Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)
በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)
በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)
Ebook459 pages3 hours

በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ሐይል የሌለን ብንሆንም የእግዚአብሄር ቃል ሐይል ስላለው ቃሉ ምድር ላይ ሲወድቅ ያለ ችግር ፍሬ ያፈራል፡፡ በተጨማሪም የእግዚአብሄር ቃል ሕያው ስለሆነ ዛሬም፤ ነገም፤ ለዘላለምም የማይለወጥ መሆኑን ራሳችን ማየት እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እንደ ሰው ቃሎች ስላይደለ ፈጽሞ አይለወጥም፡፡ ሁሌም የታመነ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሲናገር በቃሎቹ መሰረት በትክክል ይፈጸማል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስልጣን ስላለው እግዚአብሄር ‹‹ብርሃን ይሁን›› ሲል ብርሃን ሆነ፡፡ ‹‹ታላላቅ ብርሃናትና ታናናሽ ብርሃናት ይሁኑ›› ሲል ባዘዘው መሰረት ተፈጸመ፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateSep 21, 2023
ISBN9788965322610
በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)

Related to በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)

Related ebooks

Reviews for በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54)

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI) - የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ (Amharic 54) - Paul C. Jong

    paul_Am54_coverFrontflap_Am541st_page

    በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VI)

    የሰውን ዘር ከጥፋት የሚያድን የወንጌል ምስክር ሁኑ

    Smashwords Edition

    Copyright 2022 by Hephzibah Publishing House

    ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ባለቤት በጽሁፍ የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር የዚህን መጽሐፍ ማንኛውንም ክፍል ማባዛት ወይም በማንኛውም መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ በኤሌክትሮኒክ ወይም በሜካኒካል ፎቶ ኮፒ ማድረግን ጨምሮ በቅጂ መልክ ወይም መረጃን ይዞ በሚያጠራቅም ወይም መረጃን ይዞ በሚያስቀር ማንኛውም መንገድ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

    ጥቅሶቹ በሙሉ የተወሰዱት ከ1954ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    ISBN 978-89-6532-261-0

    ዲዛይን፡ በሚን ሱ ኪም

    ንድፍ፡ በዮንግ አይ ኪም

    ትርጉም፡ በካሳሁን አየለ

    የታተመው በኮርያ ነው፡፡

    Hephzibah Publishing House

    A Ministry of THE NEW LIFE MISSION

    Seoul, Korea

      የማውጫ ሰሌዳ  

    መቅድም

    1. የሰውን ዘር ከጥፋት ማዳን የሚችሉ የወንጌል ሰባኪዎች ሁኑ (ዘፍጥረት 6፡5-22)

    2. አሁንም እንኳን ከሐጢያቶቻችሁ መዳን አለባችሁ (ዘፍጥረት 6፡1-4)

    3. በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ለደህንነታችሁ ተዘጋጁ (ዘፍጥረት 6፡5-12)

    4. በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ደህንነት ላይ ደርሰናል (ዘፍጥረት 6፡5-12)

    5. እምነታችሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ በማኖር ልባችሁን ጠብቁ (ዘፍጥት 6፡13-14)

    6. ኢየሱስ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ የመደምሰሱን እውነታ ታውቃላችሁን? (ዘፍጥረት 6፡14)

    7. የእግዚአብሄር ሠራተኞች (ዘፍጥረት 7፡1-24)

    8. እየቀረበ ላለው የዓለም ፍጻሜ መዘጋጀት አለባችሁ (ዘፍጥረት 7፡1-24)

    9. ወደ ደህንነት የሚወስደን እምነት (ዘፍጥረት 7፡1-13)

    10. ዓለምን በእግዚአብሄር ዓይኖች እዩት (ዘፍጥረት 7፡1-12)

    11. ወደ መርከቡ ለመግባት ያለ ማመንታት የሐጢያቶችን ስርየት መቀበል አለባችሁ (ዘፍጥረት 7፡1-5)

    12. ወደ መርከቡ ውስጥ መግባት አለባችሁ (ዘፍጥረት 7፡1-5)

    13. እግዚአብሄር ለእኛ ያለው ዕቅድና ልብ (ዘፍጥረት 8፡20-21)

    14. በእምነት ሕይወታችን ውስጥ ስምንት ወቅቶች አሉ (ዘፍጥረት 8፡22)

    0preface.jpg

    መቅድም

    እግዚአብሄር በሕዝብ ወይም በግለሰብ ላይ የሚወስናቸው ‹‹የጥፋተኝነት ውሳኔ ፍርዶች›› እንዳሉ ከቅዱሳት መጻህፍት እናውቃለን፡፡ ይህንን በሚመለከት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተመዘገበው የታላቁ ጥፋት ውሃ ኩነት ለሁላችንም በጣም ጠቃሚ ትምህርት ይዞዋል፡፡ በኖህ ዘመን ልቦቻቸውና ድርጊቶቻቸው ፈጽመው ክፉ ስለነበሩ እግዚአብሄር የሰውን ዘር ለማጥፋት ወሰነ፡፡ ከዚህ መቅሰፍታዊ ኩነት በፊት እግዚአብሄር ዕቅደ አሳቡን ለኖህ አስታወቀው፤ የሰው ዘር ከእርሱ ፍርድ የሚያመልጥበትንም መንገድ እንደዚሁ ከፈተ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ኖህና የእርሱ ቤተሰብ እንደዚሁም ሌላው ሰው ሁሉ ከዚህ ከሚመጣው ፍርድ መዳን ይችል ዘንድ መርከብን እንዲያዘጋጅ ለኖህ ነገረው፡፡

