፈት አይመጣም። ትምህርት ማዳረስ ያለበት መንግስት ነው። ቤተክርስቲያን ትምህርት ከሰጠች ሊታይ የሚገባው ለዚያ አገር ህዝብ የፍቅር ስጦታ መሆኑን ነው። የሰው ልጅ ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ስራ ይሰጣል።

    የታላቁ ተልዕኮ አደራ ተሰጥቶናል። ይህ ሐላፊነት ለየትኛውም ሌላ ተቋም አልተሰጠውም። አስፈላጊነታችን ስለ ኢየሱስ ከመስበክ እና ከማስተማር ይመነጫል። አስፈላጊነታችን ህሙማንን ከመፈወስ ይወጣል። አስፈላጊነታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ከሚከሰቱ ተዓምራቶች እና መገለጦች ይመጣል።

    6. የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራት እና መገለጦች በእስራት ያሉ ነፍሳትን ወደ ቤተክርስቲያንህ እንዲሳቡ ያደርጋል

    በርካታ ሰዎች በዲያብሎስ ተይዘዋል። አንድ ቀን አንድ ጓደኛዬን በእጽ ሱስ ተይዞ አየሁት። በዚያም ጥልቅ ሃዘን ተሰማኝ። የእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ነው ሰዎችን ከእጽ ሱስ፣ ከአልኮል መጠጥ እንዲሁም ከስነ ምግባር ብልሹነት ነጻ የሚያወጣው። ብዙ ሰዎች ታስረዎል ። እራሳቸውን በራሳቸው ነፃ መውጣት አይችሉም። የፈውስ ቅባት ግን ካሉበት እስራትና ባርነት አርነት ያወጣቸዋል።

    የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራት እና መገለጦች ለመካን ሴቶች ተስፋ ይሰጣል። መውለድ እንድትችል ተብሎ እባብ በውስጧ እንዲቀመጥ የተደረገች ሴትን ታሪክ በጥናታዊ ፊልም አንድ ጊዜ ተመለከትኩት ። የባዕድ አምልኮ መሪ ጋር በመሔድ ልጅ ታገኝ ዘንድ የተደረገላት እርዳታ ነበር።

    ለራሴ እንዲህ ስል ተናገርኩ የመካንነት ችግሮች ከአዕምሮ በላይ ናቸው። ሁላችንም በሽቦ የታጠረባቸውን እባቦች እንኳ ቀረብ ብለን ማየት ያስፈራናል። በቴሌቪዥን እንኳ እባቦችን ስናይ በድንጋጤ ሰውነታችንን ይዘገንነናል። ልጅ ታገኝ ዘንድ እባብ በሰውነቷ ውስጥ እንዲቀመጥ የምትፈቅድን ሴት ማየት ደግሞ ፍላጎቷ ምን ያህል የናረ እንደሆን ያሳያል።

    ለስብከት አገልግሎት ስል ለምን የህክምና ሙያዬን እንደተውሁ ሰዎች ይጠይቁኛል። ሰባኪ በመሆን የሚጠቅም ምን ነገር ላደርግ እንደምችል ያስባሉ። አሁን የማረገው ነገር ግን መድሐኒቶችን ከማዘዝ እጅግ የላቀ ነገር ነው። ኢየሱስ ዓለምን በተሻለ መንገድ የሚረዳው በመድሐኒት ቢሆን ኖሮ ዶክተር በሆነ ነበር። ነገር ግን ሰባኪ ነበር ያም አንድ ነገር ሊያስተምርህ ይገባል ።

    ኢየሱስ የመጣው ለተጨቆነው ነጻነት ሊሰጥ ነው። የተጠቃ ሰው ማለት ጉዳት የደረሰበት ሰው ነው። ሕይወት በህመም፣ በጉዳት እና በሐዘን የተሞላች በመሆኗ ኢየሱስ የተጎዳውንና የተጠቃውን በፈውስ ቅባቱ ሊፈውስ መጣ።

    የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ . . .

