Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የኩራዙ ተፅኖ
የኩራዙ ተፅኖ
የኩራዙ ተፅኖ
Ebook463 pages2 hours

የኩራዙ ተፅኖ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

በግንኙነቶች ዉሰጥ የሚከሰቱ ስነ-ልቦናዊ ቀውሶችን ያትታል::
በጓደኝነት፣በቤተሰብ በትዳር፣በስራ ቦታ፣ ከሰዎች ጋር ስለሚኖሩን  ሟህበራዊ ትስስሮች እና ሰለሚያጋጥሙን እክሎች፣እንዲሁም በህይወታችን ለውጥ እንዳናመጣ አስረው ስለያዙን  ስነ ልቦናዊ ችግሮች፣መንሰኤ እና መፈሄዎች ላይ ያተኮረ ነዉ::

...እውነታውን የመገንዘብ አቅምሽን  ዝቅ አድርጎ ከሚያይ ወይም ከማይቀበል ራሱን ልክ ለማድረግ ከሚፈልግ ጋዝላይተር፣ከውይይቱ በእርግጠኝነት የምትወስጂው ነገር፣ በትክክል የተከሰተውን ነገር ሳይሆን፣ ''አንቺ ተሳስተሻል እኔ ልክ ነኝ''፣

የሚለውን ድብቅ መልክት ነው።...

 

....የራሳችንን እውነት እንድንፈልግ ወይም እንድንፈጥር ከማበረታታት ይልቅ፣ የራሳችንን ምላሽ ችላ እንድንል እና በገባያ ላይ እየተቸበቸበ ያለውን ማንኛውንም ዓይነት ፈላጎት ወይም አተሳሰብ እንደ እራሳችን እንድንቀበል፣ በሚሊዮን በሚቆጠሩ የተለያዩ ፍላጎቶች፣እንደ ቦምብ እየተደበደብን ነው።...

...እንደማስበው ይህ ነጥብ በጣም ጠቃሚ ነው።እደግመዋለሁ።ምንም  እንኳን ጥቃቅን እውነት ያዘለ ቢሆንም፣መጀመሪያውኑ አላማው ማቁሰል የሆነን ትቺት በፍጹም መስማት የለብሽም።የሆነ ሰው እውነትን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመ እንደሆነ፣የበረራ አስተናጋጆችሽ ከነገሩሽ፣ማዳመጥሽን አቁመሽ፣እራስሽን፣ከውይይት አግልይ።ካልሆነ፣እራስሽን፣በጋዝላይት ታንጎ ለመሳብ እያጋለጥሽ ነው።...

 

 

 

Languageአማርኛ
Release dateMay 27, 2020
ISBN9781716045721
የኩራዙ ተፅኖ

Related to የኩራዙ ተፅኖ

Related ebooks

Reviews for የኩራዙ ተፅኖ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የኩራዙ ተፅኖ - Haile genet

    ጋዝላይቲንግ ከድጡ ወደ ማጡ

    ጋዝላይቲንግ በደረጃ የመስራት አዝማሚያ አለው።መጀምሪያ ላይ፣ በመጠኑም ቢሆን አነስተኛ ነው።-በእርግጥ ላታገኛዝቢውም ትችያለሽ። የወንድ ጓደኛሽ፣የቢሮ ግብዣው/ፓርቲው ላይ፣ሰዓት አሳልፈሽ የመጣሽ፣ ሆን ብለሽ ልታዋርጂው እንደሆነ፣ሲወነጅልሽ፣'የጭንቀት ሰሜት ነው።' ወይም 'በእውን እንዲያ ማለት ፈልጎ አይደለም።' ብለሽ ታልፊዋለሽ። ወይም ምናልባትም፣ዝቅ ላደርገው እየሞከርሁ ይሆን እንዴ ብለሽ መጠራጠር ትጀምሪያለሽ፣ነገር ግን፣እንዲሁ ዝም ብለሽ ታልፊዋለሽ።

    ይሁን እንጂ፣ በመጨረሻ ጋዝላይቲንግ ፣ሃሳቦችሽን ተቆጣጥሮ ስሜቶችሽን የሚጎዳ፣ትልቁን የህይወትሽን ክፍል ይይዛል።በመጨረሻም፣ የራሷ አቋም ያላት፣የራሷ ስሜት ያላት ሰው እንደነበርሽ እንኳ ማስታወስ እስከሚያቅትሽ ድረስ፣ከፍተኛ ዱባቴ፣የስፋ መቁረጥ፣እና የደስታ ቢስነት አረንቋ ውስጥ ትገቢያለሽ ። በእርግጥ በሶስቱም ደረጃዎች ውስጥ ላታልፊ ትችያለሽ፣ነገር ግን፣ለብዙ ሴቶች፣ ጋዝላይቲንግ ከድጡ ወደ ማጡ ነው የሚሄደው።

