Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?
በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?
በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?
Ebook496 pages3 hours

በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

የርዕሱ ዋናው ጉዳይ ‹‹ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ›› ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ለየት ያለ ርዕስ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ መጽሐፍ ዳግመኛ መወለድ ምን እንደሆነና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በጥብቅ በተስማማ መልኩ እንዴት ከውሃና ከመንፈስ መወለድ እንደሚቻል በግልጽ ይነግረናል፡፡ ውሃው በዮርዳኖስ የሆነውን የኢየሱስ ጥምቀት ያመለክታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ይናገራል፡፡ ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪልና የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘር ነው፡፡ አሮን በስርየት ቀን በሚለቀቀው ፍየል ራስ ላይ እጆቹን ጫነና የእስራኤላውያንን አመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ በእርሱ ላይ አስተላለፈ፡፡ ይህ ሊመጡ ያሉ ነገሮች ጥላ ነበር፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት የእጆች መጫን ምሳሌ ነው፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ በእጆች መጫን መልክ ተጠመቀ፡፡ ስለዚህ በጥምቀቱ አማካይነት የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደና ለሐጢያቶች ዋጋ ለመክፈልም ተሰቀለ፡፡ የዚህ መጽሐፍ ቁልፍ ቃል የኢየሱስ ጥምቀትና የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡ ዳግመኛ ልንወለድ የምንችለው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ስናምን ብቻ ነው፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateFeb 8, 2024
ISBN9788965327257
በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?

Related to በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?

Related ebooks

Reviews for በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን? - Paul C. Jong

    paul_Am01_cover.jpgFrontflap_Am01.gif1st_page

    በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን?

    Smashwords Edition

    የታተመው 2015 በሄፍዚባህ ማተሚያ ቤት የታተመ

    ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ባለቤት በጽሁፍ የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር የዚህን መጽሐፍ ማንኛውንም ክፍል ማባዛት ወይም በማንኛውም መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ በኤሌክትሮኒክ ወይም በሜካኒካል ፎቶ ኮፒ ማድረግን ጨምሮ በቅጂ መልክ ወይም መረጃን ይዞ በሚያጠራቅም ወይም መረጃን ይዞ በሚያስቀር ማንኛውም መንገድ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

    ጥቅሶቹ በሙሉ የወሰዱት ከ1954ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    ISBN 978-89-6532-725-7

    ምስጋና

    ጌታ የደህንነትን ቃሎች ስለሰጠንና ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በምንወለድበት ወንጌል ስለባረከን የምስጋና ጸሎት ማቅረብ እንወዳለን፡፡

    ለዚህ ሕትመት በዋጋ የማይተመን አገልግሎቶችን ያበረከቱትን ሬቨረ. ጆን ኬ. ሺንንና እህት ሳንግሚን ሊን ጨምሮ ይህንን መጽሐፍ ለተረጎመችው ለሚስስ ጁንግፒል ሱንግ፣ በሔፍዚባ ፐብሊሺንግ ሐውስ ላሉ ወንድሞችና እህቶች፣ በካንግዎን ናሽናል ዩኒቨርስቲ ላለችው ኤላይን ዳዊና ለኮርያ ታይምሱ ሮስ ዋላስ፣ ለእግዚአብሄር አገልጋዮች በሙሉ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ሁሉም ለዚህ መጽሐፍ በትጋት ሰርተዋል፡፡ እንደገና ምስጋና ለሁላችሁም ይሁን፡፡

    ይህ መጽሐፍና እርሱን የሚያጅቡት የቴፕ ካሴቶች ብዙ ነፍሳቶች ዳግም እንዲወለዱ እንደሚያግዙ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እጸልያለሁም፡፡ ከእኛ ጋር ጠንክረው ለሰሩት ሁሉ እንደገና ልባዊ ምስጋናን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡

    ጌታችን በኢየሱስ በሚያምኑት አማካይነት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድን ወንጌል በመላው ዓለም እናሰራጭ ዘንድ እንዲፈቅድልን ከልቤ እመኛለሁ፡፡

    ጌታን በማይሞት እምነት አመሰግናለሁ፡፡

    PAUL C. JONG

    0Preface.jpg

    መቅድም

    ከውሃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ አለብን፡፡

    እግዚአብሄር በመጀመሪያ ሰማይና ምድርን ሲፈጥር ዘላለማዊ ዓለማትን፣ ገነትንና ገሃነምንም ፈጠረ፡፡ ሰውንም በአምሳሉ ፈጠረ፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያው ሰው አዳም በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያትን ስለሰራ ሰዎች ሁሉ አንዴ መሞት ነበረባቸው፡፡ ‹‹ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደተመደበባቸው፡፡›› (ዕብራውያን 9፡27) 

    የሥጋችን መሞት ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራን መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡ ሐጢያት የሌለባቸው ሰዎች ዘላለማዊ ወደሆነው የሰማይ ዓለም ይገቡና የእግዚአብሄር ልጆች በመሆን ይደሰታሉ፡፡ ሐጢያተኞች ደግሞ ወደ ‹‹እሳቱና ዲኑ ባህር›› (ዮሐንስ ራዕይ 20፡10) ተጥለው ለዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ፡፡  

