Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት
መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት
መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት
Ebook218 pages2 hours

መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

መጋቢዎች መልካም በሆኑ ዜናዎች ምእመኖቻቸውን ለማነቃቃትና ለመመሰጥ ግፊት አለባቸው፡፡ የመስቀሉ መልእክት እስኪጠፋ ድረስ የህዝቡ ግፊት የክርስቶስ ቃል እንዲወሳሰብ ምክንያት ሆኗል፡፡ ዛሬ ክርስቶስን ለ"ማግኘት" "መጐዳት" እንዳለብን ወደሚያሳየን ወደ ክርስትና መሰረት እንመለሳለን፡፡ መሠዋት፣ መከራ መቀበልና ለክርስቶስ መሞትን ስንሰብክ ኃይል ወደ ቤተክርስቲያን ይመለሳል፡፡ ማንም ስኬታማም ሆነ ኃይለኛ የሆነ ሰው የክርስቶስን ቃሎች ኃይል ሊደመስሰው አይችልም፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954393
መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት

Related ebooks

Reviews for መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት - Dag Heward-Mills

    መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበል እና መሞት

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ትርጉም፡- ደረጄ በቀለ

    አርትዖት፡- እስራኤል ጥበቡ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    Find out more about Dag Heward-Mills at:

    Healing Jesus Campaign

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-61395-439-3

    Write to:

    Dag Heward-Mills

    P.o.Box 114

    Korle-Bu

    Accra

    Ghana

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    ስልክ + 251912063821

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው።

    ማውጫ

    አራቱ መንፈሳዊ ቀጠሮዎች

    ለክርስቶስ እንዴት መክሰር እንደሚቻል

    የማጣት ጥበብ

    ሁለቱ የማጣት መንገዶች

    እግዚአብሔር መከራ እንድትቀበል የሚፈልግበት ምክንያት

    በክርስቶስ ሥቃይ አማካይነት ምን እንደምታከናውን

    መሥዋዕትነት እንዴት ኃይልን እንደሚለቅቅ

    የመሥዋዕት ጠላቶች

    የመሥዋዕት ምትክ

    መሥዋዕት ለፍሬያማነት ዓይነተኛ ቁልፍ ነው

    መሥዋዕትነት ወደ ቅባት ያመጣሃል

    መሥዋዕት ፈረዖንን ያስወግዳል

    መሥዋዕትነት በአገልግሎት ስፍራህን ይሰጥሃል

    መሥዋዕት ክብሩን ወደ አገልግሎትህ ያመጣል

    መስቀል - የሞት ተምሣሌት

    መስቀልን መስበክ የሚገባህ ምክንያት

    መስቀልህን ለምን መሸከም እንዳለብህ

    ምዕራፍ 1

    አራቱ መንፈሳዊ ቀጠሮዎች

    ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም ያራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ÷ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

    ሉቃስ 14፡26

    ኢየሱስን መከተል ቀላል አይደለም። ለኢየሱስ መኖር ቀላል አይደለም። ሐሰተኛ የክርስትና ትርጉም ወደ አንተ የሚያመጣን ማንንም ሰው አትመን። ክርስትና ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን መከተልና ክርስቶስን መምሰል ነው!

    ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዝሙር ስለ መሆን የተናገራቸውን ነገሮች ስትመለከት ማንም እርሱን እንዲከተል የሚፈልግ አይመስልም። እርሱን ለመከተል ሙከራ ላደረጉት የተለያዩ ሰዎች ወደ እርሱ መምጣት ስላለው አደጋ አስጠንቅቋቸዋል።

    ኢየሱስ ያስጠነቅቀናል

    ወደ እኔ ከመጣህ ወላጆችህን፣ ቤተሰብህንና ራስህን መጥላት አለብህ ብሏል። (ሉቃስ14፡26)

    እርሱን ለመከተል ለፈለገው ባለጸጋ እኔን መከተል ከፈለግህ ያለህን ሁሉ መሸጥ አለብህ አለው። (ማቴዎስ 19፡21)

    እንዲሁም የቀበሮዎችና የወፎች ያህል እንኳ የምኖርበት ቦታ ስለሌለኝ እኔን ከተከተልክ የምትኖርበት ቦታ አይኖርህም ብሏል። (ሉቃስ 9፡58)

    እንዲሁም በእርግጠኝነት እኔን መከተል ከፈለግክ ቤተሰብህን መሰናበት አትችልም ብሎአል። (ሉቃስ 9፡61)

