Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)
የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)
የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)
Ebook503 pages4 hours

የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተወሳው የጥንቱ ወንጌል ‹‹የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል›› ተብሎ የተጠራው የመጀመሪያው ወንጌል ነው፡፡ ሆኖም እስከ አሁን ድረስ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በእርግጥም የመጀመሪያው ወንጌል መሆኑን አላወቁም፡፡ በዚህ ምክንያት በተሳሳተ መንገድ ‹በገሚስ ወንጌል› አምነዋል፡፡ እምነታቸው ዕመርታን ያላደረገውና አንዳች መንፈሳዊ ዕድገት ማየት እንዳይችሉ ያደረገው ለዚህ ነው፡፡ እምነታቸው በሕግ አጥባቂ ወይም በምናባዊ አመኔታዎች የተቃኘ በመሆኑ ሁሌም በእንከን የተሞላ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ልቦቻቸው በሐጢያት በተሞላ ሁኔታ ውስጥ ቀርተው ከመኖር በስተቀር ራሳቸውን መርዳት አልቻሉም፡፡ እነዚህ ክርስቲያኖች ሐጢያት በልቦቻቸው ውስጥ እያለ እንዴት መንፈሳዊ ሐይል ሊኖራቸው ይችላል? ሐይል አልባ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ምክንያት በዚህ ዓለም ላይ ያላቸው ሕይወትም እንደዚሁ አይረቤ ነው፡፡ ስለዚህ የዘመኑ ክርስትና ከጥንቷ ቤተክርስቲያን መክሰም ጀምሮ የያዘው ገሚስ ወንጌል ነው ልንል እንችላለን፡፡ በመሆኑም ሁላችንም በጣም ከመርፈዱ በፊት አሁን የጥንቱን ወንጌል እንደገና ፈልገን ማግኘት፣ እውነተኛውን የእግዚአብሄር ፍቅር ማወቅና በዚህ የእውነት ፍቅር ማመን አለብን፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateSep 21, 2023
ISBN9788965322603
የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)

Related to የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)

Related ebooks

Reviews for የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53)

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የጥንቱ ወንጌል ጥበብ (Amharic53) - Paul C. Jong

    መቅድም

    ይህ ‹‹የጥንቱ ወንጌል ጥበብ›› መጽሐፍ ነው፡፡ ‹ጥንት› የሚለው ቃል ወንጌል በጣም ረጅም ታሪክ ያለው ቀደምት ወንጌል መሆኑን ሲጠቁም ‹የወንጌል ጥበብ› ደግሞ ለሐጢያት የተከፈለውን ካሳ ይጠቁማል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ቤት በጥበብ ይሠራል›› (ምሳሌ 24፡3) ይላል፡፡ ጌታችን በመላው ዩኒቨርስ ውስጥ የጥበብ ባለቤት ነው፡፡ እርሱ ሐጢያተኞችን ለማዳን ወደዚህ ምድር መውረዱ፣ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን መቀበሉ፣ ለዓለም ሐጢያቶች ካሳ ለመክፈል በመስቀል ላይ መሞቱ፣ ዳግመኛ መነሳቱና ሐጢያተኞችን ማዳኑ የእርሱ ጥበብ ነበር፡፡ ጌታ የወንጌልን ጥበብ ማለትም የጌታን ጥበብ የሚያምነውን ማንኛውንም ሰው ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ያድናል፡፡ የእርሱ ጥበብ አይመረመርም፡፡ በሌላ አነጋገር እርሱ በጥንቱ ወንጌል ጥበብ በጥምቀቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አዳነን፡፡ እኛ በኢየሱስ የምናምን አማኞች የሐጢያት ካሳ ለሆነው ወንጌል ራሶቻችንን አጎንብሰን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን፡፡ ከጥንቱ ወንጌል የጌታን ጥበብ እንደምትማሩና እርሱንም እንደምታመሰግኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እግዚአብሄር በለገሳቸው የጥበብ ወንጌል ላይ እምነታቸውን በማኖር ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ መዳን እንዲችሉ እጸልያለሁ፡፡

    ይህ መጽሐፍ እናንተ ደህንነትን ትቀበሉ ዘንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ቀላልና ግልጥ የደህንነት እውነት ምስክር የሚያቀርብ የጥረታችን ውጤት ነው፡፡ እናንተ በመሠረቱ ወደ ሲዖል ለመሄድ የተመደባችሁ ሐጢያተኛ መሆናችሁንና ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ አማካይነት እነርሱን በመሸከም፣ በመስቀል ላይ በመሞትና በመነሣት ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ካሳ መክፈሉን በማመን ያለ ምንም ችግር መዳን ትችላላችሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ እጅግ ታላቁን ዳግመኛ የመወለድ ስጦታ እንደሚያመጣላችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለሐጢያት ካሳን ከከፈለው ወንጌል ማለትም ከጥንቱ ወንጌል ጥበብን በማትረፍ ከሐጢያቶቻችሁ መዳን አለባችሁ፡፡ ዳግመኛ የተወለዳችሁ መሆን አለባችሁ፡፡ ከተራ ጽንሰ አሳብ ይልቅ በተጨባጭ በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት የሌለባችሁ ሆናችሁ ደህንነትን የተቀበሉ ቅዱሳኖች መሆን አለባችሁ፡፡ ያንን ለማድረግ እምነታችሁን በደህንነት ቃል ላይ ማኖር አለባችሁ፡፡ ያም ለሐጢያት ካሳ የከፈለው የጥንቱ ወንጌል ጥበብ ነው፡፡

    ይህንን መጽሐፍ በማንበብ ኢየሱስ በውሃውና መንፈሱ ወንጌል አማካይነት ወደሰጠው ግልጥና ጥርት ያለ የደህንነት አስተውሎት ላይ ትደርሳላችሁ፡፡ እነዚህ የመሰሉ ጥያቄዎችም ይኖሩዋችሁ ይሆናል፡- ‹‹ታዲያ እስከ አሁን ያመንሁት ወንጌል ምንድነው? ታዲያ አሮጌውን ወንጌል መተውና በጥንቱ ወንጌል ጥበብ ማመን ይኖርብኛልን?›› እውነተኛው አሮጌው ወንጌል እንደሆነ ወይም የጥንቱ ወንጌል እንደሆነ በእግዚአብሄር ፊት እንድታሰላስሉ እፈልጋለሁ፡፡ የጥንቱን ወንጌል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ስታነጻጽሩት እውነቱን እንደምታገኙ ተስፋ አለኝ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነተኛውን ወንጌል እንድትለዩ ያግዛችኋል፡፡

