Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

Arganon መጽሐፈ አርጋኖን
Arganon መጽሐፈ አርጋኖን
Arganon መጽሐፈ አርጋኖን
Ebook193 pages1 hour

Arganon መጽሐፈ አርጋኖን

Rating: 3 out of 5 stars

3/5

()

Read preview

About this ebook

Ethiopian Orthodox Prayer in Amharic to Holly Virgin Mary. the best & the biggest common daily prayer book.
GOD bless you!
1᎐ ባለመለየት ሶስት በተዋህዶ በአኗኗር አንድ በመለኮት ትክክል ከሰውና ከመላእክትም ዘንድ አንድ ስግደት በሚሰገድለት በእግዚአብሔር ስም አምነን ይህንን አርጋኖን የሚባል የምስጋና መጽሐፍ እንጽፋለን።
2᎐ይኸውም የምስጋና መሰንቆ የቅዳሴም እንዚራ። አምላክን የወለደች በእብራይስጥ (ማሪሃም) የተባለች መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስን የምታሰጥ የእመቤታችን የማርያምን ድንግልናዋን የማድነቅ መጽሐፍን እንጽፋለን።
3᎐ክብሯንና ገናንነቷንም የመናገር ስሟንም የማክበር ቅድስናዋንም የማመስገን ለንግስትነቷም መገዛት እንዲገባ የሚናገር መጽሐፍ እንጽፋለን።
4᎐አምላክን የወለደች እመቤታችን ይኽችውም የወርቅ መሰላል ናት ከሚያሰጥመው ባህር ማዕበል ሞገድ የተነሳ የማትነቀነቅ።
5᎐ መልኅቆቿም በሦስቱ ሥላሴ የተሸረቡ ገመዶች ናቸው አይቆረጡም ይኽችውም ደግሞ ከነፋሳት ኃይል የተነሣ የማትነቀነቅ በጭንጫ ላይ ያለች የእንቁ ባህሪይ ምሰሶ ናት። እሷንም የተጠጋ መውደቅ መሰናከል የለበትም።
6᎐ አቤቱ የልቦናዬን ደጅ ክፈት መንፈሳዊው ርግብ መንፈስ ቅዱስ በየዋህነቷ በርግብ ስለ ተመሰለችው የእመቤታችንን ምስጋና ኃይለ ቃሉን ያሳስበኝ ዘንድ እንዲገባ።
7᎐አቤቱ የጆሮዬንም መስኮት ክፈት ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት የሚሰማውን የድንግልን የምስጋናዋን ሹክሹክታ ያደምፅ ዘንድ።
8᎐ አቤቱ ሆይ ያይኔን ጽጋግ ግለጽ የብርሃን እናቱ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ምስጢሩን እመለከት ዘንድ።
9᎐ዳግመኛ አንደበቴን ክፈት አቤቱ ለእግዚአብሔር እናት እመቤታችን ለድንግልናዋ ምስጋና።
10᎐የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ያቃጠለውን የኦሪትንና የነቢያትን መጻሕፍት ቃል አጽፎ እስኪጨርስ ድረስ ዓርባ ቀን ሙሉ ሳይሰወርበት የዕዝራን አንደበት የገለጽህ ሆይ እኔንም ደግሞ እንደርሱ እርዳኝ። የአብ ሙሽራ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ለመጻፍ እንድጀምር (ዕዝ 7 ፤ 6)
11᎐ጀምሮ ከመተው አድነኝ አቤቱ እርሱንም ለመፈጸም አሰልጥነኝ ከንፈሮቼንም እንደ በገና አድርጋቸው ለሚሰሙት ያማረውን የተወደደውን ምሥጢር እንዲናገሩ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይቃኛቸው።
12᎐አንደቤቴን እንደ ማሰንቆ አድርገው በጎውንም ያማረውን የተወደደውን መዝሙር እንዲያቀነቅን የመንፈስ ቅዱስ ድኅንፃ ይደርድረው የሚያዳምጡትም እርሱን በመስማት ፈጽመው ደስ ይሰኙ።
13᎐ሐሳባቸውም ወደታች ያይደለ ወደላይ ይመሰጥ ጽድቅንም ያስቡ። ኃጢአትን ያይደለ ጽድቅን ያስቡ ርኩሰትን ያይደለ ንጽሕናን ያስቡ።
14᎐የዋህነትንም ያስቡ። ሽንገላን ያይደለ ትሕትናንም ያስቡ። ትዕቢትን ያይደለ ፍቅርንም ያስቡ። ቅናትን ያይደለ።
15᎐ልባምነትንም ያስቡ። ስንፍናን ያይደለ ክብርንም ያስቡ። ጉስቁልናን ያይደለ የሰማዩን ያስቡ። የምድሩን የማያረጀውን ያስቡ። የሚያረጀውን ያይደለ የማይጠፋውን ያስቡ የሚጠፋውን ያይደለ።
16᎐ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሁሉ አንደበቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የተጣፈጠ ከማርም ወለላና ከሦከር ምንጭ ይልቅ የተጣፈጠ ይሁን።
17᎐በዚህች ጸሎት የሚጸልይ ሁሉ የህይወት እሳትን በሚዳስስ እጅሽ በረከት የተባረክ ይሁን። የመንፈስ ቅዱስ መዓዛም በተዋሀደው አንደበትሽ የተመረቀ ይሁን።
18᎐ዓለምን ሁሉ በያዙ በሥላሴ እጅ የተባረከ ይሁን። ጸሎቱም ነገር በማብዛት የሚሰማቸው እንደሚመስላቸው እንደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጸሎት አይሁን። (ማቴ 6 ፣ 7 ፣ 23 ፣ 14)
19᎐ ባባቱ ጆሮ በለኆሳስ እንደሚናገር እንደ ተወደደ እንዳንድ ልጅ ነገር ይሁን እንጂ። አባቱም የልጁን ነገር በደስታ ለመቀበል ጸጥ ብሎ እንደሚሰማው። እንደሚያዳምጠውም። እንዲሁ ደግሞ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር በዚች ጸሎት የሚጸልየውን ሰው ልመናውን ይስማ።

