Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)
አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)
አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)
Ebook454 pages3 hours

አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ይህ መጽሐፍ አብረውን ያሉትን አጋር ሰራተኞችና ቅዱሳኖችን ለመምራትና እውነተኛ የእግዚአብሄር አገልጋይ በመሆንም እንዴት ሕይወትን እንደሚኖሩ ለማሳየት የተጻፈ የስብከቶች ስብስብ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ መጽሐፍ ‹‹አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች›› የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል፡፡
እኔ የግል ፍላጎቶቼን ትቼ በእምነት ውስጥ ካሉ አጋር ሰራተኞቻችን፣ በክርስቶስ ጽድቅ ከሙሉ ልቦቻቸው ከሚያምኑ ሰዎች ጋር ሕብረትን ለመካፈል ከልቤ እሻለሁ፡፡ ይህንን በተጨባጭ የምሻው እኛ የተገናኘነው በጌታ ጽድቅ እምነት ስለሆነና እነርሱም ደግሞ አሁን ይህንን እየሰበኩ ስለሆነ ነው፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateSep 15, 2023
ISBN9788928221493
አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)

Related to አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)

Related ebooks

Reviews for አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I) - Paul C. Jong

    paul_Am57_coverFrontflap_Am571st_page

    አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች (I)

    Smashwords Edition

    Copyright 2023 by Hephzibah Publishing House

    ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ባለቤት በጽሁፍ የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር የዚህን መጽሐፍ ማንኛውንም ክፍል ማባዛት ወይም በማንኛውም መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ በኤሌክትሮኒክ ወይም በሜካኒካል ፎቶ ኮፒ ማድረግን ጨምሮ በቅጂ መልክ ወይም መረጃን ይዞ በሚያጠራቅም ወይም መረጃን ይዞ በሚያስቀር ማንኛውም መንገድ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

    ጥቅሶቹ በሙሉ የተወሰዱት ከ1954ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ হয়েছে।

    ISBN 978-89-282-2149-3

    ዲዛይን፡ በሚን ሱ ኪም

    ንድፍ፡ በዮንግ አይ ኪም

    ትርጉም፡ በካሳሁን አየለ

    የታተመው በኮርያ ነው፡፡

    Hephzibah Publishing House

    A Ministry of THE NEW LIFE MISSION

    Seoul, Korea

      የማውጫ ሰሌዳ  

    መቅድም

    1. በዚህ በመጨረሻው ዘመን የሕይወትን እንጀራ የሚያካፍሉ ሰዎች የተባረኩ ናቸው (ማቴዎስ 24፡32-51)

    2. በጠበበው ደጅ ግቡ (ማቴዎስ 7፡13-27)

    3. የተታለሉ ልጆችን በወንጌል ብርሃን አብሩ (ኢሳይያስ 1፡21-31)

    4. እግዚአብሄር የዓለምን ሐጢያት ደምስሶዋል (ኢሳይያስ 1፡10-18)

    5. አስመሳዩ ክርስትና የተመሠረተው እንዴት ነበር? (1ኛ ነገሥት 11፡26-40)

    6. የክርስቶስ ጽድቅ፡ ፍጹም አስፈላጊ (ሮሜ 8፡1-11)

    7. ንስሐ ግቡና ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ተመለሱ (ማቴዎስ 4፡12-25)

    8. የእግዚአብሄር ቃል (ዮሐንስ 1፡1-14)

    9. እኛ ቡራኬዎችን ተቀብለናል! (ማቴዎስ 5፡1-16)

    10. ኖህ በጌታ እግዚአብሄር ዓይኖች ፊት ጸጋን አገኘ (ዘፍጥረት 6፡1-22)

    11. የወንጌል ሰባኪ ተግባራቶች (ማቴዎስ 13፡1-2)

    12. ፍጹም የሆነ ሕይወት የምንመራበትን ቀን ተስፋ ማድረግ (ሮሜ 8፡18-28)

    0Preface.jpg

    መቅድም

    ይህ መጽሐፍ አብረውን ያሉትን አጋር ሰራተኞችና ቅዱሳኖችን ለመምራትና እውነተኛ የእግዚአብሄር አገልጋይ በመሆንም እንዴት ሕይወትን እንደሚኖሩ ለማሳየት የተጻፈ የስብከቶች ስብስብ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ መጽሐፍ ‹‹አጋር ሰራተኞቻችን ለሚሆኑ የቀረቡ ስብከቶች›› የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል፡፡