    ደረጃ አንድ፦ጥርጣሬ

    ደረጃ አንድ የሚገለጸው እምነት በማጣት ነው።ጋዝላይተርሽ ያልተጠበቀ ነገር ይናገራል።-ያ፣መንገድ ጠፋብኝ ብሎ የጠየቀሽ ልጂ፣በእውነት አንሶላ መጋፈፍ ፍልጎ ነው። እና የሰማሽውን ለማመን ያቅትሻል። ያልገባሽ ነገር ያለ ይመስልሻል፣ወይም እሱ ያልገባው፣ወይም ምናልባትም ፣እየቀለደ ይሆናል።አስተያየቱ መሬት የለቀቀ ነው፣ምናልባትም፣እምብዛም ሳትጫኝ ስህተቱን ለማረም ትሞክሪያለሽ።ወይም ምናልባትም፣ዱላ ቀረሽ ንትርክ ውስጥ ትገቢያለሽ፣ነገር ግን፣አሁንም በአቋምሽ የጸናሽ ነሽ።ምንም እንኳን የጋዝላይተርሽን ተቀባይነት ብትፈልጊውም፣አጥብቀሽ መሻት ላይ አትደርሺም።

    ካቲ በዚህ ደረጃ ለብዙ ሳምንታት ቆይታለች።ስለ እሷ እና ስለምታገኛቸው ሰዎች፣ከማንም ጋር እንዳልተዳራች እና ማንም ከእሷ ጋር ለመዳራት እንዳልሞከረ ለማስረዳት ሞክራለች።አንድ አንዴ ካቲ፣ ብራየንን ለማስረዳት እየተቃረበች ያለች ያህል ይሰማታል፣ነገር ግን ብራየን በጭራሽ አልተረዳትም።

    ከዚያም፣መጨነቅ ጀመረች፦እሱ ነው? እሷ ነች? ነገሮች ጥሩ ሲሆኑ፣ ጣፋጭ ይሆናል፣አንድ አንዴ መጥፎ የሚሆነው ለምንድን ነው? እንደሚታየው የደረጃ አንድ መለስተኛ ጋዝላይቲንግ፣የግራ መጋባት፣ የመሽበር፣እና የመጨነቅ ስሜቶችን ይፈጥርብሻል።

    ደረጃ ሁለት፦መከላከል

    ደረጃ ሁለት እራስን በመከላከል ፍላጎት ይገለጻል።ጋዝላይተርሽ፣ እንደተሳሳት ለማረጋገጥ ማስረጃ ትፈልጊያለሽ፣እና በተደጋጋሚ፣የእሱን ተቀባይነት ለማግኘት በከፍተኛ ጉጉት፣አጥብቀሽ ትከራከሪዋለሽ-በአብዛኛው በጭንቅላትሽ/በውስጥሽ።

    ሊዝ፣የደረጃ ሁለት የጋዝላይቲንግ ተጠቂ ነች።የምታስባቸው ነገሮች በሙሉ፣አለቃዋ ነገሮችን እሷ እንዳሰበቻቸው እንዲያይላት ብቻ ነው። ከስብሰባዎች በኋላ፣ከአለቃዋ ጋር ያደረገቸውን እያንዳንዱን ውይይት ደጋግማ ታሰላስለዋለች።ወደ ስራ ስትሄድ-ከጓደኞቿ ጋር ምሳ ሰዓት ላይ፣እንቅልፍ እስኪወስዳት ድረስ፣ልክ እንደሆነች ለማሳየት፣ የምትችልበት መንገድ ማግኘት ትፍልጋለች።ምናልባትም ያኔ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ታገኝ እና ሁሉም ነገር እንደገና ደህና ይሆናል።

    በተጨማሪም ሚሼልም ደረጃ ሁለት ውስጥ ነው።እናቱን ሲበዛ እንደ አርዕያ ስለሚያያት፣የተወሰነ ክፍሉ፣ልክ እንድትሆን ይመኛል።እና ሚሼል እሱ እና እናቱ አለመግባባት ከፈጠሩ በኋላ አሰበ።ሳስበው ትንሽ ስነ-ምግባር ጎድሎኛል። እና እንደዚህ ዓይነት መጥፎ ልጅ በመሆኑ ክፉኛ ተሰማው።ነገር ግን፣ቢያንስ እንደዚህ ዓይነት ጥሩ ያልሆነች እናት እንዳለው መጥፎ ስሜት አልተሰማውም።ክፉ ባህሪዋን ሳይነግራት በእሷ ዘንድ ያለውን ተቅባይነት ለማግኘት መሞከር ሊቀጥል ይችላል።

