Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)
በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)
በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)
Ebook528 pages4 hours

በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ይህ መጽሐፍ ዘግይቶ በተከሰተው ጥንታዊ ታሪክ ውስጥ የተፈጠረው የኒቅያውያን የሐይማኖት መግለጫ ምን ያህል በዛሬው ክርስትና ውስጥ መጥፎ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ያብራራል፡፡
በዚህ ዘመን ዳግመኛ የመወለድን እውነት ለመገናኘት ጥቂት ጨምራችሁ ማጥናት አለባችሁ፡፡ እስከ አሁን ድረስ ስላመናችሁበትም የእምነት መግለጫ ይበልጥ በጥልቀት ማጥናት ያስፈልጋችኋል፡፡
አሁን ከኒቅያውያን የሐይማኖት መግለጫ ውስጥ የተገደፈውንና በአጥማቂው ዮሐንስ በኩል የሆነውን የኢየሱስ ጥምቀት ትርጉም ማወቅ አለባችሁ፡፡ በመሆኑም ይህ በልባችሁ ውስጥ እውነተኛ ደስታን ለመቀበል ዕድል ሊሆን ይገባል፡፡
አሁን ኢየሱስ በተቀበለው ጥምቀት ውስጥ ያለውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እውነተኛ ዋጋ ትገነዘባላችሁ፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት ቃል ምን ያህል በነፍሳችሁ ላይ ተጽዕኖ እንደሳደረ ይበልጥ በጥልቀትና በግልጥ ወደ ማወቅ ትመጡና በእምነት ለእግዚአብሄር ክብርን ትሰጣላችሁ፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateApr 21, 2024
ISBN9798224174690
በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)

Related to በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)

Related ebooks

Reviews for በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I) - Paul C. Jong

    Sermon0101

    ጌታ ከሐጢያቶች የሚያድነው ማንን ነው?

    << ሉቃስ 23:32-43 >>

    ‹‹ሌሎችንም ሁለት ክፉ አድራጊዎች ደግሞ ከእርሱ ጋር ይገደሉ ዘንድ ወሰደ፡፡ ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ በዚያ እርሱን ክፉ አራድጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ፡፡ ኢየሱስም፡- አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ፡፡ ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት፡፡ ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር፡፡ መኳንንቱም ደግሞ፡- ሌሎችን አደነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ ራሱን ያድን እያሉ ያፌዙበት ነበር፡፡ ጭፍሮችም ደግሞ ወደ እርሱ ቀርበው ሆምጣጤም አምጥተው፡- አንተስ የአይሁድ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን እያሉ ይዘብቱበት ነበር፡፡ ይሀ የአይሁድ ንጉሥ ነው ተብሎ በግሪክና በሮማይስጥ በዕብራይስጥም ፊደል የተጻፈ ጽሕፈት ደግሞ በእርሱ ላይ ነበረ፡፡ ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ፡- አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን ብሎ ሰደበው፡፡ ሁለተኛው ግን መልሶ፡- አንተ እንደዚህ ባለ ፍርድ ተይዘህ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው፡፡ ኢየሰስንም፡- ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው፡፡ ኢየሱስም፡- እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው፡፡››

    አሁን በዚህ ዓለም ላይ እየኖረ ያለው የሰው ዘር ወደ መጨረሻው ማብቂያ እየነጎዓለም አቀፉ የአቅርቦት ሰንሰለት ነው፡፡ የአየር ንብረት ቀውስ ለዚህች ፕላኔት ምድር ከበድ ያለ አደጋ በመሆኑ እያንዳንዱ አገር ኢንዱስትሪን እንደገና በማዋቀር አማካይነት የካርቦን ልቀቶችን ለመቀነስ ያቀደ ፖሊሲዎችን ለመተግበር መላው ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ ፊርማውን አኑሮዋል፡፡ መላው ዓለም እንደገና የድህረ ቀዝቃዛውን ጦርነት ዘመን እያጥለቀለቀ ባለው የሥነ ከባቢ ጦርነት ተይዞዋል፡፡ ቀጣይነት ካለው ወረርሽኝ፣ ጦርነትና ጥሬ ዕቃዎችንና ምግብን ከመሰወር በመነጨ መልኩ ዓለም አቀፉ የአቅርቦት ሰንሰለት መናወጡን ቀጥሎዋል፡፡ ግሽበትም ከቁጥጥር ውጪ በመሆን ድህነትን ለማምጣት የሚያሰጋ ሆንዋል፡፡ በዕዳ ቀውስ እየታገሉ ያሉ አገሮች አሉ፡፡ በዚህ ሁሉ መካከልም በ21ኛው ምዕተ ዓመት ታላላቆቹ ሐይሎች እርስ በርሳቸው ለጀግንነት በመፎካከር ላይ ናቸው፡፡ ይህና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች መላውን ዓለም እያናወጡና በአገራቶች መካከል እየተቃረበ የመጣ ጦርነት እንዳለ ምልክቶችን እያሳዩ ናቸው፡፡

    በእነዚህ ቀኖች ዓለም ምን ያህል በፍጥነት እየተለወጠ እንደሆነ ስንመለከት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈው የሐመሩ ፈረስ ዘመን እየተቃረበ የመጣ ይመስላል፡፡ በዚያ ዘመን መላው ዓለም በአንድ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ሥር ይሰበሰብና በጸረ ክርስቶስ ይተዳደራል፡፡ ይህ ቀን ይበልጥ እየተቃረበ ይመስላል፡፡ ይህ ዘመን በሚጀምርበት ጊዜ በዓለም ዙሪያ ያሉ ብሔራዊ መሪዎች በአሁኑ ጊዜ ባለው እንደ ተባበሩት መንግሥታት ባሉ የዓለም ድርጅቶች አማካይነት አንድ ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ የዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሥነ ከባቢያዊና ስደተኞችን የሚመለከቱ ችግሮችን ለመፍታት የጋራ የሆነ ምላሽ ለመስጠት ይሞክራሉ፡፡