    እኔ የግል ፍላጎቶቼን ትቼ በእምነት ውስጥ ካሉ አጋር ሰራተኞቻችን፣ በክርስቶስ ጽድቅ ከሙሉ ልቦቻቸው ከሚያምኑ ሰዎች ጋር ሕብረትን ለመካፈል ከልቤ እሻለሁ፡፡ ይህንን በተጨባጭ የምሻው እኛ የተገናኘነው በጌታ ጽድቅ እምነት ስለሆነና እነርሱም ደግሞ አሁን ይህንን እየሰበኩ ስለሆነ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ከማናቸውም ሰብዓዊ ስብስቦች ጋር ሳይሆን በጌታ ጽድቅ ውስጥ ካሉ ከእያንዳንዱ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ቅዱሳኖች ጋር ሕብረትን ለማድረግ ናፈቀ፡፡ እኔም ይህንን እናፍቃለሁ፡፡ እኔ ከአጋር ሰራተኞቼ ጋር እዚህ በአገሬና በውጪ አገርም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ለማሰራጨት አቅጃለሁ፡፡ ጌታ ይህንን ተግባርና በዓለም ዙሪያ ያሉትንም ሕዝቦች በአደራ ሰጥቶናል፡፡ እኔ በማናቸውም ሰብዓዊ መለኪያዎች ሳይሆን በጌታ ጽድቅ ላይ ባላችሁ እምነት አጋር ሰራተኞቼ እንደሆናችሁ አድርጌ ልመለከታችሁ የምወደው ለዚህ ነው፡፡

    ለእናንተ ያለኝ የመጀመሪያው ጥያቄ እምነታችሁ ምን እንደሚመስል እንድታስቡ ነው፡፡ ከዚያም ከምን ልትጠነቀቁ እንደሚገባችሁና የእምነት ሩጫችሁንም በምን እምነት መሮጥ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁ፡፡ የጌታ ጽድቅ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ካገኘሁበት ጊዜ ጀምሮ ቅድሚያ የምሰጠው በእርሱ ጽድቅ ላይ ያለውን እምነት መጠበቅና የጌታን ፈቃድ መከተል ነበር፡፡ የሚያሳዝነው እምነታቸውን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ካኖሩ በኋላ ትተውን ወደ ዓለም የሄዱና አሁን በኩነኔ ውስጥ እየኖሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸው ነው፡፡ እኔ እነርሱን በእግዚአብሄር ቃል በጥንቃቄ መክሬያቸዋለሁ፤ ነገር ግን ቃሎቼን ከእግዚአብሄር እንደሆኑ አድርገው አልተቀበሉዋቸውም፡፡ ውሎ አድሮ መንፈሳዊ ሙታን ሆኑና ዳግመኛም በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ የማይታዩ ሆኑ፡፡ ይህ በእጅጉ የሚያሳዝን ነው!

    እነርሱ አሁን በዓለም ላይ እየኖሩ ያሉት እንዴት ነው? ምንስ እያደረጉ ነው? ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም፡፡›› (ማቴዎስ 4፡4) እኔ ይህንን በትክክል አምናለሁ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን ሰው እንዴት በእንጀራ ብቻ ይኖራል?

    ጌታ ወንጌሉን እንድንሰብክ በአደራ ሰጥቶናል፡፡ ስለዚህ እኔ አጋር ሰራተኞቼ ከሆናችሁት ከእናንተ ከታማኞቹ ጋር አብሬ ይህንን ትዕዛዝ እከተላለሁ፡፡ ለምድራዊ ፈቃዶቻችን ሳይሆን ለእርሱ ትዕዛዝ ‹‹እሺ›› እንደምትሉና እርሱን በእምነት እንደምትከተሉ አምናለሁ፡፡ የእርሱ አገልጋይ መቀመጫ ከሆነው ተለይታችሁ እንደማትኮበልሉ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ጌታ እስከሚመለስበት ቅጽበት ድረስ ገና ለማያውቁት ሰዎች ሁሉ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እናቀርባለን፡፡

    ይህ መጽሐፍ አጋር ሰራተኞቻችን ከእንግዲህ ወዲያ እንደማይኮበልሉ ተስፋዬን ይዞዋል፡፡ እኔ ለጌታዬ ጽድቅ ስል በስደት ውስጥ ከብሬያለሁ፡፡ ይህንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስበካችን የሚያሳድደን ሰው ካለ ያ ስደት በእግዚአብሄር ፊት ክብራችን ይሆናል፡፡ እርሱ ‹‹እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ›› (ማቴዎስ 28፡20) በማለት ተስፋ እንደሰጠው አጋር ሰራተኞቻችን በሙሉ ከጌታ ጋር በመንግሥቱ ውስጥ አብረው እንደሚሆኑ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ እጸልይማለሁ፡፡

    ከደራሲው

    ታህሳስ 1፡ 2008

    Sermon0101

    በዚህ በመጨረሻው ዘመን የሕይወትን እንጀራ የሚያካፍሉ ሰዎች የተባረኩ ናቸው

    ‹‹ ማቴዎስ 24፡32-51 ››

    ‹‹ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤ ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች። ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። ያ ክፉ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥ ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆና፡፡››

    ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ከቁጥር 6 እስከ 8 ያለውን ቃል እናንብብ፡- ‹‹ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።›› ጌታ የመጨረሻዎቹ ጊዜያት ሲመጡ ጦርንና የጦርን ወሬዎች እንደምንሰማና ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ እንደሚነሣ፣ ራብና የመሬት መናወጦችም እንደሚኖሩ ተናገረ፡፡ ይህ በእርግጥም እውነት ነው፡፡

