Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?
በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?
በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?
Ebook447 pages3 hours

በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

አሁን እያንዳንዱ ሐጢያተኛ በእውነተኛው ወንጌል ማመን አለበት፡፡ እግዚአብሄር የሰጠው የደህንነት ወንጌል በእግዚአብሄር ጽድቅ ውስጥ የተገለጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ የዕብራውያን መጽሐፍ ጸሐፊ የተሳሳተውን እምነታችሁን ለማረም እየሞከረ ነው፡፡ ስለዚህ እምነታችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል መሠረት ላይ ጠልቆ መተከል ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ፍጹም የወንጌል እውነት ላይ በእርግጠኝነት ተጫምተው የሚቆሙ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ላይ ባለው እምነት እንደሚኖሩ የተረጋገጠ ነው፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateSep 15, 2023
ISBN9788928221486
በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?

Related to በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?

Related ebooks

Reviews for በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I) - እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ? - Paul C. Jong

    paul_Am56_coverFrontflap_Am561st_page

    በዕብራውያን ላይ የተሰጡ ስብከቶች (I)

    እምነታችሁን እንዴት ማጠንከር ትችላላችሁ?

    Smashwords Edition

    Copyright 2023 by Hephzibah Publishing House

    ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ባለቤት በጽሁፍ የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር የዚህን መጽሐፍ ማንኛውንም ክፍል ማባዛት ወይም በማንኛውም መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ በኤሌክትሮኒክ ወይም በሜካኒካል ፎቶ ኮፒ ማድረግን ጨምሮ በቅጂ መልክ ወይም መረጃን ይዞ በሚያጠራቅም ወይም መረጃን ይዞ በሚያስቀር ማንኛውም መንገድ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

    ጥቅሶቹ በሙሉ የተወሰዱት ከ1954ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ হয়েছে।

    ISBN 978-89-282-2148-6

    ዲዛይን፡ በሚን ሱ ኪም

    ንድፍ፡ በዮንግ አይ ኪም

    ትርጉም፡ በካሳሁን አየለ

    የታተመው በኮርያ ነው፡፡

    Hephzibah Publishing House

    A Ministry of THE NEW LIFE MISSION

    Seoul, Korea

      የማውጫ ሰሌዳ  

    መቅድም

    1. የሚሽን ትምህርት ቤት ክፍል (ዕብራውያን 1፡1-3)

    2. እግዚአብሄር በዚህ በመጨረሻው ዘመን በልጁ ተናግሮናል (ዕብራውያን 1፡1-6)

    3. የሰማናቸውን ነገሮች አጥብቀን ልናምንባቸው ይገባናል (ዕብራውያን 2፡1-18)

    4. ሊቀ ካህኑን ኢየሱስን በጥልቀት እናጢነው (ዕብራውያን 2፡15)

    5. ለጌታ ታማኝነት ምስጋና ይሁንና መዳናችሁን አሰላስሉ (ዕብራውያን 3፡1-4)

    6. የጌታ ጽድቅ በእርሱ የተባረከ የደህንነት አልብሶናል (ዕብራውያን 3፡1-19)

    7. ለልቦቻችን እውነተኛ እምነት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብን? (ዕብራውያን 4፡1-16)

    8. እንግዲያውስ ወደ እግዚአብሄር ዕረፍት ለመግባት እንትጋ (ዕብራውያን 4፡1-13)

    9. እኛም ደግሞ የእግዚአብሄር መንፈሳዊ ካህናት ነን (ዕብራውያን 5፡1-14)

    10. በእግዚአብሄር የተሾሙ ካህናት (ዕብራውያን 5፡1-11)

    11. የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ሁሌም ፍጹማን ያደርገናል (ዕብራውያን 6፡1-8)

    12. እግዚአብሄር ምን ነገረን? (ዕብራውያን 6፡1-20)

    13. እግዚአብሄር ለእኛ ያደረገልንን አውቀን ሁላችንም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እናገልግል (ዕብራውያን 6፡9-12)

    0Preface.jpg

    መቅድም

    የዕብራውያን መጽሐፍ ጸሐፊ ስለ ብሉይ ኪዳን ቃልና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አወቀና አሳምሮ መሰከረ፡፡

    የዕብራውያንን መጽሐፍ ማን እንደጻፈው አናውቅም፡፡ አንዳንድ ሰዎች በርናባስ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ፤ ሌሎች ሐዋርያው ጳውሎስ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ጸሐፊው ማንም ይሁን ስለ ጸሐፊው አንድ ነገር እርግጠኛ ነው፡፡ እርሱ በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ስርዓት ውስጥ የተገለጠውን የደህንነት ሕግ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከታየው የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ጋር አያይዞ በመተረክ ረገድ የተካነ ስለነበር የእግዚአብሄር አገልጋይ የነበረ መሆን አለበት፡፡ በአዲስ ኪዳን ዘመን የቀረበው የኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከቀረበው የመሥዋዕት ስርዓት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በዚህ ረገድ መጽሐፉ የእግዚአብሄርን ዓላማዎች ስለሚነግራቸው አሁንም ለዛሬዎቹ ክርስቲያኖች አስፈላጊ ነው፡፡

