Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ወደኋላ ማፈግፈግ
ወደኋላ ማፈግፈግ
ወደኋላ ማፈግፈግ
Ebook136 pages1 hour

ወደኋላ ማፈግፈግ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ወደኋላ ማፈግፈግ፣ ያልተለመደ ርዕስ ቢሆንም፣ በክርስቲያኖች መካከል ተዘውትሮ ስለሚታይ ክስተት ያስተምረናል፡፡ ብዙዎች ይጀምራሉ፤ እስከፍጻሜ ድረስ የሚጸኑት ግን ብዙዎች አይደሉም፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ደውሉን ያሰማል፣ እንዳንዱ ክርስቲያንም ለምን ለመንግሥተ ሰማይ መብቃት እንዳለበት በግልጽ ያሳያል !

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954270
ወደኋላ ማፈግፈግ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ወደኋላ ማፈግፈግ

Related ebooks

Reviews for ወደኋላ ማፈግፈግ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ወደኋላ ማፈግፈግ - Dag Heward-Mills

    ወደኋላ ማፈግፈግ ምንድን ነው?

    እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርሚያስን እስራኤል እና ይሁዳ በባቢሎን ግዞት ሊማረኩ ባለ ጊዜ አስነሳው። ኤርሚያስን የእስራኤላዊያንን ሕዝብ የልባቸውን ወደኋላ የማፈግፈግ ሁኔታ ለማሳየት ተጠቀመበት።

    ኤርሚያስ፤ ለምን ታለቅሳለህ?

    የኤርሚያስ መጽሐፍ ስለ ወደኋላ ማፈግፈግ ብዙ አይነት ግልፅ የሆኑ ገለፃዎችን ይሰጣል። ኤርሚያስ አልቃሻው ነብይ በመባልም ይታወቃል፣ ብዙ መልእክቶቹ ወደኋላ ማፈግፍግ በሚል ርእስ ላይ ያተኩራል። ብዙውን ጊዜ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ከክፉ ስራቸው እንዲመለሱና ንሰሐ እንዲገቡ በቋሚነት በማስጠንቀቅ ከእነርሱ ጋር ጦርነት ውስጥ ነበር።

    አልቃሻው ነብይ የህዝቡ አስቸጋሪ አስተሳሰብ ያሳስበው ነበር። በተደጋጋሚ አጥብቆ ግድ ይላቸው ነበር፣ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ። ክፉ ማድረግን ተው! ንሰሃ ግቡ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።

    ወደኋላ ማፈግፈግ ምን እንደሆነ በብዙ የተለያዩ መንገዶችን ሊያሳያቸው ሞክሯል። ነገር ግን የእስራኤል እና የይሁዳ ሕዝብ መለወጥን አሻፈረን አሉ።

    ከብዙ አመታት በፊት ከልምምዴ የተማርኩት ወደኋላ ማፈግፈግ አቅጣጫ በማያመላክት መንገድ ላይ መሄድን ይመስላል። በክርስትና መንገዳችን ውስጥ ወደኋላ ማፈግፈጋችንን የሚያስጠነቅቁ ምንም ምልክቶች የሉም። እንዲህ የሚል ምልክት የለም ሲኦል እና ጥፋት -ከ200 ሜትር በኋላ በቀላሉ እንዲህ አይነት ምልክቶች የሉንም! ወደኋላ ማፈግፈግ ራስህን ያጠበከው ቦታ እስክታገኘው ድረስ የሚከሰተው ቀስ በቀስ ነው። ቀስ በቀስ ግን በእርግጠኝነት ትንሸራተታለህ ።

    ወደኋላ ማፈግፈግ እውነት ነው እናም በኤርሚያስ የተገለፀውን የተለያዩ ወደኋላ የማፈግፈግ አይነቶችን በማጥናት ጠንቅቀን ልናውቀው እንችላለን። ነብዩ ይህ የተለመደን መንፈሳዊ ክስተት ለመግለጽ የእውነተኛ ሕይወት ሁኔታን ተጠቅሟል። በክርስትናው አለም ይህ የተለመደ ክስተት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው፡-

    . . . የተጠሩ ብዙዎች ናቸው የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው።

    ማቴዎስ 20፡16

    በሌላ አነጋገር ብዙዎች ከክርስቶስ ጋር ጀምረዋል ግን ብዙዎች ግን ወድቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስም እንደሚል።

    . . . እስከመጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

    ማቴዎስ 10፡22

    ብዙዎች ወደ ክርስቶስ የመጡ በስተመጨረሻው ክደውታል።

    አንተ እንኳን ወደኋላ ልታፈገፍግ ትችላለህ!