    በእነዚህ ቀኖች የምንሰማው የጥፋቶችን ዜና ብቻ ነው፡፡

    በእነዚህ ቀኖች በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱትን የጥፋቶች ዜና አዘውትሬ ስለምሰማ የጌታ መምጫ ጊዜ ቅርብ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ዛሬ ባነበብነው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ላይ ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።›› (ማቴዎስ 24፡32-33) የበለስ ዛፎ ቅጠሎች ይጠወልጉና ይረግፋሉ፡፡ በክረምትም ቅርንጫፎቹ መካን ሆነው ይቀራሉ፡፡ ነገር ግን በጸደይ ወቅት በመጀመሪያ በቅርንጫፎቹ ላይ ትናንሽ እንቡጦች ይበቅላሉ፡፡ በኋላም ትናንሽ በለሶች ይበቅላሉ፡፡ እያንዳንዱ በለስ በፍሬው ውስጥ የራሱ አበባ አለው፡፡ የሚያብበው በዚያ መልኩ ስለሆነ አበባውን ማየት አንችልም፡፡ የበለስ ዛፍ ፍሬ የሚበስለው ቀይ ሲሆን እንደሆነ መገመት እንችላለን፡፡ ጌታ ቅርንጫፎቹ ሲለሰልሱና በቅርንጫፎቹ ላይ ያሉት ቅጠሎችም ሲያቀጠቁጡ በጋ እንደቀረበ ማወቅ እንደሚገባን የተናገረለት የበለስ ዛፍ ይህ ነው፡፡

    ስለዚህ ጌታ ረሃቦች፣ የመሬት መናወጦችና ጥፋቶች በመላው ዓለም በሚሆኑበት ጊዜ እርሱ በደጅ እንደቀረበ ያስጠነቅቀናል፡፡ ጌታ አሁንም በስጋችን እየኖርን ላለነውና እንዲህ ባለው ዘመን መኖር እያታከተን ላለነው ለእኛ እነዚህን ምልክቶች እያሳየን ነው፡፡ በአንድ ወቅት አውዳሚ በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በቻይናዋ ጠቅላይ ግዛት በሲቹዋን ብዙ ሰዎች ተጨፍልቀው እንደሞቱ አየን፡፡ የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትርም አለቀሰና ለአገሩ ሕዝብ ዕርዳታን ጠየቀ፡፡ ብዙ የትምህርት ቤት ሕንጻዎች በመውደማቸው በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ብዙ ተማሪዎችም ሞቱ፡፡ የቻይና መንግሥትም እነዚህን ትምህርት ቤቶች የገነቡትን የግንባታ ሰራተኞች ለመመርመርና በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የግብር ይውጣ ስራ የሰሩትን ሁሉ እንደሚቀጣ ቃል ገባ፡፡ ነገር ግን እነርሱ እንዲህ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰት እነዚህ የትምህርት ቤት ሕንጻዎች እንደሚወድሙ በተጨባጭ ያውቁ እንደነበር ታስባላችሁን? በቻይና ያለችውን ዮንብዩንን ከጎበኘሁ 10 ዓመታት አልፈውኛል፡፡ በዚያን ጊዜ እነርሱ የግብር ይውጣ የግንባታ ስራ ሲሰሩ አየሁ፡፡ የሆኖ ሆኖ በሬክተር መለኪያ 7.8 የሚለካ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ የሲቹዋን ጠቅላይ ግዛት ናጣት፡፡ በዚህ አንድ ጥፋት ብቻ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሕዝቦች እንደሞቱ ተዘግቦዋል፡፡

    ጌታ በጥፋቶች ቀናት የሰው ልጅ በደጅ እንደቀረበ ማወቅ እንደሚገባን ተናገረ፡፡ ይህ ማለትም የጌታችን መምጫ ጊዜ ቅርብ ነው ማለት ነው፡፡ ጌታ ‹‹ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም›› (ማቴዎስ 24፡35) በማለት እርሱ የተናገረው እያንዳንዱ ቃል በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ተናገረ፡፡ የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ በተለያዩ መንገዶች ሊተረጎም ይችላል፤ ነገር ግን ዋናው ነጥብ የጌታችን መምጫ ጊዜ ቅርብ መሆኑ ነው፡፡ እግዚአብሄር በመጀመሪያ የፈጠረው የመጀመሪያው ዓለም በአዳምና በሔዋን አማካይነት የፈጠረው ዓለም ነበር፡፡ ነገር ግን ከኖህ ቤተሰብና በመርከቡ ውስጥ ከነበሩት ሕያዋን ነገሮች በስተቀር በጥፋት ውሃ ወቅት ፍጥረቶች በሙሉ ሞቱ፡፡ ከዚያም የኖህ ቤተሰብ ከመርከብ ከወጣ በኋላ ጌታ እኛን ሰዎችን ፍሬያማ እንድንሆንና እንድንበዛ አደረገን፡፡ እኛም ከኖህ ዘሮች ተወለድን፡፡ ስለዚህ ይህ አዲስ የሰው ዘር ተፈጠረ፡፡ ነገር ግን እኛ ሁለተኛዎቹ የሰው ዘሮች ለመጥፋት የተኮነንን ነን፡፡

