Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ልጄ ሆይ ትችያለሽ
ልጄ ሆይ ትችያለሽ
ልጄ ሆይ ትችያለሽ
Ebook164 pages3 hours

ልጄ ሆይ ትችያለሽ

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ይህ መጽሐፍ የሴት ልጆችን ጉዳት ይፈውሳል! በእዚህ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረ መጽሐፍ፣ ሴቶች የሚገጥሟቸውን በርካታ አዳጋች ሁኔታዎችን በእግዚአብሔር ጥበብ እርዳታ እንዲያሸንፉ ይነሳሳሉ፡፡ ይህን በተለይ ለሴት ልጆች የተጻፈ ኃይለኛና አዲስ መጽሐፍ ስታነብቢ እግዚአብሔር ሕይወትሽን በመንካት ያበረታሻል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954324
ልጄ ሆይ ትችያለሽ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ልጄ ሆይ ትችያለሽ

Related ebooks

Reviews for ልጄ ሆይ ትችያለሽ

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ልጄ ሆይ ትችያለሽ - Dag Heward-Mills

    ልጄ ሆይ ትችያለሽ

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    ስለ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ

    በዚህ ኢሜይል ይጻፉ፡- evangelist@daghewardmills.org

    ዌብሳይታቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.

    በፌስቡክ፣ Facebook: Dag Heward-Mills

    በትዊተር፣ Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-61395-432-4

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    ስልክ +251912063821

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    መታሰቢያ

    ለውድ ባለቤቴ አደላይድ፣ የኔ ተወዳጅ፣ በአገልግሎት ውስጥ አማካሪዬና የሥራ ባልደረባዬ፡፡ ልክ እኔ እንደማፈቅርሽ ስለምታፈቅሪኝ አመሠግናለሁ፡፡ ለጥሩ እገዛሽ እና ለጥሩ ምክርሽ አመሠግናለሁ፡፡ በህይወታችን ውጣ ውረድ ውስጥ ጸንተሻል፡፡ ስለ አገልግሎት ስለምታስቢና መንፈሣዊ ስለሆንሽም አመሠግናለሁ፡፡ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ አብረሽ ስለምታገለግዪ እና ቤተክርስቲያንን ስንገነባ ስለረዳሽኝ አመሠግናለሁ፡፡ ሁልጊዜ አፈቅርሻለሁ፡፡

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው፡፡

    ማውጫ

    1. ሴቶች

    2. ሴት ልጆች

    3. መሸፈኛው

    4. ልጄ ሆይ፣ ይህ ክብርሽ ነው!

    5. ልጄ ሆይ፣ ይህ የአንቺ ተራ ነው

    6. የሴት ልጆች ፈተና

    7. የሴት ልጆች ኃጢአቶች

    8. ልጄ ሆይ፣ተሳክቶልሻል!

    9. ያለሽን ሁሉ ቢያስከፍልሽም፣ ማስተዋልን ገንዘብሽ አድርጊ

    10. ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ከወዴት መጣ

    11. ሰባቱ የሴቶች መሰናክሎች

    12. የሴቷ ቁልፎች

    13. ልጄ ሆይ፣ እየተጠባበቅሽ ሳለ

    14. ልጄ ሆይ፣ ቅባቱን ያዥ

    15. ልጄ ሆይ፣ የሆነ ቦታ ላይ መርገም ይኖር ይሆን ?

    16. ሴቶች መንፈሳዊያን መሆን የሚያስፈልጋቸው ለምንድን ነው

    17. የሴቷን ዘር መረዳት

    18. ልጅ ከመውለድ ጋር የተያያዘውን መርገም መረዳት

    19. ልጅ ከመውለድ ጋር የተያያዘውን መርገም ማሸነፍ

    20. ከጋብቻ ጋር የተያያዘውን መርገም መረዳት

    21. ከጋብቻ ጋር የተያያዘውን መርገም ማሸነፍ

    22. ልጄ ሆይ፣ የሚያሳሱ ዓይኖች አሉሽ

    23. ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ባል ይሰጥሻል

    24. ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጥሻል

    25. ልጄ ሆይ፣ ጌታን ማገልገልሽን ቀጥይ

    26. ልጄ ሆይ፣ ኃላፊነትሽን መወጣት አትሰልቺ

    27. ስለ አቢግያዊነት

    28. የአቢጊያዊነት ስድስት ግቦች

    29. የአቢግያዊነት እርምጃዎች

    30. ልጄ ሆይ፣ ልትተኪ ትችያለሽ!

    31. ልጄ ሆይ፣ ለባልሽ ትታዘዣለሽን?