    ስለዚህ የሰው ልጅ በሙሉ ዳግም መወለድ አለበት፡፡ በእምነቶቻችን አማካይነት ዳግም መወለድ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳንና ጻድቃን መሆን ይኖርብናል፡፡ ዘላለማዊ ወደሆነው መንግሥተ ሰማይ ልንገባ የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› (ዮሐንስ 3፡5) ‹‹ከውሃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ›› ወደ እግዚአብሄር መንግሥት የምንገባበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡    

    ታዲያ ዳግም እንድንወለድ የሚፈቅድልን ይህ ‹ውሃ› እና ‹መንፈስ› ምንድነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹ውሃ› የሚያመላክተው ‹የኢየሱስን ጥምቀት› ነው፡፡ 

    አምላክ የሆነው ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀው ለምንድነው? ትህትናውን ለማሳየት ነበር? ራሱን መሲህ አድርጎ ለማወጅ ነበርን? አልነበረም፡፡

    ኢየሱስ በእጆች መጫን› (ዘሌዋውያን 16፡21) አማካይነት  በአጥማቂው ዮሐንስ ሲጠመቅ ይህ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ያስወገደ የአንድ ሰው የጽድቅ ተግባር› (ሮሜ 5፡18) ነበር፡፡ 

    በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር የመቤዠትን የምህረት ሕግ ለእስራኤል ሰጠ፡፡ ይህ የሆነው በስርየት ቀን በዚያ አመት የተሰሩት የእስራኤል ሐጢያቶች በሙሉ እጆቹን ‹‹በሚለቀቀው ፍየል›› ራስ ላይ በመጫን ሐጢያቶችን ሁሉ ወደዚያ የሚለቀቅ ፍየል ላይ በሚያስተላልፈው ሊቀ ካህን በአሮን አማካይነት ስርየትን ማግኘት ይችሉ ነበር፡፡

    እነዚህ ዘላለማዊውን የስርየት መስዋዕት የሚተነብዩ የመገለጥ ቃሎች ነበሩ፡፡ የሰብአዊ ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በአብ ፈቃድ መሰረት የሰው ሥጋ ለብሶ ወደመጣው ኢየሱስ ለአንዴና ለዘላለም መተላለፋቸውን የሚገልጥ እውነት ነው፡፡ እርሱም የአሮን ዘርና የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡

    ኢየሱስ ሲጠመቅ ለዮሐንስ እንዲህ አለው፡- ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› (ማቴዎስ 3፡15)

    እዚህ ላይ ‹‹እንዲህ› ማለት ጽድቅ ሁሉ ስለ ሁላችን ይፈጸም ዘንድ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ለማስተላለፍ ‹እጆችን መጫን› ማለት ነው፡፡ ‹‹ጽድቅ›› የሚለው ቃል በግሪክ ‹‹ዲካዮሱን› ማለት ሲሆን ትርጉሙም ‹‹እጅግ ያማረ ሁኔታ›› ወይም ‹‹ጻድቅ ወይም ገጣሚ ከመሆን አንደምታ ጋር በጠባይ ወይም በምግባሮች ቀና መሆን›› ማለት ነው፡፡ 

    ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ለሰዎች ሁሉ ቅንና ተገቢ በሆነ ሁኔታ ጽድቅን ሁሉ ፈጽሞዋል፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የሰዎችን ሐጢያቶች በሙሉ ስለወሰደ በሚቀጥለው ቀን አጥማቂው ዮሐንስ እንዲህ በማለት መሰከረ፡፡ ‹‹በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፡- እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡29)

    ኢየሱስ የሰው ልጆችን ሐጢያቶች በሙሉ በጫንቃዎቹ ላይ ተሸክሞ ወደ መስቀል ሄደ፡፡ በጥምቀቱ አማካይነት በራሱ ላይ ለወሰዳቸው ሐጢያቶች በሙሉም ፍርድን በይፋ ተቀበለ፡፡ ‹‹ተፈጸመ›› (ዮሐንስ 19፡30) በማለትም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ በእኛ ፋንታ ሙሉ ፍርድን ተቀበለ፡፡ 

    ውሃው ማለትም የኢየሱስ ጥምቀት የደህንነት ምሳሌ ነው፡፡

    ስለዚህ ‹በኢየሱስ ጥምቀት የሚያምን እምነት› ከሌለን መዳን አንችልም፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ ውሃው ማለትም የኢየሱስ ጥምቀት ‹‹ምሳሌው ሆኖ ያድነናል›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21)

    ዛሬ በኢየሱስ የሚያምኑ አብዛኞቹ ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀት ‹በውሃው› አያምኑም፡፡ የሚያምኑት በመስቀል ላይ ሞቱ ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነቱ እምነት ግን ሐጢያተኞችን ያድናልን? በኢየሱስ ደም ብቻ በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳን እንችላለን? ይህስ ደህንነትን ሊሰጠን ይችላል? 