    እንደከሰመው የመጀመሪያው የሰው ዘር ሁለተኛውም የሰው ዘር ሊጠፋ ተቃርቦዋል፡፡ ሦስተኛው የሰው ዘርም በአዲሱ ዓለም መድረክ ላይ ሊገለጥ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሦስተኛው ዓለም የሺህው ዓመት መንግሥትና የዘላለማዊው የእግዚአብሄር መንግሥት መጀመሪያ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም›› (ማቴዎስ 24፡35) የጌታ ቃል በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም መረዳት አለብን፡፡ ስለዚህ በጌታ ቃል በእምነት መኖር አለብን፡፡ አለበለዚያ ይህ ዘመን ምን እንደያዘ የማያውቁና በእምነት የማይኖሩ ሰዎች የማይረቡ ነገሮች እያሳሰቡዋቸው ከዚህ ዓለም ጋር ይጠፋሉ፡፡

    የጌታን መምጫ ቀንና ሰዓት ማንም አያውቅም፤ ነገር ግን የኖህ የጥፋት ውሃ እንደመጣ ሁሉ እርሱም ይመጣል፡፡ 

    ጌታ ሰዎች የኖህ የጥፋት ውሃ እስከሚወርድ ድረስ ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደነበር ተናገረ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም እስከሚያጠፋቸው ድረስ እንኳን የተቃረበውን ጥፋት እንዳላወቁም ተናገረ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከኖህ ቤተሰብ በስተቀር ሁሉም ነገር በጥፋት ውሃ እንደጠፋ ይናገራል፡፡ በዚያን ዘመን እነርሱ ራሳቸው እስከሚሞቱበት ቅጽበት ድረስ ከሕዝቡ መካከል ጥፋት እየቀረበ እንደነበር ያወቀ ሰው አልነበረም፡፡

    ይህንን እውነታ ማን የማያውቅ አለ? በዚህ ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ ይህንን እውነታ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን ይህም ቢሆን በኖህ ዘመን የነበሩት ሕዝቦች ኖህ ያስጠነቀቃቸውን እየመጣ ያለ ጥፋት በሚመለከት ግድ እንዳልሰጣቸው ሁሉ እነርሱም የጌታችን መምጫ ዘመን የመቃረቡ እውነታ ግድ አይሰጣቸውም፡፡ የጌታ ምጽዓት መቃረቡን ማወቅ አለብን፡፡ የዚህ ዓለም የጥፋት ጊዜ የተቃረበ መሆኑም እንደዚሁ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት ጌታችን የምጽዓቱ ጌታ ሆኖ ወደ እኛ የሚመጣበት ጊዜ ተቃርቦዋል ማለትም ነው፡፡

    ጌታችን ለሁለተኛ ጊዜ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ምን ያደርጋል? ጌታ ከሐጢያቶቻቸው ደህንነትን ያገኙትን ሰዎች በሙሉ ከእርሱ ጋር በአዲሱ ዓለም እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጌታ በእርሱ ጽድቅ የማያምኑትን ሐጢያተኞች ሊፈርድባቸው ይመጣል፡፡ ጌታችን የሚመጣበት ጊዜ መቃረቡን ማወቅና መንቃት አለብን፡፡

    ጌታችን ለእኛ ለሰባኪዎችና ቅዱሳኖች ስለ ዳግመኛ ምጽዓቱ አስተማረን፡፡ ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤ ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች። ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር፡፡›› (ማቴዎስ 24፡40-43) የጌታ ምጽዓት ዘመን በግልጥ ተቃርቦዋል፡፡ ስለዚህ ጌታ መቼ እንደሚመጣ የማያውቁ ሰዎች መንቃትና በዚህ የጌታ ቃል ማመን አለባቸው፡፡ ጌታ ወደዚህ ዓለም ይመጣና አንዱን ከእርሱ ጋር ይወስዳል፤ ሌላውን ይተወዋል፡፡