    32. ልጄ ሆይ፣ ቦታሽን ጠብቂ

    33. ባለ ዓላማዋ ልጄ ሆይ

    ምዕራፍ 1

    ሴቶች

    ይህን መጽሐፍ የምጽፈው ለሴቶች ነው፡፡ መልእክቱም በሁሉም ቦታ ላሉ ሴቶች ነው፡፡ ሴቶች ከወንዶች ለየት ብለው ስለተፈጠሩት ልዩ መልእክት እንሚገባቸው አምናለሁ፡፡

    ኢየሱስ ሴቶችን በሁለት የተለያዩ ጎራዎች ፈርጇቸዋል፡፡ ሴቶች አለበለዚያ ደግሞ ሴት ልጆች በማለት ይጠራቸው ነበር፡፡

    በሴት እና በሴት ልጅ መካከል ልዩነት አለ፡፡ እኔ ሴት ብሆን ኖሮ ኢየሱስ ሴት ልጄ ብሎ እንዲጠራኝ እወድ ነበር፡፡ እንደ እኔ መረዳት ሴት ልጅ በጥቅሉ ሀሳብን የምትቀበል፣ በጣም ግልጽ እና ትሁት ነች፡፡ በተፈጥሮ፣ በዕድሜዋ ትልቅ የሆነች ሴት እንደ ሴት ልጅ በቀላሉ ተጽዕኖ ሊደረግባት አይችልም፡፡

    የሕይወት መራርነት

    ብዙ ሴቶች ከሕይወት ልምምዳቸው የተነሳ መራራዎች ሆነዋል። እነርሱ ልበ ደንዳናና፣ ይቅር የማይሉ፣ ምህረት የማያደርጉ ናቸው፡፡ ሕመም የበዛበት የሕይወት ልምምዳቸው የእምነትንና የታማኝነትን ውበት ከውስጣቸው አጥቦ ወስዶታል፡፡ በመሆኑም እንደዚህ ይላሉ፣ በጭራሽ ወንድን አትመኑ፡፡ ለራሳቸውም እንደዚህ ሲሉ ይናገራሉ፣ ሌላዋን ሴት በጭራሽ አትመኚ፡፡ እኔ ምን ያህል ሴቶች በብቸኝነት እንደሚኖሩ ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህ ሴቶች ካለ ምንም ጓደኛ የሚኖሩ ብቸኞች ናቸው፡፡

    ኢየሱስ ሳምራዊት ሴት እንዴት እንዳናገራት ልብ በይ፡፡ የሚያናግራትን ነገሮች እንድታምን ለማድረግ እየሞከረ ነበር፡፡

    . . . አንቺ ሴት እመኚኝ፣ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፡፡

    ዮሐንስ 4፡21

    ኢየሱስ በዝሙት የተያዘችውን ሴት እንዴት እንዳናገራት ተመልከች፣ ይህች ሴት ይቅርታን ማድረግ በማያውቁ ወንዶች እጅ ሕይወቷ ልታልፍ የተቃረበች ሴት ነበረች፡፡ ኢየሱስ እንደገና በፍቅር እንድታምን ፈልገ፡፡

    . . . አንቺ ሴት፣ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት እርሷም፡- ጌታ ሆይ፣ አንድ ስንኳ አለች፡፡ ኢየሱስም፡- እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢያት አትሥሪ አላት።

    ዮሐንስ 8፡10፣11

    ለአሥራ ስምንት ዓመት በሰውነት መጉበጥ (ስኮሊዮሲስ) በሽታ ስትሰቃይ የነበረችወንም ሴት ኢየሱስ እንዴት እንዳናገራት ደግሞ ልብ በይ፡፡ ይህቺ ሴት በብዙ ነገር ውስጥ ያለፈች ናት፡፡ ለረዥም ዘመን በምሬትና በሕመም ውስጥ ነበረች፡፡ ይህች ሴት ተአምራትን ትፈልግ ነበር፡፡ ኢየሱስ በቤተ ክርሰቲያን ውስጥ እንዴት እንዳናገራት ልብ በይ፡፡

    . . . አንቺ ሴት፣ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፣ እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች፡፡

    ሉቃስ 13፡ 12፣13

    ምዕራፍ 2

    ሴት ልጆች

    በጥቅሉ ስንናገር፣ ሴት ልጆች መራርነትንና ምህረት የለሽነትን የተሞሉ አይደሉም፡፡ ጣፋጭነትና እውነተኝነት የሴት ልጆች መለያ ባህሪያቸው ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሴት ልጅ መገለጫዋ በአባቷ ላይ ያላት መታመንና መደገፍ ነው፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ፣ ሴት ልጆች ዕድሜ እየጨመሩ ሲሄዱና ትልቅ ሴት ሲሆኑ እምነታቸው፣ ተሰፋቸውና ፍቅራቸው ሁሉ እየደበዘዘ ይሄዳል፡፡

    ኢየሱስ የተወሰኑ ሴቶችን ልጆቼ ብሎ ጠርቷቸዋል፡፡ ይህም በእሱ ላይ ካላቸው እምነት የተነሳ እንደ ነበር አምናለሁ፡፡ ለእርሱ ያላቸውን ንጹህ ፍቅር ተመልክቷል፡፡

    እስኪ አሁን ደግሞ ኢየሱስ ስላገለገላቸው ሴቶች እንመልከት፡፡ አሁን ኢየሱስ እንዴት በተለያየ መንገድ እንዳናገራቸው እንመለከታለን፡፡