    የዕብራውያን መጽሐፍ እንደሚጠቁመው በዚያን ጊዜ አይሁዶች ለመላዕክቶች ይሰግዱ ነበር፡፡ ልክ እንደዚሁ እናንተም ከእግዚአብሄር ጽድቅ በእጅጉ አስበልጣችሁ ለክርስቲያን ትምህርቶች ትሰግዳላችሁ ብዬ እፈራለሁ፡፡ ስለዚህ አጋር ክርስቲያኖች ሆይ በእነዚህ የክርስቲያን ትምህርቶች የሚያምን እምነት ከመያዝ ይልቅ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን እምነት እንድትይዙ እመክራችኋለሁ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ በተገለጠው የእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን ስትመርጡ የሐጢያቶቻችሁን ስርየት ከመቀበላችሁም በላይ ከሐጢያቶቻችሁም ሁሉ ደህንነትን ትቀበላላችሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ መውሰዱ እውነት ነው፡፡ ይህ እውነት የደህንነታችን ማረጋገጫ ሆነ፡፡ ተጨባጩ ከሐጢያቶች የመዳን እውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት፣ ደምና መለኮትነት በምናምነው ሰዎች ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትነትና በጽድቁ የምናምን ሰዎች በእምነታችን አማካይነት ድል አድራጊዎች እንሆናለን፡፡

    መስከረም 15፤2008

    ጸሐፊው

    Sermon011

    የሚሽን ትምህርት ቤት ክፍል

    ‹‹ ዕብራውያን 1፡1-3 ››

    ‹‹ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤››

    እኛ በሚሽን ትምህርት ቤታችን አማካይነት የምንማረው የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ባጸናው ስርዓት ውስጥ ራሳችንን በአንድ ላይ በማስማማት ወንጌልን ማገልገልንም ደግሞ እንማራለን፡፡ እንዴት እንደምንጸልይ እንማራለን፤ ጠንካራ እምነት እንዲኖረንና በዚህ የሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ የእግዚአብሄርን ዓለም ስርዓት ደግሞ እንሰለጥናለን፤ በእግዚአብሄር የእውነት ቃልም የልቦቻችንን ደካማ አካባቢዎች መሙላት እንችላለን፡፡ በእነዚህ የሥልጠና ኮርሶች አማካይነት በእምነት ጸንተን መቆም እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ሆነን ዳግመኛ ከተወለድን በኋላ ጠላትን የመዋጋት ችሎታም እናገኛለን፡፡

    ይህንን የሚሽን ትምህርት ቤት ስለፈቀደልን ለእግዚአብሄር ምስጋናን እሰጣለሁ፡፡ ለእናንተና ለእኔም ጌታን የማገልገልና እኛን የማሠልጠን ዕድል ስለሰጠንም ደግሞ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ፡፡ እኔ ሁሌም እንዲህ ባለ ልብ ወንጌልን በአገራችንና በውጭ አገር እየሰበክሁ ነው፡፡ የምሰብክላችሁን ስብከት ይዘቶች በሙሉ በማስታወሻ ደብተሮቻችሁ ላይ ማስፈር አያስፈልጋችሁም፡፡ እናንተ የሚያስፈልጋችሁ ጠቃሚ እንደሆኑ በማሰብ በተደጋጋሚ የምጠቁማቸው ክፍሎች ላይ ትኩረት ማድረግ ነው፡፡ እርግጠኛ ስላልሆናችሁባቸው ክፍሎች በተደጋጋሚ የስብከት ቴፖቼን ብትሰሙ ይጠቅማችኋል፡፡

    በዚህ የሚሽን ትምህርት ቤት ክፍለ ጊዜ ወቅት ጌታ ከዕብራውያን መጽሐፍ በቃሉ ሊነግረን በፈለገው ላይ ትኩረት ማድረግ እወዳለሁ፡፡ የዕብራውያን መጽሐፍ ለዕብራውያን ሰዎች በእግዚአብሄር አገልጋይ የተጻፈ የዕብራውያን መልዕክት ነው፡፡ ዘመኑ እስራኤላውያን በሮማውያን ስደት ምክንያት በወቅቱ በሚታወቀው ዓለም ሁሉ የተበተኑበት የስደት ዘመን ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ምንም መንፈሳዊ መሪ ማግኘት አልቻሉም፡፡ አገልጋዩ መልዕክቱን የጻፈበት ምክንያት ይህ ነበር፡፡ ከአራቱ ወንጌሎችና ከሐዋርያት መጽሐፍ ባሻገር የአዲስ ኪዳን መጽሐፎች በሙሉ አንድ የእግዚአብሄር አገልጋይ እንዲህ ባለ ታሪካዊ አገባብ ለቅዱሳኖቹ የላካቸው መልዕክቶች ስብስብ ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ ይህንን ታሪካዊ ዳራ መረዳት አለባችሁ፡፡