    ይህ ዓለም እየተለወጠ በሄደ መጠን እኛም እንደዚሁ ከፊት ለፊታችን ያሉትን ታላላቅ መንፈሳዊ ለውጦች እንመለከታለን፡፡ የጸረ ክርስቶስ መገለጥ በዚህ ፍጥነት እየቀረበን ከሆነ ኢየሱስ በጥምቀቱ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የተሸከመበትንና የአማኞቹን ሐጢያቶች ያነጻበትን የወንጌል እውነት ለመስበክ ይበልጥ በፍጥነት መንቀሰቀስ እንዳለብን አምናለሁ፡፡ ሁላችንም የጸረ ክርስቶስን ዘመን መቋቋም የሚችል እምነት ማዘጋጀት አለብን፡፡ ያንን ለማድረግ ጌታ በተቀበለው የጥምቀት ቃል በማመን ዳግመኛ መወለድና በዚህ ዳግመኛ የመወለድ እምነትም የጌታን መመለስ መጠበቅ አለብን፡፡

    ከኢየሱስ ጋር አብረው የተሰቀሉት ሁለቱ ወንጀለኞች፡፡

    በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ከኢየሱስ ጋር አብረው የተሰቀሉ ሁለት ወንጀለኞችን እናያለን፡፡ እነዚህ ሁለት ወንጀለኞች ሁለት የተለያየ ዓይነት እምነት ያላቸውን ሁለት ዓይነት ክርስቲያኖች ያሳዩናል፡፡ ከሁለቱ ወንጀለኞች አንዱ ኢየሱስን አዳኙ አድርጎ አላመነም፡፡ ሌላው ግን የእርሱን ጽድቅ ተገነዘበ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ችሎት ሞት በተፈረደበት ጊዜ የተፈረደበት በዚህ ዓለም ላይ አንዳች ወንጀል በመሥራቱ አልነበረም፡፡ የተፈረደበት ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ በመውሰዱ ብቻ ነበር፡፡ እርሱ የተፈረደበት ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ በራሱ ላይ በመውሰዱ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ መሸከሙ የሰውን ዘር ሐጢያቶች ለማንጻት የፈጸመው የመታዘዝ ድርጊት ነበር፡፡

    ሆኖም ሰዎች በዚህ ዘመን የኢየሱስን ጽድቅ ያልተገነዘበውን ወንጀለኛ የሚመስሉ ናቸው፡፡ እነርሱ በእግዚአብሔር ቃል በማመን ፋንታ በንስሐ ጸሎት አስተምህሮትና ቀስ በቀስ በሚገኝ ቅድስና አስተምህሮት ያምናሉ፡፡ እነዚህ አስተምህሮቶች በመካከለኛው ዘመን የነበሩት የፕሮቴስታንት የተሐድሶ ሰዎች የኒቅያን የሐይማኖት መግለጫ እምነት እንዳለ በወረሱ ጊዜ የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት የታቀዱ ሰው ሰራሽ ዶግማዎች ናቸው፡፡ ሰዎች በእነዚህ አስተምህሮቶች በማመን ከሐጢያቶቻቸው መንጻት እንደሚችሉ አስበዋል፡፡ እነዚህን አስተምህሮቶች የፈጠሩት የነገረ መለኮት ምሁራንም ትልቅ ምስጋናና ክብርን ተቀብለዋል፡፡ ሆኖም እኛ ዛሬ የምንፈጽማቸውን እጅግ ብዙ ሐጢያቶች በተጨባጭ ማንጻት የሚችል ትምህርት የትም ቦታ የለም፡፡ ከዚህም በላይ በ21ኛው ምዕተ ዓመት እየኖሩ ያሉ ሰዎች የሠሩዋቸው ሐጢያቶች ቀደም ያሉት ትውልዶች ከሠሩዋቸው ሐጢያቶች ጋር ሲነጻጸሩ አስከፊ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስላል፡፡

    በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶችን ያቀረባችሁ ብትሆኑም አሁንም እስከዚህ ቀን ድረስ መፍትሄን ካላገኙት ሐጢያቶቻችሁ ጋር እየኖራችሁ ነው፡፡ እንዲህ ያሉት የንስሐ ጸሎቶች ያደረጉት ነገር ቢኖር የልቦቻችሁን ሐጢያቶች ይበልጥ እንድትገነዘቡ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ዛሬ ክርስቲያኖች ያቀረቡዋቸው የንስሐ ጸሎቶች የደህንነት እውነት አለመሆናቸው ነው፡፡ ሰው ሰራሽ አስተምህሮቶች በተፈጥሮዋቸው የማንኛውንም ሰው ሐጢያቶች መፍታት የማይችሉ ሐይማኖታዊ አስተምህሮቶች እንጂ አንዳች ሌላ ነገር አይደሉም፡፡

    ስለዚህ የሐጢያቶች ስርየት የሚገኘው በሁለቱም የመፅሐፍ ቅዱስ ኪዳናቶች ውስጥ እንደተነገረው በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በተደረገው የስርየት መሥዋዕት በማመን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልገናል፡፡ በጌታ ጥምቀትና በደሙ ከሐጢያቶቻችን የነጻን የመሆኑን እምነት ይዘን መኖር አለብን፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የሚያምነው ይህ እምነት በእግዚአብሄር ፊት ትክክለኛው እምነት መሆኑን መገንዘብ አለብን፡፡

    ኢየሱስ ለምን በጲላጦስ ችሎት ሞት እንደተፈረደበትና በመስቀል ላይም ደሙን እንዳፈሰሰ ለመረዳት በመጀመሪያ ኢየሱስ በእርሱ ለመጠመቅ አጥማቂውን ዮሐንስን የመሻቱን እውነታ መገንዘብ አለብን፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ኢየሱስ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ መሸከም የቻለው በመጠመቅ ስለነበር ነው፡፡ (ማቴዎስ 3፡13-7) ኢየሱስ አሁን በ21ኛው ምዕተ ዓመት የተሠሩትን ሐጢያቶች እንኳን ሳይቀር ሁሉንም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ በመቀበሉ ምክንያት በጲላጦስ ችሎት ሞት እንዲፈረድበትና የመስቀልን ቅጣት እንዲሸከም ተገደደ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት የእግዚብሄር አብን ፈቃድ የተከተለ እጅግ ጻድቅ የሆነ ድርጊት ነበር፡፡

