Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ
የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ
የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ
Ebook113 pages44 minutes

የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በርካታ ተፈላጊ መጽሐፍ የጻፉና ከእነዚሁም ውስጥ “ታማኝነትና ታማኝ አለመሆን” የተባለው በዓለም ላይ ታዋቂ በሆነውን መጽሐፋቸው ይታወቃሉ። በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ዲኖምኔሽን ኦርጂኔትድ ፍሮም ዘ ላይትሃውስ ግሩፕ ኦፍ ቸርች (United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches) ተብሎ የሚጠራው ቤተ ክርስቲያን መስራች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሶስት ሺህ ቤተክርስቲያኖች አሉት።
ዳግ ሂዋርድ ሚልስ፣ በዓለማቀፍ ደረጃ ወንጌላዊ ሲሆኑ “ፈዋሹ ኢየሱስ ክሩሴድ (HEALING JESUS CRUSADE) ” በተሰኘው እና በአለም ዙሪያ በተለያዩ ኮንፈረንሶች ላይ በአገልግሎታቸው ይታወቃሉ፡፡ ይበልጥ መረጃ ከፈለጉ ድህረ ገጻቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.

Languageአማርኛ
Release dateAug 14, 2018
ISBN9781641348010
የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ

Related ebooks

Reviews for የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የዝግጅት ሥነ ሥርዓት መጽሐፍ - Dag Heward-Mills

    የስም ስያሜ ስነ ስርዓት ባህላዊ ኩነት ሲሆን ህጻን ልጅ ከተወለደ በኋላ የሚከናወን ነው፡፡ አንዳንድ ቤተሰቦች እጅግ ባህላዊ ከመሆናቸውም በላይ ከኩነቱ ጋር በተያያዘ በዕለቱ እና በጊዜው ይመራሉ፡፡ እዚህ ጋር የመጋቢው ሚና በዋናነት የክብረ በዓሉን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና መንፈሳዊ ይዘት ማስተዋወቅ ነው፡፡ በርግጥ ይህ በወላጆች ጥያቄ እና ፈቃድ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

    1. የመክፈቻ ጸሎት

    2. አምልኮ፡ ኑና እርሱን እንውደድ

    ኑና እርሱን እንውደድ             እርሱ ብቻ የተገባው ነውና

    ኑና እርሱን እንውደድ             እርሱ ብቻ የተገባው ነውና

    ኑና እርሱን እንውደድ             እርሱ ብቻ የተገባው ነውና

    ክርስቶስ ጌታን                     ክርስቶስ ጌታ

    3. የስነ ስርኣቱ ምክንያት

    ዛሬ በዚህ ከወንድማችን እና ከእህታችን፣ አቶ እና ወ/ሮ . . . (ሙሉ ስማቸው ይጠቀሳል) የተሰበሰብነው በሁለት ምክንያት ነው፤

    1. እግዚአብሔር ባደረገላቸው ነገር ሃሴት ለማድረግ እና

    እግዚአብሔር ባደረገላቸው ነገር ሃሴት ለማድረግ ማንኛውም ለምናደርገው ነገር መሰረት መጽሐፍ ቅዱስ ስለሆነ ለዛሬ የምናነበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡

    የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች።

    ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።

    በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ።

    እናቱ ግን መልሳ። አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።

    እነርሱም፦ ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት።

    አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት።

    ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።

    ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ። 

    ሉቃ 1፡57-64

    በዚያ ዘመን ይደረግ እንደነበረው እኛም የህጻኑን አባት መስጠት የፈለገውን የልጁ/ልጆቹ ስም/ስሞች እና ትርጉሙን/ትርጉማቸውን እንዲናገር እድል እንሰጣለን፡፡

    4. ስም በአባት ይሰጣል (አባት ይነሳና የልጁን/ልጆቹን ሙሉ ስም እንዲሁም ትርጉሙን/ትርጉማቸውን ይናገራል)

    5. የልጁ ስም ይታወጃል፣ ይቀደሳል ይጸናል

    1. አገልጋዩ  ወስዶ ህጻኑን ከታቀፈ በኋላ ታዳሚውን ሁሉ እንዲቆሙ ይጠይቃል፡፡

    2. አገልጋዩ በህጻኑ ላይ እጁን ጭኖ ከጸለየ በኋላ ዘይት ይቀባዋል፡፡

    6. ጸሎት

    አገልጋዩ፡ አባት ሆይ በአንድያ ልጅህ በኢየሱስ ስም ዛሬ ስለተሰጠው ስም/ስሞች እናመሰግንሃለን፡፡ ይህንን/እነዚህን  ስም/ስሞች እንቀድሳለን እናም የልጁ ስም/ስሞች  . . . በማለት እናውጃለን… ከዛሬ ጀምሮ የስሙን ትርጉም መኖር እንዲችል እጸልያለሁ፡፡