    ወላጆቹ ለሞቱበት አንድ ሰውም በእርግጠኝነት ደቀ መዝሙሬ ለመሆን ከፈለግክ በአባትህ ቀብር ላይ ለመገኘት አትችልም አለ። (ሉቃስ 9፡59)

    ኢየሱስ ለማንም መስፈርቱን አይቀንስም

    በእርግጥ ኢየሱስ ነገሮችን ለማንም ለማቅለል አልፈለገም። መሰናከሉን ለማንም ዝቅ አላደረገም። ለማንም ልዩ ድጋፍ አላደረገም። ለሰው ልጅ ተሰጥቶ ወደማያውቀው ወደ ትልቁ ዕድል እየጋበዘን እንደ ሆነ ያውቅ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የመዳን ዕድል፣ እግዚአብሔርን የማወቅ ዕድልና ወደ መንግሥተ ሰማያት የመግባት ዕድል!

    እነዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች በቀላሉ ለእርሱ ድንቅ ፍቅር ምላሽ የሚሰጡ ሚሊዮኖችን አላገዳቸውም። ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ለመከተል አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያስቀመጠ ቢሆንም ሚሊዮኖች ይወዱታል።

    ለማንኛውም፣ ሕያው እግዚአብሔርንና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ለሚያጋጥሙን መከራዎች ከበቂ በላይ የሆነ ማካካሻ ነው።

    ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል መባረክ፣ ሀብታም መሆንና ስኬት ማግኘት ነው ብሎ የሚልህን ማንንም ሰው አትስማ። ያ ክርስትና አይደለም። ክርስትና መጐዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበልና መሞት ነው።

    በሁሉም ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሱ ችግሮችና መከራዎች በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ሊመደቡ ይችላሉ። እነርሱም መጎዳት፣ መሠዋት፣ መከራ መቀበልና መሞት ናቸው።

    እነዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድም ወይም በሌላ መጠበቅ ያለባቸው አራቱ መንፈሳዊ ቀጠሮዎች ናቸው። ማንም በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስን ቢከተል ከእነዚህ ከአራቱ ቀጠሮዎች አያመልጥም።

    የዚህ ተቃራኒ የሆነ ነገር የሚነግርህን ማንኛውንም ሰው ችላ በል! የእንዲህ ዓይነት ሰው ሥራ የሚያሳክከውን ጆሮህን እያከከልህ ነው። በእውነት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሆንህ በአንድ ሁኔታ፣ በአንድ ዓይነት ወይም በሌላ ምናልባትም በሌላ ስም የእርሱን መስቀል ትለማመዳለህ።

    አራቱ ቀጠሮዎቻችን መጎዳት፣ መሥዋዕት መሆን፣ መከራ መቀበልና መሞት ናቸው። እነዚህ ቀጠሮዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው? ከታች የተዘረዘሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በእምነታችን፣ በጥሪአችንና ስለ መንፈሳዊ ዓላማችን ለመጎዳት፣ መከራ መቀበል፣ መሥዋዕት ለመሆንና ለመሞት እንዴት እንደ ተመረጥን ያመለክታሉ።

    ይህ መጽሐፍ እነዚህ ቀጠሮዎች ምን ያህል የእውነት እንደሆኑ ለማሳየት የታቀደ ነው። አንተ እንደምታስበው መጥፎ አይደለም። በመጨረሻም ወደ በረከት ይለወጣል። ከታች እንደ ተጠቀሰው የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እነዚህን ቀጠሮዎች እንዴት በግልፅ እንደዘረዘሩ አስተውል።

    ከማጣትናከመጎዳትጋርያለህቀጠሮ

    ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።

    ማቴዎስ 16÷25

    ነገር ግን ለለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቆጥሬዋለሁ። አዎን÷ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጎዳሁ÷ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ÷

    ፊልጵስዩስ 3÷7-8

    በክርስቶስ ምክንያት ከኪሳራና ከማጣት ጋር ያለን ቀጠሮ ትለማመዳለህ። ስለዚህ ማሰብ ግድ ለሚለው ለማንም ይህ ትልቅ ትርጉም አለው።

    ሀ) ኪሳራ ማለት አንዳንድ ነገሮችን ታጣለህ ማለት ነው። እነዚህን ያጣኻቸውን ነገሮች መልሶ የማግኘት ትንሽ ወይም ምንም ተስፋ ላይኖረው ይችላል።