    እግዚአብሄር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ተናግሮናል፡

    ዛሬ በዋናነት ከዕብራውያን መጽሐፍ 1፡1-3 እናገራለሁ፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤››

    በብሉይ ኪዳን ዘመን ነቢያቶች የእግዚአብሄርን ቃል ተቀበሉና ለእስራኤላውያን ተናገሩ፡፡ እንደዚሁም የተቀበሉትን መዝግበው አስቀመጡ፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የዘፍጥረትን መጽሐፍ ስናነብ ይዘቶቹ የሰማያትንና የምድርን ፍጥረት፣ የአብርሃም ዘሮች የሆኑትን የያዕቆብን አስራ ሁለት ልጆችና ወደ ግብጽ የመሄዳቸውን ቃል የሚመለከቱ ናቸው፡፡ የዘጸዓት መጽሐፍ በግብጽ ለአራት መቶ ዓመታት ያህል በባርነት የነበሩትንና ከግብጽ ወደ ከነዓን ምድር የፈለሱትን እስራኤላውያን ይመለከታል፡፡ የዘሌዋውያን መጽሐፍ ስለ መሥዋዕት ስርዓት ይናገራል፡፡ የዘዳግም መጽሐፍ የእግዚአብሄር ሕዝብ ወደ ከነዓን ምድር ለመግባት ያደረጉትን ጉዞ ይመለከታል፡፡ እግዚአብሄር ስለ እነዚህ ሁሉ ሒደቶች በተለያዩ ክፍሎች ተናገረ፡፡

    እግዚአብሄር ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሙሴ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ኢሳይያስና ሌሎች ባሉ የተለያዩ ነቢያቶች አማካይነት በተለያዩ ክፍሎችና በተለያዩ መልኮች ተናገረ፡፡ ቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሄር ኢየሱስ ክርስቶስን ከጥንት ጀምሮ ለሕዝቡ ለእስራኤለውያን በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ሊገልጥላቸው እንዳቀደ ይነግሩናል፡፡

    የሰው ዘር የጋራ ቅድመ አያት የሆኑት አዳምና ሔዋን ከተፈጠሩና በኤድን ገነት ውስጥ እንዲኖሩ ከተፈቀደላቸው በኋላ ሐጢያትን ሠሩ፡፡ ከዚያም ከበለስ ቅጠል የተሠፉ ልብሶችን ለበሱ፡፡ ከዚያ በኋላ እግዚአብሄር ወደ እነርሱ መጣና የእንስሳ ቁርበት ልብሶችን በማበጀት በደምብ አለበሳቸው፡፡ ይህ ታሪክ እግዚአብሄር የሐጢያቶችን ስርየት እንዴት ለሐጢያተኛው እንደሚሰጥ እውነቱን ይጠቁማል፡፡

    ታዲያ የእግዚአብሄር ሕዝብ የሆኑት ዕብራውያኖች የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የተቀበሉት እንዴት ነበር? እነርሱ እንዲህ ያለውን ትልቅ የደህንነት ስጦታ መቀበል የቻሉት እንዴት ነበር? እዚህ ላይ እነርሱ የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበሉት ባከማቹት የራሳቸው ጽድቅ ይሁን ወይም በምትኩ ደህንነትን የተቀበሉት በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ይሁን ማሰላሰል አለብን፡፡ እነርሱ በእርግጥም የዳኑት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ባዳናቸው የእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ነው፡፡ እግዚአብሄር እነርሱን በጽድቁ ያዳናቸው ምንም የራሳቸው የሆነ ጽድቅ እንደሌላቸው በማወቁ ነበር፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው ዘር ውድቀትና ጌታ ለሐጢያቶቻችን ስርየት ስለሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሚናገር ቃል ይዞዋል፡፡