Languageአማርኛ
Publishergadeal 72
Release dateDec 31, 2014
ISBN9781310264375
Arganon መጽሐፈ አርጋኖን

Related to Arganon መጽሐፈ አርጋኖን

Related ebooks

Related categories

Reviews for Arganon መጽሐፈ አርጋኖን

Rating: 3 out of 5 stars
3/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    Arganon መጽሐፈ አርጋኖን - gadeal 72

    የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

    በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተደረሰ

    ይህንን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋና መጽሐፍ መፃፍ የማይገባኝ ኃጢአተኛ ሆኜ ሳለሁ በምሕረቱ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ለልዑል እግዚአብሔር ኃይል ክብር ምስጋና ይግባው።

    በኢየሱስ ክርስቶስ ባርያ

    በጋድኤል72 ለኢቡክ ተዘጋጀ

    Copyright gadeal72 http://houseofhabesha.com

    የዚህ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ

    ለደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ በትህትና እገልፃለሁ።

    ማውጫ

    Monday

    Tuesday

    Wednesday

    Thursday

    Friday

    Saturday

    Sunday

    ዘሰኑይ

    ምዕራፍ ᎐1

    ክፍል 1

    1᎐ ባለመለየት ሶስት በተዋህዶ በአኗኗር አንድ በመለኮት ትክክል ከሰውና ከመላእክትም ዘንድ አንድ ስግደት በሚሰገድለት በእግዚአብሔር ስም አምነን ይህንን አርጋኖን የሚባል የምስጋና መጽሐፍ እንጽፋለን።

    2᎐ይኸውም የምስጋና መሰንቆ የቅዳሴም እንዚራ። አምላክን የወለደች በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታሰጥ የእመቤታችን የማርያምን ድንግልናዋን የማድነቅ መጽሐፍን እንጽፋለን።

    3᎐ክብሯንና ገናንነቷንም የመናገር ስሟንም የማክበር ቅድስናዋንም የማመስገን ለንግሥትነቷም መገዛት እንዲገባ የሚናገር መጽሐፍ እንጽፋለን።