    አይሰጠንም፡፡ በኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞት ማመን ብቻ በእግዚአብሄር ፊት መዳን አንችልም፡፡

    በብሉይ ኪዳን ዘመን የእስራኤል ሕዝብ የስርየት መስዋዕት ሲያቀርቡ መስዋዕቱን ከመግደላቸው በፊት አስቀድመው እጆቻቸውን በእንስሳው ራስ ላይ ጭነው ሐጢያቶቻቸውን ወደ እርሱ ካላስተላለፉ መስዋዕቱ ትክክል አይሆንም ነበር፡፡ ስለዚህ በጥምቀቱ ሳያምኑ በኢየሱስ መስቀል ብቻ ማመን ስህተትና ሕገ ወጥነት ነው፡፡ 

    ስለዚህ ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡፡›› (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21)

    በኖህ ዘመን በታላቁ ‹ውሃ› (የጥፋት ውሃ) ያላመኑ ሰዎች እንደጠፉ ሁሉ አሁንም ‹በውሃው› ማለትም ‹በኢየሱስ ጥምቀት› የማያምኑ ሰዎች መጥፋታቸው የተረጋገጠ ነው፡፡  

    ወደ እውነተኛ ደህንነት የሚመራን ምሉዕ የሆነው እምነት ‹‹በውሃና በደም በመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ›› (1ኛ ዮሐንስ 5፡6) በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እምነት ነው፡፡ 

    ሐዋርያው ዮሐንስም ትክክለኛው እምነት ‹‹በመንፈሱ፣ በውሃውና በደሙ ምስክርነት›› (1ኛ ዮሐንስ 5፡8) ማመን እንደሆነ ተናገረ፡፡ 

    እውነተኛውን እምነት የሚያዋቅረው እንዲህ ያለ ማመን ነው፡፡ ‹‹ኢየሱስ ራሱ እግዚአብሄር ነው፡፡ እንዲሁም ሥጋን ለብሶ በድንግል ማርያም ሥጋ በኩል ወደ ምድር በመምጣት የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ በዮርዳኖስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ተሸክሞ ወደ መስቀል ሄደ፡፡ ስለ ሁላችንም ይፋ የሆነውን ፍርድ ተቀበለ፡፡ ስለዚህ ወንጌል ያለ ‹‹ኢየሱስ ጥምቀት›› ያለ ‹‹ውሃው›› ምሉዕ ሊሆን አይችልም፡፡ ምንም ያህል በኢየሱስ አጥብቀን ብናምንም ወንጌሉን ሳናምን ከቶውኑም ዘላለማዊ ደህንነትን ማግኘት አንችልም፡፡ 

    እውነተኛው ወንጌል ከቤተክርስቲያን የጠፋበት ታሪካዊ መሰረት፡፡

    በዚህ ዘመን እውነተኛው ‹የውሃና የመንፈስ ወንጌል› እንዲህ ብርቅዬ የሆነውና በምትኩ ሐሰተኛ ወንጌሎች በስፋት በመላው ዓለም የተሰራጩት ለምንድነው?

    ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳና ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ሐዋርያቶች ይህንን ‹የውሃና የደም ወንጌል› አስተማሩ፡፡ አዲስ ኪዳንን በጥንቃቄ ካነበብነው ‹የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል› በግልጽ የሰበኩት ጳውሎስን፣ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ጨምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ብቻ ሳይሆኑ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሐዋርያቶችና ሰራተኞች ሁሉ ነበሩ፡፡    

    ዲያብሎስ ለጊዜውም ቢሆን ወንጌልን ደረጃ በደረጃ ለመለወጥና የሕይወትን ሐይል ከቤተክርስቲያን ለመውሰድ ሲያሴር ነበር፡፡ ስለዚህ በ313 አ.ም ከወጣው የሚላን ድንጋጌ ዘመን ጀምሮ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን በጥንቃቄ በተጠመደው የዲያብሎስ ወጥመድ ተይዛ ነበር፡፡ የሮም ንጉሠ ነገሥት ፖለቲካዊ ሐይሎች ክርስትና የመንግሥት ሐይማኖት ሆኖ እንዲታወቅ በማድረግ በልዋጩ የፖለቲካ መረጋጋትን አግኝተው ነበር፡፡    

    ‹‹ወደ ቤተክርስቲያን የገባውን ሁሉ ማጥመቅ›› የሚለውን በግልጥ በማስቀመጥ የሮም ንጉሠ ነገሥት በተለያዩ ቅኝ ግዛቶች ውስጥ ያለውን አንድነት ጠብቆ አቆየ፡፡

    የሐዋርያቶችን የእምነት መግለጫ ማነብነብ የሐይማኖት ስልጠና መሰረት ሆኖ እንዲተካ የተደረገውም ከእነዚህ ሁኔታዎች የተነሳ ነበር፡፡ በዚያ ምክንያት ‹‹በሐይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙም መረዳት›› (1ኛ ተሰሎንቄ 1፡5) የተሰጠን ‹ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በጥብቅ የሚጣጣመው ወንጌል› ማለትም ‹የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል› በሐሰተኛ ወንጌል ተተካ፡፡ ሰይጣን እንዳቀደውም ማንም ዳግም እንዲወለድ የማይፈቅደው የሐሰት ወንጌል በመላው ዓለም ተስፋፋ፡፡