    በዘሌዋውያን መጽሐፍ ላይ ሰዎች በመገናኛው ድንኳን ውስጥ መሥዋዕቶችን ሲያቀርቡ ማየት እንችላለን፡፡ እስራኤላውያን በምድረ በዳ ሲኖሩ ሳለ በተደጋጋሚ ቢሰሩዋቸውም በእግዚአብሄር ፊት ሕጉ ስላልነበራቸው ሐጢያቶቻቸውን አላወቁም፡፡ በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ሲና ተራራ ጠራውና የሕጉን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ሰጠው፡፡ እግዚአብሄር ሕጉን ለሙሴ በሰጠው ጊዜ የመገናኛውን ድንኳን ዝርዝር ገጽታም ደግሞ አሳየውና የመገናኛውን ድንኳን እንዲገነባ ነገረው፡፡ ይህ እስራኤላውያን ሐጢያቶቻቸውን በሕጉ አማካይነት እንዲያውቁና ሐጢያተኛ ሰዎችም እግዚአብሄር ባቋቋመው የመሥዋዕት ስርዓት መሠረት እነዚህን መሥዋዕቶች በማቅረብ የሐጢያቶቻቸውን ሁሉ ስርየት እንዲቀበሉ ለማድረግ ነበር፡፡ ስለዚህ ጌታ ለእነርሱ ስለ ሐጢያቶች ስርየት በተለያዩ መንገዶችና በተለያዩ መልኮች እንደነገራቸው ማየት እንችላለን፡፡ እርሱ እስራኤላውያን እንዴት በእግዚአብሄር ወደ ማመን እንደመጡና እንዴት እንዲህ ባለ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉም ተናገረ፡፡ እጅግ አስፈላጊው ነገር እኛ በዚህ የእግዚአብሄር ቃል አማካይነት እንዴት የሐጢያቶቻችንን ስርየት እንደምንቀበልና እንዴት እምነታችንን መኖር እንደሚገባን መረዳት ያለብን መሆኑ ነው፡፡

    በተለያዩ ጊዜያትና በተለያዩ መንገዶች ለእምነት ቀደምቶች ቃልን የተናገረው እግዚአብሄር በዚህ በመጨረሻው ዘመን ለእኛም ደግሞ በልጁ በኩል እንደተናገረ ተጽፎዋል፡፡ እግዚአብሄር ጥንት ለእስራኤላውያን በእግዚአብሄር አገልጋዮች አማካይነት ተናገረ፡፡ ነገር ግን አሁን ለእኛ የሚናገረው እንዴት ነው? በዚህ በአሁኑ ዘመን ለምንኖር አማኞች እግዚአብሄር የሚናገረው እንዴት ነው? እግዚአብሄር በዚህ በመጨረሻው ዘመን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ተናግሮናል፡፡

    በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የዕብራውያን መጽሐፍ የተጻፈው ከ1,900 ዓመት በፊት ነው፡፡ ነገር ግን በዚያን ዘመን የነበሩት ሰዎችም እንኳን እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደተናገራቸው አወቁ፡፡ ታዲያ እናንተና እኔ እንደዚሁም በዚህ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ለእኛ የተናገረውን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅና ማመን የምንችለው እንዴት ነው? መረዳት የቻልነው እግዚአብሄር በእግዚአብሄር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጽድቁን በመናገሩ ነው፡፡

    በዚህ የሚሽን ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍሎች አንዳች አዲስ ነገር ለመረዳት መሞከር ወይም የእግዚአብሄር ቃል በሙሉ እስከ አሁን ከነበራችሁ እሳቤ ጋር እንዲገጥም መሞከር አያስፈልጋችሁም፡፡ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሄርን ቃል ማወቅ ሁሉም ነገር አይደለም፡፡ ነገር ግን በቃሉ ላይ ያላችሁ እምነት መቀጠል አለበት፡፡ ሆኖም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመንና የእግዚአብሄር ታማኝ ሠራተኞች ሆነን እንዴት እንደምንታደስ መማር አለብን፡፡ ስለዚህ እኔ እዚህ ላይ የምናገረውን በትኩረት ማድመጥና በራሳችሁ ስጋዊ የአስተሳሰብ መንገድ ውስጥ እንዳትወድቁ መጠንቀቅ አለባችሁ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በልባችሁ ውስጥ መጻፍ አለባችሁ፡፡ ቃሉ በዚህ መልኩ በልባችሁ ውስጥ ሲጻፍ በጭራሽ አይከስምም፡፡

    መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሄር የተነገረ ቃል ነው፡፡ በቃሉ ላይ እንዲህ ያለ አስፈላጊ እምነት ሊኖራችሁ ይችል ዘንድ ጥሩ ስብከት የእምነትን ቃል በተደጋጋሚ በእውነት ሙላት የሚያብራራ ነው፡፡ እግዚአብሄር በልጁ አማካይነት እውነትን ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር አብ የሐጢያተኞች ዘሮች ሆነን በመወለድ ሐጢያተኞች በሆንን ጊዜ በልጁ የሐጢያቶቻችንን ስርየት እንደሰጠን ተናገረ፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘሌዋውያን መጽሐፍ ላይ እንደተመዘገበው የመሥዋዕት ስርዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጣና ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በአንድ ጊዜ የሐጢያቶችን ሁሉ ስርየት ሰጠን፡፡ ጌታ ይህንን የእውነት ወንጌል ለመላው ዓለም እንድንሰብክ ነገረን፡፡ ጌታ እምነታችንንም ደግሞ እንድንኖር ነገረን፡፡ እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፡- ‹‹ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፡፡›› (2ኛ ቆሮንቶስ 6፡14) ጌታ ዳግመኛ ካልተወለዱ ጋር እንዳንቀላቀል፣ ከሐጢያተኞች ጋር እንዳንተባበርና ከእነርሱ ጋር እንዳንሠራ በግልጥ ነግሮናል፡፡ ይልቁንም የእግዚአብሄርን መንግሥት ለማስፋት ከእምነት ሰዎች ጋር እንድንተባበር ነገረን፡፡