    በተደጋጋሚ አንድ ነገር ላይ ከተጨነቅሽ፣እና ተስፋ በመቁረጥ የሰዎችን ተቀባይነት በጣም ከፈለግሽ ፣ደረጃ ሁለት ውስጥ እንደሆንሽ ታውቂያለሽ ።የጋዝላይተርሽን ይሁንታ/ተቀባይነት ማግኘትሽን እርግጠኛ አይደለሽም፣ ነገር ግን፣ሙሉ ለሙሉ ተስፋ አልቆረጥሽም።

    ደረጃ ሶስት፦ዱባቴ

    የደረጃ ሶስት ጋዝላይቲንግ-ዱባቴ፣ከሁሉም የከፋው የጋዝላይቲንግ ደረጃ፣ነው።በዚህ ደረጃ ውስጥ ጋዝላይተርሽ ትክክል እንደሆነ ለማሳየት በንቃት እየሞከርሽ ነው።ምክኒያቱም ያኔ ነገሮቹን እሱ እንዳለው በማድረግ፣በመጨረሻ የእሱን ተቀባይነት ለማግኘት ትችይ ይሆናል።ደረጃ ሶስት አድካሚ ነው።በአብዛኛው ለመጨቃጨቅ ሃይል ያጥርሻል።

    የእኔ ታካሚ የሆነችው ሜላኒ፣ሙሉ ለሙሉ በደረጃ ሶስት ጋዝላይቲንግ ውስጥ ነበረች።ሜላኒ እድሜዋ ወደ 35 ዓመት የሚጠጋ፣በአንድ ታዋቂ የኒዮርክ የማስታወቂያ ድርጅት ውስጥ፣በሽያጭ ትንተና ባለሞያነት የምትሰራ ተወዳጅ ሴት ናት።መጀመሪያ ወደ እኔ እንደመጣች አካባቢ፣ በከፍተኛ የአስተዳደር እርከን ላይ ያለች ሰራተኛ አልመሰለችኝም(ናት ብየ አልገመትኩም)።ቅርጽ አልባ በሆነው ሹራብ ታፍጋ፣በድካም እየተንቀጠቀጠች ፣እምባዋን መቆጣጠር አቅቷት፣ከሶፋው ላይ ቁጭ አለች።

    ይህን ጉብኝት እንድታደርግ የቀሰቀሳት አጋጣሚ ወደ አንድ የገበያ መደብር ያደረገችው ጉዞ ነበር።በዚያ ምሽት ለባሏ እና ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለምታዘጋጀው ድግስ/ፓርቲ፣የሚያስፈልጓትን ሽቀጣ ሽቀጦች ለመሽመት በመደብሩ መተላለፊያዎች ላይ፣እና ታች ስትጣደፍ ነበር።ጆርዳን፣ልዩ የተጠበስ ስጋ እና ሳልመን(የትልቅ ዓሳ ስጋ ዓይነት ነው)፣ጓደኞቹ ለጤናቸው የሚጠነቀቁ ዓይነቶች ስለሆኑ፣'ዋይልድ ሳልመን'(ከውቅያኖስ የተገኘ) እንድታዘጋጅ አስጠንቅቆ ይነግራታል።ነገር ግን፣ ሜላኒ፣ወደ መደብሩ ስትሄድ ያለው ከውቅያኖስ የተሰገር ሳልመን ሳይሆን በእርባታ ያደገ ሳልሞን ብቻ ነው።ሁለት ምርጫዎች አሏት፦ዝቅተኛውን ሳልመን መግዛት ወይም ሌላ የእቅድ ለውጥ ማድረግ።

    መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ። እምባዎቿ ሲገቱ ነገረችኝ።የማስበው ነገር በሙሉ እንዴት ጆርዳን እንደሚበሳጭ ነው።ሳልመን ማግኘት አልቻልኩም ብየ ስነግረው፣ፊቱ ላይ ያየሁት ገጽታ እዛ ያልነበረ ነው። የምጋፈጣቸው ጥያቄዎች፦አስቀድመሽ ለመሄድ አላሰብሽም ነበር ሜላኒ? ይህን ምግብ ከዚህ በፊት ሰርተሽው ታውቂያለሽ፣ምን ምን እንደሚያስፈልገው ታውቂያለሽ።የዚህ ምሽት ዝግጅት ግድ አልሰጠሽም ማለት ነው? ለእኔ እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ ነግሬሽ ነበር።ይህን እራት በጥሩ ሁኔታ ከማዘጋጀት በላይ ምን እንገብጋቢ ነገር አገኘሽ? የለም በእውነት ማወቅ እፍልጋለሁ፣ንገሪኝ?