    እስከ አሁን ድረስ ባወቃችሁት በአሮጌው ወንጌልና በጥንቱ ወንጌል ጥበብ መካከል ልዩነቶችን ታገኛላችሁ፡፡ ነገር ግን በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ላይ ተመሥርታችሁ አሮጌውን ወንጌል ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ጋር ብታነጻጽሩት በእውነቱ ላይ የተሻለ አስተውሎትና መተማመን ታተርፋላችሁ፡፡ ስለዚህ ይህንን መጽሐፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያነጻጸራችሁ እንደምታነቡት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ብያኔያችሁና እምነታችሁ በሙሉ መመሥረት ያለበት በእግዚአብሄር ቃል ላይ ሊሆን ይገባል፡፡

    አሁን ለሐጢያቶቻችሁ ካሳ የሆነውንና ዳግመኛ እንድትወለዱ የሚያደርጋችሁን የጥበብ ወንጌል እየሰማችሁ ነው፡፡ ዳግመኛ እንደምትወለዱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እባካችሁ ለማመን አታመንቱ፡፡ የወንጌልን ጥበብ በመማር ከዓለም ሐጢያቶች ዳኑ፡፡

    አሁን ስለ ሌሎች ነፍሶች የምትጨነቁበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሌሎች የሐይማኖት ድርጅቶች ምን እንደሚያምኑ ለማሰብም ጊዜው አይደለም፡፡ ከሁሉም በላይ ነፍሳችሁ ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ደህንነትን መቀበል ይገባታል፡፡ በዚህ መጽሐፍ አማካይነት ለሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ካሳ ተከፍሎ እንደሆነ ነፍሳችሁን መርምሩ፡፡ በእግዚአበሄር ፊት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃል ዳግመኛ እንድትወለዱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

    በኢየሱስ ካመናችሁ በኋላ ሐጢያት አልባ ሆናችኋል ወይስ አሁንም ሐጢያት አለባችሁ?

    ነፍሳችሁ በእምነት ትሞላ ዘንድ ተስፋ በማድረግ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እጸልያለሁ፡፡ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት አካባቢ ጌታችን ሰማያዊውን ዙፋኑን ተወ፤ ወደዚህ ምድር ወረደ፤ ለዓለም ሐጢያት ቅጣትን ለመክፈል ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን ተቀበለ፤ የዓለምን ሐጢያት ወደ መሰቀል ተሸክሞ ወሰደ፤ ደሙን አፈሰሰና ሞተ፤ በሦስት ቀናት ውስጥም ከሙታን ተነሣ፤ ከሐጢያቶች የሚያድነውንም የዘላለም ደህንነት ወንጌል ሰጠን፡፡

    አሁን እምነታችንን በጥንቱ ወንጌል ጥበብ ላይ እናኑር፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት በእምነት እንቀበል፡፡ እኔ ይህንን መጽሐፍ ለረጅም ጊዜ በኢየሱስ አምነው ቢሆንም እንኳን ዳግመኛ ላልተወለዱ ሰዎች በስጦታ አበረክታለሁ፡፡

    Sermon0101

    የሰዎች ጥንተ አብሶ ምንድነው?

    ‹‹ ማርቆስ 7፡20-23 ››

    ‹‹እርሱም አለ፡- ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው፡፡ ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነት፣ መጎምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ናቸውና፡፡ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውንም ያረክሰዋል፡፡››

    ሰዎችን በተጨባጭ በምናስተውላቸው ጊዜ ሁሉም ሰዎች የሐጢያት ክምር መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡ ሰዎች በሕይወት ዘመን ሁሉ ሐጢያትን የሚሠሩ የፍትወት ሐጢያት ዘሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሰዎች በፍትወት፣ በትዕቢት፣ በክፉ አሳቦች፣ በጥላቻ፣ በመግደል፣ በመስረቅና በሁሉም ዓይነት ክፉ ሐጢያቶች የተሞላ ሐጢያት ይሠራሉ፡፡ ሰዎች እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ፍጡራኖች መሆናቸውን ስነግራችሁ ታምኑ ይሆን? ሰዎች ብዙ የሚያጭበረብሩና የሚሰርቁ ፍጡራን መሆናቸውን ታምናላችሁን? ሰዎች ምንዝርናን የሚፈጽሙ ፍጡራን መሆናቸውን ብነግራችሁ ታምኑ ይሆን? እናንተ እንዲህ ዓይነት ሰዎች እንደነበራችሁ ብነግራችሁ ታምኑ ይሆን?

    እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ሰዎች ናቸው፡፡ በቅዱሳት መጽሐፍት መሠረት ሰዎች ክፉ ሐጢያቶችን ይዘው የተወለዱና በርካታ መጠን ያላቸው ክፉ ሐጢያቶችን የሚሠሩ መሆናቸውን በሚናገረው ጥንታዊ የውርስ ሐጢያት ቃል ታምናላችሁን? የሰው ስጋ በሕይወት ዘመን ሁሉ ሐጢያትን ብቻ ይሠራል፡፡ የሰው አካል ሐጢያትን የሚያመርት ፋብሪካ ነው ብሎ መናገሩ ማጋነን አይደለም፡፡ የሰው አካል እግዚአብሄር የሚጠላውን ሐጢያት እንደ ዘወትር ምግብ እየበላ ይኖራል፡፡ የሰው ስጋ ሐጢያትን መሥራት ይወዳል፡፡ ምንዝርናን፣ የፍትወት ሐጢያት መሥራትንና እግዚአብሄርን መቃወምን ይደሰትበታል፡፡

    የሰው አካል ከውልደት እስከ ዕለተ ሞት ቅጽበት ድረስ ሐጢያትን ይሠራል፡፡ የሰው አካል ሐጢያትን መሥራት ከመውደዱም በላይ ስጋዊ መሻቶቹንም ብቻ ደግሞ ይከተላል፡፡ ኢሳይያስ 1፡4 ሰዎች ‹‹የክፉ አድራጊዎች ዘር›› መሆናቸውን መዝግቦዋል፡፡ ኢሳይያስ 59ም በሰው ልብ ውስጥ ሁሉም ዓይነት የረከሱና የሚያሳፍሩ ነገሮች እንዳሉ መዝግቦዋል፡፡ በመሆኑም ሰው የሐጢያት ክምር ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ሰው የሐጢያት ክምር›› መሆኑን ከእግዚአብሄር ቃል ደምድመን ማረጋገጥ ከቻልን እንግዲያውስ ይህንን የእግዚአብሄር ቃል በልባችን ውስጥ መቀበል አለብን፡፡ በእግዚአብሄር ፊትም እኛ እንዲህ ያለን ሐጢያተኞች መሆናችንን መቀበልና ከዚያም የኢየሱስን ትምህርት መጠበቅ አለብን፡፡