    ከሚላኑ ድንጋጌ በኋላ ለብዙ ሺህ አመታት የክርስትና ዘመን መላውን የአውሮፓ አለም አሽመደመደው፡፡ ምንም እንኳን ሰዎችን ወደ ‹ቃሉ፣ ጸጋውና እምነት› እንዲመለሱ የሚያግባቡ ተከታታይ አዳዲስ የተሐድሶ እንቅስቃሴዎች ቢነሱም አንዳቸውም እውነተኛ ወንጌል የሆነውን ‹የውሃና የደም ወንጌል› አላገኙም፡፡  

    ይህ እውነተኛ ወንጌል ከሐዋርያቶች ዘመን ጀምሮ ቃሎቹን በተከተሉት ጥቂቶች እጅ ሕያው ሆኖ ተጠብቆ ነበር፡፡ መሬት ውስጥ ዘልቆ እንደተሰወረና ዝቅ ባሉ ሸንተረሮች ላይ ዳግመኛ እንደሚፈልቅ ምንጭ ለመላው ዓለም ይሰራጭ ዘንድ ዳግመኛ በመጨረሻው ዘመን ብቅ አለ፡፡

    በዚህ ዘመን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው መሰረት የኢየሱስን ጥምቀት ወንጌል የሚሰብክ የመጀመሪያው መጽሐፍ ይህ ነው፡፡ 

    በዚህ ዘመን በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ በተጻፈው መሰረት የኢየሱስን ጥምቀትና ደም ወንጌል ለመስበክ የመጀመሪያው መጽሐፍ ይህ ነው፡፡ እውነተኛው ወንጌል እርሱ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደና በመስቀል ላይም ለሐጢያቶቻችን በሙሉ ፍርድን እንደተቀበለ በግልጽ ይነግረናል፡፡ ከዚህ መጽሐፍ በበለጠ ‹የውሃውንና የደሙን ወንጌል› ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድና በታማኝነት የሚሰብክ ሌላ መጽሐፍ እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ፡፡  

    ኢንተርኔት (በይነ መረብ) ለምርምርና ለእውቀት ጠቃሚ መሳርያ በሆነበት በዛሬው ዓለም የኢየሱስን ጥምቀት ምስጢር የሚያውቁና እውነተኛውን ወንጌል የሚሰብኩ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈውም የኢየሱስን ጥምቀት ምስጢር የሚያውቁና በእምነት የሚሰብኩ አንዳንድ አጋር ሰራተኞችን ለማግኘት ሞክሬ ነበር፡፡ እስከ አሁን ድረስ ግን አልተሳካልኝም፡፡ ስለዚህ ይህንን መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ለማተም ወስኛለሁ፡፡   

    ጎርፉ መላውን ዓለም በሚሸፍንበት ጊዜ ውሃው ለዓለም በሙሉ ይተርፍ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ማንም የሚጠጣው ጥሩ ውሃ አይሆንም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አስመሳይ ወንጌልን የሚሰብኩ ብዙ ‹‹የእግዚአብሄር አገልጋዮች›› ተብዬዎች አሉ፡፡ ነገር ግን እውነተኛውን ሕይወት የሚሰጠን ማንም የለም፡፡ 

    በየቀኑ ከያዕቆብ ጉድጓድ ስትጠጣ የነበረችው ሳምራዊቷ ሴት መንፈሳዊ ጥማቷን ማርካት አልቻለችም፡፡ ነገር ግን ከኢየሱስ ዘንድ የሕይወትን ውሃ በጠጣች ጊዜ ደህንነትን አገኘች፡፡

    በኢየሱስ ውስጥ ያለው የሕይወት ውሃ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ባለው እያንዳንዱ ሽንቁርና ክፍል ውስጥ እየፈሰሰ ነው፡፡ ከዚህ የሚጠጣ ሁሉ ለዘላለም ከሐጢያቱ ይድናል፡፡ ይህ ሰው ዳግመኛ በሐጢያት አይታሰርም፡፡ ነገር ግን በዙሪያው ያሉትን የሌሎች ነፍሳቶች ጥማት ለማርካት ሕያው ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፡፡  

    ሰባራውን ጠጋኝ የእግዚአብሄር ሰራተኞች እንሁን፡፡

    እኛ እየኖርን ያለነው ወደ ዓለም ፍጻሜ በተቃረበ ዘመን ነው፡፡ ይህ ዘመን የሰው ዘር ሐጢያቶች ጽዋውን የሞሉበትና የእግዚአብሄርም ጻድቅ ፍርድ የቀረበበት ዘመን ነው፡፡ አንዳንድ ሳይንቲስቶች ‹ዶሊ› የተባለች በግ በዘረ መል ያራቡበት ዘመን ነው፡፡ ሰዎችም በዘረ መል የተፈለፈሉ ሰብአዊ ፍጡራኖችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል፡፡ 

    ዛሬ እኛ ሌላ የባቤል ግምብ እየገነባን ነው፡፡ የሰው ዘር እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ለመጨረሻ ጊዜ የሞከረው እግዚአብሄር ቋንቋቸውን በመደባለቅ በምድር ሁሉ ላይ በበተናቸው ጊዜ ነበር፡፡ ታላቁ መከራ ማለትም የእግዚአብሄር ጻድቅ ቁጣዎች በቅርቡ ገና ዳግም ባልተወለዱ የጠፉ ነፍሳቶች ላይ የሚወርዱበት ጊዜ አሁን ነው፡፡