    ሜላኒ በረዥሙ ተነፈሰች እና ናፕኪን/ሶፈት አነሳች። ችግሩ፣እነዚህ ጥያቄዎች ማቆሚያ የላቸውም።ስቄ ለማለፍ እሞክራለሁ፣ለማስረዳት፣ ይቅርታ ለመጠየቅም ቢሆን፣ለምን አንድ ነገር እንደማይሰራ ላስረዳው ሞክሬአለሁ፣ነገር ግን፣አያምነኝም። በሶፋው ላይ ትንሽ ዝቅ ብላ ተንሽራተተች እና ሹራቧን በዙሪያዋ አጥብቃ ሳበችው።ምናልባት እሱ ልክ ነው።በጣም ሁሉንም ነገር በስርዓት የማስኬድ፣ነገሮችን በብቃት የምስራ ሰው ነበርኩ።እንዴት እንደተመሰቃቀልሁ ለእኔ ለራሴ ይታወቀኛል።አንድን ነገር በትክክል ማድረግ እንዴት እንደተሳነኝ አላውቅም።በቃ አልቻልኩም።

    ሜላኒ የጋዝላይቲንግ ተጽኖ የመጨረሻው ደረጃ ምሳሌ ናት።ጋዝላይተሯ ስለ እሷ ያለውን አሉታዊ አመለካከት ሙሉ ለሙሉ አምና የተቀበለች እና እውነተኛ ማንነቷን ለማግኘት የተሳናት ዓይነት ሴት ናት።በተወሰነ ደረጃ ሜላኒን ልክ ነች።ጋዝላይተሯ በተደጋጋሚ፣እራሷን መከላከል የማትችል፣ ችሎታ የሌላት፣ ነሽ እያለ የሚላትን ሰው፣ሆናለች። ባለቤቷን፣ ከመጠን በላይ ከፍ አድርጋ ታየዋለች፣እናም በእሱ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት አጥብቃ ትሻለች።ባላደረገችው ነገር እንኳን ሲወነጅላት፣እሱ ባለው ነገር ትስማማለች።-በዚህ አግባብ ለድግሱ/ለፓርቲው ግዴለሽ መሆኗ ነው-።ጆርዳን ልክ ነው ብሎ መስማማት እና እጅ መስጠቱ፣ተገቢ ያልሆነ ባህሪ እያሳየ ነው ብሎ፣እውነታውን ከመጋፈጥ ይልቅ፣በጣም ቀላል ነው። የሙሉነት ስሜት እንዲሰማት፣ምናልባትም፣ክእሱ አጥብቃ የምትፈልገውን፣ ወይም ያስፈልገኛል ብላ ያሰበችውን፣በሙሉ ልብ ቋሚ ተቀባይነትን ላታገኝ ትችላለች።

    የጋዝላይቲንግ ሶስት ደረጃዎች፦

    ጠመዝማዛ መንገድ

    የጋዝላይቲንግ ሶስት ደረጃዎች፣በምንም ዓይነት መልኩ የማይቀየሩ ናቸው? አንድ አንድ ሰዎች፣ህይወታቸውን በደረጃ አንድ ይገፋሉ።ወይ በአንድ ተመሳሳይ ግንኙነት ውስጥ አልያም፣በተደጋጋሚ በሚያናድድ የፍቅር ግንኙነት፣ጓደኝነት፣ወይም የስራ ሁኔታ ውስጥ፣ራሳቸውን ሁሌም ነገ ጠባ፣በተመሳሳይ ጭቅጭቅ ውስጥ ሆነው ያገኙታል። እና ግንኙነቱ መራር እየሆነ ሲሄድ በቀላሉ ያፈርሱታል።ከዚያም፣ተጣድፈው እየሮጡ ወጥተው ሄደው፣ሌላ ጋዝላይተር ያገኙ እና ኡደቱ እንደገና ይደገማል።

    አንድ አንድ ሰዎች የደረጃ ሁለትን ጋኔል ያለማቋረጥ እየታገሉ ነው። አሁንም መንቀሳቀስ ይችላሉ፣ነገር ግን፣ስሜቶቻቸው እና ሃሳቦቻቸው በጋዝላይቲንግ ግንኙነት ተውጠው ያለቁ ናቸው።ሁላችንም ምናልባትም አንድ፣ስለ እብድ የሆነው አለቃዋ፣ወይም ነጭናጫ እናቷ፣ስሜት አልባ ከሆነው የወንድ ጓደኛዋ ውጭ ስለምንም ነገር ያማታወራ የሴት ጓደኛ ኖሮን ያውቃል።ከደረጃ ሁለት ውስጥ መውጣት አቅቷት፣ያን አንድ ንግግር ያለማቋረጥ ትደጋግማለች።ምንም እንኳን ሌሎች ግንኙነቶች አሪፍ ቢሆኑም፣ጋዝላይቲንግ ሁሉንም ነገር ይመርዘዋል።