    አገረ ገዥው ጲላጦስ የስህተት ድርጊቶችን ፍለጋ ኢየሱስን በራሱ ችሎት ቢመረምረውም ፈጽሞ አንዳች ነገር ማግኘት አልቻለም፡፡ ጲላጦስ የሰው ዘር አዳኝ የሆነው ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በገዛ ሥጋው ስለመቀበሉ አንዳች የሚያውቀው ነገር ስላልነበረ ይህ የሚጠበቅ ነበር፡፡ አሁን ኢየሱስ በጲላጦስ ችሎት የተመረመረው የአባቱን ፈቃድ ለመታዘዝ ነበር፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በጥምቀቱ አማካይነት በዚህ ዓለም ላይ ያለውን የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በመሸከሙና የእግዚአብሄር በግ በመሆኑ ነበር፡፡

    ማናችንም በራሳችን ሐጢያተኞች መሆናችንን አናውቅም፡፡ ሁላችንም ሐጢያተኞች መሆናችንን ያወቅነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው የእግዚአብሄር ሕግ ቃል በማመን ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደም በማመን ሐጢያቶቻቸውን ለማንጻት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ ሐጢያቶቻቸው በዚህ ዓይነቱ እምነት እንደማይነጹ በጊዜ ሒደት ውስጥ ይበልጥ ወደ መረዳት ይመጣሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ ካመናችሁ በኋላ ባሉት አስር ዓመታቶች ውስጥ በእግዚአብሄር ፊት የበለጠ ሐጢያተኞች መሆናችሁን በእርግጠኝነት ወደ ማወቅ ትመጣላችሁ፡፡ ከዚህ የተነሣ ሐጢያተኛ ማንነታችሁን በማየት የሐጢያቶችሁን ስርየት እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ይበልጥ ፍላጎት ሊያድርባችሁ ይጀምራል፡፡

    ለዚህ ምክንያቱ ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሀ ካመናችሁ በኋላም እንኳን አሁንም ሐጢያተኛ በመሆናችሁ፤ እንዲያውም የአሁኑን ማንነታችሁን ስትመለከቱ አሁን ከዚህ በፊት ከነበራችሁት የበለጠ አስከፊ ሐጢአተኛ መሆናችሁን በማየታችሁ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመፍራት ትመነምናችሁ፡፡ ከዚህ የተነሣ የዘወትር ሐጢያቶቻችሁን የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ለማንጻት ትሞክራላችሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን በተጨባጭ መከወን አትችሉም፡፡ ከዚህ የተነሳ መጨረሻችሁ በሐጢያቶች መታሰር ይሆናል፡፡ ሰዎች በሙሉ በደመ ነፍስ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሐጢያቶች ሲሠሩ ራሳቸውን በሚመለከቱበት ጊዜ ልቦቻቸው ይደክማሉ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ሐጢያተኞች ለሐጢያቶቻቸው ፍርድን መቀበል የሚገባቸው መሆኑን ስለሚያውቁ ማለቂያ በሌለው ፍርሃት ውስጥ ከመኖር በቀር የሚያደርጉት ነገር የለም፡፡

    ዛሬ ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ሁሌም ሐጢያት አልባ የሆኑ ጻድቃን ሆነው በእግዚአብሔር ፊት ለመኖር ይናፍቃሉ፡፡ ይህንን ናፍቆታችንን እውን ለማድረግ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የተሸከመውን የጌታ ኢየሱስን ጥምቀት የሚያውቅና የሚያምን እምነት ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና እነርሱንም ወደ መስቀል በመውሰድ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ የተሸከመውን ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ወደ መረዳት የምንመጣው አስቀድመን ሐጢያቶቻችንን ከተገነዘብን በኋላ ነው፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት የምንቀበለው በእኛ ምትክ ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ለመኮነን የተጠመቀውንና ደሙን ያፈሰሰውን ጌታ በእምነት በመመልከትና በማመን ነው፡፡ ሁላችንም ጌታ በተቀበለው ጥምቀትና ለእኛ ባፈሰሰው ደም ከሙሉ ልባችን በማመን ከሐጢያቶቻችን መንጻት ይገባናል፡፡

    ከሐጢያቶቻችን መዳናችንን የምናውቀው መቼ ነው?

    ኢየሱስ ከ2,000 ዓመታት በፊት ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅም የሰውን ዘር ሐጢያቶች ተሸከመ፡፡ ሁላችንም ስለ ኢየሱስ ጥምቀት መማርና ትርጉሙንም መረዳት ያስፈልገናል፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀው የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች ለመሸከምና እነርሱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማንጻት ነው፡፡ እርሱ እናንተንና እኔን ከዓለም ሐጢያቶች ለማዳን በጥምቀቱ አማካይነት የዘወትር ሐጢያቶቻችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ተሸከመ፤ ወደ መስቀል ሄደ፤ ክቡር ደሙንም አፈሰሰ፤ በዚህም ከዚህ ዓለም ሐጢያቶች አዳነን፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በመውሰድ የሐጢያቶቻችን ማስተሰርያ አድርጎ ራሱን እንዳቀረበ ማየት እንችላለን፡፡ በዚህ ሥራ አማካይነትም አሁን እኛ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ላይ ባለን እምነታችን በኩል ደህንነትን መቀበል እንችላለን፡፡

    የሐጢያቶች መንጻት ወንጌል በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ተሰውሮዋል፡፡ ይህም የደህንነት ስጦታ በመሆኑ በዓለም ላይ ካለው ከማንኛውም የሎተሪ ዕጣ በላይ በላጭ የሆነ ስጦታ ነው፡፡ ይበልጥ ግልጥ ለማድረግ ይህ ወንጌል የሚናገረው ኢየሱስ ከአጥማቂው የሐንስ ስለተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ስለሆነው ሞቱ ነው፡፡ ይህ ሁሉ እውነት ልክ እንደተሰወረ ሥዕል በሁለቱም ኪዳናቶች ቃል ውስጥ ተሰውሮዋል፡፡