    ለ) ኪሳራ ማለት የአንዳንድ ነገር መነፈግ ያጋጥምሃል ማለት ነው።

    ሐ) ኪሳራ ማለት ነገሮችን በሕይወትህ ማኖር ወይም ማቆየት አትችልም ማለት ነው።

    መ) ኪሳራ ማለት አንዳንድ ነገሮች ከይዞታህ እንዲወጡ እጅ ትሰጣለህ ወይም ታስረክባለህ ማለት ነው።

    መከራከመቀበልጋርያለህቀጠሮ

    በክርስቶስ ምክንያት መከራ ከመቀበል ጋር ያለ ቀጠሮን ትለማመዳለህ። መከራ መቀበል ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ግድ ለሚለው ለማንኛውም ሰው ይህ ትልቅ ትርጉም አለው። በእውነት እርምጃቸው መከራ የመቀበልን ፅንሰ ሀሳብ የማያካትቱን ሰዎች ችላ በል። ታላላቅ የእምነት ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር በማማነቸው መከራን ተቀብለዋል።

    ሀ) መከራ መቀበል ማለት ለህመም፣ ጭንቀት፣ ኪሣራ፣ ጉዳት፣ ወይም የሆነ ደስ የማያሰኝ ነገር መዳረግ ማለት ነው።

    ለ) መከራ መቀበል ማለት መከራ፣ ጥቃት፣ ችግር እና ሰቆቃን በሕይወትህ ታሳልፋለህ ማለት ነው።

    ሐ) መከራ መቀበል ማለት በመጥፎ ዕድል፣ በጉስቁልና እና በችግር ውስጥ ታልፋለህ ማለት ነው።

    መ) መከራ መቀበል ማለት ሥቃይ፣ መከራና ጉስቁልና ይደርስብሃል ማለት ነው።

    ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤ በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት÷ ያው መጋደል ደርሶባችኋልና።

    ፊልጵስዩስ 1÷29-30

    ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤ በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ÷ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።

    በእውነት ከእናንተ ጋር ሳለን÷ መከራ እንቀበል ዘንድ እንዳለን አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ አንዲሁም ደግሞ ሆነ÷ ይህንም ታውቃላችሁ።

    ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ - ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።

    1ኛ ተሰሎንቄ 3÷2-5

    የደቀ መዛሙርቱን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፡- ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ÷

    የሐዋርያት ሥራ 14÷22

    ከመሥዋዕትነትጋርያለህቀጠሮ

    በክርስቶስ ምክንያት ከመሥዋዕትነት ጋር ያለን ቀጠሮ ትለማመዳለህ። ይህም መሥዋዕት መሆን ማለት በእርግጥ ምን ማለት እንደ ሆነ ለማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ ትልቅ ነገር ነው። እባክህን እንደ ክርስቲያን መክፈል ስላለብን መሥዋዕትነት የማይሰብኩትን ክርስቲያኖች አትስማቸው። መሥዋዕትነት ያለንበት ሃይማኖት አንዱ አካል ነው።

    ሀ) መሥዋዕት ማድረግ ማለት እግዚአብሔርን ለማምለክ ቁሳዊ ሀብትህን ማቅረብ ማለት ነው።

    ለ) መሥዋዕት ማድረግ ማለት የተሸለመን ወይም የሚያስመኝን ነገር ከዚያ በላይ ከፍተኛ ለሆነው ነገር አሳልፎ መስጠት ማለት ነው።

    ሐ) መሥዋዕት ማድረግ ማለት ለአንድ ለሌላ ነገር ብለህ ለመጎዳት ወይም ጥቅም ለማጣት መፍቀድ ማለት ነው።

    መ) መሥዋዕት ማድረግ ማለት ምንም ትርፍ ባታገኝም እንኳን ንብረቶችህን መጣል ማለት ነው።

    እንግዲህ ወንድሞች ሆይ÷ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ÷ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።

    ሮሜ 12÷1

    እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት÷ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ÷ በእርሱ እናቅርብለት።

    ዕብራውያን 13÷15

    ከሞትጋርያለህቀጠሮ

    በክርስቶስ ምክንያት ከሞት ጋር ያለን ቀጠሮ ትለማመዳለህ። አንድ ሰው ይሞታል ማለት ትልቅ ነገር ነው። ኢየሱስ መስቀላችንን ተሸክመን እንድንከተለው የነገረን ለዚህ ነው።