    አንዳንዶች ይህን ርዕስ ንቀውት እንዲህ ይላሉ እራሴን ወደኋላ ሳፈገፍግ አይታየኝም ይህች አስተሳሰብ የሚያሳየው ወደኋላ ለማፈግፈግ እጩ መሆንህን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡22 "ስለዚህ የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ብሎ ያስጠነቅቀናል ።

    ይህ መጽሐፍ በክርስትና ሩጫህ ላይ የመጽናት ሐይልህን እንድታዳብር ይረዳሃል። ይበልጥ ባወቅህ መጠን ትድናለህ እናም በይበልጥም የመጽናት ሐይል ይኖርሃል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል፡-

    . . . የእርሱን አሳብ አንስተውምና።

    2ኛ ቆሮንቶስ 2፡11

    ይህ መጽሐፍ የሚሰጠው ትምህርት የአለማወቅ በሽታን ያባርርልሃል። አስታውስ የማያነቡ ሰዎች ማንበብ ከማይችሉ የተሻሉ አይደሉም። በሌላ አነጋገር እውቀትን ለመፈለግ የማይጥሩ ሰዎች ይህን ለማድረግ ችሎታው ከሌላቸው ሰዎች ምንም አይሻሉም።

    በሚቀጥለው ምዕራፍ የማሳይህ ወደኋላ ማፈግፈግን በተለያዩ መንገዶች ማየት የምትችልበትን ነው።

    ምዕራፍ 2

    ስለ ወደኋላ ማፈግፈግ የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫዎች

    ምንጮችን በተቀደዱ ጉርጓዶች መለወጥ

    . . . እኔን የሕያዋን ውሃ ምንጭ ትተዋልና ÷ የተቀደዱትንም ጉድጓዶች ውሃውን ይዩዙ ዘንድ የማይችሉትን ጉድጓዶች ÷ለራሳቸው ቆፍረዋል።

    ኤርምያስ 2፡13

    የህክምና ተማሪ እያለሁ፣ ለስራ ጉብኝት ድንፋ በምትባለው የጋና ገጠር ለሁለት ሣምንት ተላክሁ። በዚህ የስራ ስምሪት ጉዞ ላይ ውሃ ምንም የሌለበትን ሌላ ገጠር አገኝን። ይህ ገጠር ውሃ ስለሌለው ትልቅ ጉድጓድ ቆፍረው ውሃ እንዲያጠራቅም አድርገውታል። ብዙ ጊዜ ይህ ውሃ ቆሻሻና ቡናማ ነው።

    ቆሻሻና ቡናማውን ውሃ ይጠጣሉ!

    በገጠሩ ያሉ ሰዎች ገላቸውን እዚያ ይታጠባሉ ፣ይጸዳዱበታል እናም ይሸኑበታል። ይህንኑ ውሃ ደግሞ ይጠጡታል ለማብሰልም ይጠቀሙበታል። ይህ ውሃ በግልጽ የተለያዩ በሽታዎች እና ህመም አስከትሎባቸዋል።

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደኋላ የሚያፈገፍጉ ሰዎች ልክ ንፁሑን የሚፈሰውን ውሃ ማግኘት የሚችሉበት መንገድ እያለ በቆሻሻ እና በሚሸተው ውሃ የለወጡትን ይመሰላሉ ልክ በዚያ ገጠር እንዳየሁት።

    እርግጠኛ ነኝ አንድ ሰው ለምን መልካሙን እና በበሽታ ከመበከል ነጻ የሚያደርገውን ውሃ ትቶ በምትኩ ቆሻሻውን ለምን እንደሚመርጥ ስታይ ትገረማለህ። እግዚአብሔርን የመምሰል እና የቅድስና ሕይወት እድሉ ያላቸው አማኞች አሉ። ቢሆንም ሐጢያተኝነት እና አጋንንቶች የሚቆጣጠሩት ሕይወት ለመኖር ይህን እድል ገፍተውታል።

    ቆሻሻና ቡናማ ከሆነው ውሃ የተሻለውን እንድትመርጥ እግዚአብሔር እድሉን ሰጥቶሃል። እግዚአብሔር እየነገረህ ያለው ወደኋላ ስታፈገፍግ በሚያስፈራ እና በመጨረሻም በሚገድልህ መንገድ እየሄድክ እንደሆነ ነው። እርሱም የሚነግርህ ጭቃማውን ውሃ እንደገና በመጠጣት ይህን ግራ የሚያጋባ ነገር እዳታደርግ ነው።

    ወደ ክፉ የዱር ወይን ግንድ መለወጥ

    ... አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ ... ?