    የጌታ ጸሎት ‹‹ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን›› ይላል፡፡ እግዚአብሄር ከዓለም ሕዝቦች መካከል የራሱን ብዙ ሰዎች መረጠና ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊወስዳቸውና ለዘላለም ከእነርሱ ጋር አብሮ ሊኖር ፈለገ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ይህንን ሥራ በኢየሱስ ክርስቶስ አቀደ፡፡ የዚህ ዕቅድ ጅማሬም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመደምሰስ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የዓለም አዳኝ አድርጎ መላክ ነበር፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በዚህ በመጨረሻው ዘመን ልጁን እንደላከልን ማስታወስ አለብን፡፡ ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ የመላው ዩኒቨርስ ባለቤት ነው፡፡ በዩኒቨርስ ውስጥ ያሉትም ነገሮች በሙሉ እንደዚሁ የእርሱ ሥራ ናቸው፡፡

    እግዚአብሄር አብ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ዓለም ላከውና ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ስርየት ጥምቀትን ከአጥማቂው ዮሐንስ እንዲቀበል ፈቀደለት፡፡ ይህ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ከሙታን በመነሣትም በአንድ ጊዜ አዳነን፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለሚያምኑ ሁሉ የሐጢያቶችን ስርየት ሰጠና የእግዚአብሄር መንግሥት እውነተኛ ሕዝብ እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡ ጌታ ለዚህ ዋና ዓላማ የዓለምን ታሪክ አንቀሳቀሰ፡፡ ጌታ ጻድቃን በእግዚአብሄር ጽድቅ እንዲኖሩና እምነታቸውንና እውነተኛውን ወንጌል እንዲጠብቁ ይነግራቸዋል፡፡

    የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ውብ ነገር ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለዘላለም ድል አድራጊ ሕይወትን መኖር እንድንችል ይባርከናል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ባለቤት ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሄር አብ ልጁን ሰጠንና እኛን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምነውን አማኞች የራሱ ሕዝብ አደረገን፡፡ ይህ እውነት እንዴት ያለ አስገራሚ የደህንነት ዕቅድ ነው?

    ስለዚህ እግዚአብሄር በቃሉ ውስጥ ሊነግረን የሚፈልጋቸው በጣም ብዙ ትምህርቶች ስላሉ ቅዱሳት መጻህፍትን ስናነብ ጭንቅላቶቻችንን በመስማማት መነቅነቅ ብቻ አይገባንም፡፡ እግዚአብሄር አብ በልጁ አማካይነት እንደተናገረን ፈጽሞ ማስታወስ አለብን፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ ጽድቅ ማመንና በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ እምነታችንን መኖር አለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ድምጽ መስማት፣ ማመንና እርሱን መከተል የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ በጽድቃችን በመመጻደቅ ፋንታ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያምኑና የሚከተሉ ክብርንም ለእግዚአብሄር የሚመልሱ የእምነት ሰዎች መሆን አለብን፡፡

    በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ጨቅላዎች የሆኑ ሰዎች የሆነ ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተውሎት ላይ እንደደረሱ ሲያስቡ ትልቅ ሰው እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ተመሳሳይ ነገርን የማያስተውሉ ከሆነ ሌሎች ሰዎችን ችላ ይሉዋቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በመንፈሳዊ ሁኔታ የበሰሉ አይደሉም፡፡ በራሳቸው አስተውሎት በራሳቸው የሚመጻደቁና እነርሱ ብቻ ትክክል እንደሆኑ የሚያስቡ እነዚህ ሰዎች በመንፈሳዊ ሁኔታ ሲታይ ያሉት በተጨባጭ ጨቅላ በሆነ የእምነት ደረጃ ላይ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስማት ከሐጢያቶቻቸው ቢድኑም የራሳቸውን ጽድቅ የሚያሳዩ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ቅዱሳኖች አሁንም የሚሄዱበት ረጅም መንገድ አለ፡፡ እነዚህ ሰዎች በልጁ አማካይነት የተነገረንን የእግዚአብሄር ቃል በትክክል አያስተውሉም፡፡ ይልቁንም እኛ እግዚአብሄር በልጁ አማካይነት ያከናወነውን ደህንነት ማመንና በእርሱም መመጻደቅ አለብን፡፡ እግዚአብሄር ጽድቃችንን ከፍ እንድናደርግ የሐጢያቶችን ስርየት እንድንቀበል አልፈቀደልንም፡፡