    ስለዚህ ይህንን መጽሐፍ በጥንቃቄ እንድታነቡት እጠይቃችኋለሁ፡፡ ‹ዳግም ከውሃውና ከመንፈሱ እንድትወለዱም› እጸልይላችኋለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ ወንጌልን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው መሰረት በግልጽ ይሰብካል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ተብሎዋል፡-

    ይህንን መጽሐፍ በጥልቀት የሚያነብ ማንኛውም ሰው በትክክል ዳግም መወለድ አይሳነውም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፡- እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፡፡ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው፡፡›› (ዮሐንስ 8፡31-32) በዚህ መጽሐፍ አማካይነት የእውነትን ቃሎች አግኙና ከሐጢያትና ከሞት ዳኑ! ቤዛነትን አግኝታችሁ በእርሱም የዘላለምን ሕይወትን አግኙ!   

    ‹የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል› በመስበክ የጠፉትን ነፍሳት ለማዳን የአብን ሥራ በጋራ እንስራ፡፡ እውነተኛው ወንጌል በመላው ዓለም እንደሚያበራ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እውነተኛው ወንጌል በእውነት ቃሎች የዘመኑን የክርስትና እምነት ስብራት እንድትጠግኑ እንደሚያደርጋችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ 

    ‹‹ከድሮ ዘመን የፈረሱት ሕንጻዎች ይሰራሉ፤ የብዙ ትውልድ መሰረትም ይታነጻል፡፡ አንተም፡- ሰባራውን ጠጋኝ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትላለህ፡፡›› (ኢሳይያስ 58፡12)

    ብዙዎቻችሁ ከውሃውና ከመንፈሱ ዳግም የመወለድ ወንጌል ጋር እንደማትተዋወቁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ ስብከት ውስጥ በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል ላይ ትልቅ ትኩረት ለማድረግ ሞክሬአለሁ፡፡

    የኢየሱስ ጥምቀት ባይኖር ኖሮ የመስቀል ላይ ሞቱ ለሁላችንም ትርጉም የለሽ ይሆን ነበር፡፡ በእርሱ ጥምቀት ላይ ደጋግሜ ትኩረት የማደርግባቸው ምክንያቶች እነዚህ ናቸው፡፡

    የእኔ አላማ ይህንን ለእናንተ ግልጽ ማድረግ ነው፡፡ ሁላችሁም በውሃውና (በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት) በመንፈሱ ወንጌል እስክትባረኩ ድረስ ልደጋግምላችሁ እወዳለሁ፡፡  

    ከሐጢያት ለመዳን ሁላችሁም በእርሱ የጥምቀትና የደም ወንጌል ወደማመን እንድትመጡ በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ ከውሃውና ከመንፈሱ ትወለዱ ዘንድ እንደሚመራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

    ማውጫ

    መቅድም

    ክፍል አንድ — ስብከቶች

    1. ለመዳን አስቀድመን ስለ ሐጢያቶቻችን ማወቅ አለብን (ማርቆስ 7፡8-9,20-23)

    2. ሰዎች ሐጢያተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው (ማርቆስ7፡20-23)

    3. ነገሮችን በሕጉ መሰረት ብናደርግ ሕጉ ሊያድነን ይችላልን? (ሉቃስ10፡25-30)

    4. ዘላለማዊ ቤዛነት (ዮሐንስ 8፡1-12)

    5. የኢየሱስ ጥምቀትና የሐጢያቶች ስርየት (ማቴዎስ 3፡13-17)

    6. ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በውሃ፣ በደምና በመንፈስ ነው (1ኛ ዮሐንስ 5፡1-12)

    7. የኢየሱስ ጥምቀት ለሐጢያተኞች የደህንነት ምሳሌ ነው (1ኛ ጴጥሮስ 3፡20-22)

    8. የተትረፈረፈው የስርየት ወንጌል (ዮሐንስ 13፡1-17)

    ክፍል ሁለት — አባሪ

    1. የደህንነት ምስክርነቶች

    2. ተጨማሪ ማብራሪያ

    3. ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

    Sermon01.gif01.jpg

    ለመዳን አስቀድመን ስለ ሐጢያቶቻችን ማወቅ አለብን

    < < ማርቆስ 7፡8-9 > >

    ‹‹የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። እንዲህም አላቸው። ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።››

    < < ማርቆስ 7፡20-23 > >

    ‹‹እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።፡››

    በመጀመሪያ ሐጢያት ምን እንደሆነ ለማብራራት እወዳለሁ፡፡ በእግዚአብሄር የተብራሩ ሐጢያቶች አሉ፤ በሰው የተብራሩም ሐጢያቶች አሉ፡፡ በጥንቱ የግሪክ ቃል ሐጢያት ማለትም ‹‹αμαρτία ሃማርትያ›› ‹‹ኢላማን መሳት›› ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ስህተት የሆነን ነገር ማድረግ ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ አለመታዘዝ ሐጢያት ነው፡፡ በመጀመሪያ ሰው ስለ ሐጢያት ያለውን ምልከታ እንመልከት፡፡