    ኤርምያስ 2፡21

    ስለ ወደኋላ ማፈግፈግ ቀጣዩ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ጥሩ ስለ ነበረው ተክል እናም ወደ ክፉ እሾሀማ እና እንግዳ ወይን ሆኖ ስለተለወጠው ነው።

    እዚህ ጋር እግዚአብሔር እያሳየን ያለው መልካምን ፍሬ እየጠበቀበት የነበረው የገበሬው ማሳ እንዴት ወደ እሾህና ጥቅም የሌለው አረም ሆኖ እንደተለወጠ ነው። እናንተም አማኞች ጥሩ የሆነው የጌታ ተክሎች ናችሁ። በዚህ ምድር ላይ ራስህን እሾህና ጥቅም ወደሌለው ቁጥቋጦነት ለመለወጥ ለምን ፈቀድክ? ወደኋላ ስታፈገፍግ እንደዚህ ነው እግዚአብሔር የሚያይህ።

    እግዚአብሔር ከእስራኤላዊን ጋር የነበረው ችግር እጅግ ብዙ ፍቅር፣ ጥበቃ፣ ርህራሄ እና ጊዜ በሕይወታቸው ላይ ማፍሰሱ ነበር። ግን የማይታዘዙ ፤ልበደንዳና እና ክፉ ሕዝብ ሆነው ተለወጡ። በእግዚአብሔር ፊት ጥቅም የሌለው ፍጥረት ለመሆን ትፈቅዳለህን? መልሱም በእርግጠኝነት ‹‹አይደለም›› መሆን አለበት!

    የበርሃ ግመል መሆን

    . . .በመንገድ ላይ እንደተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ሆነሻል።

    ኤርምያስ 2፡23

    ወደኋላ ያፈገፈገ ክርስቲያንም በመንገድ ላይ እንደተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ይመስላል። ይህችም በየትም ቦታ የምትኖር የዱርና ፈጣን ፍጡር ነች።

    ወደኋላ ያፈገፈገ ሰው ልብ እንደተለቀቀ እንደ ምድረበዳ ግመል ነው። በማናቸውም ነገር ቁጥጥር ስር አይደለም። የተፈታና መረን ነው። ከተወሰነ አመት በፊት በለንደን አገር ውስጥ ወደኋላ ያፈገፈገ ክርስቲያንን ልጎበኝ መሄዴን አስታውሳለሁ።

    ወዳጄ መረን ወጥቶ ነበር

    ይህን ሰው ልገልፅበት የምችልበት የተሸለ መንገድ የተፈታና መረን ነበር። ወደ ጌታ ልመልሰው እየሞከርኩ ነበር። ቤቱን ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወስዶብኛል። በስተመጨረሻ ከእኩለ ሌሊት በኋላ የሚኖርበትን ፎቅ ደረስኩ። ሲያየኝ ተደነቀና ወደ ቤቱ እንድገባ ጋበዘኝ። መጫወታችንን ስንቀጥል የመጣሁበትን አላማ ተረዳ። ወደኋላ ቢያፈገፍግም በአንድ ወቅት የበሰለ ክርስቲያን ስለነበረ ልጠቅሳቸው ያሰብኩትን ጥቅስ ሁሉ ያውቅ ነበር።

    በንግግሬ ጣልቃ በመግባት እንዲህ አለ:- ምን ለማለት እንደፈለክ አውቃለሁ በዚህ ምሽት ልትለው የምትፈልገውን ጥቅሶች አውቃለሁ ግን ስለምንም ግድ እንደማይለኝ እንድታውቅ እወዳለሁ።

    ከዚያም ሲጋራውን አውጥቶ በፊቴ ማጨስ ጀመረ።

    እንዲህ አለ:- ሳጨስ እድታየኝ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም በምንም ቁጥጥር ስር አይደለሁም።

    ከዚያም አልበሙን አውጥቶ ከሴት ጓደኛው ጋር የተነሳውን ፎቶዎች አሳየኝ። አንዳንድ ፎቶግራፎቹ አሳሳቢና ስሜታዊ ነበሩ።

    እንዲህ አለ:- በእርግጥ የሆንኩትን እንድታየኝ እወዳለሁ። አሁን እንደዚህ ነው ያለሁት። የማደርገውም ይህን ነው። ማንም ሰው ስለዚህ ምንም ማድረግ አይችልም!

    በድጋሚ ሀሳቡን በመግለፅ የፈለኩትን ማንኛውንም ማድረግ የምፈልገውን ነገር ማድረግ እችላለሁ፣እናም ማንም ሰው ሊቆጣጠረው አይችልም። አየህ፣ ወደኋላ ያፈገፈጉ ሰዎች ልክ እንደ በርሃ ግመል ምንም ገደብ እና ድንበር የላቸውም። የክርስትና

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1