    በቅርቡ በአሜሪካ በአነድ የነዳጅ ማደያ አካባቢ የተሸጠ ሎተሪ ቲኬት ጃክፖቱን ሰብሮ $1.34 ቢሊዮን እንዳሸነፈ በዜና ሰማሁ፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ተሸከመ፡፡ እኛ በኢየሱስ ጥምቀት ቃል ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መንጻት እንደምንችል የምንገነዘብና የምናምን ከሆነ ይህ ማለት በእምነት አማካይነት ከዚህ ሎተሪ በእጅጉ የሚበልጥ ስጦታ ማለትም የደህንነት ስጦታን መቀበል እንችላለን ማለት ነው፡፡ እናንተ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አስገራሚ ደህንነትን መለማመድና በልቦቻችሁ ውስጥ የተደበቁት ሐጢያቶች በሙሉ የሚነጹበትን የሐጢያቶች ስርየት መቀበል ትችላላችሁ፡፡ እናንተ ይህንን የሐጢያቶች ስርየት እንደተቀበለ ሰውም በእውነቱ በዚህ ዓለም ላይ ከሁሉም በላይ እጅግ በጣም ዕድለኞች ናችሁ፡፡ ሆኖም በእጅጉ የሚያሳዝነው ነገር ክርስትናን የሚለማመዱ በጣም ብዙ ሰዎች እስከዚህ ቀን ድረስ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የመሸከሙንና የማስወገዱን እውነት መረዳትና ማመን አለመቻላቸው ነው፡፡

    እውነተኛው የደህንነት ወንጌል፡፡

    በማቴዎስ 13፡44-46 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሸጠና ያን እርሻ ገዛ፡፡ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት፡፡›› ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች እንደተሸከመና ወደ መስቀል እንደወሰዳቸው ታምናላችሁ፡፡ በዚህ ምንባብ ላይም ጌታ በዓለም ላይ እጅግ ዋጋዋ የበዛ አንዲት ዕንቁን በሚሻ ነጋዴ ተምሳሌታዊ ትርክት አማካይነት ስለ እምነታችሁ እየተናገረ ነው፡፡ ነጋዴው በዚህ ዓለም ላይ ዋጋዋ የበዛ አንዲት ዕንቁ ካገኘ በኋላ ያለውን ሁሉ ሸጠና ዕንቁዋን ገዛ፡፡ ታዲያ ዋጋዋ የበዛው ዕንቁ እዚህ ላይ ለእኛ ምንድነች? ይህች ዕንቁ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች መውሰዱን፣ እነርሱን ተሸክሞ ወደ መስቀል መሄዱን፣ የሐጢያቶቻችንን ቅጣት መሸከሙንና በዚህም እኛን ከእነርሱ ማዳኑን የሚያውጀው ወንጌል ነው፡፡

    ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ ከመጠመቁ ጥቂት ቀደም ብሎ በማቴዎስ 3፡13-16 ላይ ‹‹እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና›› አለ፡፡ እዚህ ላይ ‹‹የእግዚአብሔር ጽድቅ ሁሉ›› ማለት ምን ማለት ነው? በእርግጥ ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በተሸከመ ጊዜ የሠራውን ሥራ ነው፡፡ ጌታ ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ማድረግ የነበረበት የመጀመሪያው ዋና ነገር በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የሰውን ዘር ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ መሸከም ነበር፡፡ ኢየሱስ በዚህ ዓለም ላይ ያለውን እያንዳንዱን ሐጢያተኛ ከሐጢያቶቹ ለማዳን ጥምቀቱን ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ለዚያ ነው፡፡

    ስለዚህ ኢየሱስ ማስተሰርያችን ሆኖ የተሰቀለውና የሕይወት ደሙን ያፈሰሰው የዚህ ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ሰውነት በመተላለፋቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት ጌታ የእናንተነና የእኔን ሐጢያቶች በሰውነቱ ላይ እንዲሸከምና ለአንዴና ለመጨረሻ እንዲያነጻቸው የሚያደርግ የደህንነት መንገድ ነበር፡፡ በዚህ የምናምን ከሆነ የእናንተና የእኔ ሐጢያቶች በሙሉ በእርግጥም ይነጻሉ፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቁና በመስቀል ላይ ደሙን ማፍሰሱ ሐጢያቶቻችንን ያነጻበትና በተመሳሳይ ጊዜም ለሐጢያቶቻችን ስርየት ያደረገበት የደህንነት ሥራ ነው፡፡

    ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ለሐጢያቶቻችን ያደረገውን የስርየት መሥዋዕት ያዋቅራል፡፡ እዚህ ላይ መገንዘብ የሚገባን ነገር ቢኖር እኛ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ ምክንያት አሁን በእምነት በልቦቻችን ውስጥ የሐጢያቶችን ስርየትና ቤዛነትን መቀበል የምንችል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ማለት ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ስርየታችን መሆኑን ማመን አለብን ማለት ነው፡፡ ይህ እምነት እስከሌለን ድረስ በኢየሱስ ብናምንም ደህንነት ላይ መድረስ ስለማንችል ልክ እንደ ዓለም ሐይማኖተኞች በንስሐ ጸሎቶቻችን በከንቱ ሐጢያቶቻችንን ለማንጻት በመሞከር ሞኝነት ውስጥ እንወድቃለን፡፡

    ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ብቻውን ተሸከመ፡፡ ኢየሱስ በዚህ መልኩ ሐጢያቶቻችንን በሰውነቱ ላይ ከወሰደ በኋላ ወደ መስቀል ሄደና ለእኛ የሐጢያቶችን ቅጣት ተሸከመ፡፡ በዚህም በዚህ እውነት የምናምነውን ሰዎች ለዘላለም አድኖናል፡፡ ጌታ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በመውሰድ ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ ለዘላለም ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድኖናል፡፡