    ኖህ እያንዳንዱን ሕያዋን ዝርያዎች ጠብቆ ለማቆየት ቢያንስ ከእያንዳንዱ እንስሳ ዓይነት ሁለት ጥንዶችን እንዲወስድም በእግዚአብሄር ታዞ ነበር፡፡ ከዚያም በእግዚአብሄር መመሪያዎች መሠረት በትክክል መርከብን ሠራ፡፡ ውሎ አድሮ ታላቁ የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜም ኖህና ቤተሰቡ ከእንስሶች ሁሉ ጋር የመትረፊያ መጠጊያ አገኙ፡፡ ውሎ አድሮም የጥፋት ውሃው ሲጎድል መርከቢቱ በአራራት ተራሮች ላይ ስታርፍ ኖህና ቤተሰቡ እንስሶችንም ሁሉ ጨምሮ ከመርከቢቱ ወጡ፡፡

    ታዲያ እኛ ሰዎች ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ከሚጠብቀን ከዚህ የተረጋገጠ ፍርድ ለማምለጥ ምን ማድረግ ይገባናል? ሁላችንም ከዚህ ጥፋት መዳን የምንችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን እንደሆነ በግልጥ በማሳየት መልሱን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አቀርባለሁ፡፡ እግዚአብሄር ማናቸውም ሰዎች በሥራዎቻቸው ላይ በመደገፍ ከእርሱ ፍርድ እንዲድኑ አይፈቅድም፡፡ ለዚያ ምክንያቱ እግዚአብሄር የሰውን ዘር በእርሱ ጽድቅ፣ ጸጋና ቅድስና ላይ ባላቸው እምነት ሊያድናቸው የወሰነ መሆኑ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የሰውን ዘር በሙሉ አድኖዋል፡፡ እግዚአብሄር አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት አማካይነት በፈጸመው የውሃና የመንፈስ ወንጌል እውነት የሚያምኑትን ሰዎች በሙሉ ከጥፋት ታድጎዋቸዋል፡፡ የእግዚአብሄር ፍትህና ምህረት በተገለጠበት የውሃና የመንፈስ ወንጌል የሚያምነው ይህ እምነት እግዚአብሄር አብና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መላውን የሰው ዘር ከሐጢያቶቹ ሁሉ የታደጉበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡

    ይህ የአሁኑ ዘመን የጥፋት ዘመን እንደሆነ ተረድታችሁ ታምናላችሁን? በዚህ ዓለም ላይ የምናየውና የሚገጥመን እያንዳንዱ ነገር እግዚአብሄር የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች ሁሉ ሊፈጽም እንደተዘጋጀ በተግባር ግልጥ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚያምን የሚናገር እያንዳንዱ ሰው አሁኑኑ የእርሱ ጽድቅ በተጨባጭ ምን እንደሆነ መገንዘብና በዚህ ጽድቅም ብቻ ማመን አለበት፡፡ የእርሱን ጽድቅ ሳታስተውሉ በክርስቶስ እንደምታምኑ የምትናገሩ ከሆነ እምነታችሁ ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ ነው፡፡

    ይህ መጽሐፍ የዓለም ፍጻሜ በእኛ ላይ በደረሰበት ዘመንና ጊዜ ላይ መጽሐፉን ለሚያነቡ አንባቢዎች ሁሉ ከፍርዳቸው እንዲድኑ የሚያስችለውን እውነት የሚናገር ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉት ስብከቶቼ የእግዚአብሄርን ጥልቅ ችሮታ እንዲያስተውሉ ሁሉንም እንደሚያግዙና ለእያንዳንዳችሁም እውነተኛ እምነትን እንደሚያመጡ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እጸልይማለሁ፡፡