    ሁላችንም በክርስቶስ እንደሞትን ታውቃላችሁ አይደል? በእርግጥ በራሳችሁ ጽድቅ የበለጠጋችሁ አንዳንዶቻችሁ ይህንን እውነት አሳምራችሁ ላታውቁት ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ጌታ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የእነዚህን ሰዎች እነዚህን ሐጢያቶች እንኳን ወሰደና የራሳቸው ጽድቅ ለሌላቸው ሰዎች ሁሉ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ሞተ፡፡ ስለዚህ እኛ በእግዚአብሄር ጽድቅ የምናምን ሰዎች በክርስቶስ አዲስ ፍጥረቶች ሆነናል፡፡ ጌታም በአዲሱ ዓለም እንድንኖር ሊያደርገን አስነሳንና የሐጢያትን እርግማኖች በሙሉ ደመሰሰ፡፡ ስለዚህ እኛ ሁላችን ብቁ ያልሆንን ሰዎች ብንሆንም ጌታ እኛን ከዓለም ሐጢያቶች ባዳነበት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ማመን አለብን፡፡ በዚህ እምነትም ጌታን መከተል አለብን፡፡ ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል አብዝተን በኖርን መጠን ለዚህ ወንጌል አብዝተን አመስጋኞች እንሆናለን፡፡ ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስብከት አገልግሎት ከልባቸው የማይወዱና እንደሚወዱ የሚያስመስሉ ሰዎች በተሳሳተ ጎዳና ላይ ናቸው፡፡

    በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ ትሁቱ ሰው ማነው? ምንም ያህል በምቾት ቢኖርም ጌታ ሁሉንም ለእርሱ እንዳደረገለት የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ ጌታ ጸጋውን የሰጠን የጌታን ወንጌል እንድናገለግል እንጂ ስለዚህ ጉዳይ በስጋዊ መንገድ እንድንመጻደቅና በዕብሪት እንድንቀሳቀስ አይደለም፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳናገለግል እንኳን በራሳችን ጉልበት አንዳች ነገር ላይ እንደደረስን አስመስለን መኖር የለብንም፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሄር ቢላ ከሰጠን ያንን የሰጠን ለጽድቅ ሥራ እንድንጠቀምበት እንጂ ሌሎች ሰዎችን በእርሱ እንድንጎዳ አይደለም፡፡

    አሁን እናንተ ወደዚህ የሚሽን ትምህርት ቤት ገብታችኋል፡፡ የመጀመሪያ ተግባራችሁ የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ፍሰት ማወቅ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የተለያዩ ዓይነት ሰዎች አሉ፡፡ የተለያዩ ዓይነት አገልጋዮችም አሉ፡፡ ስብዕናቸውም አንዳቸው ከሌላኛቸው ይለያል፡፡ ነገር ግን ሁሉም የሚሹት ሌላ ሳይሆን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መስበክ ነው፡፡ እግዚአብሄር አብ በልጁ በኩል ቃል ከሰጠን በኋላ የእምነትን ሕይወት እንድንኖር ስላደረገን ስብዕናዎቻችን የተለያዩ ቢሆኑም ሁላችንም በእግዚአብሄር ጽድቅ በሚያምን እምነት በአንድነት መኖር አለብን፡፡ ለስጋችን ብቻ በመኖር ፋንታ የእግዚአብሄርን ጽድቅ በእምነት ከፍ ማድረግና ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል ስብከት መጠንቀቅ፣ መጸለይና ይህንን ተልዕኮ በመላው ዓለም ለማከናወን ጠንከረን መሥራት አለብን፡፡ ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፣ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡›› ይህ ምንባብ እንደሚለው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከፍ የምናደርግና በእግዚአብሄር ፈቃድ የምንኖር ከሆነ እግዚአብሄር ለስጋችን የምንፈልገውን እያንዳንዱን ነገር እንደሚሰጠን እርግጠኛ ነኝ፡፤

    እኛ እንዲህ ባለው እምነት መኖር አለብን፡፡ ነገር ግን ገና እንደዚህ ያልሆኑ ሰዎች ብዙ ሥልጠና መቀበል አለባቸው፡፡ ስለዚህ እናንተም እንደዚሁ በዚህ የሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ እያላችሁ እነዚህን ነገሮች መማር አለባችሁ፡፡ ሰዎች ወደ ጌታ ፈቃድ ከተቃረቡ በኋላም እንኳን እንደገና ከፈቃዱ የሚርቁት ልቦቻቸውን በጌታ ፈቃድ ላይ በጽኑ ባለማኖራቸው ምክንያት ነው፡፡