    እውነተኛው የሐጢያቶቻችን ስርየት፡፡

    ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ለመሸከም በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ባቀረበው የስርየት መሥዋዕት ባይሆን ኖሮ የእናንተና የእኔ ሐጢያቶች መንጻት አይችሉም ነበር፡፡ እርሱ የደህንነት ሥራውን ያከናወነው ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን ሳይቀበል ደሙን አፍስሶ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለው ድርጊት ጻድቅም ሆነ ቅን ሆኖ ሊገለጥ ባልቻለም ነበር፡፡ እዚህ ላይ ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን በምናምንበት ጊዜ ሐጢያቶቻችን በተጨባጭ የሚደመሰሱት አስቀድመን ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ሐጢያቶቻችንን መሸከሙን ስንገነዘብና ስናምን እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ እውነት የሚያምን እምነት በሌለበት እውነተኛ ደህንነት ላይ መድረስ እንደማይቻል ልነግራችሁ እችላለሁ፡፡ አሁን የሐጢያቶችን ስርየት በልባችሁ ውስጥ የምትቀበሉት በተሰቀለው ኢየሱስ በማመን እንደሆነ የምታምኑ ከሆነ ይህ በዓለማዊ ሐይማኖት ከማመን የተለየ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ዓለማዊ ሐይማኖቶች ደህንነታችሁን በምትፈልጉት በማንኛውም መንገድ ልታስቡትና ልታምኑበት እንደምትችሉ ይናገራሉ፡፡

    ነገር ግን እግዚአብሔር ልጁ ኢየሱስ ሕዝቡን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን በአጥማቂው ዮሐንስ እንደተጠመቀ ይናገራል፡፡ ኢየሱስ በመጀመሪያ ጥምቀቱን ሳይቀበል ለስርየታችን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ቢሆን ኖሮ ይህ በብሉይ ኪዳን ዘመን አስቀድሞ እጆቹን በራሱ ላይ ሳይጭንና ሐጢያቶቹን ወደ እርሱ ሳያስተላልፍ የመሥዋዕት እንስሳውን ብቻ በማረዱ ሕገ ወጥ የሆነ መሥዋዕት ከሚያቀርብ ሐጢያተኛ ጋር ተመሳሳይ ይሆን ነበር፡፡ እንዲህ ያለ ወንጌልና እንዲህ ያለ እምነት ተጨባጭ የደህንነት እውነት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከዳግመኛ ልደት እውነት በእጅጉ የራቁ ናቸው፡፡

    ዛሬም እኛ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ቅዱሳኖች የነበራቸው ዓይነት ተመሳሳይ እምነት እንዲኖረን በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ በተሸከመው፣ በተሰቀለውና በዚህም ስለ ሐጢያቶቻችን ማስተሰርያ ሆኖ ራሱን መሥዋዕት ባደረገው ጌታ ፍትህ በማመን መዳን አለብን፡፡ የጌታ ጥምቀትና ደሙ እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን የፈጸመውን የኢየሱስ ክርስቶስን ፍትህ እንደሚያዋቅሩ ማመን አለብን፡፡ የጌታ ደቀ መዛሙርት መሆን የምንችለው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ በሚያምን እምነት አማካይነት ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ አሁን እኛ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ የዳንበት ደህንነታችን መሆናቸውን ማመን አለብን፡፡

    በእርግጠኝነት ከሐጢያቶቻችን ድነናል ብለን መናገር የምንችለው የኢየሱስን ጥምቀትና ደሙን ደህንነታችን አድርገን ስናምን ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ እኛን ከሐጢያቶች ሁሉ ለማዳን በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅ ነበረበት፡፡ እርሱ የተሰቀለው፣ በተሸከመው ቅጣትም የሐጢያቶችን ደመወዝ የከፈለውና አሁን አዳኛችን የሆነው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሐጢያቶቻችን ለአንዴና ለመጨረሻ መንጻት የቻሉት ኢየሱስ ማስተሰርያችን ሆኖ ሐጢያቶቻችንን በሰውነቱ ላይ በመሸከሙ ብቻ ነው፡፡

    ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ክቡር ደሙን ብቻ እንደሚያምኑ የሚናገሩትን የዛሬዎቹን ክርስቲያኖች እምነት በምንመለከትበት ጊዜ አስቀድመው ሐጢያቶቻቸውን ወደ እርሱ ሳያስተላልፉ በኢየሱስ ደም ብቻ ከሐጢያቶቻቸው መንጻት እንደሚችሉ ሲናገሩ እናያቸዋለን፡፡ ሆኖም እዚህ ላይ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ክቡር ደሙን ማፍሰስ የቻለው አስቀድሞ በአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ሐጢያቶቻችሁን በመሸከሙ እንደነበር መገንዘባችሁ ፈጽሞ አስፈላጊ ነው፡፡

    ዛሬ ክርስቲያኖች የተሰቀለውን ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው በሚያምኑበት ጊዜ ወደፊት ስለሚሠሩዋቸው ሐጢያቶች በተጨባጭ አያስቡም፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ እንደተጻፈው ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች እንዴት እንደተሸከመ ሳያስቡ በመስቀሉ ብቻ ስለሚያምኑ ሐጢያቶቻቸውን ለማንጻት በመሞከር በየቀኑ ለመጸለይ የመገደድ ስሜት የሚሰማቸው ተራ ሐይማኖተኞች ሆነው ተለውጠዋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ቢያምኑም ይህንን የሚያደርጉት በጥምቀቱ አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በመሸከም ያከናወነውን ሥራ በመተው ነው፡፡ በተሰቀለው ኢየሱስ ብቻ የሚያምኑት የዛሬዎቹ ክርስቲያኖች በእርሱ ጥምቀትና በሐጢያቶቻቸው መንጻት መካከል ግንኙነትን ማድረግ ባለመቻላቸው እምነታቸው የኢየሱስን በእጅጉ ጠቃሚ የሆነ ጥምቀት አስወግዶታል፡፡