    አንድ አንዴ ጥንዶች፣በተለይ በደረጃ ሁለት፣ግንኙነቶች ውስጥ ያሉት፣የጋዝላይተርነትን ሚና እየተፈራረቁ ይወስዳሉ።ወይም ሙሉ ለሙሉ ሚና ይቀያየራሉ።ለምሳሌ፦ደስ የማይልሽ ነገር ሲያደርግ ወይም ሲናገር በእውነት ምን እያለ እንደሆነ በመንገር፣ የህይወት አጋርሽን ስለ ስሜታዊ ጉዳዮች፣ጋዝላይት ለማድረግ 'ፍቃድ' ሊኖርሽ ይችላል።

    ይህ በእንዲህ እያለ እሱ፣በማህበራዊ ግንኙነቶችሽ ውስጥ ስለ ባህሪዎችሽ-በጣም ብዙ ታወሪያለሽ ብሎ፣በመወንጀል ወይም፣እንግዶችን የፖለቲካ አቋሟን በመተንተን፣ምቾት ትነሳለች በማለት፣ ገደብ ለመጣል ወይም ህግ ለመደንገግ ‘ሊፈቀድለት’ ይችላል።በተለያዩ  ርዕሶች ላይ ቢሆንም፣ ሁለታችሁም ልክ ለመሆን ወይም የሌላውን ተቀባይነት ለማግኘት እየጣራችሁ ነው።

    አንድ አንዴ ጋዝላይቲንጉ ከመጀመሩ በፊት፣ግንኙነቱ፣ለወራት፣አመታት ድረስ በሰላም ይቀጥላል።ምናልባትም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ-በመንገድሽ ላይ የሚያጋጥሙ አባጣ ጎርባጣ-ምቾት የማይሰጡ-የጋዝላይቲንግ አጋጣሚዎች ሊኖሩ ይችላሉ።ይሁን እንጂ፣ግንኝነቱ ጤናማ ነው።ከዛም ባልየው ከስራ ይፈናቀላል፣ወይም ጓደኛው ከትዳሩ ይለያያል፣ወይም እናትየዋ በእርጅና ምክኒያት ነጭናጫ ትሆናለች፣እና ጋዝላይቲንጉ በቅንነት ይጅምራል።ምክኒያቱም ጋዝላይተሩ አዳጋ ውስጥ የሆነ የሚመስለው ያኔ ስለሆነ ነው።ስለዚህ እንደገና ሃይል እንዲሰማው ጋዝላይቲንጉን ይጀምራል።ወይም ምናልባት አንቺ አዳጋ ውስጥ የሆንሽ ያህል ይሰማሻል እና በድንገት የጋዝላይተርሽን ተቀባይነት ለማግኘት፣ አጥብቀሽ መሻት ትጀምሪያለሽ።ያንቺ ተስፋ መቁረጥ/እጥብቆ መሻት፣የአቅመቢስነት ስሜት እንዲሰማው ያደርገዋል።ስለ አንድ የሆነ ነገር ልክ እንደሆነ እና አንቺ እንደተሳሳትሽ በማሳመን ሃይሉን እንደገና ያረጋግጣል።ስለዚህ ጋዝላይቲንጉ ይጀምራል።

    አንድ አንዴ፣ለአመታት፣አንቺን ሳይሆን እጮኛዋን፣ልጇን፣ወይም ሌላ ጓደኛዋን ጋዝላይት ያደረገች የሴት ጓደኛ ይኖርሻል።በዚያ በነበረችበት ግንኙነት ውስጥ ምን ሲካሄድ እንደነበረ ባለማገናዘብ ከእሷ ጎን ቆመሽ ይሆናል።ያኛው ሰው እንዴት መጥፎ ባህሪ እያሳየ እንደነበር፣ከእርሷ ጋር ጥምረት ፈጥረሻል።ከዚያ ባለቤቷ ትቶ ይሄዳል፣ልጁ ያድጋል ወይም ወይም ሌላኛው ጓደኛዋ ምዝበራው ይሰለቸዋል፣እና በድንገት ከአንቺ ውጭ ጋዝላይት የምታገርገው ሰው ታጣለች።የቅሬታዎቿ እና የሃዘኗ ተካፋይ ስለነበርሽ፣አሁን እንዴት ጥሩ ባልሆነ መንገድ እያስተናገደቺሽ እንደሆነ ከመረዳትሽ በፊት፣ሳምንታት ወይም ወራት ይወስድብሻል።