    4᎐አምላክን የወለደች እመቤታችን ይኽችውም የወርቅ መሰላል ናት ከሚያሰጥመው ባህር ማዕበል ሞገድ የተነሳ የማትነቀነቅ።

    5᎐ መልኅቆቿም በሦስቱ ሥላሴ የተሸረቡ ገመዶች ናቸው አይቆረጡም ይኽችውም ደግሞ ከነፋሳት ኃይል የተነሣ የማትነቀነቅ በጭንጫ ላይ ያለች የዕንቁ ባህሪይ ምሰሶ ናት። እሷንም የተጠጋ መውደቅ መሰናከል የለበትም።

    6᎐ አቤቱ የልቦናዬን ደጅ ክፈት መንፈሳዊው ርግብ መንፈስ ቅዱስ በየዋህነቷ በርግብ ስለ ተመሰለችው የእመቤታችንን ምስጋና ኃይለ ቃሉን ያሳስበኝ ዘንድ እንዲገባ።

    7᎐አቤቱ የጆሮዬንም መስኮት ክፈት ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት የሚሰማውን የድንግልን የምስጋናዋን ሹክሹክታ ያደምፅ ዘንድ።

    8᎐ አቤቱ ሆይ ያይኔን ጽጋግ ግለጽ የብርሃን እናቱ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ምሥጢሩን እመለከት ዘንድ።

    9᎐ዳግመኛ አንደበቴን ክፈት አቤቱ ለእግዚአብሔር እናት እመቤታችን ለድንግልናዋ ምስጋና።

    10᎐የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ያቃጠለውን የኦሪትንና የነቢያትን መጻሕፍት ቃል አጽፎ እስኪጨርስ ድረስ ዓርባ ቀን ሙሉ ሳይሰወርበት የዕዝራን አንደበት የገለጽህ ሆይ እኔንም ደግሞ እንደርሱ እርዳኝ። የአብ ሙሽራ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ለመጻፍ እንድጀምር (ዕዝ 7፦6)

    11᎐ጀምሮ ከመተው አድነኝ አቤቱ እርሱንም ለመፈጸም አሰልጥነኝ ከንፈሮቼንም እንደ በገና አድርጋቸው ለሚሰሙት ያማረውን የተወደደውን ምሥጢር እንዲናገሩ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይቃኛቸው።

    12᎐አንደቤቴን እንደ ማሰንቆ አድርገው በጎውንም ያማረውን የተወደደውን መዝሙር እንዲያቀነቅን የመንፈስ ቅዱስ ድኅንፃ ይደርድረው የሚያዳምጡትም እርሱን በመስማት ፈጽመው ደስ ይሰኙ።

    13᎐ሐሳባቸውም ወደታች ያይደለ ወደላይ ይመሰጥ ጽድቅንም ያስቡ። ኃጢአትን ያይደለ ጽድቅን ያስቡ ርኩሰትን ያይደለ ንጽሕናን ያስቡ።

    14᎐የዋህነትንም ያስቡ። ሽንገላን ያይደለ ትሕትናንም ያስቡ። ትዕቢትን ያይደለ ፍቅርንም ያስቡ። ቅናትን ያይደለ።

    15᎐ልባምነትንም ያስቡ። ስንፍናን ያይደለ ክብርንም ያስቡ። ጉስቁልናን ያይደለ። የሰማዩን ያስቡ። የምድሩን ያይድለ። የማያረጀውን ያስቡ። የሚያረጀውን ያይደለ የማይጠፋውን ያስቡ የሚጠፋውን ያይደለ።

    16᎐ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሁሉ አንደበቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የጣፈጠ ከማርም ወለላና ከሦከር ምንጭ ይልቅ የጣፈጠ ይሁን።

    17᎐በዚህች ጸሎት የሚጸልይ ሁሉ የሕይወት እሳትን በሚዳስስ እጅሽ በረከት የተባረክ ይሁን። የመንፈስ ቅዱስ መዓዛም በተዋሀደው አንደበትሽ የተመረቀ ይሁን።

    18᎐ዓለምን ሁሉ በያዙ በሥላሴ እጅ የተባረከ ይሁን። ጸሎቱም ነገር በማብዛት የሚሰማቸው እንደሚመስላቸው እንደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጸሎት አይሁን። (ማቴ 6፦7 ፣ 23፦14 )