    ኃጢአትን የምናውቀው በሕሊናችን መሠረት ነው።  ይሁን እንጂ የሰው ልጅ የኃጢአት መለኪያው እንደ አንድ ሰው ማህበራዊ እሴት፣ የአዕምሮ ሁኔታ፣ በተሰጡት ሁኔታዎች እና ሕሊና ይለያያል።

     ስለዚህም የኃጢአት ፍቺ እንደየ ግለሰቦች ይለያየ ነው።  በእያንዳንዱ ሰው መመዘኛዎች ላይ በመመስረት ተመሳሳይ ድርጊት እንደ ኃጢአተኝነት ሊቆጠርም ላይሆንም ይችላል።  ለዚህም ነው እግዚአብሔር 613 የሕጉን አንቀጾች እንደ ፍፁም የኃጢአት መመዘኛ እንድንጠቀም የሰጠን።

    ከዚህ በታች ያለው ገላጭ ስዕል የሰው ልጆችን ሐጢያት ያብራራል፡፡

    no1_20p

    በማህበራዊ ስርዓቶች ላይ ተመስርተን በሕሊናዎቻችን ላይ የሐጢያትን መለኪያዎች ከቶውኑም መደንገግ አይገባንም፡፡ 

    በሕሊናዎቻችን የምንሰራቸው ሐጢያቶች እግዚአብሄር ሐጢያት ብሎ ከገለጠው ጋር አይስማሙም፡፡ ስለዚህ ሕሊናዎቻችንን ማድመጥ የለብንም፡፡ ነገር ግን የሐጢያትን መለኪያዎች በእግዚአብሄር ትዕዛዛት ላይ መመስረት ይገባናል፡፡  

    እያንዳንዳችን ሐጢያት ምን እንደሆነ የራሳችን እሳቤ አለን፡፡ አንዳንዶች ሐጢያትን የራሳቸው ጉድለቶች አድርገው ሲመለከቱት ሌሎች ደግሞ በተዛባ ባህርይ ላይ የተመሰረተ ነገር እንደሆነ አድርገው ያስቡታል፡፡

    ለምሳሌ በኮርያ ሰዎች የወላጆቻቸውን መቃብሮች በሳር ይሸፍኑዋቸውና እስኪሞቱ ድረስ የመንከባከቡን ሐላፊነት እንዲወስዱላቸው ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም በፓፑዋ ኒው ጊኒ ውስጥ ካሉት ኋላ ቀር ነገዶች አንዱ የሞቱ ወላጆቻቸውን የሚያከብሩት ሬሳውን ከቤተሰብ አባላት ጋር በመመገብ ነው፡፡ (ሬሳውን ከመብላታቸው በፊት ይቅቀሉት እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡) ሬሳው በትሎች እንዳይበላ መከላከላቸው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይህ ባህል ሰው ስለ ሐጢያት ያለው እሳቤ በሰፊው የተለያየ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡  

    በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የሚደረግ ሰናይ ምግባር በሌላው ማህበረሰብ ውስጥ አረመኔያዊነት ሆኖ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ አለመታዘዝ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ‹‹የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት ጥሳችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፡፡ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ፡፡ እንዲህም አላቸው፡- ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል፡፡›› (ማርቆስ 7፡8-9) አካላዊ ገጽታዎቻችን በእግዚአብሄር ዘንድ ምንም ዋጋ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም እርሱ የልባችንን ጥልቅ ይመለከታልና፡፡

    የሰው መስፈርት በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት ነው፡፡

    እንደ ፈቃዱ ከመኖር መውደቅ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት ነው፡፡ ቃሉን ከአለማመን ጋርም ተመሳሳይ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት እንደናቁትና በራሳቸው ትውፊታዊ ትምህርቶች ላይ ይበልጥ ጠቀሜታ እንዳኖሩት ፈሪሳውያን መኖር ሐጢያት እንደሆነ እግዚአብሄር ተናገረ፡፡ ኢየሱስ ፈሪሳውያኖችን እንደ ግብዞች ቆጠራቸው፡፡

    ‹‹የምታምኑት በየትኛው አምላክ ነው? በእርግጥ እኔን ታከብሩኛላችሁ? ከፍስ ታደርጉኛላችሁ? በስሜ ትኮራላችሁ፤ ነገር ግን በእርግጥ ታከብሩኛላችሁ?›› ሰዎች ውጫዊ ገጽታዎቻችንን ብቻ ተመልክተው ቃሉን ሊንቁ ይችላሉ፡፡ በጣም አሳሳቢው ሐጢያት የእርሱን ቃል መናቅ ነው፡፡ ይህንን ታውቃላችሁን?  