    በዚህ ቃል ውስጥ ያሉት እነዚህ ሁለት ሰዎች ሁለት ዓይነት ሰባኪዎችን ያመለክታሉ፡፡ ሰባኪዎች በሙሉ በዚህ ዓለም ላይ የእግዚአብሄርን ስራ እየሠሩ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ ሰባኪዎች ሁሉ የወንጌልን ቃል ለሰዎች እየሰበኩ ነው፡፡ ጌታ በተጨባጭ ወደዚህ ዓለም ሲመለስ አንዱ ይወሰድና ሌላው ይቀራል፡፡ አንዱ በጌታ የሚወሰድ መሆኑ ወይም አለመሆኑ የሚወሰነው ያ ግለሰብ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን በመሆኑ ወይም አለመሆኑ ነው፡፡ ሁሉም የጌታን ስራ ይሰራሉ፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ የሚወሰነው በጌታ ዓይኖች ቅቡልነት ያገኙ በመሆኑ ወይም አለመሆኑ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ በሆነ መሠረት በጌታ ይወሰዳል ወይም በጌታ ይተዋል፡፡ በሰባኪዎችም መካከል እንኳን አንዳንዶች በጌታ ሲወሰዱ ሌሎች ይቀራሉ፡፡ ይህ ማለት ጌታችን የእምነታችንን የመጨረሻ ውጤት ይወስናል ማለት ነው፡፡ በጌታ የምንወሰድ መሆኑ ወይም አለመሆኑ የሚመረኮዘው በእኛ መለኪያ ሳይሆን በጌታ መለኪያ ነው፡፡ ጌታ ወደዚህ ዓለም ይመጣና መወሰድ የሚገባቸውን ይወስድና መጣል የሚገባቸውን ይጥላል፡፡ ጌታ እኛን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምነውንና ለእርሱ ታማኞች የሆንነውን ወደ ጌታ መንግሥት ይወስደንና በዚያ ለዘላለም እንድንኖር ያደርገናል፡፡

    ዛሬ ባነበብነው የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ላይ ጌታ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች፡፡›› (ማቴዎስ 24፡41) እዚህ ላይ ጌታ የሚናገረው ለማን ነው? ጌታ ይህንን ቃል እየተናገረ ያለው በዚህ ዓለም ላይ ለሚኖሩ ሰባኪዎች ነው፡፡ ጌታ እዚህ ላይ ለእኛ እየተናገረ ነው፡፡ ጌታ ለእናንተና ለእኔ እየተናገረ ነው፡፡ ጌታ እንድንነቃ እየነገረን ነው፡፡ ጌታ የጌታ የምጽዓት ጊዜ እየተቃረበ ስለሆነ መንቃት እንዳለብን እየተናገረ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ጌታ ለዳግመኛ ምጽዓቱ እንድንዘጋጅ እየነገረን ነው፡፡

    ጌታ ይህንን ወንጌል በታማኝነት እንድንሰብክም እየነገረን ነው፡፡ ጌታ ይህንን ወንጌል ለዚህ ዓለም ሰዎች ሁሉ በታማኝነት እንድንሰብክ እየነገረን ነው፡፡ ይህ ማለት ወንጌልን በዚህ መልኩ እየሰበክን ጊዜው ሲደርስ ወደ ጌታ መንግሥት እንገባለን ማለት ነው፡፡ ጌታ ‹‹ንቁና ይህንን ወንጌል ስበኩ፡፡ ወደዚህ ዓለም ስመለስና ሰዎች በዚህ መልኩ ሲኖሩ ሳይ እነዚህን ሰዎች እባርካለሁ፡፡ ነገር ግን የሚሰክርና ከዚህ ዓለም ሰዎች ጋር የሚቀላቀል ሰው ካለ ጠንካራ ቅጣት እቀጣዋለሁ›› አለ፡፡ ጌታ ክፉውን ከጻድቁ እንደሚለይም ተናገረ፡፡ (ማቴዎስ 13፡49) እጅግ አስፈሪው ቅጣት በእግዚአብሄር መጣል ነው፡፡ ጌታ ጊዜው በደምብ ሲደርስ እነዚህን ነገሮች እንደሚያደርግ ተናገረ፡፡

    እኛ አሁን በመላው ዓለም ሁሉ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እየሰበክን ነው፡፡

    ጌታ አሁን ጌታችን ወደፊት ሲመጣ የሚያደርጋቸውን ነገሮች አስቀድሞ እየነገረን ነው፡፡ ጌታ ጥፋቶች በዚህ ዓለም ላይ በየስፍራው ሲከሰቱ የሰው ልጅ በደጅ እንደቀረበ እንድናውቅ እየነገረን ነው፡፡ ሆኖም ጌታ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም፡፡›› (ማቴዎስ 24፡36) ጌታ እዚህ ላይ እነዚህን ሁለት ነገሮች ያለ ማቋረጥ ይደጋግማቸዋል፡፡ ጌታ የምጽዓቱን ጊዜ ይጠቁመናል፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓለም ሕዝቦች መካከል የጌታን ምጽዓት ጊዜ የሚያውቅ የለም፡፡ ከዚህም በላይ የዓለም ሕዝቦች የጌታን ምጽዓት ጊዜ ማወቅ የለባቸውም፡፡ ጌታ የጌታ ምጽዓት መቃረቡን ማንም እንደማያውቅ የተናገረው ለዚህ ነው፡፡