    ሕዳር 8፡2007

    ፖል ሲ. ጆንግ፤ ደራሲ

    Sermon0101

    የሰውን ዘር ከጥፋት ማዳን የሚችሉ የወንጌል ሰባኪዎች ሁኑ

    ‹‹ ዘፍጥረት 6፡5-22 ››

    ‹‹እግዚአብሄርም የሰው ክፋት በምድር፣ ላይ እንደበዛ፣ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ፡፡ እግዚአብሄርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፣ በልቡም አዘነ፡፡ እግዚአብሄርም፡- የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፣ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ስለፈጠርኋቸው ተጸጸቼአለሁና አለ፡፡ ኖህ ግን በእግዚአብሄር ፊት ሞገስን አገኘ፡፡ የኖህ ትውልድ እንዲህ ነው፡፡ ኖህም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበር፤ ኖህ አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር አደረገ፡፡ ኖህም ሦስት ልጆችን ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ፡፡ ምድርም በእግዚአብሄር ፊት ተበላሸች፤ ምድርም ግፍን ተሞላች፡፡ እግዚአብሄርም ምድርን አየ፣ እነሆም ተበላሸች፤ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና፡፡ እግዚአብሄርም ኖህን አለው፡- የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፤ ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና፤ እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፡፡ ከጎፈር እንጨት መርከብን ለአንተ ሥራ፤ በመርከቢቱም ጉርጆችን አድግ፣ በውስጥም በውጭም በቅራጥን ለቅልቃት፡፡ እርስዋንም እንዲህ ታደርጋታለህ፤ የመርከቢቱ ርዝመት ሦስት መቶ ክንድ፣ ወርድዋ አምሳ ክንድ፣ ከፍታዋ ሠላሳ ክንድ ይሁን፡፡ ለመርከቢቱም መስኮትን ታደርጋለህ፤ ከቁመትዋም ክንድ ሙሉ ትተህ ጨርሳት፤ የመርከቢቱንም በር በጎንዋ አድርግ ታችኛውንም ሁለተኛውንም ሦስተኛውንም ደርብ ታደርግላታለህ፡፡ እኔም እነሆ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውሃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል፡፡ ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አቆማለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ፡፡ ከአንተ ጋር በሕይወት ይኖር ዘንድ ሥጋ ካለው ከሕያው ሁሉ ሁለት ሁለት እያደረግህ ወደ መርከብ ታገባለህ፤ ተባትና እንስት ይሁኑ፡፡ ከወፍ እንደ ወገኑ፣ ከእንስሳም እንደ ወገኑ፣ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንደ ወገኑ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ፡፡ ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ፤ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል፡፡ ኖህም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሄር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ፡፡››

    እግዚአብሄር በዓለም ላይ ፍርድን ያስተላለፈው ለምን ምክንያት ነው?

    እግዚአብሄር በኖህ ዘመን ዓለምን በውሃ እንደፈረደ ሁሉ እግዚአብሄር ይህንን ዓለም በእርግጠኝነት በእሳት ይፈርድበታል፡፡ እግዚአብሄር ይህንን ዓለም ለማጥፋት አንድ ምክንያት ብቻ ቢኖር ያ ምክንያት የዓለም መንፈሳዊ ምስቅልቅልና ክህደት ይሆናል፡፡ በኖህ ዘመን የእግዚአብሄር ልጆች የሰውን ሴት ልጆች ውበት አዩና ሚስቶቻቸው አድርገው ወሰዱዋቸው፡፡ በሒደትም መንፈሳዊውን እውነት በመጣላቸው ምክንያት የእግዚአብሄር መንፈስ ዳግመኛ ከእነርሱ ጋር ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለዚህ በዚህ ዓለም ላይ ለሚኖሩ ለእነዚያ ሰዎች ጥፋት መጣ፡፡ ይኸው አሳዛኝ ነገር በዚህ ዘመንም እንደገና ይሆናል፡፡ ገና የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ካልተቀበሉ ወንጌላውያኖች ጋር የሚተባበሩና አብረው የሚሠሩ ከሆነ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል አማኞች ጋር አብሮ ሊሠራ አይችልም፡፡

    ልቦቻችንን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ገና ዳግመኛ ካልተወለዱ ሰዎች ጋር ማቆራኘት እጅግ ትልቅ ክህደት ሆኖ የሚቆጠር ነው፡፡ ዳግመኛ የተወለደ ቅዱስ የእግዚአብሄርን ሥራ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከማያምን ሰው ጋር የሚሠራ ከሆነ በእግዚአብሄር ፊት ትልቅ ሐጢያት እየሠራ ነው፡፡ በጥብቅ አነጋገር ይህ ከጠላት ጋር አብሮ እንደ መተኛት ነው፡፡ በአጋጣሚ በመካከላችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ሰዎች ካሉ በተቆራኙ ልቦች ከእኛ ጋር አብረው መሥራት አይችሉም፡፡ በእርግጥ እነርሱ ማድረግ የሚኖርባቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ እውነተኛ ወንጌል ለማመን አሻፈረን ቢሉ ምን ይከሰታል? የሕይወት ዓላማው ከእናንተ የሕይወት ዓላማ የተለየ ከሆነ ሰው ጋር አብራችሁ ብትኖሩ ሕይወታችሁ ሲዖል ይሆናል፡፡

    ለጻድቃን የትዳር ዓላማው ለእግዚአብሄር ክብር መኖር ነው፡፡ ስለዚህ ‹በጌታ ሆኖ ማግባት› የሚፈልግ ማንኛውም ዳግመኛ የተወለደ ቅዱስ የሕይወት ዓላማዋና እምነቷ በትክክል ተመሳሳይ ከሆነች አጋር ጋር መገናኘት ወሳኝ ነው፡፡ አንድ ወጣት ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለው እምነት ዳግመኛ መወለዱ እውነት ቢሆንም ገና ከሐጢያቶችዋ ሁሉ ደህንነትን ያልተቀበለችን ሴት ካገባ የእግዚአብሄር መንፈስ በመካከላቸው ሊሠራ አይችልም፡፡ በመሆኑም ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ለእግዚአብሄር ክብርን ማምጣት አይችልም፡፡ ይህ ከተከሰተ ብዙ ችግሮች ይወርዱባቸዋል፡፡ በዚህ ቀንና ዘመን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግመኛ የተወለደ ግለሰብ ሐጢያተኛን ከተከተለ በእግዚአብሄር ዘንድ ከእርሱ እንደተለየ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ባለ ትዳር ጥንዶች አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩ ዳግመኛ የተወለደ ግለሰብ ገና ዳግመኛ ያልተወለደችን አንዲት ሰው ካገባ ያ ዳግመኛ የተወለደ ቅዱስ ከባድ መንፈሳዊ ክስረት ይገጥመዋል፡፡ ጥፋት በዚህ ዓለም ላይ እንዲያው በዘፈቀደ አይወርድም፡፡ ይልቁንም ጥፋት የሚወርደው ጻድቃን ሲበላሹ ነው፡፡