    ከድክመቶቻችን የመነጩ የአመጽ ምግባሮች ተራ በደሎች ናቸው፡፡ ፍጹማን ባለመሆናችን የምንሰራቸው ስህቶችና የምንፈጽማቸው ጥፋቶች መሰረታዊ ሐጢያቶች ሳይሆኑ ስህተቶች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶችን ከበደሎች ለይቶዋቸዋል፡፡ የእርሱን ቃል የሚንቁ ሰዎች ስህተቶች ባይኖሩባቸውም እንኳን ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ ኢየሱስ ፈሪሳውያንን የወቀሳቸው ለዚህ ነው፡፡    

    ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ድረስ ያሉትን መጽሐፎች በያዘው ፔንታቱክ ውስጥ ምን እንደምናደርግና ምን ማድረግ እንደሌለብን የሚነግሩን ትዕዛዛቶች አሉ፡፡ እነዚህ የእግዚአብሄር ቃል የእርሱ ትዕዛዛቶች ናቸው፡፡ እነርሱን 100% ልንጠብቃቸው አንችል ይሆናል፤ ነገር ግን የእርሱ ትዕዛዛት መሆናቸውን መቀበል አለብን፡፡ እርሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ እነርሱን ሰጥቶናል፡፡ እኛም የእግዚአብሄር ቃል አድርገን ልንቀበላቸው ይገባናል፡፡   

    ‹‹በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ፡፡ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ፡፡›› ከዚያም እንዲህ አለ፡- ‹‹ብርሃን ይሁን አለ ብርሃንም ሆነ፡፡›› እርሱ እያንዳንዱን ነገር ፈጠረ፡፡ ከዚያ በኋላ ሕጉን አጸና፡፡

    ‹‹ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡1,14) እግዚአብሄር ራሱን የሚገልጥልን እንዴት ነው? ራሱን የሚገልጥልን በትዕዛዛቶቹ በኩል ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር ቃልና መንፈስ ነውና፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ምን ብለን እንጠራዋለን? የእግዚአብሄር ቃል ብለን እንጠራዋለን፡፡

    እዚህ ላይ እንዲህ ተብሎዋል፡- ‹‹ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል፡፡›› በእርሱ ሕግ ውስጥ 613 አንቀጾች አሉ፡፡ ይህንን አድርግ፤ ያንን ግን አታድርግ፤ ወላጆችህን አክብር ወ.ዘ.ተ…፡፡ በዘሌዋውያን ውስጥ ወንዶችና ሴቶች እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸውና አንድ የቤት እንስሳም ገደል ውስጥ ሲወድቅ ምን እንደሚያደርጉ ተጽፎዋል፡፡…በሕጉ ውስጥ እንደዚህ ያሉ 613 አንቀጾች አሉ፡፡ 

    እነዚህ የሰው ቃሎች ስላልሆኑ ደጋግመን ልናስብባቸው ይገባናል፡፡ የእርሱን ሕጎች በሙሉ መጠበቅ ባንችልም ቢያንስ እነርሱን ማወቅና እግዚአብሄርን መታዘዝ ይገባናል፡፡

    በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ትክክል ያልሆነ አንድ ምንባብ እንኳን አለ? ፈሪሳውያን የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት ትተው የሰዎችን ወጎች ከትዕዛዛቱ በላይ አድርገው ያዙ፡፡ ከእግዚአብሄር ቃሎች ይልቅ የሽማግሌዎቻቸው ቃሎች ይበልጥ ክብደት ነበራቸው፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ያየው ይህንን ነበር፡፡ እርሱን እጅግ ያቆሰለው ሕዝቡ የእግዚአብሄርን ቃል ቸል ማለቱ ነበር፡፡  

    እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን እንድናውቅ ለማድረግና እርሱ ቅዱስ የሆነ የእውነት አምላክ መሆኑን ሊያሳየን የሕጉን 613 አንቀጾች ሰጠን፡፡ እኛ ሁላችን በእርሱ ፊት ሐጢያተኞች ስለሆንን በእምነት መኖርና እርሱ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ ከእግዚአብሄር ዘንድ ወደ እኛ በተላከው ኢየሱስ ማመን ይገባናል፡፡ 

    የእርሱን ቃል ገለል የሚያደርጉና የማያምኑ ሰዎች ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ የእርሱን ቃል መጠበቅ ያልቻሉ ሰዎችም እንደዚሁ ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ የእርሱን ቃል መናቅ አሳሳቢ ሐጢያት ነው፡፡ እንዲህ ያለውን የከበደ ሐጢያት የሚሰሩ ሰዎች መጨረሻቸው ሲዖል ይሆናል፡፡ በእርሱ ቃል አለማመን በእርሱ ፊት እጅግ አስከፊ ሐጢያት ነው፡፡

    እግዚአብሄር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት፡- 

    እግዚአብሄር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት ምን ነበር? ሐጢያቶቻችንን ተገንዝበን ወደ እርሱ እንድንመለስ ለማድረግ ነበር፡፡ ሐጢያቶቻችንን ተገንዝበን ወደ እርሱ እንድንመለስ ለማድረግ ነው፡፡ ሐጢያቶቻችንን እንድንገነዘብና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ቤዛነትን እንድናገኝ የሕጉን 613 አንቀጾች ሰጠን፡፡ እግዚአብሄር ሕጉን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡

    ሮሜ 3፡20 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡›› ስለዚህ እግዚአብሄር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት በእርሱ እንድንኖር ሊያስገድደን አልነበረም፡

    ታዲያ ከሕጉ የምናገኘው እውቀት ምንድነው? እኛ ሕጉን በሙላቱ ለመጠበቅ በጣም ደካሞችና በፊቱም የከፋን ሐጢያተኞች መሆናችንን ነው፡፡ ከ613ቱ የሕጉ አንቀጾች የምንገነዘበው ምንድነው? በሕጉ ለመኖር ያለንን ጎዶሎነትና አቅመ ቢስነት እንገነዘባለን፡፡ እኛ የእግዚአብሄር ፍጡራኖች በእርሱ ፊት አቅመ ቢስ ፍጥረታቶች እንደዚሁም የከፋን ሐጢያተኞች ነን፡፡ በሕጉ መሰረትም የሁላችንም መጨረሻ ሲዖል ሊሆን ይገባው ነበር፡፡  