    በቤልጅየም ጁሊያን ቻደርተን የተባለ ሰው ነበር፡፡ አሁን 50 ዓመት አካባቢ ይሆነዋል፡፡ እርሱ መጽሐፎቻችንን ካነበበ በኋላ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ስርየት እንደተቀበለና ወንጌልን ከእነርሱ ጋር ከተካፈለ በኋላም ሚስቱና ሴት ልጆቹም ወንጌልን በጉጉት እንደተቀበሉ ተናገረ፡፡ እኛም እርሱን በሚሽናችን ከተሾሙ ወንጌላውያኖች አንዱ አድርገን ልንሾመውና ወንጌልን በአገሩ ዌስት ኢንዲስ፣ ሴይንት ኪቲስና ኔቪስ ለሚገኙ ሰዎች የመስበኩን ስራ በአደራ ልንሰጠው እያቀድን ነው፡፡

    በኮርያ ያሉ ወንድሞችና እህቶች እንደዚሁም በውጪ አገር ያሉ አጋር ሠራተኞቻችን በእግዚአብሄር ፊት የወንጌል ሰባኪዎች ሆነው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመላው ዓለም እየሰበኩ ነው፡፡ ጌታ እዚህ በማቴዎስ ምዕራፍ 24 ከቁጥር 45 እስከ 46 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤›› ይህ ማለት የእግዚአብሄርን ሕዝብ የሚንከባከቡና በጊዜው መንፈሳዊ ምግብ የሚሰጡዋቸው ሰዎች ይባረካሉ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር አምሳል መልክ ላላቸው ሰዎች በጊዜው መንፈሳዊ ምግብን የሚሰጡ ሰዎች እነማን ናቸው? እነርሱ እስከ ጌታ ምጽዓት ድረስ የጌታን እውነት ቃል የሚሰብኩ ሰዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሄርን የሕይወት እንጀራ በመላው ዓለም የሚሰብኩ ሰዎች የተባረኩ ሰዎች ናቸው፡፡ አጋር ሰራተኞቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የእግዚአብሄር መንፈሳዊ ምግብ የሆነውን ወንጌል ለማካፈል የወርቃማው መቅረዝ ጌጠኛ ጉብጉቦች ሆነው እየሰሩ ነው፡፡

    እኛ የእግዚአብሄርን ስራ ያለ ማቋረጥ እንሰራለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ይህንን ወንጌል ሲቀበሉ ሌሎች አይቀበሉም፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚቀበሉ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ይወሰዳሉ፤ ነገር ግን ይህንን ወንጌል የማይቀበሉ አላማኒዎች ይቀራሉ፡፡ እኛ አሁን የጌታ ምጽዓት እየተቃረበ ሳለ ወንጌልን እየሰበክን ነው፡፡ ጌታ ሲመጣ እነዚህ ነገሮች በእርግጠኝነት ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ መንፈሳዊ ምግብን በጊዜው የሚያሰራጩ ሰዎች እንድንሆን ከልቤ እሻለሁ፡፡ በመላው ዓለም በጣም ብዙ ሰዎች አሁን በእኛ አማካይነት የሐጢያቶችን ስርየት እየተቀበሉ ነው፡፡ ነገር ግን እኛን የሚቃወሙን ብዙ ሰዎችም ደግሞ አሉ፡፡ የሆኖ ሆኖ አንድ ግልጥ የሆነ ነገር አለ፤ ያም የጌታ ምጽዓት የተቃረበ መሆኑ ነው፡፡

    በኖህ የጥፋት ውሃ ዘመን የጥፋት ውሃ ዓለምን እስከሚያጠፋ ድረስ የሰዎች ፍላጎት ማግባትና መጋባት፣ እንደዚሁም ሌሎች የዚህ ዓለም ስጋዊ ነገሮች ብቻ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ አጥፊው ዝናብ ለ40 ቀናት ቆየ፡፡ ነገር ግን የጥፋት ውሃ እስከሚጀምርበት ቅጽበት ድረስ እንኳን እነርሱ ሲበሉና ሲጠጡ ነበር፡፡ እንደሚጠፉ በጭራሽ አላሰቡም፡፡ በቶሎ ስለሚመጣው የዓለም ጥፋት የሚናገረውን የእግዚአብሄር ቃል የታዘዙትና መርከብን ያዘጋጁት ኖህና ቤተሰቡ ብቻ ነበሩ፡፡ ከኖህ ቤተሰብ በስተቀር በዚያ መልኩ ያሰበ ሌላ ሰው አልነበረም፡፡ ሰዎች ‹‹ምንም ያህል ብዙ ቢዘንብ በጣም የተንቦረቀቀውን መላውን ምድር ሊያጠለቀልቅ ይቻለዋል? ምንም ያህል ብዙ ቢዘንብ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ ብዬ አላስብም፡፡ የፍሳሽ ማሳለጫ ስርዓቱ በትክክል እየሰራ መሆኑን ብቻ ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ ውሃው የቆሻሻ መውረጃ ቱቦውን አጥለቅልቆ ወደ ውጪ የሚፈስ ከሆነ ጣሪያዎች ላይ መሰቀል ይኖርብናል፡፡ ውሃው ወደ ጣሪያዎች ከደረሰ ወደ ተራሮች ጫፎች መሄድ ይኖርብናል፡፡ ውሃው ወደ ተራራው ጫፍ ከደረሰ ከፍ ወዳለ ተራራ መሄድ ይኖርብናል›› ብለው አሰቡ፡፡ እነርሱ ‹‹ምንም ያህል ብዙ ቢዘንብ መላው ዓለም እንደሚጥለቀለቅ እጠራጠራለሁ›› ብለው አሰቡ፡፡