    ሰዎች ሴሰኛ ናቸው፡፡ ሰው ራሱን በግልጥ ሲመለከት ሴሰኛና ሴሰኝነትም ራሱ ግለሰቡ መሆኑን መደምደም ይችላል፡፡ ለራሱ ታማኝ የሆነ ሰው ሰዎች እግዚአብሄር የተናገራቸውን አሥራ ሁለት ዓይነት ሐጢያቶች መያዛቸውን ይቀበላል፡፡ እንደዚያም ሆኖ እርሱ ራሱ በሴሰኝነት የተሞላ መሆኑን፤ የሐጢያት ክምር መሆኑን የማይቀበሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ብዙ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ እንደ እንሰሶች ዓይነት ሕይወት የሚኖሩት ሴሰኛ እንደሆኑ ስለማያስቡ ነው፡፡

    ሰዎች ራሳቸው ሴሰኛ ባህልን ያበጁት ሰዎች ‹‹የክፉ አድራጊዎች ዘር›› በመሆናቸው ነው፡፡ አንድ ሰው በዚህ ዓለም ላይ ሴሰኛ ባህሪያቶችን የሚያደርገው እርሱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ያፍር ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱ እንዲህ ያለ ሴሰኛ ባህልን በማበጀታቸው የማያፍሩት ሌላውም ሰው ሁሉ እንደዚሁ ሴሰኛ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም የእያንዳንዱ ሰው ልብ ስለ ሐጢያት ባህሪዎቹ በሕሊናው ውስጥ ሐፍረት ይሰማዋል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ እግዚአብሄር ለሰዎች ሕሊናን መስጠቱ ነው፡፡ የሰው ሕሊና እግዚአብሄር የእርሱ ምክትል አድርጎ የላከው የእግዚአብሄር አገልጋይ ነው፡፡

    አዳምና ሔዋን ሐጢያት ከሠሩ በኋላ በብዙ ዛፎች መካከል ተሸሸጉ፡፡ ብዙ ዛፎች የሚያመለክቱት በሴሰኛ ባህል የተሸፈነውን የሰው ማህበረሰብ ነው፡፡ ሆኖም እነርሱ በልባቸው ውስጥ ያለውን ክፋት መሸሸግ አልቻሉም፡፡ አሁንም እንኳን የሐጢያት ክምር የሆኑ ብዙዎች በብዙ ሕዝቦች መካከል በመሰግሰግ በክፉ ሐጢያቶች ባህል በስተ ጀርባ ራሳቸውን ሸሽገው የሞት ቅጣቱን እንደሚጠብቅ እስረኛ እየኖሩ ነው፡፡

    እያንዳንዱ ሰው የሚኖረው ራሱን በተሳሳተ መንገድ በመረዳት ነው፡፡

    ሰዎች ራሳቸውን በተሳሳተ መንገድ ተረድተው ይኖራሉ፡፡ አስደንጋጭና አሳፋሪ ክስተት ሲከሰት ሰው እንዴት እንዲህ ያሉ ነገሮችን ሊያደርግ እንደሚችልና ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ እንዴት በወላጆቻቸው ላይ እንዲህ ያሉ ሰቅጣጭ ነገሮችን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይጠይቃሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች በሙሉ እንደዚያ ቢሆኑም እነርሱ ከመጀመሪያም እንደዚያ እንዳልሆኑ ክችች ይላሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች በተጨባጭ ልናስተውላቸው የማንችላቸው ፍጡራን ናቸው፡፡ ሰው ራሱን በትክክል ለመረዳት እርሱ ወይም እርስዋ በእውነተኛው ወንጌል ፊት መቅረብና በእውነተኛው የጥበብ ቃል ወንጌል ዳግመኛ መወለድ አለባቸው፡፡

    በዚህች ፕላኔት ላይ መላውን ሕይወታቸውን ከኖሩ በኋላም እንኳን እውነተኛ ማንነታቸውን ሳያውቁ የሞቱ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ይህንን ዓለም በጥንቃቄ ስንመለከት በጣም ብዙ የተዘበራረቁ ኩነቶች አሉ፡፡ ሰዎችን በጥንቃቄ ስንመለከት በጣም ጻድቅ እንደሆኑ የሚያስመስሉ አንዳንድ ሰዎችን ማየት እንችላለን፡፡ አንድ ሰው አፉ እንዳመጣለት ሲናገር እንኳን እነርሱ ‹‹ያ ምንድነው! አንድ የተማረ ሰው እንዴት እንዲህ ያለ ነገር ሊናገር ይችላል?›› ይላሉ፡፡ እነርሱ ግለሰቡ የተሳሳተ አንድ ነገር እየጠቆመ ቢሆንም እንኳን ሰው እንዲህ ያለ ነገር መናገር እንደማይገባው ይናገራሉ፡፡ እነርሱ ሌባን ‹‹አቶ ሌባ›› ብለን መጥራት እንደሚገባን ይናገራሉ፡፡ ያ ግብዝነትና ዕብሪት ነው፡፡

    እግዚአብሄር ‹‹ራስህን እወቅ›› ይላል፡፡

    እንዲህ ያለውን ግለሰብ ስንመለከት ይህ ግለሰብ ራሱን እንደማያውቅ ወደ ማወቅ እደርሳለሁ፡፡ ሶቅራጥስ ‹‹ራስህን እወቅ›› ቢልም ሰዎች በተጨባጭ ፈጽሞ ራሳቸውን አያውቁም፡፡ በውስጣቸው ምን ሐጢያቶች እንደተከማቹ አያውቁም፡፡ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 7 ከቁጥር 21-23 ከቀድሞውም በሰው ልብ ውስጥ 12 ዓይነት ሐጢያቶች እንዳሉ መዝግቦዋል፡፡ መግደልን የሚፈጽም ልብ፣ የፍትወት ልብ፣ የቅናት ልብ፣ የስርቆት ልብ፣ የክፉ አሳቦች ልብ፣ የስንፍና ልብና ሌሎች ብዙ ሐጢያቶች በእነርሱ ውስጥ አሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ግብዞች እንደሆኑና በልቦቻቸው ውስጥ የእባብ መርዝ ቢኖርም የተሸፋፈኑ የበጎነት ቃላቶችን ብቻ እየተናገሩ ሲኖሩ አያለሁ፡፡ ለዚያ ምክንያቱ ራሳቸውን አለማወቃቸው ነው፡፡

    በዚህ ዓለም ላይ ራሳቸውን የማያውቁ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ስለዚህ ራሳቸውን ካታለሉና በእውነተኛው ወንጌል ደህንነት ሳያምኑ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በራሳቸው ተታልለው ከኖሩ በኋላ ሲዖል ውስጥ የሚወድቁ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ከመነሻውና ከመሠረቱ በራሳቸው ተታልለው ሲዖል የሚሄዱ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ ከኖሩ በኋላ ወደ ሲዖል ሲሄዱ የሲዖል አለቃ ‹‹ለምን ወደ ሲዖል መጣችሁ?›› ብሎ ይጠይቃቸው ይሆናል፡፡ እነዚያ ሰዎችም ‹‹ጎረቤቴ ሆኖ የሚኖረው አቶ እከሌና እከሌ እዚህ መምጣት እንዳለበት ያሰብሁ ብሆንም ቢያንስ እኔ ሰማይ እሄዳለሁ ብዬ አስቤ ነበር፡፡ እዚህ መምጣቴ ተገቢ አይደለም›› ብለው ይመልሱ ይሆናል፡፡ እነርሱ ምናልባት ‹‹ቢያንስ እኔ ከሌሎች ሰዎች ትንሽ የተሻልሁ ነኝ ብዬ አስቤ ነበር፡፡ ለምን እዚህ እንደመጣሁ አላውቅም›› ብለው አስበው ይሆናል፡፡ ራሳቸውን የማያውቁና እውነተኛውን የደህንነት ወንጌል የማያውቁና የማያምኑ ሰዎች ሁሉ ወደ ሲዖል ሄደዋል፡፡