    እነዚህ ክርስቲያኖች ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ የመሸከሙንና እነርሱን ወደ መስቀል የመውሰዱን እውነት ስለማያውቁ የሚያውቁት ኢየሱስ መሰቀሉን ብቻ ነው፡፡ ይህንን የተሰቀለውን ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ያምናሉ፡፡ በዚህም በየቀኑ ለሚሠሩዋቸው ሐጢያቶች መፍትሄን ለማግኘት በመሞከርም በራሳቸው የንስሐ ጸሎቶች ላይ መደገፍን መርጠዋል፡፡ በኢየሱስ ጥምቀት በማመን ሐጢያቶቻቸው የመንጻታቸውን እውነት ፈጽሞ ስለማያውቁ በዚህች ቅጽበትም እንኳን ጌታ የሚሠሩዋቸውን ሐጢያቶች በሙሉ እንዲያነጻላቸው በመጠየቅ በመስቀሉ ላይ ብቻ ተንጠልጥለው ቀርተዋል፡፡

    እነርሱ በንስሐ ጸሎቶቻቸው ከዘወትር ሐጢያቶቻቸው ይቅርታን ለማግኘት ከሞከሩ በኋላ ውለው አድረው በተሰቀለው ኢየሱስ ፊት የሐፍረት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ስለዚህ በመጨረሻ በእምነት ሕይወታቸው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡ የዘወትር ሐጢያቶቻቸው በጣም ብዙ በመሆናቸው እምነታቸው ሁሌም ጎዶሎ እንደሆነ ያያሉ፡፡ ከዚህ የተነሣ የንስሐ ጸሎቶችን መጸለይ በቂ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል፡፡ እነርሱ ኢየሱስ በተቀበለው ጥምቀት በኩል ለሐጢያቶቻቸው ገና መፍትሄን መስጠት ባለመቻላቸው ሁሌም ሐጢያተኛ ሆነው ለመኖር የተኮነኑ ናቸው፡፡ እኛ አሁን ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት ለአንዴና ለመጨረሻ የተሸከማቸው የመሆኑን እውነታ በማመን የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች ማንጻት ያለብን ለዚህ ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ለሐጢያቶቻችን ቅጣት እንደሆነም አሁኑኑ ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ እነርሱን ወደ መስቀል የወሰዳቸው፣ ደሙን ያፈሰሰውና በእኛ ምትክ የሞተው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ በመሸከሙ ነው፡፡

    እዚህ ላይ በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች በእጅጉ መንፈሳዊ መቀዛቀዝ ውስጥ እየወደቁ ያሉት ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደም ብቻ በማመን ለሐጢያቶቻቸው መፍትሄን ማግኘት ባለመቻላቸው እንደሆነ መረዳት ያስፈልገናል፡፡ አሁን ከሐጢያቶቻችሁ መንጻት ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የተሸከመና ደሙንም በመስቀል ላይ ያፈሰሰ አዳኝ መሆኑን ስታምኑ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእናንተና ለእኔ ያለው ፍቅር እንዴት እንደተገለጠ ማወቅ አለባችሁ፡፡ አሁን የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠልን ኢየሱስ የሰው ዘር ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ በመሸከሙና በመስቀል ላይ በመሞቱ እንደሆነ ልትገነዘቡ ይገባል፡፡

    ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ ከመጠመቁ በፊት ‹‹እንዲህ›› የሚለውን ቃል በተጠቀመ ጊዜ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚወስድበትን ጥምቀቱን መናገሩ ነበር፡፡ ኢየሱስ ጥምቀቱን ከተቀበለ በኋላ በመስቀል ላይ ተሰቀለና ክቡር ደሙን አፈሰሰ፡፡ አሁን በዚህ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሰው ዘር እያሳየ ነው፡፡

    ታዲያ አሁን ሐጢያቶቻችሁ ያሉት የት ነው? አሁንም በልባችሁ ውስጥ ናቸው ወይስ ወደ ኢየሱስ ሰውነት ተላልፈዋል? ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት በዚህ ዓለም ላይ የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች በሙሉ በሰውነቱ ላይ የተሸከማቸውና ለእንዴና ለመጨረሻም ያስወገዳቸው የመሆኑን እውነታ ታምናላችሁ? ወይስ ገና ይህንን እውነታ ባለማወቃችሁና በተሰቀለው ኢየሱሰ ብቻ የምታምኑ በመሆናችሁ ሐጢያቶቻችሁ አሁንም በልቦቻችሁ ውስጥ አሉ? የዓለምን ሐጢያቶች በጥምቀቱ አማካይነት የተሸከመውን የኢየሱስን ፍቅር በተጨባጭ አውቃችሁ ከሆነ አሁን በልባችሁ ውስጥ የቀረ አንዳች ሐጢያት ሊኖር ይችላልን? የለም በእርግጥ አይችልም! አትስማሙምን? ይህ በእርግጥም የማይቻል ነው! ታዲያ እናንተና እኔ ጥፋተኛ የሆንን ሐጢያተኞች ነን ወይስ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በማመን የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበልን ጻድቃን ነን? እኛ ጻድቃን ነን!

    አሁን እያደረጋችሁት እንዳለው በመስቀሉና በንስሐ አስተምህሮት ብቻ የእምነት ሕይወታችሁን የምትኖሩ ከሆነ ከባድ ስህተት ውስጥ ትወድቃላችሁ፡፡ ሐጢያቶቻችሁ በእርሱ ጥምቀት ወደ ኢየሱስ መተላለፋቸውን ባለማወቃችሁ በየቀኑ በምታቀርቡዋቸው የንስሐ ጸሎቶች ሐጢያቶቻችሁን ለማንጻት እየሞከራችሁ ነው፡፡ ለጌታ የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ በተጨባጭ ሐጢያቶቻችንን ማንጻት የሚቻለን ቢሆን ኖሮ ሊደረግ የሚገባው ትክክለኛ ነገር ይህ በሆነ ነበር፡፡ ነገር ግን ሐጢያት በምትሠሩበት ጊዜ ሁሉ የንስሐ ጸሎቶችን የምታቀርቡ ከሆነ አብዝታችሁ በጸለያችሁ መጠን ይበልጥ ትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ትወድቃላችሁ፡፡ ያን ጊዜ በዓለማዊ ሐይማኖት ትጠመዱና ከዚያ ማምለጥ የማይቻላችሁ ይሆናል፡፡ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያሉት ሐጢያቶች የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚወርድባቸው መገንዘብ አለባችሁ፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ሐጢያቶች በልብ ጽላት ላይ ተጽፈዋል፡፡ ስለዚህ ኢምንት ሐጢያት እንኳን ያለበት ማንኛውም ሰው እግዚአብሔር በሐጢያቱ ምክንያት እንደሚኮንነው ራሱ ያውቃል፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ደሙ ደህንነታችን መሆኑን በሚያውጀው እውነት በማመን መዳን አለብን፡፡ ይህ የዳግመኛ ልደት እውነት ጌታ ለእኛ ከተናገረው ቃል ሊታወቅ የሚችል ነው፡፡