    ኢየሱስ ካደረጋቸው ታላላቅ ተአምራቶች አንዱ በሆነው ደም ይፈሳት በነበረችው ሴት ታሪክ ውስጥ፣ ኢየሱስ ይህችን ሴት፣ ልጄ ብሎ ሲጠራት እንመለከታለን! ምንም እንኳን በዙሪያው ይጋፉት የነበሩት ምንም ነገር ባይሰማቸውም ይህች ሴት ቅባቱን መንካት ችላ ነበር፡፡

    . . . ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነቷ አወቀች፡፡

    ማርቆስ 5፡29

    ኢየሱሱ ግን፣ አንድ ሰው ነክቶኛል፤ ኀይል ከእኔ እንደወጣ ዐውቃለሁና አለ።

    ሉቃስ 8፡46 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

    ስለዚህች ሴት እንድትገነዘቢ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በኢየሱስ ችሎታ ላይ ትልቅ መታመን ነበራት። እያመማትና እየደከማት በሕዝቡ መካከል ተጋፍታ የኢየሱስን የልብሱን ጫፍ ነካች፡፡

    ለእዚህች ሴት በእዚያ ሁሉ በሚጋፋ ሰው መካከል ሰንጥቆ ለማለፍ ትልቅ እምነት እንዲኖራት ያስፈልጋል፡፡ ያ እምነቷና መተማመኗ ነው በትክክል ታላቅ ሴት ልጅ ያደረጋት፡፡ ለአሥራ ሁለት ዓመት ያህል ከብዙ ሰዎች ጋር ያሳለፈቻቸው መራራ የመከራ ጊዜያት የእምነት ልቧን አላጠፋባትም ነበር፡፡

    ተጠራጣሪ ሴቶች

    አንዳንድ ጊዜ፣ አንዲት ሴት ከብዙ ወንዶች ጋር ከነበራት ብዙ ዓይነት የኀጢአት ልምምድ ወንዶችን እንዳታምን ሁኔታዎችን አስቸጋሪ ያደርግባታል፡፡ እንደዚህ ዓይነቷ ሴት በአባቷ፣ በመጋቢዋ፣ ወይም በማንኛው የእግዚአብሔር ሰው በሆነ ወንድ ላይ የሚኖራት እምነት በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ይህች ሴት በመልካምነትና በንጽህና ይኖራል ብላ በቀላሉ ማመን አትችልም። አንዳንድ ጊዜ በጥርጣሬና በሀሜት ባህል ውስጥ ማደጓ በውስጧ የጥርጣሬ ዘር ለዘላለም እንዲዘራባት ሊያደርግ ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሴቶች ለዘለቄታው ተጠራጣሪ እና የማያምኑ ይሆናሉ፡፡ በተለይ፣ በሌሎች ለመተማመን የማትችል ሴት ለማፍቀርም አትችልም፡፡ በፍርሃት የተሞላች ነች፡፡ እውነተኛ ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡-

    ፍቅር. . ሁሉን ያምናል . . .

    1ኛ ቆሮንቶስ 13፡7

    ሴት ልጆች የአባቶቻቸውን ቅባት ይቀበላሉ

    ሌላው የእዚህች ሴት ልጅ (ደም ይፈሳት የነበረችው ሴት) አስደናቂ መለያዋ የኢየሱስን ቅባት መቀበሏ ነበር፡፡ ይህ ክፍል፣ ሁለቱም ሰዎች በግልጽ እየተሰማቸው ቅባት ከአንዱ ወደ ሌላው ሲተላለፍ የምናይበት ብቸኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ነው፡፡ ኢየሱስ ቅባት ከእርሱ ሲወጣ ተሰምቶታል፤ ይህች ሴት ልጅም ቅባት ወደ ሰውነቷ ሲገባ ታውቋታል፡፡

    አየሽ፣ ከወላጆቻቸው የከበረ ስጦታ የሚቀበሉ ልጆች ናቸው፡፡ ከአባቶቻቸው ውርስ የሚቀበሉት ልጆች እንጂ ባልንጀሮች ወይም የሥራ ባልደረቦች አይደሉም፡፡

    በሴት ሕይወት ውስጥ የወንድን ሥልጣን የምትገዳደርበት ዘመን መጥቷል፡፡ እኔ እርሷን አልኮንናትም፤ ምክንያቱም ብዙ ወንዶች ኀላፊነት የማይሰማቸውና ታማኞች ስላልሆኑ ነው፡፡

    ነገር ግን፣ ወንዶችን በመቃወም መዋጋት እንደዚሁም የእነርሱን ሥልጣን በመቃወም የምታደርጊው ዘመቻ በቀላሉ ከቅባቱ ሊያርቅሽ ይችላል፡፡ በእግዚአብሔር ስጦታ ላይ የማያቋርጥ የተቃውሞ አመለካከት ይኖርሻል፡፡ አየሽ፣ አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው ዕቃዎች ወንዶች ናቸው፡፡

    አንድን ሰው

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1