    በኖህ ዘመን ምናልባትም በሒማልያ የተራሮች ሰንሰለት ላይ እንዳለው የኤቨረስት ተራራ ከፍ ያለ ተራራ አልነበረ ይሆናል፡፡ የዚህ ዓለም ከፍ ያሉ ተራሮች በዲያስትሮፒክ የምድር ለውጦች የተፈጠሩ ነበሩ፡፡ የሆኖ ሆኖ በኖህ ዘመን ከፍ ያሉ ተራሮች የነበሩ ስለመሆናቸው አላውቅም፡፡ ነገር ግን መላው ዓለም በጥፋት ውሃ መጥለቅለቁ እውነት ነው፡፡ ሆኖም በዚያን ዘመን የነበሩት ሰዎች እንዲህ ያለ ነገር መቼም የሚከሰት ስለመሆኑ ተጠራጠሩ፡፡ እነርሱ ‹‹እነዚህ ነገሮች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ቢከሰቱ እንኳን እኔ ብቻ ሳልሆን ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ›› ብለው አሰቡ፡፡ እነርሱ በዚህ መልኩ በደብዛዛው አሰቡ፡፡ ነገር ግን የጥፋት ውሃ በተጨባጭ ተከሰተ፡፡

    በዚህ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች እሳቤ በኖህ ዘመን ይኖሩ ከነበሩት ሰዎች እሳቤ ጋር ሲነጻጸር እንዴት ነው? ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በኖህ ዘመን እንደመጣው የጥፋት ውሃ ጥፋት በዚህ ዓለም ላይ ድንገት ይመጣል፡፡ ይህ ጥፋት በተጨባጭ ድንገት ይመጣል፡፡ መቼ? ያ ጊዜ በጣም ቅርብ ነው? ያ ጊዜ የተቃረበ ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑ መከራከርና መወያየት አይኖርብንም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በክርስትና ውስጥ ስላሉት የቤተክርስቲያን ድርጅቶችም እንኳን ክፍፍሎችን ማድረግም አያስፈልግም፡፡ አንጃዊነትን አጥብቆ መያዝ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? የየትኛውም የቤተክርስቲያን ድርጅት ወገን ብትሆኑም በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያቶች የሚኖሩ ከሆነ ትጠፋላችሁ፡፡ ስለዚህ ማድረግ የሚኖርባችሁ ብቸኛው ነገር ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ጋር ስትገናኙ በእርሱ በማመንና የሐጢያቶቻችሁን ስርየት በመቀበል ልባችሁን ለእውነተኛ እምነት ማዘጋጀት ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን እምነት ያለው ሰው ሆናችሁ ማደግ፣ በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ያንን ክቡር እምነት መጠበቅና ጌታ ሲመለስም እርሱን በምስጋና መቀበል ይኖርባችኋል፡፡ ስለዚህ በጌታ የምንወሰድ ከሆነ ዓላማችንን እንፈጽማለን፡፡ ታዲያ ማድረግ ያለብን ይህንን ብቻ ሆኖ ሳለ አሁን የቤተክርስቲያን ድርጅቶችን የምንከፋፍለው ለምንድነው? በእነዚህ የመጨረሻ ጊዜያት በክርስቲያን ማህበረሰቦች ውስጥ በአንጃነት እርስ በርስ የምንጣላው ለምንድነው?

    ሰዎች የእግዚአብሄርን ፈቃድ ስለማያውቁ በዚህ ዓለም ላይ ለሺህ ዓመታት ያህል የሚኖሩ ይመስል ለስጋቸው የሚሆኑ ነገሮችን ብቻ ያዘጋጃሉ፡፡ ነገር ግን በዚያ መልኩ የሚኖሩ ከሆነ ይጠፋሉ፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ክርስቲያን አማኞችም በሙሉ እንደዚሁ በዓለማዊ ጉዳዮች መካከል ይህንና ያንን የሚያስቡበት ጊዜ የለም፡፡ ሰው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በአንድ ሰው ሲሰበክ ወይም ከመጽሐፎቻችን አንዱ ሲነበብ ሲሰማ በእርሱ ለማመን ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ አሁን ሐጢያተኞች በሙሉ የጌታን ዳግመኛ ምጽዓት ለመገናኘት መዘጋጀት አለባቸው፡፡ እነርሱ ጌታን ለመገናኘትና ወደ ጌታ መንግሥት ለመግባት መዘጋጀት አለባቸው፡፡ እኛ ዳግመኛ የተወለድን ሰዎች አሁን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመላው ዓለም ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ መስበክ ያለብን ለዚያ ነው፡፡ እውነተኛ ሕይወት የሚሰጠውን ይህንን የሕይወት እንጀራ ማሰራጨት አለብን፡፡