    ሰው ምንድነው? በመግቢያው ላይ እንደተናገርሁት ሰው ሴሰኛ ፍጡር ነው፡፡ ሰው ‹‹የክፉ አድራጊዎች ዘር›› ልጅ ነው፡፡

    እያንዳንዱ ሰው ሴሰኛ ነው ብሎ መናገር ትክክል ይመስላል፡፡ ነገር ግን አንድን ግለሰብ ነጥዩ ባወጣና ‹‹አንተ ሴሰኛ ሰው ነህ›› ብል ያለውን ሸክፎ ወዲያውኑ ከዚህ ስፍራ ይሄዳል፡፡ ነገር ግን ማንኛውንም አንድ ግለሰብ ጠቁሜና ‹‹አንተ የሐጢያት ክምር ነህ፡፡ አንተ ሴሰኛ ሰው ነህ›› ብለ ኖሮ ያ ሙሉ በሙሉ እውነት ይሆናል፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ፊት ልክ እንደዚያ ነን፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሄር ፊት ልክ እንደዚያ ነን፡፡ አንድ ግለሰብ ሰው ከመጀመሪያውም የክፉ አድራጊዎች ዘር መሆን ሲሰማ ‹‹ኦ እንደዚያ ነው›› ብሎ ያስባል፡፡ ይህ ስለ ሌሎች ሰዎች የተነገረ እንደሆነ አድርጎም በግድየለሽነት ይሰማል፡፡ ሆኖም ‹‹አንተ በትክክል እንዲህ ያለህ ሰው ነህ›› ተብሎ ሲነገራችሁ ‹‹አዎ ነኝ›› ብላችሁ የምትመልሱ ከሆነ ታማኝ ሰው ናችሁ፡፡ ሆኖም ማማኻኛዎችን የሚያቀርቡና ሌሎች ሰዎችን የሚወቅሱ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እንዲህ ያለ ሰው በመሠረቱ ገና ራሱን ማየት የማይችል መሃይም ግለሰብ ነው፡፡ እርሱ ራሱ፣ እናንተ ራሳችሁና እኔም ራሴ የሐጢያት ክምር ነን፡፡ እኛ ከመጀመሪያውም ሴሰኛ የሆንን ‹‹የክፉ አድራጊዎች ዘር›› ነን፡፡ እኛ ሴሰኛ የሐጢያት ዘር ስለሆንን የኢየሱስ እውነተኛ ወንጌል ጥበብ አስፈለገን፡፡ አንዳች ጉድለቶች የነበሩብን ቢሆንና ከሴሰኛ ዘር ያልሆንን ብንሆን ኖሮ የኢየሱስ እውነተኛ ወንጌል ጥበብ ለምን ያስፈልገን ነበር? እኛ ከመጀመሪያውም ክፉ ባንሆን ኖሮ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መምጣት ባልነበረበት ነበር፡፡

    ሰዎች በየቅጽበቱ ሐጢያቶችን የሚያፈስሱት ከመጀመሪያውም ሐጢያተኞች በመሆናቸው ነው፡፡

    ሐጢያቶች በሰው ልብ ውስጥ፣ በሰው ነፍስ ውስጥ ሞልተዋል፡፡ በዚህ ኩባያ ውስጥ ያለው ውሃ የአንድ ግለሰብ ነፍስ ሐጢያት ነው እንበል፡፡ በዚህ ኩባያ ውስጥ ያለው ሐጢያት ግለሰቡ በዚህ ዓለም ላይ በሚያጋድልበት ጊዜ ሁሉ ይፈስሳል፡፡ አይደለም እንዴ? ይፈስሳል፡፡ ሰው ከአንድ ጎን ወደ ሌላው ጎን ሲናወጥ ሐጢያት ይፈስሳል፡፡ ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በዚያ መልኩ ሐጢያቶችን እያንጠባጠቡ በዓለም ዙሪያ ይዞራሉ፡፡ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ ሲኖሩ ሐጢያትን የሚሠሩት የሐጢያት ክምር ስለሆኑ ነው፡፡

    ሰዎች ምን ዓይነት ሐጢያተኞች እንደሆኑ በደምብ አያውቁም፡፡ እኛ የሐጢያትን ልብ የሐጢያት ክምር አድርገን ወደብ የያዝንና በሕይወታችን ሁሉም ሐጢያትን የምንሠራ ብንሆንም ‹‹እኔ ከመጀመሪያውም በፍትወት የተሞላሁ አይደለሁም፡፡ እንዲህ የሆንሁት የሆነ ሰው በፍትወት የተሞላሁ እንድሆን ስለገፋኝ ነው፡፡ እኔ ከመጀመሪያውም ሴሰኛ ሰው አይደለሁም፡፡ በተጨባጭ የሠራኋቸውን የሴሰኛ ሐጢያቶች ጠራርጌ ማስወገድ እፈልጋለሁ›› ብለው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ‹‹እኔ ከመጀመሪያውም ሴሰኛ ሰው አይደለሁም!›› ይላሉ፡፡ ሐጢያቶቻቸው ወደ ውጪ በሚፈሱበት ጊዜ ሁሉም ያለ ማቋረጥ በመልካም ምግባሮች ወይም በንስሐ ጸሎቶች ጠርገው ያስወግዳሉ፡፡ ጠርጋችሁ ስታስወግዱት ሐጢያት እንደገና አይፈስስምን? ይፈስሳል፡፡ ከውስጥ ያለው የሰው ልብ የሐጢያት ክምር ስለሆነ ሰው በባህሪም እንደዚሁ ሐጢያትን ይሠራል፡፡ አንድ ግለሰብ ውጫዊውን ግለሰብ ምንም ያህል ቢጠርገው የሚለወጥ ነገር የለም፡፡ አንድ ግለሰብ ውጪውን (ሥራዎችን) በሥነ ምግባር ወይም በሥነ ድርጊት ቢጠርግ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ካለ ጥቅም የለውም፡፡ ሰው በሕይወቱ ሁሉ በመግደል ልብ፣ በምንዝርና ልብ፣ በስርቆት ልብና ወ.ዘ.ተረፈ ሐጢያትን ይሠራል፡፡ ስለዚህ ሰዎች በሕይወታቸው ሁሉ እዚህና እዚያ ብዙ ሐጢያቶችን ይሠራሉ፡፡