    ወደ ጋዝላይቲንግ ግንኙነቶች መጀመሪያውኑም፣ከመግባት በላይ፣ ለአመታት እምነት በጣልሽበት ሰው ጋዝላይት መደረግ በጣም የሚያዳክም ሆኖ ታገኝዋለሽ።ምክኒያቱም እምነትሽ የጸና መሰረት ያለው ነው።እራስሽን ጥሩ ባልሆነ መንገድ እያስተናገዱሽ እንደሆነ ስትረጂ፣ በጣም ግራ የሚያጋባ ይሆናል።እናም ምናልባትም፣እራስሽን ይበልጥ ለመውቀስ ልትገደጂ ትችያለሽ።ችግሩ እንዴት የእሱ ሊሆን ይችላል? ያንቺ መሆን አለበት።

    በእነዚህ በየትኛወቹም አጋጣሚዎች ጋዝላይቲንግ በደረጃ አንድ ወይም በደረጃ ሁለት ላይ ሊቆይ ይችላል።ወይም በሁለቱም መካከል እየተፈራረቀ ሊቆይ ይችላል-እና በቂ የሆነ ህመም ይፈጥራል።ይሁን እንጂ ጋዝላይቲንግ ወደ ደረጃ ሶስት ሲቀጥል ውጤቱ በጣም አስደንጋጭ ሊሆን ይችላል።በዚህ ደረጃ፣ጋዝላይቲንግ፣ያለ ካርታ እና በጉልህ የሚታይ ጠቋሚ ምልክት በሌለበት በማይታወቅ በረሃ፣ግራ ተጋብተሽ እንደምትንቀዋለይ እና ትንሽ እንኳን ውሳኔ መወሰን እስኪሳንሽ ድረስ፣ተስፋ ቢስ፣እራስሽን መከላከል የምትችይ አቅመቢስ እና ደስታ አልቦ አድርጎሻል።

    የጋዝላይቲንግ ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት፣ማን እንደነበርሽ እንኳን አታስታውሽም።የምታውቂው ነገር ቢኖር የሆነ ነገር ክፉኛ እንደጎደለ ነው።ምናልባትም ችግሩ ከእናቺ ጋር ነው።በዚያ ላይ፣በእውነት ጥሩ ሰው ብትሆኝ፣ተፎካካሪ ሰው ብትሆኝ በጋዝላይተርሽ ዘንድ ተቀባይነት ታገኝ ነበር።አይደለም?

    በዚህ ስርዓተ-ጥለት ትግል ውስጥ ያሉ፣ከደርዘን በላይ የሆኑ ሴቶችን፣ህክምና ከሰጠሁ እና በእኔ በራሴ ላይ ተከስቶ ካስተናገድሁት በኋላ፣የጋዝላይቲንግ ተጽኖ በእውነት ነፍስ የሚያመሳቅል እንደሆነ እውነቱን አረጋግጫለሁ።ምንልባትም እጅግ አስከፊው አጋጣሚ፣ከእራስሽ ጥሩ ገጽታ ወይም እውነተኛ ማንነት እንዴት እርቀሽ እንደመጣሽ ስታገናዝቢ ነው።በራስ የመተማመን ስሜትሽን አጥተሻል፣ለራስሽ ያለሽን ዋጋ አጥተሻል፣የራስሽን አመለካከት/ገጽታ አጥተሻል፣ድፍረትሽን አጥተሻል፣እና ከሁሉም የከፋው ደስታሽን አጥተሻል።ለአንቺ ዋጋ የሚሰጥሽ ነገር በጋዝላይተርሽ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ብቻ ነው፣እና በደረጃ ሶስት ይህን ማድረግ እንደማትችይ መረዳት ትጀምሪያለሽ።

    ሶስት ዓይነት ጋዝላይተሮች

    ጋዝላይቲንግ በብዙ ዓይነት መንገድ ነው የሚመጣው።አንድ አንዱ ምዝበራ/ጥቃት ነው የሚመስለው።ነገር ግን፣የህይወት አጋርሽ እንደ ጥሩ ሰው ወይም አፍቃሪ እንደሆነ መስሎ የሚቀርብበት አጋጣሚ አለ።ስለዚህ ጋዝላይቲንግ ሊይዛቸው የሚችላቸውን ቅርጸቶች እና የተወሰኑ ምሳሌዎች ልስጥሽ።