    እግዚአብሄር በዚህ በመጨረሻው ዘመን በልጁ አማካይነት ተናግሮናል፡፡ ይህ እንዴት አስገራሚ ነው? እኛ የኢየሱስ ክርስቶስን ጽድቅ ማወቅ፣ ኢየሱስ ራሱ አምላክ መሆኑን መገንዘብና ኢየሱስ ክርስቶስን የላከውን እግዚአብሄር አብን ማወቅ አለብን፡፡ ከዚህም በላይ ኢየሱስ የፍቅር አምላክ እንደዚሁም የቁጣ አምላክ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ እግዚአብሄር እንዴት መኖር እንደሚገባን እንደነገረንም ደግሞ ማወቅ አለብን፡፡ እንዲህ ያለ እምነት ካለን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ መኖርና አዳኛችን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ምን እያለንና ምን እንድናምን እየነገረን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ጽድቅ በልቦቻችን ማዕከል ላይ ባኖረው እምነት ማመን አለብን፡፡ ይህንንም እምነት በልብ መከተል አለብን፡፡ በምትጸልዩበት ጊዜ ራዕዮችን እንደ ማየት ያሉ ነገሮችን ብቻ መሻት የለባችሁም፡፡ ይልቁንም ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ዘር ሁሉ የሰጠውን የደህንነት ሥራ መረዳት አለባችሁ፡፡ ይህንንም በልቦቻችን ውስጥ መቀበል አለብን፡፡

    መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ቃል በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንደተጻፈው በትክክል መቀበል አለብን፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ባሉ የእምነት ሰዎች ይሠራል፡፡ እኛ እንዲህ ያሉ የእምነት ሰዎች ለመሆን በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ አብረን መኖርና የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከማመንና ከመከተል የሚያግደን ማንኛውም ነገር ከእምነታችን ጋር ተቀለቅሎ እንደሆነ ለማየት ራሳችንን መመርመር አለብን፡፡ በልቦቻችን ውስጥ ከእግዚአብሄር ቃል በሻገር አንዳች ሌላ ነገር ካለ ሁሉንም ሙሉ በሙሉ ማጥራት አለብን፡፡

    ይህንን እውነት ባለማወቁ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በትክክል የማይሰብክ ማንኛውም ጉባኤ ከእግዚአብሄር ቤተክርስቲያኖች እንደ አንዱ ሆኖ ሊጠራ አይችልም፡፡ እንዲህ ያለው ጉባኤ ልክ እንደ ባዶ የእህል ቅንጣት ክምር የሞቱ ነፍሳቶች ስብስብ ነው፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ብዙ የሥነ መለኮት ሴሚናሪዎች የእግዚአብሄር ጽድቅ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በትክክል ማስተማር አይችሉም፡፡ እነርሱ እየሳቱ ያሉት የደህንነት እውነት የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማስተማር ፋንታ ከዓለም ፍልስፍናዎች የገለበጡዋቸውን ይዘቶች ስለሚያስተምሩ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ከእነርሱ የተለየች ነች፡፡ እኛ እውነተኛውን የደህንነት እውነት ለዚህ ዓለም ሰዎች እንሰብካለን፡፡

    እግዚአብሄር አብ በልጁ ተናገረን፡፡

    የሚያድነንና በቀን ተቀን ሕይወታችን የሚናገረን የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ በእውነተኛ እምነትም ቃሉን መታዘዝ አለብን፡፡ ይህ እውነተኛ እምነት ራሱን በልባችሁ ውስጥ መግለጥ የሚችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስን በእውነተኛ እምነት ስንከተል በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የተመዘገበው የእግዚአብሄር ቃል ሁሉ በልቦቻችን ውስጥ ይሠራና የእግዚአብሄርን ሥራ እንድንሠራና በእምነትም ይህንን ቃል እንድንሰብክ ያደርገናል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ቃል በእምነት መቀበል አለብን፡፡

    በዕብራውያን 1፡2 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤›› ‹ሁሉን› የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመላውን ዩኒቨርስ ሁሉንም ነገሮች ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው የሚታዩትን እንደዚሁም የማይታዩትን ሁሉንም ነገሮች ነው፡፡ አሁን የመጀመሪያው ዓለም ሊያልፍ ተቃርቦዋል፡፡ በቅርቡም የሚመጣ አዲስ ዓለም አለ፡፡ የሺህ ዓመቱን መንግሥት ወደ ኑባሬ ያመጣውና በእርሱ ለሚያምኑ አማኞች የሚሰጠው አካል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሄር አብ ኢየሱስ ክርስቶስን የሁሉም ነገሮች ወራሽ አድርጎታል ማለት ነው፡፡