    ሰዎች ራሳቸውን በማያውቁበት ጊዜ ራሳቸውን ለመሸፋፈን ጠንክረው ይሞክራሉ፡፡

    ሰዎች ከመጀመሪያውም የሐጢያት ክምር መሆናቸውን በማያውቁበት ጊዜ ራሳቸውን ለመሸፈን ጠንክረው ይሞክራሉ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ሐጢያት ጥቂት ፈሰሰ እንበል፡፡ ያንን ከጠረገ በኋላ ተጨማሪ ሐጢያትን ያፈሳል፡፡ ያለ ማቋረጥም በመሃረብና በፎጣ መጥረግ ይኖርበታል፡፡ ያ በቂ ሳይሆን ሲቀርም በስጋጃም እንኳን ሳይቀር ደጋግሞ መጥረግ ይኖርበታል፡፡ ሰው ሐጢያት ላለመሥራት ከወሰነ በኋላ ሐጢያትን ባያንጠባጥብ ግሩም በሆነ ነበር፤ ነገር ግን ሰው የሚፈስሰውን ሐጢያት ምንም ያህል ብዙ ጊዜ ቢጠርገውም ንጹህ አይሆንም፡፡ እኛ እስከምንሞትበት ቅጽበት ድረስ ሐጢያትን እናንጠባጥባለን፡፡ ሰዎች እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ሴሰኛ ባህሪዎችን የሚፈጽሙ ፍጡራኖች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሐጢያትን የሚሠራ ግለሰብ ደህንነትን ለመቀበል ኢየሱስን ከሐጢያቶቹ ያዳነው አዳኝ አድርጎ መቀበል አለበት፡፡ ሰው የሐጢያቶችን ስርየት ለመቀበል በመጀመሪያ እውነተኛ ማንነቱን እንዳለ ማወቅ አለበት፡፡

    እዚህ ላይ በውሃ ተሞልተው እንዳሉት ሁለት ተመሳሳይ ኩባያዎች በውስጣቸው ተመሳሳይ ሐጢያቶች ያሉባቸው ሁለት ግለሰቦች አሉ እንበል፡፡ አንድ ሰው ወደ ራሱ ተመለከተና ‹‹እኔ ከመጀመሪያውም የሴሰኛ ዘር ነኝ›› ብሎ አሰበ፡፡ ስለዚህ ራሱን የማሻሻል ሙከራውን ተወና አዳኙን ለማግኘት ፈለገ፡፡ ሌላኛው ግለሰብ በራሱ ውስጥ ያለውን የሐጢያት ክምር መመልከት አልቻለምና ‹‹እኔ በመጠኑም ጨዋ ነኝ›› ብሎ አሰበ፡፡ ጨዋ ግለሰብ እንደሆነ የሚያምን ግለሰብ በሕይወቱ ሁሉ ሐጢያቱን ይጠርጋል፡፡ ሐጢያቶቹ ሞልተው እንዳይፈሱም ይጠነቀቃል፡፡ በሕይወቱ ሁሉም እርሱ ከመጀመሪያውም የሐጢያት ክምር መሆኑን ለመደበቅ እዚህ የሚፈስሰውን ይህንን ሐጢያት በመሸፈንና እዚያ የሚፈስሰውን ያንን ሐጢያት በመሸፈን ጠንክሮ ይሞክራል፡፡

    በዚህ መልኩ መላውን ሕይወታቸውን በልባቸው ውስጥ ባሉት የሴሰኛ ሐጢያቶች ተሞልተው እየኖሩ ሐጢያት ሞልቶ እንዳይፈስስ በመፍራት በጥንቃቄ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፡፡ እንዲህ በጥንቃቄ መኖር ሰማይ ለመሄድ ብዙም የሚያግዝ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቀድሞውኑም በውስጣቸው የሐጢያት ክምር አለ፡፡ ነገር ግን እነርሱ በዚያ መልኩ በጥንቃቄ መኖር ወደ ሲዖል የሚያደርስ ዱካ መሆኑን እንኳን አያውቁም፡፡ እነርሱ በጥንቃቄ ከኖሩ በኋላ ሲዖል ይወርዳሉ፡፡ በጥንቃቄ የሚኖር ግለሰብ የሐጢያት ክምር ብዙ ባይፈስም እንኳን ተሸሽጎ ሁሉንም ዓይነት ሐጢያቶች የሚሰራ ሐጢያተኛ ነው፡፡

    አንድ ግለሰብ ሴሰኛ ልብ፣ ክፉ አሳቦች፣ የስርቆት ልብና በግለሰቡ ውስጥም የትዕቢት ልብ እንዳለው አምናችሁ ትቀበላላችሁን? እኛ ሰዎች ማንም ባያስተምራቸውም ሁሉንም ዓይነት ሴሰኛ ሐጢያቶች አሳምረው እንደሚሠሩ በማየት ሰው ሴሰኛ ዘር መሆኑን ማወቅ እንችላለን፡፡ አንድ ግለሰብ ወጣት ሳለ ይህንን በደምብ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም ብዙ አይገለጥም፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ በዕድሜ ሲሸመግል የሐጢያት ክምር መሆኑን የሚሸሽግበት ምንም መንገድ የለም፡፡ ሰው ያለ ማቋረጥ ሐጢያቶቹን ከማንጠባጠብ በቀር ሊያደርገው የሚችለው ነገር የለም፡፡ እርሱ ሐጢያትን እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት እያደረገ ያንጠባጥባል፡፡ ከዚያም ይጸጸታል፡፡ ‹‹እንደዚያ ማድረግ አይገባኝም ነበር›› እያለ ይጸጸታል፡፡ ነገር ግን በዚያ መልኩ ቢጸጸትም በሕይወቱ ሁሉ ሐጢያትን ማንጠባጠቡን ይቀጥላል፡፡ እርሱ የሐጢያት ክምር ሆኖ ስለተወለደ እንደዚያ ነው፡፡

    እኔ ሰው ጌታ የሚሰጠውን ፍጹም የሆነ የሐጢያቶች ስርየት መቀበል የሚችለው ከመጀመሪያውም የክፉ አድራጊዎች ዘር መሆኑን ሲያውቅ ብቻ እንደሆነ እየተናገርሁ ነው፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የሐጢያት ክምር መሆኑን የሚያውቅ ግለሰብ አንድ ሰው ኢየሱስ እንዲህና እንዲህ ባለው የጽድቅ ሥራ ሐጢያቶቹን በሙሉ እንደደመሰሰ ቢነግረው ያለ ማመንታት ያምናል፡፡ ሆኖም ‹‹እኔ እስከ አሁን ድረስ የሠራሁት ይህን ያህል ሐጢያት ብቻ ነው፤ ያን ያህል ብዙ ሐጢያቶችን አልሠራሁም›› የሚል ግለሰብ በመሠረቱ ኢየሱስ ጥምቀትን በመቀበል ሐጢያቶቹን በሙሉ በራሱ ላይ የመውሰዱንና ሐጢያቶችን በሙሉ በመስቀል ላይ የመሸከሙን እውነታ በማጣጣል አያምንበትም፡፡ ሆኖም መዳን የሚገባው ግለሰብ ሙሉ በሙሉ የሐጢያት ክምር መሆኑን በማመንና ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ ጥምቀትን ከተቀበለ በኋላ ሐጢያቶችን በሙሉ በመስቀል ላይ ፈጽሞ በማስወገዱ የእውነት ቃል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ይቀበላል፡፡