    እኔ በእግዚአብሄር ፊት ስለ ራሴ በማስብበት ጊዜ ሁሉ ሁሌም ጎዶሎ እንደሆንሁ በደምብ አውቃለሁ፡፡ የስጋን መሻቶች በመከተል የመጋቢነት ተግባራቶቼን የማከናወን ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ እግዚአብሄር ግን እንዲህ ብቁ ያልነበርሁትን ሰው ወደ ጽድቅ መንገድ መራኝና የውሃና የመንፈስ ወንጌል የሆነውን የእግዚአብሄር ጽድቅ ወንጌል ማሰራጨት የሚችል ሰው አደረገኝ፡፡ ቀድሞ ከእነዚህ ወንጌላውያን ጋር ሕብረትን ለመካፈል የሞከርሁበት ጊዜ ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱ በውስጣቸው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የላቸውም፡፡ ስለዚህ ይህ እውነተኛ ወንጌል ከሌላቸው ሰዎች ጋር አብሮ በመሥራት መቀጠል ለእኔ የማይቻል ነበር፡፡ እውነተኛውን ወንጌል ይረዱና የእኔም አጋር ሠራተኞች ይሆኑ ዘንድ እግዚአብሄር ክርስቲያን ወደሆኑ እውነት ፈላጊዎች ቡድን የመራኝና እውነተኛውን ወንጌል እንዳካፍል የረዳኝ ብዙ ቆይቶ ነበር፡፡ በእነዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት እግዚአብሄር የወንጌልን እውነት አብረን እንድንሰብክ ያደረገን እንደዚህ ነው፡፡

    ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ አገልግሎትን የሚያደርጉ ብዙ ሰዎች ይህ ወንጌል ለማየት በጣም ግልጥና በዚህ ዓለም ላይም ብቸኛው እውነተኛ ወንጌል ቢሆንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አያምኑም፡፡ ዛሬ ክርስቲያኖች የሚያምኑት ወንጌል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ሳይሆን አስመሳይ ወንጌል ነው፡፡ እኔም ደግሞ በዚህ አስመሳይ ወንጌል ለአስር ዓመታት ያህል አምኜ ነበር፡፡ በወቅቱ ዋጋ ያለው እንደሆነ አድርጌ ይህንን አስመሳይ ወንጌል የሙጥኝ በማለት ምንም ያህል በግለት የንስሐ ጸሎቶቼን ባቀርብም የከፋሁ ሐጢያተኛ ነበርሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ሆኖ ሳለ እግዚአብሄር ድንቅ የሆነውን ጸጋውን ለገሰኝ፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ላይ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ከብሉይ ኪዳን ጋር እያነበብሁ ሳለሁ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት ተረዳሁ፡፡ በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ ያሉትን ምንባቦች ሳነብ የእውነት ብርሃን በልቤ ላይ አበራ፡፡

    የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሲያስተምረኝ የነበረው እግዚአብሄር እንደነበር አምናለሁ፡፡ በዚያን ወቅት የዚህን እውነት ብርሃን ከተረዳሁ በኋላ እንዲህ ባለ ትልቅ መደነቅ በመመሰጤ ምክንያት ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች ያህል አንድም ቃል መናገር አልቻልሁም፡፡ በዚያን ወቅት አንድ ሰው በኩሬ ላይ ድንጋይን ወርውሮ በጣም ብዙ ሰፋፊ ሞገዶችን የሚሠራ ይመስል በልቤ ውስጥ የሞገዶች ክበቦች ይሸከረከሩ ነበር፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በልቤ ውስጥ በገባበት በዚያች ወሳኝ ቅጽበት የእኔ ሐጢያቶች ሁሉና የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ‹ለአንዴና ለመጨረሻ› ተወገዱ፡፡ በእኔ ላይ የበራው እውነትም መንፈስ ቅዱስ ለዘላለም በልቤ ውስጥ እንዲያድር ፈቀደ፡፡

    በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የመጣውን ጌታ ከተገናኘሁ በኋላ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማሰራጨት ጀመርሁ፡፡ እግዚአብሄር የእርሱን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እንዳሰራጭ ይረዳኝ ዘንድ ከልቤ የጸለይሁት ከዚህ ልምምድ በኋላ ነበር፡፡ እግዚአብሄርም ጸሎቴን በተጨባጭ መለሰልኝ፡፡ ይህንን የእግዚአብሄር ክቡር ሥራ በኮርያና በመላው ዓለም ሁሉ ካሉ አጋር ሠራተኞች ጋር አብሬ መሥራት የቻልሁት አሁን ነው፡፡ ከእምነት አጋር ሠራተኞቼ ጋር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመላው ዓለም ማሰራጨት በመቻሌ በጣም አመስጋኝ ነኝ፡፡ ሁላችንም በተባበሩት ልቦቻችን ወንጌልን ለማገልገል ወስነናል፡፡ በዚህ ክቡር ተግባር ውስጥም የተቻለንን እያደረግን ነው፡፡ እኛ በሥነ ጽሁፍ አገልግሎታችን አማካይነት የሰበክነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከሰሙ በኋላ በልቦቻቸው ውስጥ የሐጢያቶች ስርየት ከተቀበሉ ከእነዚህ በትክክል ዳግመኛ ከተወለዱ ሰዎች በየቀኑ መደበኛ መልዕክቶች እንቀበላለን፡፡

    እኔ እዚህ በኮርያ ካሉ አጋር ሚሲዮናዊ ሠራተኞቼ ጋር አብሬ የእግዚአብሄርን ሥራ በመሥራት በጣም ባተሌ ሆኛለሁ፡፡ በአገልግሎቴ መጀመሪያ ላይ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማሰራጨት በመንገዶች ላይ እኔን አልፎኝ ለሚሄድ ለማንኛውም ሰው በገሃድ መናገር አዘወትር ነበር፡፡ እነርሱ ለእኔ እንግዶች ቢሆኑም ‹‹በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት አለ?›› ብዬ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ሐጢያት ካለባቸውና የእግዚአብሄርን ቃል ለመስማት ከተመኙ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል በዝርዝር እነግራቸዋለሁ፡፡ በዚያች ቦታ ላይ በዚህ የወንጌል ቃል በማመን ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የሐጢያትን ስርየት ተቀበሉ፡፡ ሰዎች መጀመሪያ ላይ ይደነግጣሉ፤ በኋላ ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከሰሙና በልቦቻቸውም ከተቀበሉ በኋላ ፊቶቻቸው ሲያበሩ ስመለከት እግዚአብሄርንና እኔንም የመንገድ ላይ ሰባኪውን ያመሰግኑ ነበር፡፡ በእርግጥ በደካማ ምኞቶቻቸው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የተገዳደሩ አንዳንዶችም ደግሞ ነበሩ፡፡ በእነዚህ አጋጣሚዎች ‹‹ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጪ አንዳች ሌላ ወንጌል ለማሰራጨት የሚሞክር ሁሉ ከእግዚአብሄር እርግማን በታች ነው›› ብዬ በመንገር ገሰጽኳቸው፡፡

    ይህ ሆኖ ሳለ የእግዚአብሄርን እርግማን በራሳቸው ላይ ያመጡ ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ አትገምቱም፡፡ ነገር ግን ለእነዚህ ግትር ሰዎችም እንኳን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰበክሁ፡፡ ሰዎች የሐጢያቶችን ስርየት እንዲቀበሉ የሚያስችል ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጪ አንዳች ሌላ ወንጌል አለ? አንድም አይገኝም፡፡ ብዙ ሰዎች ቢቃወሙኝም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምን እምነት ላሸንፋቸው የቻልሁት ለዚያ ነው፡፡

    በወንጌላውያኖቹ መካከል አንድ መጋቢ በተከታዮቹ ቃሎች ሰዎችን እያሳተ ነበር፡፡ እርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል መጀመሪያ ላይ የተስተዋወቀው ለኮርያ ነው፡፡ የኮርያ ሕዝብ ግን የዚህን ወንጌል ዋና አሳብ ለውጦታል፡፡›› እውነታው ግን በኮርያውያን ሚሲዮን መጀመሪያ ላይ ምዕራባውያን ሚሲዮናውያን ወደ ኮርያ ያመጡት ወንጌል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ያልነበረ መሆኑ ነው፡፡ እርሱ ትክክል ከሆነ አሁን ሕዝቡ ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን እውነታው እንደዚያ አይደለም፡፡ በኮርያ ያሉት የሥነ መለኮት ትምህርት ቤቶች በእርሱ ላይ እምነት ኖሮዋቸው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እያስተማሩ ናቸው? አይደለም፡፡ እነርሱ ይህንን አያደርጉም፡፡ ታዲያ ይህንን እውነታ የምንለማመደው እንዴት ነው? ጌታ እንዲህ ነግሮናል፡- ‹‹ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፡፡›› ወንጌላውያኖች እስከ አሁን ድረስ አንድም ጻድቅ ሰው ፍሬያቸው አድርገው አልወለዱም፡፡ ታዲያ በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ወንጌላውያን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አላቸው? በእርግጥም የላቸውም፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመላው ዓለም ተሰራጭቶ ቢሆን ኖሮ በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ብዙ ሰዎች በእርሱ በማመን የሐጢያቶቻቸውን ስርየት በተቀበሉ ነበር፡፡ በተጨባጭ ግን ጉዳዩ ይህ አይደለም፡፡ ይህ እውነት አይደለምን?