    ማራኪ ጋዝላይተር፦ላንቺ ልዩ የሆነ ዓለም ሲፈጥርልሽ

    ምንም እንኳን ብዙ መልዕክቶችን ብትተይለትም፣ጓደኛሽ ለሁለት ሳምንት አልደወለልሽም ብለን እናስብ።ሲመጣ የምትወጃቸውን ትልቅ የአበቦች ስጦታ ፣ ወድ የሻምፓኝ ጠርሙስ፣እና በሳምንቱ መጨረሻ ከከተማ ወጣ ብላችሁ ለመዝናናት የሚያስችላችሁ ትኬት ይዟል።በጣም ተናደሽ እና ተስፋ ቆርጠሻል።የት ነው የነበረው? ለምንድን ነው ስልኮችሽን ያልመለሰለሽ? ነገር ግን፣ሳይነግርሽ በመጥፋቱ፣ጥፋተኛ እንደሆነ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን፣ይልቁንም አሁን ያዘጋጀውን፣የፍቅር ሽርሽር አብረሽው እንድትሄጂ ጫና እያሳደረብሽ ነው።ልክ እንደ ሁሉም ጋዝላይተሮች፣እውነታውን በመሽፋፈን፣ መሽፋፈኛውን እንድትቀበይ እያደረገ ነው።ልክ ፣ለመናደድሽ ምክኒያታዊ ያልሆንሽ አንቺ እንደሆንሽ ለማስመሰል፣ከተለመደው ውጭ ምንም ነገር ያላደረገ ለመምሰል እየጣረ ነው፣ነገር ግን፣ማራኪነቱ እና ፍቅሩ መጀመሪያ ላይ እንዴት ባህሪው ተገቢ እንዳልነበር እና አሳዛኝ ሆኖ እንዳገኘሽው ሊሽፋፍነው ይችላል።

    ማራኪ ጋዝላይተር የምለው ይህን ነው።አንድ አንድ ወንዶች፣ በእንደዚህ ዓይነት ጋዝላይቲንግ ያለማቋረጥ ተጠምደው ታገኛቸዋለሽ። ሌሎች ልክ እንደ ካቲ ፣ተቆጣጣሪ ፍቅረኛ፣ብራየን፣ያሉት እንደዚህ ዓይነቱን የመማረክ እንቅስቃሴ፣ምናልባትም ለየት ካለ የሚያናድድ ጥል በኋላ፣አልፎ አልፎ ሊሞክሩት ይችላሉ።በሁለቱም አቅጣጫ ማራኪ ጋዝላይቲንግ ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል።

    የሆነ ነገር ልክ እንዳልሆነ ታውቂያለሽ፣ነገር ግን ፣የፍቅር ግንኙነቱን ትወጂዋለሽ።ስለዚህ ችግሩ እንዳለ ልታሳምኝው ካልቻልሽ፣ሁሉም ነገር ልክ እንደሆነ፣ከእሱ ጋር መስማማት ትጀምሪያለሽ።

    ከማራኪ ጋዝላይተር ጋር የነበረኝን፣የራሴን ግንኙነት ዞር ብየ ስመለከት፣ በአለም ላይ ያሉ ብቸኛ እድለኛ ፍቅረኞች የሚያገኙት አስደሳች ህይወት ውስጥ እንደገባን ያህል ስሜት እንዲሰማኝ በሚያደርግ ምህታታዊ ድግምት ውስጥ እንደወደቅሁ ይሰማኝ ነበር።በግንኙነቶች መጀመሪያ ላይ፣ጋዝላይተሩ በአብዛኛው ደስ የሚልበት ምርጥ ደረጃ ላይ ነው።በኋላ ላይ ችግር የሚፈጥሩት ጥሩ ባህሪዎቹ፣በዚህ ለጋ ደረጃ ላይ፣የመጀመሪያ ደረጃ ተጽኖ እንዲያደርግ ይረዱታል።በአለም ላይ ያለች ምርጥ ሴት፣በህይወቱ የተረዳሽው ብችኛ ሴት፣እና የለወጥሽው ምህታታዊ ልዕልት፣እንደሆንሽ እንድታውቂ ያደርጋል።እሱም ያንቺን ህይወት እቀይራለሁ ይላል ወይም በፍቅር እንደሚያጥብሽ፣ምርጥ ምርጥ ቦታዎች እንደሚወስድሽ፣በስጦታዎች ብዛት፣በታማኝነት ኑዛዜ፣ወይም ወሲባዊ ክትትል፣ከዚህ በፊት አይተሽው በማታውቂው መልኩ ጮቤ እንደሚያስረግጥሽ ቃል ይገባል።

    ድንቅ እና ልዩ የሆንሽ፣የአብሮነት ስሜት ይሰማሻል፣ያበራል እና አንቺም አብረሽው ታበሪያለሽ።በፍቅር መውደቅ ምህታታዊ ይሆናል ብለው ለሚያስቡ ሴቶች-እና ከመሃላችን፣ማን ነው ይህን አንድ አንዴ አንደማይሆን የሚያምነው?-ምክኒያቱም ምህታቱን የመፍጠር አቅሙ፣ተስጦው ስለሆነ፣ ማራኪው ጋዝላይተር ምርጡ ወይም ተወዳጁ ሰው ይሆናል።