    ሉቃ 4፡18

    በውሃው ውስጥ አንዳች ክፉ ነገር ስለነበር ኤልሳዕ የከተማይቱን ውሃ ይፈውስ ዘንድ ወጣ።

    የከተማይቱም ሰዎች ኤልሳዕን፦ እነሆ፥ ጌታችን እንደምታይ የዚች ከተማ ኑሮ መልካም ነው፤ ውኃው ግን ክፉ ነው፥ ምድሪቱም ፍሬዋን ትጨነግፋለች አሉት። እርሱም፦ አዲስ ማሰሮ አምጡልኝ፥ ጨውም ጨምሩበት አለ ያንንም አመጡለት። ውኃው ወዳለበቱም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ ከዚህም በኋላ ሞትና ጭንገፋ አይሆንበትም አለ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ነገር ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል። (2ኛ ነገ. 2፡19-22)

    እግዚአብሔር ውሃዎችህን ሲፈውስ፣ መሰረታዊ ፍላጎቶችህን እያሟላ ነው ማለት ነው። በዚህ ዓለም ላይ እግዚአብሔር ብዙ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳሉ ያሳይሃል። ለህመማቸው ህክምና ያጡ በርካቶች አሉ። በድሀ አገራት አንዳንዴ ሴቶች የሚወልዱት ከዛፎች ስር ሆነው ነው። በዚህም ምክንያት ነው ለድሆች የምስራችን እንሰብክላቸው ዘንድ የተቀባነው።

    የዚህ ዓለም ድሆች ቁጥር ከባለጸጉቱ በእጅጉን የበለጠ ነው። እግዚአብሔር ልባችንን ለድሆች ማስፋት ይፈልጋል። አንድ የሆነ የምስራች ከሌለህ ወደዚህ ምድር ድሆች መሄድና መናገር አትችልም። ወንጌል በተጨባጭ ሁኔታ እንዴት ህይወታቸውን ሊነካ እንደሚችል መረዳት ይፈልጋሉ። የወንጌልን አስተምህሮዎች ከእነ በርካታ ችግሮቻቸው፣ ህመሞቻቸው እንዲሁም ከጠሊቁ ድህነታቸው ጋር እንዴት ሊገነዘቡ ይችላሉ?

    ለበርካታ ተዓምራት መጸለይ ይኖርብናል። ልባችን ብዙ ተዓምራትን መናፈቅ ያስፈልገዋል! ይህ ካልሆነ ግን ብዙዎች ወደ ሲዖል እየወረዱ ትናንሽ ጥጋ ጥጎቻችንን ይዘን እየተሟሟቅን እንሰነብታለን።

    7. የመንፈስ ቅዱስ ተዓምራት እና መገለጦች በአገልግሎትህ ውስጥ እግዚአብሔርን ያገነዋል።

    አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ አድነኝ እኔም እድናለሁ አንተ ምስጋናዬ ነህና።

    ኤርምያስ 17፡14

    የኤርምያስ ጩኸት ይህ ነበር፣ አቤቱ ፈውሰኝ እኔም አፈወሳለሁ! እግዚአብሔር ከፈወሰህ፣ በርግጥ ተፈውሰሃል! እግዚአብሔር ካዳነህ፣ በርግጥም ድነሃል! የሰው የፈውስ መንገድ በርካታ ህጸጾች አሉት። በፈውስ ቅባት አማካኝነት እግዚአብሔር በሰዎች ህይወት ውስጥ የሚጫወተውን ሚና ማጉላት ትችላለህ።