    አገልጋዩ የልጁን ስም በማውሳት የስሙን ዓላማ መኖር እንዲችል ይጸልይለታል፡፡ (ለምሳሌ፡ ዮሐንስ˝ ማለት ያህዌ ቸር ነው˝ ማለት ሲሆን ለዚህ ህጻን ሁልጊዜም ያህዌ ቸርነት ያድርግለት˝)

    አገልጋይ፡ ይህንን ህጻን የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ በሆነው በዘይት እቀባዋለሁ፤ በዚህም በህይወት ዘመኑ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ይሆን ዘንድ ነው፡፡ አሜን፡፡

    7. መዝሙር፡ የበረከት ዝናብ

    የበረከት ዝናብ ይሆናል፤       የበረከት ዝናብ

    ይህ የአምላክ ተስፋ ነው፤      የምንለምነው የበረከት ዝናብ

    የመታደስ ዘመን ይሆናል፤      የምህረቱ ጠል ይንጠባጠባል

    ከላይ ከአዳኙ የሚመጣ/ የምንለምነው ዝናብ

    8. ለህጻኑ ቡራኬ የመስጠት ጊዜ

    አገልጋዩ፡ አባት ሆይ በጎ እና ፍጹም ስለሆነው ስለ ህይወት ስጦታ በርግጥ እናመሰግንሃለን፡፡ ይህንንም ቤተሰብ በዚህ ልጅ ስለባረካቸው ተመስገን፡፡ በዚህ ልጅ ህይወት እና ስም ላይ የሚሰነዘር ማናቸውንም መርገም እና የጠላት ሃሳብ እሰርዛለሁ፣ አመክናለሁ፣ እገለብጣለሁ እንዲሁም አስወግዳለሁ፡፡

    በዚህ ልጅ ህይወት እና ስም ላይ ከፍ የሚልን ማናቸውም የሚቋቋም የተቃውሞ ምሽግ፣ ተገዳዳሪ፣ አስጨናቂ ነገርን ሁሉ አፈርሳለሁ፡፡ በዚህ ህጻን ህይወት ላይ ጠላት ባቀደው፣ ባለመውና ባነጣጠረው ፈንታ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲበረታ እና እንዲያይል ጸለይኩ፡፡

    በህይወትህ ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እናገራለሁ፡፡

    በህይወትህ ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር በጎነትና ሞገስ እድል ፈንታህ ይሁን፡፡

    ለወላጆችህ በረከት ሆነህ ኑር፡፡

    ለትውልድህ በረከት ሆነህ ኑር፡፡

    እግዚአብሔር እንድትሆን የወሰነውን ሁን፡፡ ብርቱ በሆነው በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

    9. ማሳሰቢያ ለወላጆች

    አገልጋዩ፡ ይህ ህጻን ባደገ ጊዜ ፈቀቅ እንዳይል በጌታ መንገድ በመምራት ለማሳደግ ቃል ትገባላችሁን?

    በዘዳግም 6፡7 መሰረት "የእግዚአብሔርን ቃል በቤት ስትቀመጡ ፣በመንገድ ስትሄዱ፣ ስትተኙም፣ ስትነሱም ልታስተምሩት ቃል ትገባላችሁን?˝

    አባት፡ አዎን፡፡

    እናት፡ አዎን፡፡

    ሁለቱም ወላጆች በጋራ፡ አዎን፡፡

    አገልጋዩ፡ አሜን! እናጨብጭብላቸው! (አገልጋዩ ልጁን ለወላጆቹ ይመልሳል)

    10. መዝሙር፡ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን

    ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን          ጌታ ይመስገን! ጌታ ይመስገን

    ታላቅ ነገር አድርጓል                   ምድር ድምጹን ትስማ

    አለምን ስለወደደ                      ጌታ ይመስገን! ጌታ ይመስገን!

    ልጁን ሰጠን                            ህዝቦች ደስ ይበላቸው

    እርሱም ህይወቱን ሰጠን               ኦ ወደ አብ በልጁ በኢየሱስ ኑ

    ለሐጢያታችን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1