    ደህና፣ስለዚህ በዚህ ምስል ውስጥ ችግሩ ምንድን ነው? እርግጥ ነው በፍቅር መውደቅ ምህታታዊ ተሞክሮ ሊሆን ይችላል፣እና እኔ ይህን አዲስ ፍቅር ከማጣጣም የማደናቅፋቹ፣የመጨረሻው ሰው ብሆን እመርጣለሁ።ይሁን እንጂ አንድ አንዴ፣ይህን  'ምህታት' በመፍጠር የተካኑ ወንዶች፣በዋነኛነት ‘የግንኙነቱን ጽንሰ ሃሳብ’ የሚወዱ ወንዶች ናቸው።’ድራማዊ’ መድረካቸውን ለማዘጋጀት ብዙ ልምምድ አድርገዋል። የጎደላቸው መሪ ተዋናይት ነው።እና አንቺን ሲያገኝ፣ ምናልባትም የፊልም ጽሁፍ ነው የሰጠሽ።እና በጥድፊያ ወደ ዝግጅቱ እንድተገቢ ነው የተደረግሽው።ምርጥ ሬስቶራንቶች፣የፍቅር ትዕይንቶች፣የወዳጅነት ጊዜዎች፣ወሲቡ-ይህ ለተወሰነ ጊዜ አጓጊ ይሆናል።ይህ ሰው መሪ ተዋናይ መሆን የሚወድ ሰው ነው።

    በመጀመሪያው የመማረክ/የውበት ወቅት እንኳን፣ሌላው ግንኙነት ማራኪ ስለሆነ ብቻ፣አንድ አንድ፣ችላ የምትያቸው፣ችግሮችን ማየትሽ አይቀርም።ለምሳሌ፣ካቲ እና ብራየን ለመጀመሪያ ጊዜ የፍቅር ግንኙነት ሲጀምሩ፣ካቲ የብራየንን የፍቅር አኳኋን ወዳዋለች፦አበቦችን በሚያመጣበት ጊዜ፣እግሮቿን ማሳጅ በሚያደርግበት ጊዜ-ነገር ግን፣በተደጋጋሚ በጣም የዋህ/ቂል እና ተዳሪ እንደሆነች በመወንጀሉ፣መረበሿ አልቀረም።ይሁን እንጂ፣የፍቅር እንክብካቤውን ስለወደደችው፣ውንጀላዎቹን ያን ያህል ጠቃሚዎች አይደሉም ብላ እራሷን አሳምናለች።ብራየን በደምብ እያወቃት ሲሄድ ይጠፋሉ ወይም ምናልባትም እሷ መጀመሪያውኑም የተሳሳተ ግንዛቤ ይዛ ይሆናል።

    በሌላ የጋዝላይቲንግ ግንኙነት፣የመጀመሪያው እንከን እስኪፈጠር ድረስ-ለመጀመሪያ ጊዜ ባልሰራሽው ስራ እስኪወነጅልሽ እና እንድትስማሚ እስኪጠብቅ ድረስ-ሁሉም ነገር በእውነት ምርጥ ሊሆን ይችላል።በዚያ የፍቅር ወላፈን ውስጥ፣ለሳምንታት ለወራትም ቢሆን፣ ለሁለት ሳምንት በመጥፋቱ እና ስልኮችሽን ባለማንሳቱ በመበሳጫትሽ፣ እስኪወነጅልሽ ወይም ጥፋተኛ እስኪያደርግሽ ድረስ፣ልትቀጥይ ትችያለሽ።ይሁን እንጂ፣ በዚያን ወቅት፣በፍቅሩ ውስጥ ተጠምደሻል።ምንም እንኳን፣መጥፎ ባህሪውን ወይም ጋዝላይት ማድረጉን ባትወጂውም፣ያን የመጀመሪያውን ወላፈን እንደገና ለማግኘት በመጓጓት፣ግንኙነቱን የሙጥኝ ትያለሽ።

    በእነዚህ ማራኪ ጋዝላይተሮች የደረሰባትን፣እያደገ የመጣ ምቾት ማጣት፣ አንድ ታካሚየ ስትገልጸ እየሰማኋት፣እራሴን የበረዶ ሉል ምስል ላይ አፍጥጨ አገኘሁት።-የሚያምር እና ተሰባሪ የሆነ ዓለምን በዙሪያው የያዘ የጠርሙስ ኳስ።ሉሉ፣ብትንትኑ እስኪወጣ ድረስ ያምራል።ሲበታተን ሙሉ ዓለሙ ይጠፋል፣እና መልሶ እንደነበር ለማድረግ የሚያስችል ምንም መንገድ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1