    እግዚአብሄር የመጀመሪያውን ዓለም ያጠፋበት እጅግ ትልቁ ምክንያት ምን ነበር? ክፋት በምድር ላይ የመብዛቱ እውነታ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዋናው ምክንያት የእግዚአብሄር ልጆች በሰዎች ሴቶች ልጆች ውስጥ ውበትን ማግኘታቸውና ሚስቶቻቸው አድርገው መውሰዳቸው ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሄርን ትልቅ ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡ እግዚአብሄር ለዚያ ትልቅ ሐጢያት ምድርን በትልቅ የውሃ ጥፋት ጠራርጎ አጠፋ፡፡ ምንም ነገር ቢፈጠር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ እምነት ያለው ግለሰብ የእግዚአብሄርን ሥራ በዚህ ወንጌል ከማያምኑ ሰዎች ጋር አብሮ መሥራት የለበትም፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ባለው አንድነት ውስጥ በጭራሽ ደስታን አያገኝም፡፡

    እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያትን ስርየት ከተቀበልን በኋላ ልቦቻችንን በዚህ ተመሳሳይ ወንጌል ከሚያምኑ ቅዱሳኖች ጋር በማቆራኘት ይህንን ወንጌል መስበክና በእግዚአብሄር ጸጋ መኖር አለብን፡፡ እኔ ይህንን ክቡር የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማገለግለው የተለየ ችሎታ ስላለኝ ይመስላችኋልን? እኔ ምንም ችሎታ የለኝም፡፡ እኛ ወንጌልን የምናገለግለው እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በምናምነው ሁሉ በእኔና በአጋር ሠራተኞቼ ላይ የደህንነት ጸጋውን በመለገሱ ነው፡፡ እናንተና እኔ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ደህንነትን መቀበል የቻልነው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ምክንያት ነው፡፡ እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ለአንዴና ለመጨረሻ የሐጢያቶቻችንን ስርየት ከተቀበልን በኋላ ለዘላለም በእግዚአብሄር ፊት ለመኖር ተባርከናል፡፡

    እነዚህ የአሁኑ ጊዜያቶች ከኖህ ቀኖች ጋር በትክክል ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በኖህ ቀኖች የእግዚአብሄር ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ሚስቶቻቸው አድርገው እንደወሰዱ ተነግሮዋል፡፡ እነርሱም ሃያላን የሆኑ ልጆች ነበሩዋቸው፡፡ በዚህ ቀንና ዘመንም ቢሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዋቂ መጋቢዎች የሉንምን? በኮርያ ብቻ ወደ አስር ሺህ የሚጠጉ አባላቶች ያሉዋቸውን ቤተክርስቲያኖቻቸውን የሚያስተዳድሩ ብዙ መጋቢዎች አሉ፡፡ አንድ መጋቢ በሚሰብክበት ቤተክርስቲያን ውስጥ የአባላቶቹ ቁጥር 500 ሺህ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ለአንዲት ቤተክርስቲያን ይህ በዓለም ላይ እጅግ ትልቁ ሆኖ ይቆጠራል፡፡ ፖለቲከኞች እንኳን ያንን መጋቢ ችላ አይሉትም፤ ነገር ግን በፋንታው ያከብሩታል፡፡ እነርሱ በእርግጥም የእነዚህ ጊዜያቶች ሃያላን ሰዎች ናቸው፡፡ ሆኖም በሥነ መለኮት ትምህርት ቤቶቻቸው ውስጥ የሚማሩትን ተማሪዎቻቸውን ሲያስተምሩ እውነተኛውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማስተማር ፋንታ ሰው ሰራሽ ሥነ መለኮትን ብቻ ያስተምሩዋቸዋል፡፡ እነርሱ በመንፈሳዊ መልኩ በእግዚአብሄር ፊት ሲታዩ ዕጣቸው በእርግጥም አሳዛኝ ነው፡፡

    ጌታ ‹‹የልቡ አሳብ ምኞትን ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ›› (ዘፍጥረት 6፡5) እንደተባለው እስከ አሁን ድረስ ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማገልገል ስለማይችሉ ሁልጊዜም ክፋትን ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ሰዎች በማህበረሰቡ መካከል ብዙ መልካም ምግባሮችን የሚያደርጉ መስሎ ሊታይ ይችላል፡፡ እነዚህ ግን በተጨባጭ ሰናይ ምግባሮች አይደሉም፡፡ እነርሱ የእግዚአብሄርን እውነተኛ ጽድቅ ስለማያውቁ በፋንታው ሰብዓዊ በጎነቶቻቸውን ለመገንዘብ ይሞክራሉ፡፡ እግዚአብሄር ግን በሰዎች ውስጥ አንዲትም የእውነተኛ በጎነት ቅንጣት እንደሌለ ነገረን፡፡

    በኖህ ዘመን ዓለም ፈጽሞ ጠፋ፡፡ ኖህ ግን በእግዚአብሄር ዓይኖች ፊት ሞገስን አገኘ፡፡ ኖህ በእግዚአብሄር ዓይኖች ሞገስን ስላገኘና የእግዚአብሄርን ቃል ስለተከተለ እግዚአብሄር ኖህ በትውልዱ ፍጹምና እንከን አልባ እንደነበር ተናገረ፡፡ እኛም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን ሰዎች በእግዚአብሄር ዓይኖች ልክ እንደ ኖህ ፍጹም ነን፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስናምንና ጌታን ስንከተል እግዚአብሄር ፍጹማን እንደሆንን ይናገራል፡፡ እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን ጻድቃን ነን፡፡ እኛ በእርግጥም የእግዚአብሄርን ጸጋ ለብሰናል፡፡