    እኔ የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልም ይሁን ወይም አይሁን እየኖርን ያለነው ራሳችንን በጥቅሉ በተሳሳተ መንገድ በማስተዋል መሆኑን እየተናገርሁ ነው፡፡ ጌታ የእኛን የሰዎችን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱና በደሙ ከደመሰሰና በእርሱ አምነን የሐጢያቶችን ስርየት ተቀብለን ከሆነ ሐጢያት የለብንም፡፡

    ስለዚህ እግዚአብሄር ‹‹እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል እግዚአብሄር›› (ኤርምያስ 31፡31) በማለት አዲስ ኪዳን አደረገ፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሄር በአሮጌው ኪዳን ፋንታ አዲስ ኪዳን ይመሠርታል ማለት ነው፡፡ አዲሱ ኪዳን ጌታ ራሱ ወደዚህ ዓለም የመምጣቱ፤ የአዳም ሐጢያቶችንና የግል ሐጢያቶችን፣ በሕይወታቸው ሁሉ ሴሰኛ ሐጢያቶችን የሚሠሩ የሴሰኛ ዘር ሐጢያቶችን ሁሉ በራሱ የመውሰዱና ፈጽሞም በመደምሰስ ያልታመኑ ሐጢያተኞችን የማዳኑ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነበር፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ሰዎች የሚያድናቸውና አምላካቸው የሚሆነው በዚህ ኪዳን ነበር፡፡ እርሱ ‹‹የሴሰኛ ሰዎችን ሐጢያቶች በሙሉ እደመስስና አምላካቸው እሆናለሁ፡፡ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ›› አለ፡፡ አዲሱ ኪዳን እንዲህ በማለት ይቀጥላል፡- ‹‹እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን እያንዳንዱም ወንድሙን እግዚአብሄርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና ይላል እግዚአብሄር፡፡ በደላቸውንና ሐጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና፡፡›› (ኤርምያስ 31፡34)

    አዲሱ የእግዚአብሄር ኪዳን ሕጉን በመጠበቅ ጻድቅ መሆን የማንችል መሆናችንን ያሳየናል፡፡ ምክንያቱም ሕጉን ለመጠበቅ በመሞከር ጻድቃን መሆን አንችልም፡፡ ሕግ አጥባቂዎች እነዚህን ብዙ ሐጢያቶች ደግመው ይሠሩና ጌታን ‹‹ጌታ ሆይ ሐጢያቶቼን አንጻ፡፡ ዛሬ አንድ የተሳሳተ ነገር አድርጌያለሁ፡፡ ጌታ ሆይ አንጻኝ፡፡ እባክህ አንጻኝ›› በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ይህ በሕግ ላይ የተመሠረተ እምነት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት ሥርዓት ውስጥ ሰው እጆቹን በፍየሉ ወይም በጠቦቱ ራስ ላይ በመጫን የዘወትር ሐጢያቶቹን ማስተላለፍ ነበረበት፡፡ በሊቀ ካህኑ እጆች መጫንም አመታዊ ሐጢያቶችም ደግሞ መተላለፍ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ እነርሱ ቁርባኖችን በማቅረብ ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን ደግሞ ሐጢያት ከሠራ ያ ሰው አሁንም ሐጢያተኛ ነበር፡፡ ስለዚህ የሐጢያት ይቅርታ በሕግ በኩል የሚቻል አልነበረም፡፡ በመሆኑም ጌታ ‹‹ሐጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና›› እንዳለው የእግዚአብሄር አዲስ ኪዳን ለእያንዳንዱ ሐጢያተኛ አስፈላጊ ነበር፡፡

    እግዚአብሄር እንደ ሆሴዕ ሚስት የመሰሉትን እነዚህን ሴሰኛ ሰዎች የራሱ ሚስት አድርጎ ለመውሰድ ወስኖዋል፡፡ ቀደም ብዬ በሰጠሁት ምሳሌ ውስጥ እንዳለው ሁለቱም ግለሰቦች በሐጢያቶች የተሞሉ ናቸው፡፡ የተወለዱት በተመሳሳይ ስጋ ከተመሳሳይ ሐጢያቶች ጋር ነው፡፡ ነገር ግን አንዱ ሐጢያቶችን ላለማፍሰስ በጥንቃቄ ኖረ፡፡ እርሱ በኢየሱስም እንኳን በጣም በጥንቃቄ አመነ፡፡ ይህ ማለት አንዳንድ ሰዎች ስለ ሐጢያቶቻቸው መፍሰስ በጣም ጥንቁቆች ናቸው ማለት ነው፡፡ አንዲት የሐጢያት ጠብታ ስትፈስስ ‹‹ጌታ ሆይ ዛሬ ሐጢያትን ሠርቻለሁ፡፡ እባክህ ይህንን ሐጢያት ብቻ ይቅር በል›› በማለት ይህንን ሐጢያት ለመጥረግ የንስሐ ጸሎቶችን ያቀርባሉ፡፡ እነርሱ ያነጹና በተናዘዙት መጠን ልክ ብቻ ያምናሉ፡፡ እነርሱ ሁሌም ከውስጥ ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ በስተ ውጪ በግብዝነት ጥሩ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ቢያስመስሉም ሁሌም በውስጥ ሐጢያተኞች ናቸው፤ ሁሌም የተደበቱ ናቸው፡፡

    ውድ አጋር ምዕመናን እኛ ሴሰኛ ሰዎች ነን፡፡ እናንተና እኔ ወደ ሲዖል የምንሄድ ሰዎች እንደነበርን ማወቅ አለብን፡፡ ጌታ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ መደምሰሱን ማመስገን የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት ከቀበልን በኋላ ሐጢያቶቻችን በሚፈሱበትና ጌታ እኛን የመሰሉ ሴሰኛ ዘሮች የማዳኑን እውነታ በምናስታውስበት ጊዜ ሁሉ አመስጋኞች ነን፡፡ ያን ጊዜ ሁሌም አመስጋኞች መሆን እንችላለን፡፡