    ታዲያ ለእያንዳንዱ ነፍስ የሚሆነው ይህ መንፈሳዊ ምግብ ምንድነው? የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እውነተኛ ሕይወት ያለው በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ነው፡፡ ይህ ቃል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሕይወት ቃልና የእውነት ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ነፍሶቻችንን ያድስና እንድንባረክ ያደርገናል፡፡

    አሁን የዓለም ጥፋት እየተቃረበ ነው፡፡ ስለዚህ ሐጢያተኞች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቀበል የሚገባቸው ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑ ተዝናንተው ለማሰብ ጊዜ የላቸውም፡፡ እኛ አሁን የስብከት መጽሐፎቻችንን ለሚያሰራጩ አጋር ሰራተኞቻችን በብዛትና ለግለሰብ ጠያቂዎችም በትናንሽ ካርቶኖች እየላክን ነው፡፡ አልፎ አልፎ ለግለሰቦች አንድ ወይም ሁለት መጽሐፎችን ከመላክ ባሻገር በአንድ ጊዜ ከ3,000 እስከ አስር ሺህ ያህል ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መጽሐፎቻችንን እየላክን ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ብዙ መጽሐፎችን እየላክን ነው፡፡ እኛ እነዚህን መጽሐፎች በዚህ መልኩ ለእያንዳንዱ አገር ስንልክ አንዳንድ ሰዎች እነዚህን መጽሐፎች አንብበው ይህንን ወንጌል ሲቀበሉ አንዳንዶች አይቀበሉም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ትንሽ ካነበቡ በኋላ ያስቀምጡዋቸዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎችም ለሌሎች ሰዎች ይሰጡዋቸዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነርሱ ከተማሩት የተለየ እንደሆነ ያዩና መጽሐፉን ዘግተው ኑፋቄ ነው ብለው ይፈርጁታል፡፡

    ነገር ግን እነርሱ በአስቸጋሪ ሁኔታቸው ውስጥ እንደዚህ ሊሆኑ ይችላሉን? ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ስለሆኑ እንዲህ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በሐጢያቶቻቸው ምክንያት አሁኑኑ ለመጥፋት የተዘጋጁ ሐጢያተኞች ሆነው ሳሉ የእግዚአብሄርን ወንጌል አለመቀበል አይችሉም፡፡ እነርሱ በእርግጠኝነት መጥፋት የሚገባቸው ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ ታዲያ በዚያ መልኩ በእጅጉ ግትሮች ከሆኑ ከዚህ እየቀረበ ከሚመጣው ጥፋት እንዴት ደህንነትን ሊቀበሉ ይችላሉ? እነርሱ አመስጋኞች መሆንና በፍጥነት ይህንን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቀበል አለባቸው፡፡ እግዚአብሄር ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ሊያድናችሁ የሚሻ ከሆነ እናንተም ደግሞ አመስጋኝ መሆን አለባችሁ፡፡

    ሰዎች የሚሰጡት ምላሽ ምንም ይሁን እኛ ሰባኪዎች በጊዜው መንፈሳዊውን ምግብ ከእነርሱ ጋር መካፈል አለብን፡፡

    እኛ የሕይወትን እንጀራ በትጋት መስጠት አለብን፡፡ እኛ ሰባኪዎች ይህንን ምግብ ስናሰራጭ ማዳላት የለብንም፡፡ ምግቡን ለምንወዳቸው ሰዎች መስጠትና ለማንወዳቸው ሰዎች መከልከል የለብንም፡፡ የሥነ ጽሁፍ አገልግሎትን እየሰራን ያለነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ እኛ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የያዙትን ብዙ መጽሐፎች እያተምንና እያሰራጨን ነው፡፡ እነዚህን የሚሽን መጽሐፎች በዚህ መልኩ ስናሰራጭ አንዳንድ ጊዜ ችግሮች ውስጥ እንገባለን፤ ችግሮችም ይገጥሙናል፡፡ ነገር ሰዎች ያነቡዋቸውና ደህንነትን ይቀበላሉ፡፡ ማመን የሚገባቸው አንባቢዎች በእውነተኛው ወንጌል ያምናሉ፡፡ ሌሎች አንባቢዎች ግን እውነተኛውን ወንጌል አያምኑትም፡፡ ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ይህንን መጽሐፍ ይወረውሩት ወይም ለአንዳንድ ሌሎች ጓደኞች ይሰጡት ይሆናል፡፡ እነርሱ ‹‹ይህንን መጽሐፍ ትፈልጋለህ? ቤተክርስቲያን ትሄዳለህ አይደል? ቀጥል ይህንን መጽሐፍ አንብብ፡፡

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1