    19᎐ በአባቱ ጆሮ በለኆሳስ እንደሚናገር እንደተወደደ እንዳንድ ልጅ ነገር ይሁን እንጂ። አባቱም የልጁን ነገር በደስታ ለመቀበል ጸጥ ብሎ እንደሚሰማው። እንደሚያዳምጠውም። እንዲሁ ደግሞ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር በዚች ጸሎት የሚጸልየውን ሰው ልመናውን ይስማ።

    ምዕራፍ 2

    1᎐በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤታችን የተመረጥሽ ድንግል ማርያም ሆይ አንቺም ደግሞ አመፀኛው በደለኛው ኀጥኡ እኔ በዚህች ጸሎት በጸለይሁ ጊዜ ወደ አንደበቴ ነገር ጆሮሽን ዘንበል አድርገሽ ስሚ። ሰምተሽም ቸል አትበይ። በብሩህ ልቦና በንጹህ አሳብ የአንደበቴን ነገር ተቀበይው እንጂ።

    2᎐ስለኃጢአቴም ብዛት የከንፈሮቼም ድካም እንደተናቀ ምናምን ነገር አታድርጊው።

    3᎐እመቤቴ ሆይ ወርቅና ብር የማቀርብልሽ አይደለም። የሚያበራውን ዕንቁም የማቀርብልሽ አይደለም። ያማረውን የተወደደውን ምስጋና ለገናንነትሽ የሚቀርበውን ንጹሁን ውዳሴ ነው እንጂ።

    4᎐ንግሥት ሆይ የከበረውን ልብስ በፍታውን ነጭ ሐሩን የወርቅ የዕንቁ ጌጥ ፈርጥ ያለበትን ብሩሁን ልብስ የማቀርብልሽ አይደለም። በወርቅና በዕንቁ ስለተሠራው ክቡር ልብስሽ ነፍሴንና ሥጋዬን በፊትሽ እዘረጋለሁ እንጂ።

    5᎐የታላቁ ሊቀ ካህናት እናት ሆይ ኃጢአቴን ለአንቺ እናዘዛለሁ ከዚህ ዓለም መቅሠፍት ከምድራዊም ጥፋት መሸሻ አንቺን አገኘሁ ።

    6᎐በኃይል ከሚነጥቁ በቅሚያም ከሚገሱ ከዓረብ አንበሶች መሸሻ አንቺን አገኘሁ አውሮቹን ይነጥቃሉ ለጠቦቶቹም አይራሩም። አሮጊቶቹንም አይምሩም ሁልጊዜም ለመዋጥ አፋቸው የተለቀቀ ነው።

    7᎐ለነገም ከማያሳድሩ ከዓረብ ተኩላት መሸሻ አንቺን አገኘሁ። አውራውን ይነጥቃሉ ጠቦቲቱን አያስቀሩም ለእናቲቱም አይራሩም ለጠቦቱም አያዝኑም።

    8᎐ ከሰይፍ ስለት ከጦር ሐፎት ከፀብ ክርክርም ሁሉ ከፀብም መሣሪያ ሁሉ መሸሻ አንቺን አገኘሁ ከጠላቶቼም እጅ መሸሻ ሰውነቴንም ከሚጠሏት ሁሉ እጅ መሸሻ አንቺን አገኘሁ።

    9᎐በስምሸ ያመነውን ማን ያስፈራዋል።በልጅሽ ያመነውን ማን ያስፈራዋል። የአንበሳም ጩኸት እንደ ውሻ ጩኽት ይመስለዋል። የነብሮቹም ኃይል እንደ ድመት ድካም ነው።

    10᎐ፈረስም ቢሮጥ አይደርስበትም ጦርም ቢወረወር አያገኘውም የፍላፃም ሐፎት አይቆነጥጠውም በደንጊያም መወገር ነፋስ እንደሚበትነው ትቢያ ይመስለዋል።