    በታሰሩት ሰዎች መካከል በጣም ብዙ የማይታመኑ እስረኞች አሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል አንዳንዶቹ ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹም ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸዋል፡፡ በዘረፋ የታሰሩ፣ በስርቆት የታሰሩና በብዙ እንግዳ የሆኑ ጥፋቶች የታሰሩ ብዙ ዓይነት ሐጢያተኞች አሉ፡፡ ቃሉን ለመስበክ እዚያ ስሄድ ‹‹መጋቢ ሐጢያት ሠርተህ አታውቅም? እኛ የታሰርነው ዕድለ ቢስ ስለሆንን ነው፡፡ እኛ ተይዘናል፡፡ ነገር ግን አንተ መጋቢው አሁን ውጪ ሆነህ እየኖርህ ነው፡፡ ምክንያቱም ተሸሽገህ በደምብ ሐጢያትን ስለምትሠራ አልተያዝክም፡፡ አንተ ከእኛ ብዙ የተሻልህ እንደሆንህ ታስባለህ? እነርሱ በዚህ መልኩ ያሰሩን ለምንድነው? ከአማካዩ ሕዝብ ጋር ስንነጻጸር ምን ሐጢያት ሠራን?›› ይላሉ፡፡ ስለዚህ እስረኞች ሐጢያት እንደሠሩ በጭራሽ አያስቡም፡፡

    ጠንከር ባለ አነጋገር እነርሱ በእርግጥም ትክክል ናቸው፡፡ እኛ አንድን ሰው እስከ ሞት ድረስ ባንደበድብም በልባችን ሰዎችን ጠልተናል፡፡ ይህም ከእግዚአብሄር ምልከታ አንጻር መግደልን መፈጸም ነው፡፡ ይህ ማለት ሰው አንድን ግለሰብ በተጨባጭ የገደለው ወይም ያንን ግለሰብ የጠላው የመሆኑ ጉዳይ በእግዚአብሄር ዓይኖች ተመሳሳይ ሐጢያት ሆነው ይቆጠራሉ ማለት ነው፡፡ ቃሉ እግዚአብሄር ውጫዊ ገጽታን ሳይሆን የግለሰቡን ልብ ማዕከል እንደሚመለከት ይናገራል፡፡ ስለዚህ እኛም ደግሞ መታሰር ይገባን ነበር፡፡

    ከረጅም ጊዜ በፊት ወደ እርሻ መሄድን ስናዘወትር በነበረ ጊዜ ከሰሌን በተሠሩ ምንጣፎች የተሸፈኑ ዕበቶች ነበሩ፡፡ የሰሌን ምንጣፎቼ እስካልተገለጡ ድረስ ዕበቶቹ ሊታዩ አይችሉም፡፡ ሰዎችም ደግሞ ልክ እንደዚያ በጣም የከረፉ ናቸው፡፡ የሰውን መልካምነትና አስመሳይ የጽድቅ ድርጊቶች ሽፋኖችን ስናነሳ በጣም ብዙ ሐጢያቶች እንዳሉባቸው እንደ ሰዎች የከረፋ ፍጥረት የለም፡፡ አንድ ግለሰብ ሽፋኖቹን ሙሉ በሙሉ ሲያነሳና በእግዚአብሄር ፊት ውስጡን ሲመለከት በእርሱ ውስጥ ሁሉም ዓይነት ሐጢያቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ጌታ በታማኝነት ‹‹እኔ እንዲህ ያለሁ ግለሰብ ነኝ›› ብሎ ያመነውን ግለሰብ በእርሱ አዲስ ኪዳን መሠረት በእውነተኛው ወንጌል ደህንነት ጻድቅ ግለሰብ አድርጎታል፡፡

    የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልነው በእግዚአብሄር ጽድቅ ምክንያት እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ የኢየሱስን እውነተኛ ደህንነት ባመጣልን የጥምቀት ጽድቅ ምክንያት የሐጢያቶችን ስርየት ተቀብለናል፡፡ ማንም ሰው በራሱ ጽድቅ የሐጢያቶችን ስርየት ሊቀበል አይችልም፡፡ የራሱ የሆነ አንዳች ጽድቅ የሌለው ግለሰብ በጌታ ሕልውና ፊት በመቅረብና ጌታ በሰጠው ጽድቅ በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ይቀበላል፡፡

    እግዚአብሄር ‹‹ትናንሽ ሐጢያተኞችን›› አላዳነም፡፡

    እግዚአብሄር ‹‹ትናንሽ ሐጢያተኞችን›› አያድንም፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሄር ‹‹እግዚአብሄር ሆይ እኔ ያሉብኝ ጥቂት ሐጢያቶች ናቸው›› የሚለውን ግለሰብ ቦታ አይሰጠውም ማለት ነው፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር የሚገደው ለማነው? እግዚአብሄር የሚመለከተው ‹‹እግዚአብሄር ሆይ እኔ ወደ ሲዖል ልሄድ ነው፡፡ እኔ ፈጽሞ የሐጢያት ክምር ነኝ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ እባክህ አድነኝ›› በማለት ሙሉ ሐጢያተኞች የሆኑ ሰዎችን ነው፡፡ ጌታ ‹‹አቤቱ አንተ ስታድነኝ ደህንነትን እቀበላለሁ፡፡ አንተ የማታድነኝ ከሆነ ሲዖል እወርዳለሁ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ የንስሐ ጸሎቶችን ማቅረብ አልችልም፡፡ የንስሐ ጸሎቶችን ካቀረብሁ በኋላም እንኳን እንደገና ሐጢያት እሠራለሁ፡፡ ጌታ ሆይ እባክህ አድነኝ›› ብሎ በመጸለይ ራሱን ሙሉ በሙሉ ለጌታ በአደራ የሚያቀርበውን ግለሰብ ያድነዋል፡፡

    አንድ ግለሰብ የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ከሐጢያቶቹ ማምለጥ አይችልም፡፡ ‹‹እግዚአብሄር ሆይ ማረኝ፤ ከሐጢያቶችም አድነኝ›› ብሎ የሚናገረው ግለሰብ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ሐጢያቶችን በራሱ ላይ በመውሰድ ለሐጢያቶቹ ሁሉ ማስተሰርያን እንዳደረገ በማመን ደህንነትን መቀበል ይችላል፡፡

    በኢሳይያስ መጽሐፍ ምዕራፍ 59 ቁጥር 1 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እነሆ የእግዚአብሄር እጅ ከማዳን አላጠረችም፤ ጆሮውም ከመስማት አልደነቆረችም፡፡››