    እንደምናውቀው በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የተፈጸመው የደህንነት ስጦታ ለአማኞች የዘላለም ሕይወት ነው፡፡ እዚህ ላይ የጌታ የደህንነት ስጦታ የዘላለም ሕይወት ነው ማለት እንዲህ ማለት ነው፡- ጌታ ሐጢያቶቻችንን ለመሸከም በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ወሰደ፤ ተሰቀለ፤ ደሙንም አፈሰሰ፡፡ ይህ ቃል የሐጢያቶችን ስርየት መቀበል የሚያስችለን የደህንነት ስጦታ ነው፡፡ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በጥምቀቱ አማካይነት የተሸከመውንና ወደ መስቀል የወሰደውን ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ የምታምኑበት እምነት ካላችሁ ዘላለማዊውን የሐጢያቶች ስርየትና የዘላለምን ሕይወት መቀበል ትችላላችሁ፡፡

    በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የምታምኑ ከሆነ ከጌታ የሚመጣውን ሰላም ታገኛላችሁ፡፡ ስለዚህ ጌታ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና ለእኛም ደሙን በማፍሰስ የፈጸመው ይህ የስርየት እውነት ለእኛ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ የሚያዋቅር መሆኑን በመገንዘብ አማኝ እንድትሆኑ እወተውታችኋለሁ፡፡ በመስቀሉ ብቻ በመታመን ስታቀርቡዋቸው በነበሩት የንስሐ ጸሎቶች መቼም ቢሆን ሐጢያቶቻችሁን ማንጻት አትችሉም፡፡ ስለዚህ አሁኑኑ በኢየሱስ ጥምቀትና ክቡር በሆነው የመስቀል ላይ ደሙ እንመን፤ በዚህ እምነትም ደህንነታችን ላይ እንድረስ፤ ጻድቃን እንደ መሆናችንም እምነታችንን እንጠብቅ፤ በአመስጋኝነትም እንኑር!

    በመስቀሉ ቃል ብቻ በተመሠረተው እምነታችሁ በምታቀርቡዋቸው የንስሐ ጸሎቶች ሐጢያቶቻችሁን እንደ አመዳይ ማንጻት እንደማትችሉ እናንተው ራሳችሁ ማየት የምትችሉ ከሆነ አሁን ጊዜው አዲስ አማራጭ የምትፈልጉበት ነው፡፡ እኛ ጌታችን ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት በዓለም ላይ ያሉትን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደተሸከመና እንዳስወገዳቸው እናውቃለን፡፡ እንዲህ ያለን ሰዎች በመሆናችንም የሐጢያቶቻችን መንጻት በጌታ ጽድቅ ላይ ባለን እምነታችን እንዲጠነክር በሕይወታችን ወደ ጌታ መጸለይ አለብን፡፡

    ሕይወታችንን በመኖር ስንቀጥል የኢየሱስን ጥምቀት ቃል አጥብቀን በእምነት መያዝ አለብን፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን መሸከሙን ይበልጥ ሳንናወጥ ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ በመሰቀልና ደሙን በማፍሰስ ኩነኔያችንን መሸከሙንም ማመን አለብን፡፡ እንዲህ በትጋት ስታቀርቡዋቸው የነበሩት የንስሐ ጸሎቶችም በችግሮች የተሞሉ እንደሆኑ ልትገነዘቡ ይገባል፡፡ የዚህ ዓለም ሐጢያቶችም ጌታችን ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው የጥምቀት ቃል ወደ ኢየሱስ መተላለላፋቸውን ማወቅና ማመን አለባችሁ፡፡ በአጭሩ ኢየሱስ ደሙን በማፍሰስና በመስቀል ላይ በመሞት የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ ያስወገደው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቁ የመሆኑን እውነታ መረዳትና ማመን አለባችሁ፡፡

    ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ የምታምኑ ከሆነ ጌታ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና ደሙን በማፍሰስ የሠራውን የደህንነት ሥራ በሚያምነው እምነታችሁ አማካይነት ዘላለማዊው የሐጢያቶች ስርየት ትቀበላላችሁ፡፡ እውነቱ ይህ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ የተቀበለበትን የጥምቀት ቃል እንገንዘብና እንመን፡፡ ከሐጢያቶቻችንም እንንጻ፡፡ ወደ መስቀል የሄደውና በዚያ ላይም ደሙን አፍስሶ የሞተው ኢየሱስ የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ የተሸከመው ጌታ መሆኑን በማመን ዘላለማዊውን የሐጢያቶች ስርየት በልቦቻችን ውስጥ መቀበል የምንችል በመሆኑ አመስጋኝ ልንሆን ይገባል፡፡

    ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀትና ደሙ አሁን ከሐጢያቶቻችንና ከኩነኔ እንደታደጉን እንመንና እንወቅ፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ተሸከመ፡፡ እርሱን አዳኛችን አድርጎ ማመን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ የሆነ የእምነት ድርጊት ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም የእናንተንና የእኔን ሐጢያቶች ያነጻበትና ኩነኔያቸውን የተሸከመበት ዘዴ ናቸው፡፡ እነዚህ ለደህንነታችን አስፈላጊ የሆነውን የወንጌል ቃል ያዋቅራሉ፡፡ እናንተም በጌታችን ጻድቅ የደህንነት ሥራ በማመን አመስጋኝ መሆን አለባችሁ፡፡

    በጌታ ጥምቀትና በደሙ ላይ ባለው እምነታችሁ ላይ እየቆማችሁ ነውን?