    እግዚአብሄር አብ ልጁን ለሰው ዘር ሁሉ ሰጥቶዋል፡፡ እርሱ አሁን በዓይናችን ልናየው ከምንችለው ከዚህ ዓለም የተለየ አዲስ ዓለም፣ አዲስ ዩኒቨርስ፣ አዲስ ምድር፣ ውብ ስፍራ ያበጅልናል፡፡ እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልን ሰዎች በዚያ አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለምን ሕይወት እንድናጣጥም እግዚአብሄር አብ የእግዚአብሄር ልጆች ሊያደርገን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጥቶናል፡፡ ሁለተኛው ዓለም ለእኛ የሚሰጠን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ምክንያት ነው፡፡ እግዚአብሄር በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ለተቀበልነው ለእናንተና ለእኔ አዲሱን ዓለም አበጅቶልናል፡፡ ጌታ አዲሱን ዓለም አበጅቷል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሁሉን ወራሽ ባደረገው፤›› ይህ ማለት እግዚአብሄር ዓለምን አበጅቶ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ዓለም እንዲገዛ አደርጎታል ማለት ነው፡፡ እንዲህ ተብሎም ተጽፎዋል፡- ‹‹ዓለማትን በፈጠረበት፤›› ይህ ምንባብ ጌታ ኢየሱስ የፈጠረው የሚታየውን ዓለም ብቻ ሳይሆን በዓይኖቻችን የማይታየውንም ሌላ ዓለም እንደሆነ ይናገራል፡፡ እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሄር ጽድቅ ለምናምን ለእኛ ለአማኞች የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ የሚቻለው በማን አማካይነት ነው? ይህ የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያቶቻችንንና በደሎቻችንን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ የደመሰሰ አምላካችን፣ ጌታችንና አዳኛችን ነው፡፡

    እግዚአብሄር አብ ሰማይንና ሲዖልን ፈጠረ፡፡ እግዚአብሄር ሰማይን እንደዚሁም ሲዖልን ወደ ኑባሬ አምጥቷል፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር ሲዖልን ያበጀው ለምንድነው? እግዚአብሄር ከመጀመሪያውም ሰዎች እርሱን ብቻ እንዲታዘዙት ያላደረገውና እንዳያምጹ ማድረግ ያልቻለው ለምንድነው? ብዙ ሰዎች እንዲህ ያለ ጥያቄ እንዳላቸው አስባለሁ፡፡

    እግዚአብሄር ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ዓለም መንፈሳዊ ፍጡራኖችን የያዘ ነበር፡፡ ነገር ግን ሉሲፈር የተባለ መልአክ በእግዚአብሄር ላይ ዐመጸ፡፡ ያ መልአክ ነጻ ፈቃድ የነበረው ፍጡር ነበር፡፡ እግዚአብሄር ያንን መንፈሳዊ ፍጡር እግዚአብሄርን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሚያገለግል ሮቦት አድርጎ ከመፍጠር ይልቅ ለእርሱ ባለው አክብሮት በገዛ ራሱ እርሱን ማገልገልና በተሰጠው ነጻ ፈቃድም እርሱን መቃወም የሚችልበትን ነጻ ፈቃድና ጠባይ ሰጠው፡፡ በዚህ መልኩ የተፈጠረው ሉሲፈር ብቻውን ከፍ ለማለት ፈለገ፡፡ በዚህ የተነሣ በሆነ ምክንያት በእግዚአብሄር ላይ ባመጸ ጊዜ ውሎ አድሮ ከሰማይ ተጣለ፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር ፍጥረታቶች በሙሉ በነጻ ፈቃዶቻቸው ሊያደንቁት የሚችሉት እጅግ ግርማዊ ሕላዌ መሆን ፈለገ፡፡ እግዚአብሄር ይህንን ነጻ ፈቃድ ለእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር የሰጠበት ምክንያት ያ ነው፡፡

    ሰማይና ሲዖል እንደዚሁም አሁን እየኖርንበት ያለነው ይህ ዓለም በሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሄር የተፈጠሩ ነበሩ፡፡ ሲዖልም እግዚአብሄር ያበጀው ዘላለማዊ ስፍራ እንጂ ለጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ የሚጠፋ ስፍራ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ሰማይንም ደግሞ አበጅቷል፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ነገር አበጅቷል፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት አበጀ፡፡ እኛ በእነዚህ ሁሉ እውነታዎች ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሄር የፍጥረት አምላክ ነው፡፡ እርሱ ጊዜ ከመጀመሩ በፊትም እንኳን ኖሮዋል፤ ለዘላለምም ይኖራል፡፡ እርሱ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ለዘላለም የሚኖር አምላክ ነው፡፡ እኛ ከእናቶቻችን ማህጸኖች ውስጥ ወጥተን ወደዚህ ዓለም ተቀላቀልን፡፡ በዓለም ላይ ለጥቂት ጊዜ እንኖራለን፤ ለመኖርም ጠንክረን እንሠራለን፤ እድሜያችን ገፍቶ ወይም በሕመም ምክንያት እንሞታለን፡፡ ነገር ግን በተጨባጭ የፈጠረን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እናቶቻችን በማህጸኖቻቸው ውስጥ እንዲጸንሱን ሐይል የሰጣቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

    ‹‹ኢየሱስ›› የሚለው ቃል አዳኝ ማለት ሲሆን ‹‹ክርስቶስ›› የሚለው ቃል ንጉሡን ያመለክታል፡፡ እርሱ ለምን ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ ሰየመ? እግዚአብሄር አዳኛችን ሆኖ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ነገር ግን ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሎ የሰየመው ንጉሥና ነቢይ ሆኖ ስለተቀባና የሊቀ ካህንን ተግባር ራሱ ብቻውን ስለወሰደ ነው፡፡

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1