    እግዚአብሔር መፈወሱ የህክምናን ሳይንስ አይደግፍም ማለት አይደለም። እግዚአብሔር የህክምና ተቃዋሚ አይደለም። እንዲያውም ሰዎች የመድኃኒትን ጥበብ እንዲያሳድጉ ብልሐትንና እውቀት የሚሰጣቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። የዚህ ስጦታ ምንጭ ነው። እንደ ህክምና ዶክተር በህክምና ሳይንስ አምናለሁ። ስለ ህክምና ሳይንስ እና ስለ ህክምና ዶክተሮች እግዚአብሔር ይመስገን ። ከእነርሱ ውጪ ማድረግ የምንችለው የለም። ሆኖም ግን ከህክምና ሳይንስ በላይ እግዚአብሔር በርሱ ዘንድ የተቀመጠ የላቀ ነገር አለው። የህክምና ሳይንሱ የማይቻለውን እግዚአብሔር ማድረግ ይችላል። አንዳንዴም በህክምናው ሳይንስ የማይቻለውንም ያደርገዋል። ልናውቅ የሚገባው ነገር እርሱ መልካም ነገሮችን እንደሚያድርግ ነው።

    በሳን ፍራንሲስኮ በተከሰተው የመሬት ነውጥ ውስጥ የተረፈውን የአንድ ሰው ታሪክ ብነግራችሁ ደስ ይለኛል። ከመሬት መናወጡ በኋላ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ነበር። በአንድ ህንጻ ፍርስራሽ ስር ለሶስት ሌትና ቀን በህይወት ቆይቷል። በፈረሰ ህንጻ ስር እንዴት ለረጅም ጊዜ እንደቆየ ተጠይቆ ነበር።

    ምላሹ እንዲህ የሚል ነበር እኔ ጠንካራ ፈቃድ ያለኝ ሰው ነኝ። አንድ ነገር ለመስራት ስወስን፣ ምንም ነገር አያቆመኝም። በዚያ ባለሁበት ሁኔታ ላይ እቆያለሁ! ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልልም! ጠንካራ የሆነ ቁርጠኝነትና የፈቃድ ኃይል ስላለኝ ሞትን እንቢኝ አልኩኝ! በህይወት ለመኖር ስለቆረጥኩኝ፣ በህይወት ልቆይ ቻልኩ!

    ሚስቱም ቃለ መጠይቅ ሲደረግላት የሰጠችው ምላሽ የሚከተለው ነበር "በርግጥ፣ ከባለቤቴ ጋር ለበርካታ አመታት ተጋብተን ስለኖርን በሚገባ አውቀዋለሁ። እጅግ ጠንካራ የሆነ የፈቃድ ኃይል አለው! አንድ ነገር ለመስራት ሲወስን ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ሊያንቀሳቅሰው የሚችል ነገር የለም፣ ጽኑ የሆነ ሰው ነው። ቁርጠኛ ሰው ነው። ፕሮጀክቶቹን ይጨርሳል! ወደ ፊት ይገሰግሳል። በተግዳሮቶች የማይዋዥቅ ሰው ነው።ባሌን አውቀዎለሁ። ለ27 ዓመታት በትዳር አብረን ስለቆየን ባሌን በሚገባ አውቀዋለሁ፤ በህይወት ለመኖር ከቆረጠ በህይወት መቆየት ይችላል።

    የዚህ ሰው ዶክተር ራሱ በዚህ አስደናቂ ሁኔታ ውስጥ በህይወት ስለተረፈው ሰው ምን ትላለህ? በማለት ተጠይቆ ነበር። ሲመልስም "በርግጥ፣ ታካሚዬ ጠንካራ ፈቃድ ያለው ሰው ነው። በህይወት ሊተርፍም የቻለው የፈቃድ ኃይል ለአንድ ታማሚ እጅግ አስፈላጊ ነገር በመሆኑ ነው። አንድ ታማሚ ለመሞት ሲወስን ይሞታል። ለመኖርም ሲወስን ይኖራል።

    ይህ ታላቅ የፈቃድ ኃይል ያለው ሰው ግን ከስምንት ቀናት በኋላ በልብ ህመም እንደተጠቃ ታምናለህ? ወዲያውኑም

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1