    አሁን ጌታ ኢየሱስ የሰው ዘር አዳኝ እንደሆነ እንድናምን ለእናንተና ለእኔ እየነገረን ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የተሸከመና በመስቀል ላይ የሞተ አዳኛችን መሆኑን ማመን አለብን፡፡ በሉቃስ 23፡35-38 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር፡፡ መኳንንቱም ደግሞ፡- ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ ራሱን ያድን እያሉ ያፌዙበት ነበር፡፡ ጭፍሮችም ደግሞ ወደ እርሱ ቀርበው ሆምጣጤም አምጥተው፡- አንተስ የአይሁድ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን እያሉ ይዘባበቱበት ነበር፡፡ ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው ተብሎ በግሪክና በሮማይስጥ በዕብራይስጥም ፊደል የተጻፈ ጽሕፈት ደግሞ በእርሱ ላይ ነበረ፡፡››

    የዛሬዎቹ የፕሮቴስታንት የተሐድሶ ሰዎች ዘሮች አብዝተው የሚያደንቁት ‹‹የሐዋርያት የሐይማኖት መግለጫ›› ምንጩ የኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ነው፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የመሸከሙ እውነታ ከኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ውስጥ ወጥቶዋል፡፡ የኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ እስከዚህ ዘመን ድረስ ባለበት ሁኔታ ስለተላለፈና ክርስቲያኖችም በዚያው መሠረት ስለሚያምኑ ሁሉም አዳኛቸው አድርገው የሚያውቁት የተሰቀለውን ኢየሱስን ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነቱ እምነት ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የተሸከመበትን ሥራ ትቶ በመስቀሉ ላይ ብቻ ያነጣጠረ እምነት ነው፡፡ ዛሬ የፕሮቴስታንት የተሐድሶ ሰዎች ዝርያዎች ከአጥማቂወ ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች የመሸከሙን፣ ደሙን የማፍሰሱንና በመስቀል ላይ የመሞቱን እውነታ ስለማያውቁ ኢየሱስን በትክክል አያውቁትም፡፡

    ስለዚህ እኛ አሁን ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለውን ጥምቀት ቃል እንደገና በሐዋርያት የሐይማኖት መግለጫ ውስጥ መልሰን በማስገባት ደግመን በትክክል ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ መሸከሙን እያንዳንዱ ሰው እንዲያውቅ እውነቱን መስበክ አለብን፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ አዳኛችን መሆኑን የምናምን ከሆነ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖሩ በርካታ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ጥምቀት በማወቅና በማመን ከሐጢያቶቻቸው የሚድኑበትን የደህንነት ጸጋ መቀበል እንዲችሉ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለውን የጥምቀት ሥራ በሐዋርያት የሐይማኖት መግለጫ ውስጥ ደግመን ማስገባትና በዚያው መሠረት የማመን ግዴታ አለብን፡፡

    ኢየሱስ ለምን ወደዚህ ዓለም መጣ? እርሱ የመጣው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና ራሱን ለሞት በመስቀል በዚህ ዓለም ሐጢያቶች ውስጥ የወደቀውን የሰው ዘር በሙሉ ለመታደግና ሐጢያቶቻችንንና የሐጢያቶቻችንን ቅጣት ለማክሰም መሆኑን ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ በ30 ዓመቱ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የዚህን ዓለም ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ በሰውነቱ ላይ የተሸከመው፣ የተሰቀለውና ደሙን አፍስሶ የሞተው ለዚያ ነው፡፡ እርሱ በጥምቀቱና በደሙ ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉም ዘላለማዊውን የሐጢያቶች ስርየት ፈቅዶዋል፡፡ አየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የመላውን ሰው ዘር ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ወሰደ፤ ተሰቀለ፤ ደሙን አፈሰሰ፤ ዳግመኛም ከሙታን ተነሣ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በውሃና በመንፈስ ወደዚህ ምድር በመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አለብን፡፡ በዚህም ከሐጢያቶቻችን ዳግመኛ መወለድ አለብን፡፡ ጌታ በውሃ ሥራውና ሐጢያቶችን በመኮነን ሥራው ለሚያምኑ ሰዎች ሁሉ አዳኝ ነው፡፡ እኛ በጌታችን ጥምቀትና ደም የምናምን አማኞች መሆን አለብን፡፡

    በዚህ ዓለም ላይ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያች የመውሰዱን እውነታ የሚደብቁ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን የሰውን ዘር በመስቀሉ ብቻ እንዳዳነ አድርገው ይገልጡታል፡፡ እነርሱ በዚህ ምድር ላይ ብቸኞቹ ትክክለኛ ክርስቲያኖች በመስቀሉ የሚያምኑ ሰዎች እንደሆኑ አድርገው ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የተገለጠው ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች እንደተሸከመና እንዳነጻ ይመሰክራል፡፡

    ጥንት የኒቅያን የሐይማኖት መግለጫ ያበጁት ሰዎች እነርሱ ራሳቸው የተሰቀለውን ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ከማመናቸውም ባሻገር በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር እያንዳንዱም ሰው እንደዚያ እንዲያምን ደግሞ ይህንኑ አሰራጭተዋል፡፡ እነርሱ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለውን ቃለ ጥምቀት አውጥተው በመጣላቸውና የእነርሱ ዝርያዎችም ማንም ሰው ስለ ኢየሱስ ጥምቀት እንዳያውቅ በኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ላይ የተመሠረቱ አስተምህሮቶችን ባስተማሩት ባለፉት 1,700 ዓመታት በርካታ ሰዎች እስከዚህ ቀን ድረስ ሳይቀር መስቀሉን ብቻ ደህንነታቸው አድርገው አምነዋል፡፡ ጥንት የተስፋፋው የኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ የመሸከሙን እውነት አውጥቶ የዛሬዎቹን ክርስቲያኖች ወደተሰቀለው ኢየሱስ በስህተት እየመራቸው ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ ዛሬ ክርስቲያኖች ኢየሱስ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1