    11᎐የፈሳሽም ውሀም ማዕበል ሞገድ አይበረታታበትም የነፋሳትም ኃይል አያነዋውጠውም የሰውም አንደበት ክፉ ሊያደርግበት አይችልም። የአመፀኛ ከንፈርም አይጎዳውም በተዋቀሰው ጊዜ ልጅሽ ድል አያስነሳውምና።

    12᎐ይህንንም ሁሉ ዐውቄ ለመረዳቴ በአንቺም በልጅሽም በኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ፈጽሜ ደስ ተሰኘሁ።

    13᎐ፍቅርሽም በሰውነቴ አዳራሽነት ፈጽሞ ተዘረጋ እጅግም ከፍ ከፍ አለ በዛም። እንደ ወንዝ ፈሳሽም ሞላኝ እንደ ግዮን ወንዝ በክረምት ጊዜ እንደ ጤግሮስም ፈሳሽ በአዝመራ ጊዜ። እንደ ኤፍራጥስም ወንዝ በእሸት ጊዜ። እንደ ኤፌሶንም ፈሳሽ በጮርቃ (እንጭጭ) ጊዜ።

    14᎐ጉምም በምድር ላይ እንዲጎተት ደመናም በአየር ላይ እንዲረብ እንዲሁ በኔ ዘንድ ሆነ።

    ምዕራፍ 3

    ክፍል 2

    1᎐በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ አንቺም በተድላ በደስታዬ ጊዜ ሽልማት ሆንሽኝ። በኃሤትም ጊዜ ክብ ዘውዴ ሐቲም ቀለበቴ ነሽ።

    2᎐በሐሳቤም ሁሉ አንቺን አደንቃለሁ። እንዲህም እላለሁ። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ምን ያህል ጸጋ ክብር ሰጠ።

    3᎐እግዚአብሔር ከሰው ልጅ የማይተባበሩ ሦስት ልደታትን ተወለደ። እኔም ዐውቄ አደነቅሁ። በአራተኛው እንጂ የበጎ ዕረፍት አላገኘሁም።

    4᎐አዳም ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው። እኔን ግን የጠቀመኝ የለም። ሔዋንም ከአዳም ግራ ጎን ተወለደች እሷም በተፈጥሮ ነው። ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም።

    5᎐ቃየልም እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም። እንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም። እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም።

    6᎐ክርስቶስ ግን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ።

    7᎐ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል። ክብር ምስጋና ለዚህ ልደት ይገባል ጌትነትና ገናንነት ኅያልነት አዚዝነት እልልታ ግርግታ ለዚህ ልደት ይገባል።

    8᎐ይህ ጥበብ ፍልስፍና ዕጹብ ድንቅ ነው። ለዚህ አንክሮ ይገባል ይህም የሥጋዊ ምሥጢር ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ። ለዚህ አንክሮ ይገባል። ይህም ሰው መሆን ሥጋ መልበስ እጅግ ዕፁብ ድንቅ ነው።

    9᎐የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው።

    10᎐የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት እመቤታችን ሆይ የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር በአንቺ ተደረገ።

    11᎐እሳትና ውሀም በአንድነት ተስማምተው መኖራቸው እጅግ ድንቅ ነው የሚያስፈራውንም የአንበሳ ደቦል ፀዓዳ በግዕት በክንዷ መያዟ እጅግ ድንቅ ነው።

    12᎐ከድንግልም ብላቴና ጡቶች ወተት መፍሰስ እጅግ ድንቅ ነው። በበረትም ለድኆች ልጅ የሰማይ ሠራዊት መስገድ እጅግ ድንቅ ነው።

    13᎐ዓለምን ሁሉ የመላ አምላክም ከበረት ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ መገኘቱ እጅግ ድንቅ ነው። በረት ከጽርሐ አርያም ቁመት ረዘመ ከሰማይም ዳርቻ ሰፋ።

    14᎐ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ ይኸውም አደፍ ጉድፍ ሳይኖርበት ንጽሕት የወለደችው ንጹህ በግ ነው። በረት ለንጹሑ መሥዋዕት ሸታ መሰብሰቢያ ሆነ።

    15᎐ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው ወሰነውም። በረት የተመሰገነ ነው። የኃያላን ጌታ በውስጡ ተገኝቷልና።