    ጌታ ወደዚህ ዓለም የመጣበት ዓላማ ሰዎችን ከሐጢያት ለማዳን ነበር፡፡ የደህንነትም ዘዴ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ከሆነ በእርግጠኝነት ሐጢያት አለባቸው፡፡ ለእነዚህ ሐጢያቶችም ፍርድን ይቀበላሉ፡፡ እግዚአብሄር ከረጅም ጊዜ በፊት የሰዎችን ክፋት በተመለከተ ጊዜ በሰዎች ላይ ፍርድን አስተላለፈ፡፡ አሁን ግን እርሱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባለማመናቸው በሰዎች ሐጢያት ላይ ፍርድን ያስተላልፋል፡፡ እንደዚሁም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ያመኑ ቢሆኑም ለእግዚአብሄር የማይሠሩ ነገር ግን በፋንታው ወደ ዓለም ሄደው ከእነዚህ ዓለማዊ ሰዎች ጋር በአንድነት የሚኖሩ ሰዎች ተመሳሳይ ፍርድ ይፈረድባቸዋል፡፡

    እኛም ደግሞ በእግዚአብሄር ዓይኖች የደህንነትን ጸጋ አግኝተናል፡፡ ስለዚህ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ወደ ማወቅና ማመን መጥተናል፡፡ እኛ አሁን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በዓለም ሁሉ እያሰራጨን ነው፡፡ እግዚአብሄርም ከእኛ ጋር ነው፡፡ እኛ ይህንን ዓለም ከሚጠብቀው ጥፋት መጠራታችንና መዳናችን የእግዚአብሄር አስገራሚ ስጦታ ነው፡፡ እስከዚህ ቅጽበት ድረስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በሰፊው አሰራጭተናል፡፡ ነገር ግን ቁጥራችን ጥቂት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በዓለም ላሉ አገሮች ሁሉ ማለትም ለ200 አገሮች አካባቢ እያሰራጨን ለመሆኑ እውነታ አመስጋኝ ነኝ፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር እየሠራ ያለው እንደዚህ ነው፡፡ በበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አማካይነት ወንጌልን በዓለም ሁሉ ለማሰራጨት በጣቢያ ገጻችን ላይ በእያንዳንዱ ቋንቋ ድረ ገጾችን አበጅተናል፡፡ አንድ ቻይናዊ የክርስቲያን ጽሁፋችንን በቻይንኛ ማየት ቢፈልግ ማድረግ ያለበት በጣቢያችን ገጽ ላይ ያለውን የቻይንኛ ድረ ገጽ ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ስፓንኛ የሚናገሩ ሰዎች ከስፓንኛ ድረ ገጻችን በስፓንኛ የተጻፉ መጽሐፎቻችንን ማዘዝ ይችላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ሌሎች ቋንቋዎችና ልሳናት የሚናገሩ ሰዎች ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል እንዲገናኙ ቀላል መንገድ ከፍተናል፡፡ በዓለም ሁሉ ያሉ ሰዎች ይህንን ሥራ ከልባቸው እያወደሱት ነው፡፡ ነገር ግን ይህና ሌሎች ሥራዎች በሙሉ በእግዚአብሄር ጸጋ ባይሆን ኖሮ ሊሠሩ ባልቻሉም ነበር፡፡

    በእግዚአብሄር ፊት ፍጹም ማነው? በእርሱ ፊት ፍጹማን የሆኑ ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር የሚራመዱ ሰዎች ናቸው፡፡ ድርጊቶቻችን ጎዶሎ ቢሆኑም ከእርሱ የደህንነትን ጸጋ ተቀብለን የእግዚአብሄርን ጽድቅ በሚያምን እምነታችን በመኖር የእግዚአብሄርን ሥራ የምንሠራ እኛ በእግዚአብሄር ፊት ፍጹም ነን፡፡ ለጽድቁ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ፡ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር የምንራመድበትን ሕይወት እንድንመራ ስለፈቀደልን ከዚህም በላይ አብዝቼ እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ፡፡

    እነዚህ ጊዜያቶች በእውነትም ክፉ ናቸው፡፡

    በዚህ ቀንና ዘመን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት በመቀበላችን አመስጋኝ ነኝ፡፡ የዚህ ዓለም ፍጻሜ እየተቃረበ በመሆኑ ምክንያት ጥረቶቼን ሁሉ ይህንን ወንጌል በማሰራጨት ላይ የማዋል ልብ አለኝ፡፡ እኔ እየተናገርሁ ሳለሁ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ጥፋት ውስጥ እየወደቁ ነው፡፡ ዛሬ ብቻ በዓለም ሁሉ ብዙ ሰዎች በስጋና በመንፈስ እየሞቱ ነው፡፡ እኛ አሁን የምንፈልገው ነገር ቢኖር ቢያንስ አንድ ተጨማሪ ነፍስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት በመዳን የእግዚአብሄር ሠራተኛ እንዲሆን ነው፡፡ ይህ ዓለም ይበልጥ ክፉ እየሆነ ሲሄድ የጌታ መመለሻ ጊዜ በጣም እንደተቃረበ ማየት እንችላለን፡፡ እንዲህ ባሉት ጊዜያቶች በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመንና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለማሰራጨት ብዙ ጥረቶቻችንን መዘርጋት አለብን፡፡