    ሀ) መሞት ማለት የሕልውና መቋረጥና የእንቅስቃሴዎች መቆም ማለት ነው።

    ለ) መሞት ማለት ጥንካሬ ማጣት እና ኃይል ማጣት ማለት ነው።

    ሐ) መሞት ማለት ቀስ በቀስ ማለፍ ወይም ቀስ በቀስ ደብዝዞ መጥፋት ማለት ነው።

    መ) መሞት ማለት ለዘለቄታው መቆም ማለት ነው።

    ለሁሉም እንዲህ አላቸው፡- በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር÷ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።

    ሉቃስ 9÷23

    እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

    ገላትያ 2÷20

    በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ በእናንተ ትምክህት እየማልሁ÷ ወንድሞች ሆይ÷ ዕለት ዕለት እሞታለሁ።

    1ኛ ቆሮንቶስ 15÷31

    ምዕራፍ 2

    ለክርስቶስ እንዴት መክሰር እንደሚቻል

    አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤

    ፊልጵስዩስ 3÷8

    ጳውሎስ እንዳደረገው አንተም ሁሉን ነገር ለኢየሱስ ክርስቶስ ማጣትን መቀበል አለብህ። ጳውሎስ ብዙ ነገሮችን በማጣት ተሰቃይቷል። ካላጣህ አታገኝም። አሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስን በመከተላቸው ሁሉን ነገር አጥተዋል። ሁሉን ትተዋል! ሥራዎቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና ጓደኞቻቸውን ኢየሱስን ለመከተል ሲሉ አጥተዋል። ይህ ለእነርሱ ትልቅ የግል ኪሳራ ነበር። የሆነ ነገር ለማጣት ዝግጁ ካልሆንክ በቀር ኢየሱስን መከተል አትችልም።

    ጴጥሮስም፦ እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ይለው ጀመር።

    ማርቆስ 10÷28

    አገልግሎትህ ለመተው ባልፈለግሃቸው ነገሮች ልክ የተገደበ ነው። ሩጫ ስትሮጥ አንድ ነገር ተሸክመህ ከሆነ በተገቢው ፍጥነት ለመሮጥ አትችልም። እግዚአብሔር ነገሮችን ከኋላችን ትተን እንድንከተለው ይጠብቅብናል። ምናልባት ኢየሱስን ለመከተል እንቅልፋችንን፣ ጓደኝነቶቻችንን፣ ቴሌቪዥኖቻችንን፣ ሙያችንን እና ሥራችንን መተው ይኖርብን ይሆናል።

    ገንዘብህን መሠዋት አለብህ

    ወደ አገልግሎት መግባት የተወሰነ ገንዘብን ማጣትን ያካትታል። ወደ አገልግሎት ስትገባ በገንዘብ አቅጣጫ ትከስራለህ። ብዙ መጋቢዎች ገንዘባቸውን ለአገልግሎት መስጠት እንደሚኖርባቸው አያውቁም። እያንዳንዱ አገልጋይ በግሉ ለአገልግሎት ገንዘብ ማውጣት አለበት ። በእርግጥ የግልህ ገንዘብ ከቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ለብቻው የተለየ ካልሆነ ያንን ማድረግ አትችልም።

    የግልህን ንብረትህ ከቤተ ክርስቲያን ንብረት የተለየ መሆኑ አስፈላጊ ነው። ይህ ልዩነት ግልጽ ካልሆነ ከመስጠት የሚገኘውን በረከት ታጣለህ። ያለህ ነገር ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ንብረት ስለ ሆነ የምትሰጠው ነገር የለህም ማለት ነው። ቀድሞውኑ የቤተ ክርስቲያን የነበረውን ነገር እንዴት ለቤተ ክርስቲያን ትሰጣለህ?

    ምቾቶችህንና የተደላደለ ኑሮህን መሠዋት አለብህ

    የእረፍት ጊዜህን ከጌታ ጋር ለመሆን ካልሠዋህ ምንም እውነተኛ ፍሬ አይገኝም። ብዙ አገልጋዮች ከጌታ በስተቀር ለሁሉ ነገር ጊዜ አላቸው። ለቴሌቪዥን፣ ለጥቅም የለሽ ማህበራዊ ግንኙነት፣ ለኮምፒውተሮች፣ ለንግድና ለስፖርት ጊዜ አለ። ከጌታ ጋር ላለ የግል ሕብረት ግን ጊዜ የለም። አገልግሎትህ ከጌታ ጋር ያለህ የግል ጊዜህ ነፀብራቅ ነው።

    በአገልግሎት ውስጥ ምቾቶችህን ሊወስዱብህ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ። የሕይወትን ትናንሽ ነገሮች

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1