    ምዕራፍ 4

    1᎐ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች እመቤታችን የተመረጠች ድንግል የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው። የዓለም ጌጥ ሽልማት የሁሉ አባት የሚሆን መላእክትን የፈጠረ ጌታ ከርሷ ተወልዷልና።

    2᎐በረት ተመሰገነ ምድርን በውሃ ላይ ያጸናት እርሱ ስለተጠጋባት ድንግልም የመላእክትን አለቆች ገዛቻቸው በኪሩቤል ላይ የሚቀመጥ እርሱ በማኅፀኗ ስላደረ።

    3᎐በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ስፍራው እንደ ጽርሐ አርያም ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅልሎ ተገኘ።

    4᎐ዮሴፍና ሰሎሜ በወዲህና በወዲያ ላምና አህያ በወዲህና በወዲያ በበረቱ ጎንና ጎን በአራቱ ማዕዘን በዙፋኑ ቀኝና ግራ በጎንና በጎኑ አራቱ እንስሶች እንዳሉ።

    5᎐የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ተሠራ። ቤተልሔም ሰማይን መሰለች ስለ ፀሐይም በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት ጥፋትም የሌለበት እውነተኛ ፀሐይ በውስጧ ተገኘ።

    6᎐የብርሃኑም ክበብ መሙላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምስጋና በሁሉ የመላ ነው። ለዘወትርም የማይጎድል እመቤታችን የተመረጠች ድንግል ማርያም ተገኘች ስለ ክዋክብትም መላእክተ ብርሃን ታዩ።

    7᎐ወደዚህ ማህበር አንድነት እኖር ዘንድ ማን በከፈለኝ ከመላእክት ጋር እንዳመሰግን ከወላጅቱም ጋር እንዳደንቅ ከአርበኞችም ጋር እንዳገለግል።

    8᎐በረቱንም እጅ እነሣ ዘንድ ማን በከፈለኝ የሙት ሕይወት የኃጥአንም ንጽሕና የቅቡአን ተስፋ የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደ ተቀመጠበት።

    9᎐የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበትን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ።

    10᎐ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ። የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ።

    11᎐አሁንም ያንጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም ሀሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌያለሁና።

    12᎐በሥጋ አልነበርኩም በመንፈስ ግን አለሁ። በአነዋወር አልነበርኩም በሃይማኖት ግን አለሁ በገፅ አልነበርኩም በማመን ግን አለሁ።

    13᎐ሳልኖር እራሴን እንዳለሁ ያደረግሁ እኔ የተመሰግንኩ ነኝ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው።

    14᎐እኔ ባሪያህ ሰለሃይማኖቴ የተመሰገንኩ ነኝ። ስለ እውነቴ አይደለም ስለመረዳቴም የተመሰገንኩ ነኝ። ስለንፅህናዬም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ አመንኩ የተመሰገንኩ ነኝ። በእናቱም ጸሎት ስለ አመንኩ ንዑድ ክቡር ነኝ

    ምዕራፍ 5

    ክፍል 3

    1᎐በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ እመቤቴ የተመረጥሽ ድንግል ማርያም ሆይ የጸሎትሽ ረዳትነት ጋሻ ጦር ይሆነኝ ዘንድ ወደ አንቺ እማልዳለሁ።

    2᎐የልጅሽ የልዑል ክንዱ ኃይል ለማዳን ይውረድ ተራሮችን የሚፈትታቸው ኃይል በረድኤት ወደኔ ይምጣ። ጠላቶቼን ይገለብጣቸው ዘንድ።

    3᎐ሰማዩን እንደ ክርታስ የሚጠቀልለው ኃይል በረድኤት ወደኔ ይምጣ የሚጣላኝን ያስጨንቀው ዘንድ ምድርን የሚያነዋውጥ ባሕርንም የሚዳስስ ኃይል ይምጣ ጠላቶቼን ይዋጋቸው ዘንድ።

    4᎐በሌጌዎን አጋንንት የሪያዎቹንም መንጋ ያሰጠመ ኃይል ይምጣ ሰውነቴን የሚከራከሯትን ያሰጥማቸው ዘንድ። ጉሙንም እንደ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1