    በኖህ ዘመን የጻድቃን መንፈሳዊ ሁኔታ የተበላሸ ነበር፡፡ እነርሱ የሰዎችን ሴቶች ልጆች ሚስቶቻቸው አድርገው ወሰዱና በጥንት ዘመን ሃያላን ሰዎች ተብለው የተጠሩ ልጆችን ወለዱ፡፡ ይህ ማለት እነርሱ የዚያ ዘመን የታወቁ ሰዎች ሆኑ ማለት ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ዓለም በመንፈሳዊ ምስቅልቅል ውስጥ ነበር፡፡ እግዚአብሄርም በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ፍርዱን እንደሚያወርድባቸው ነገራቸው፡፡

    በዚህ ቀንና ዘመንም እንደዚሁ የክርስትና አገልጋዮች በመንፈሳዊ ምስቅልቅል ውስጥ እየኖሩ ነው፡፡ እነርሱ ከብዙ ሐሰተኛ ትምህርቶች ጋር በተቀየጠ የእግዚአብሄር ቃል ያምናሉ፡፡ በመንፈሳዊ መልኩ የተበላሸ እምነት በሰው ሰራሽ ትምህርቶች በተቀላቀለ የተጻፈ የእግዚአብሄር ቃል ማመን ነው፡፡ ለጻድቃን ተገቢው ነገር የእግዚአብሄርን ልጆች ብቻ ማግባት ነው፡፡ ነገር ግን በኖህ ዘመን የእግዚአብሄር ሰዎች ማለትም ጻድቃን የሰዎችን ሴቶች ልጆች ማለትም (ዳግመኛ ያልተወለዱትን ሰዎች) ሚስቶቻቸው አድርገው ወሰዱ፡፡ ይህ ሁኔታ ከሰው ሰራሽ የክርስቲያን ትምህርቶች ጋር በተቀየጠው ንጹህ የእግዚአብሄር ቃል ማመንን ይጠቁማል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ጻድቃን በመንፈሳዊ መልኩ ከተበላሹ እነዚህን ትምህርታዊ እምነቶች ሊያገቡ ይችላሉ፡፡ እውነተኛው እምነት በክርስትና ሐሰተኛ ትምህርቶች ከተቀየጠ ያን ጊዜ ጻድቃን በእግዚአብሄር ፊት ልዩ የሚያደርጋቸው ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ነገር ግን ይህ ሆኖ ሳለ እነዚህ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ ታዋቂ መጋቢዎች ሆኑ፡፡ እነርሱ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አያውቁም፤ አያምኑምም፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ሆኑና በበርካታ ሰዎች እውቅና ተሰጣቸው፡፡ እነዚህ ግን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የማያውቁና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ዛሬ በክርስትና ውስጥ እንዲህ ያሉ ብዙ ሰዎች ማግኘት እንችላለን፡፡

    የዚህ ዓለም ፍጻሜ ሲቃረብ መንፈሳዊ ዝቅጠት ጫፍ ላይ ይደርሳል፡፡ ያ በሚከሰትበት ጊዜና እግዚአብሄርም በዚህ ዓለም ላይ የቀረ ምንም ተጨማሪ ተስፋ እንደሌለ ሲወስን ፍርዱን ያወርዳል፡፡ ጻድቃን ባለበት ሁኔታ በተጻፈው ንጹህ የእግዚአብሄር ቃል የማያምኑ ከሆነ እምነታቸው መድከም ይጀምራል፡፡ እንዲህ ያለው ክስተት በኖህ ዘመን በተጨባጭ ሆኖዋል፡፡ አሁንም በዚህ ዘመን እንደዚሁ እንደዚያ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል መሠረት የማናምን ከሆነ መድከም በእውነተኛ እምነታችንን ላይ ፈጥኖ ይመጣል፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ሳናሞግስ በክርስቲያን ትምህርት ለማመን የምንሞክር ከሆነ እምነታችንም እንደዚሁ ይደክማል፡፡ የእምነታችን መድከም የሚከሰተው መንፈሳዊ አሳቦችን ከስጋ አሳቦች ጋር ቀይጠን በምናምንበት ጊዜ ነው፡፡

    ስለዚህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ከተቀበልን በኋላ እምነታችንን እንዴት መከላከል እንደምንችል ማወቁ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ስጋዊ አሳቦቻችን በመሠረቱ ክፉ የመሆናቸውን እውነታ መቀበል አለብን፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በመጣው የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ውስጥ በእምነት የምናድርና ለእግዚአብሄር ጽድቅ የምንኖር ከሆነ መንፈሳዊ እምነት እንደማይደክም ማወቅ አለብን፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልን ብንሆንም ለስጋችንና ለዓለም ብቻ የምንኖር ከሆነ ወዲያውኑ ምስቅልቅል ይወረናል፡፡ በኖህ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1