    ሐጢያቶቻችንንና በሕጉ ለመኖር አቅመ ቢስነታችንን ስንገነዘብ ምን እናደርጋለን? ፍጹም የሆንን ፍጥረታቶች ለመሆን እንሞክራለን? አይደለም፡፡ እኛ ሐጢያተኞች መሆናችንን መቀበል፣ በኢየሱስ ማመን፣ በእርሱ የውሃና የመንፈስ ደህንነት አማካይነት ቤዛነትን ማግኘትና እርሱን ማመስገን አለብን፡፡ 

    እርሱ ሕጉን የሰጠን ሐጢያቶቻችንን እንድንገነዘብና ለእነዚያ ሐጢያቶችም የሚገቡንን ቅጣቶች እንድናውቅ ለማድረግ ነበር፡፡ ስለዚህ ያለ ኢየሱስ ከሲዖል መዳን እንደማይቻል እንገነዘባለን፡፡ ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ብናምን ቤዛነትን እናገኛለን፡፡ እርሱ ሕጉን የሰጠን ወደ አዳኙ ኢየሱስ እንዲመራን ነበር፡፡

    እግዚአብሄር ሕጉን የፈጠረው እኛ ምን ያህል ፍጹም ሐጢያተኞች እንደሆንን እንድንገነዘብ ለማድረግና ነፍሳችንን ከዚህ ሐጢያት ለማዳን ነው፡፡ እርሱ ሕጉን ሰጠን፡፡ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ በመውሰድም ሊያድነን አንድ ልጁን ኢየሱስን ላከልን፡፡ በእርሱ ማመን ሊያድነን ይችላል፡፡ 

    እኛ ከሐጢያታችን ነጻ ለመውጣት፣ የእርሱ ልጆች ለመሆንና እንደገና ወደ እግዚአብሄር ክብር ለመመለስ በኢየሱስ ማመን የሚገባን ተስፋ ቢስ ሐጢያተኞች ነን፡፡

    በቃሉ አማካይነት መረዳት፣ ማሰብና መወሰን ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚፈልቀው ከእርሱ ነውና፡፡ በቃሉ አማካይነትም የቤዛነትን እውነት መረዳት ይገባናል፡፡ ትክክለኛውና እውነተኛው እምነት ይህ ነው፡፡ 

    በሰው ልብ ውስጥ ያለው ምንድነው?

    እምነት መጀመር ያለበት በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እኛም በቃሉ አማካይነት በእርሱ ማመን ይገባናል፡፡ ካላመንን ስህተት ላይ እንወድቃለን፡፡ ያም የተሳሳተና እውነተኛ ያልሆነ እምነት ይሆናል፡፡  

    ፈሪሳውያንና ጸሐፍት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ባልታጠቡ እጆች እንጀራ ሲበሉ ባዩ ጊዜ ከእግዚአብሄር ቃል አንጻር ቢያዩት ኖሮ ባልነቀፉዋቸውም ነበር፡፡ ቃሉ ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ማንኛውም ነገር እርሱን/እርስዋን እንደማያረክስ ይነግረናል፡፡ ምክንያቱም ወደ ሆድ ገብቶ ልብን ሳይነካ ከሰውነት ይወጣልና፡፡ 

    በማርቆስ 7፡20-23 እንዲህ ተባለ፡- ‹‹እርሱም አለ፡- ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው፡፡ ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነት፣ መጎምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ናቸውና፡፡ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል፤ ሰውንም ያረክሰዋል፡፡›› ኢየሱስ ሰዎች ከሐጢያት ጋር ስለተወለዱ ሐጢያተኞች እንደሆኑ ተናገረ፡፡

    ይህ ምን ማለት እንደሆነ ይገባችኋልን? እኛ ሐጢያተኞች ሆነን የተወለድነው ሁላችንም የአዳም ዘሮች ስለሆንን ነው፡፡ ነገር ግን እውነቱን ማየት አልቻልንም፡፡ ምክንያቱም የእርሱን ቃሎች በሙሉ አልተቀበልናቸውም፤ አላመንናቸውም፡፡ ታዲያ በሰው ልብ ውስጥ ምን አለ?

    ከላይ ያለው ምንባብ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነት፣ መጎምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ናቸውና፡፡ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል፤ ሰውንም ያረክሰዋል፡፡››

    በመዝሙረ ዳዊት እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሰራሃቸውን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጎበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድርነው?›› (መዝሙረ ዳዊት 8፡3-4)

    እግዚአብሄር ራሱ የሚጎበኘን ለምንድነው? እርሱ የሚጎበኘን ስለሚወደን፣ ስለፈጠረንና ለእኛ ለሐጢያተኞች ስለሚያዝን ነው፡፡ እርሱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ደምስሶ ሕዝቡ አደረገን፡፡ ‹‹አቤቱ ጌታችን ስምህ በምድር ላይ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1