    ሰዎች ከመጀመሪያውም የሐጢያት ክምር በመሆናቸው ምክንያት እግዚአብሄር ቅቡል እንደሆኑ አድርጎ ሊቆጥራቸው አይችልም፡፡ እግዚአብሄር አንድ ወይም ሁለት ሐጢያቶች ያሉበት ቢሆን አንድን ሰው ቅቡል አድርጎ ሊቆጠረው ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ማንኛውንም ግለሰብ በዚያ መልኩ ሊመለከተው ያልቻለው ሁሉም ሰው ሙሉ በሙሉ የሐጢያት ክምር በመሆኑ ነው፡፡ በኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ ያለው ቃል የእግዚአብሄር እጅ ከማዳን እንዳላጠረችና ጆሮዎቹም ‹‹እባክህ ሐጢያቶቼን ይቅር በል›› እያሉ የሚጮሁትን የጩኸት ቃሎች ከመስማት እንዳልደነቆሩ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ አለ፡- ‹‹ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፤ እንዳይሰማም ሐጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፡፡›› (ኢሳይያስ 59፡2) ይህ ማለት እግዚአብሄር የሰማይን በረከት፣ የሰማይን በር የከፈተ ቢሆንም እንኳን ሰዎች በእግዚአብሄር ዓይን በጣም ብዙ ሐጢያቶች ስላሉባቸው ማንም ወደዚያ ሊገባ አይችልም ማለት ነው፡፡

    የሐጢያት ክምር የሆነው ግለሰብ በየጊዜው ለሠራው የተወሰነ የተሳሳተ ነገር የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ይቅርታን አግኝቶ ቢሆን ኖሮ ያን ጊዜ ግለሰቡ ለሐጢያቶች ይቅርታ በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሄር ልጁን በገደለው ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ልጁን እየደጋገመ መግደል አይፈልግም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር እንዲህ አለ፡- ‹‹በየቀኑ የምትሠሩትን ሐጢያቶች ይዛችሁ ወደ እኔ አትምጡ፡፡ በፋንታው ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ በመደምሰስ ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ እንዲያድናችሁ ልጄን እልክላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ ልጄ የምትሠሩዋቸውን ሐጢያቶች በሙሉ እንዴት እንደወሰደ አስተውሉና ይህ እውነት እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ አይታችሁ ልጄ ለእናንተ በፈጸመው የደህንነት ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት ተቀበሉ፡፡ ይህ እጅግ ትልቅ ፍቅር ነው፡፡›› እርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹በልጄ በማመን ደህንነትን ተቀበሉ፡፡ እኔ የሆዋ አምላክ ልጄን እልክና የሕዝቡን የሐጢያት ክምሮች ሁሉ፣ የግል ሐጢያቶች ሁሉና በደሎች ሁሉ እደመሰሳለሁ፡፡ በልጄ እመኑና የሐጢያት ክምር ከሆነው በሐጢያት የተሞላ ማንነታችሁ ደህንነትን ተቀበሉ፡፡››

    መጽሐፍ ቅዱስ በግለሰብ ልብ ውስጥ ምን ዓይነት ሐጢያት እንዳለ መዝግቦዋል፡፡ በኢሳይያስ መጽሐፍ ምዕራፍ 59 ከቁጥር 3 እስከ 8 ያሉትን ቃሎች እናንብብ፡- ‹‹እጃችሁ በደም ጣታችሁም በበደል ረክሳለች፤ ከንፈራችሁም ሐሰትን ተናግሮአል፤ ምላሳችሁም ሐጢአትን አሰምቶአል፡፡ በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በምናምንቴ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጉዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል፡፡ የእባብን እንቁላል ቀፈቀፉ፤ የሸረሪትንም ድር አደሩ፤ እንቁላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፤ እንቁላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል፡፡ ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑላቸውም፤ በሥራቸውም አይሸፈኑም፤ ሥራቸው የበደል ሥራ ነው፤ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው፡፡ እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፤ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የሐጢአት አሳብ ነው፤ ጉስቁልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ፡፡ የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በአካሄዳቸውም ፍርድ የለም፤ መንገዳቸውን አጣምመዋል፤ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም፡፡››

    እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፡- ‹‹እጃችሁ በደም ጣታችሁም በበደል ረክሳለች፤›› ይህ ማለት አንድ ግለሰብ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እርሱ ወይም እርስዋ ሐጢያትን ይሠራሉ ማለት ነው፡፡ ሰው የሚሠራው እያንዳንዱ ነገር ሐጢያት ነው፡፡ ቀጥሎ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ከንፈራችሁም ሐሰትን ተናግሮአል፤›› ይህ ማለት ሰው የሚናገረው ሁሉ ውሸት ነው ማለት ነው፡፡ ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፤ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና፡፡›› (ዮሐንስ 8፡44) ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎች ‹‹ይህንን የምናገረው ከልቤ ነው›› ወይም ‹‹እውነት እልሃለሁ›› የሚሉ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ እነርሱ በሚናገሩት ነገር ሁሉ ‹‹ከልቤ›› ወይም ‹‹በእውነት›› የሚለውን ቃል ያያይዛሉ፡፡ ነገር ግን ከልባቸው የተናገሩዋቸው ይሁኑም አይሁኑም ሁሉም ውሸቶች ናቸው፡፡ የተጻፈው ቃል ይህንን ይመሰክራል፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐሰትን ሲናገር [ዲያብሎስ] ከራሱ ይናገራል፡፡››

    የተለየ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው እንደዚያ ነው፡፡ ሐጢያት ከግለሰብ ውስጥ በግድየለሸነት ይፈስሳል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት እያንዳንዱ ሰው የሐጢያት ክምር በመሆኑ ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሄር ሐይል በጣም አስገራሚ ነው፡፡ እንዲህ የሐጢያት ክምር የሆነው ግለሰብ ከሐጢያቶች ደህንነትን የሚቀበለው በእግዚአብሄር ሐይል ነው፡፡ ሰው ሲበሳጭና ሲቅበጠበጥ ሐጢያት ይፈስሳል፡፡ የሰው ልብ ሰላም በሆነና ስጋም ምቾት በተሰማው ጊዜም እንደዚሁ ሐጢያት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ይፈስሳል፡፡ ሁኔታው ምንም ይሁን ሐጢያት በዚያ መልኩ ይፈስሳል፡፡ አስገራሚው ነገር ግን ሐጢያቶቹ የሚፈስሱበት እንዲህ ያለው ሐጢያተኛም እንኳን ከጌታችን የሐጢያቶችን ስርየት ሊቀበል የሚችል መሆኑ ነው፡፡ ጌታ እንዲህ ያሉ ሐጢያተኞችን ለማዳን መጣ፡፡ ራሳችሁን እንድታውቁና በውሃና በመንፈስ በመጣው ኢየሱስ በማመን ከሐጢያቶቻችሁ ደህንነትን እንድትቀበሉ እፈልጋለሁ፡፡

    በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 7 ላይ ያለው ቃል የሰው ጥንተ አብሶ (ሐጢያት) ምን እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ሰዎች ጥንተ አብሶን (ሐጢያትን) በሚመለከት የራሳቸው ግላዊ ዝንፈት አላቸው፡፡ ሰዎች የራሳቸው ግላዊ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1