Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች
በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች
በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች
Ebook561 pages4 hours

በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ሐይል የሌለን ብንሆንም የእግዚአብሄር ቃል ሐይል ስላለው ቃሉ ምድር ላይ ሲወድቅ ያለ ችግር ፍሬ ያፈራል፡፡ በተጨማሪም የእግዚአብሄር ቃል ሕያው ስለሆነ ዛሬም፤ ነገም፤ ለዘላለምም የማይለወጥ መሆኑን ራሳችን ማየት እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እንደ ሰው ቃሎች ስላይደለ ፈጽሞ አይለወጥም፡፡ ሁሌም የታመነ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሲናገር በቃሎቹ መሰረት በትክክል ይፈጸማል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስልጣን ስላለው እግዚአብሄር ‹‹ብርሃን ይሁን›› ሲል ብርሃን ሆነ፡፡ ‹‹ታላላቅ ብርሃናትና ታናናሽ ብርሃናት ይሁኑ›› ሲል ባዘዘው መሰረት ተፈጸመ፡፡

Languageአማርኛ
PublisherPaul C. Jong
Release dateSep 15, 2023
ISBN9788928221479
በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች

Related to በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች

Related ebooks

Reviews for በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII) - የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች - Paul C. Jong

    paul_Am55_coverFrontflap_Am551st_page

    በዘፍጥረት ላይ የተሰጡ ስብከቶች (VII)

    የአብርሃም እምነት ያላቸው ሰዎች

    Smashwords Edition

    Copyright 2023 by Hephzibah Publishing House

    ሙሉ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ባለቤት በጽሁፍ የተገኘ ፈቃድ ሳይኖር የዚህን መጽሐፍ ማንኛውንም ክፍል ማባዛት ወይም በማንኛውም መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ በኤሌክትሮኒክ ወይም በሜካኒካል ፎቶ ኮፒ ማድረግን ጨምሮ በቅጂ መልክ ወይም መረጃን ይዞ በሚያጠራቅም ወይም መረጃን ይዞ በሚያስቀር ማንኛውም መንገድ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

    ጥቅሶቹ በሙሉ የተወሰዱት ከ1954ቱ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ হয়েছে।

    ISBN 978-89-282-2147-9

    ዲዛይን፡ በሚን ሱ ኪም

    ንድፍ፡ በዮንግ አይ ኪም

    ትርጉም፡ በካሳሁን አየለ

    የታተመው በኮርያ ነው፡፡

    Hephzibah Publishing House

    A Ministry of THE NEW LIFE MISSION

    Seoul, Korea

      የማውጫ ሰሌዳ  

    መቅድም

    1. አሳቦቻችሁን ጣሉ፡ ከአገራችሁ፣ ከቤተሰባችሁና ከአባታችሁ ቤት ውጡ (ዘፍጥረት 12፡1-5)

    2. የሚቃጠለው ቁርባን መሠውያ እምነት (ዘፍጥረት 12፡1-9)

    3. በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን በኩል የሚገኙ በረከቶች (ዘፍጥረት 12፡5-20)

    4. በእምነት የሚቆሙ ሰዎች (ዘፍጥረት 12፡10-20)

    5. የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን ማወቅ አለባችሁ (ዘፍጥረት 12፡10-20)

    6. ልባችሁን በከነዓን ምድር ላይ አኑሩ (ዘፍጥረት 13፡1-18)

    7. ጌታ ልቦቻቸውን ካዘጋጁ ሰዎች ጋር ነው (ዘፍጥረት 13፡1-18)

    8. በመንፈስ ተመላለሱ (ዘፍጥረት 13፡1-18)

    9. እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ ነው (ዘፍጥረት 13፡14-18)

    10. ሐብታችሁን ለጌታ አውሉ (ዘፍጥረት 14፡1-24)

    11. እኛ ከዓለም የተቀደስን የእግዚአብሄር ልጆች ነን (ዘፍጥረት 14፡1-16)

    12. የእምነት ሕይወት የመተባበር ጉዳይ ነው (ዘፍጥረት 14፡1-24)

    13. አብርሃም ስጋን በመከተል ፋንታ እግዚአብሄርን ተከተለ (ዘፍጥረት 14፡17-24; 15:1)

    14. ቁሳዊ ሐብቶችን የተወው የአብርሃም እምነት (ዘፍጥረት 14፡17-24; 15:1)

    15. አብርሃም በትክክል ታላቅ ሰው ነበር (ዘፍጥረት 14፡17-24)

    16. እግዚአብሄርን ከዓለም አስበልጣችሁ ውደዱት (ዘፍጥረት 15፡1)

    17. ከአብርሃም እምነት ጋር ተመሳሳይ የሆነ እምነት (ዘፍጥረት 15፡1-6)

    18. አብርሃም ከእግዚአብሄር የተቀበለው ጽድቅ (ዘፍጥረት 15፡1-7)

    19. ልባችሁን ከቁሳዊ ስስት ማራቅ አለባችሁ (ዘፍጥረት 15፡1-7)

    20. አብርሃም የነበረው እምነት ይኑራችሁ (ዘፍጥረት 15፡1-21)

    21. በእግዚአብሄር ቃል የሆነው የደህንነት ዘር (ዘፍጥረት 15፡3-11)

    0preface.jpg

    መቅድም

    የእውነተኛ እምነት ፋና ወጊዎች የአብርሃም ዓይነት ተመሳሳይ እምነት በመያዝ እግዚአብሄርን የተከተሉ ሰዎች ነበሩ፡፡

    አብርሃም ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሄርን ቃሎች ለሚያምኑና ለሚከተሉ ሰዎች ሁሉ የእምነት አባት ተብሎ ይጠራል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ አብርሃም በተነገረው ቃል መታመኑና እግዚአብሄርን መከተሉ ነው፡፡ እርሱ ራሱንም ደግሞ በዚህ ቃል አድሶዋል፡፡ በአብርሃም ዘመን ጣዖት አምልኮ በጣም ተስፋፍቶ ስለነበር የራሱ አባትም እንኳን ጣዖታትን አምላኪ ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር አብርሃምን በተናገረው ጊዜ እርሱን በመታዘዝ በደፍረት ተከተለው፡፡ አብርሃም የእግዚአብሄርን ቃል በሰማና እርሱን ለመከተል በወሰነ ጊዜ 75 ዓመቱ ነበር፡፡ በዚህ ዕድሜው አብርሃም በርካታ የራሱ ቀደምት እሳቤዎች የነበሩት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄርን መከተል የቻለው እነዚህን ጠንካራ አሳቦች በካደ ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ አብርሃም የእግዚአብሄር አሳቦች ትክክል እንደነበሩ በማመኑ በእርግጥም አሳቦቹን መካድና የእግዚአብሄርን ቃል በእምነት መከተል ቻለ፡፡

    እናንተስ ታዲያ? እናንተም ደግሞ የእግዚአብሄርን አሳቦች ለመከተል የራሳችሁን አሳቦች ክደችኋልን? እናንተና እኔ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያቶችንን ስርየት ተቀብለናል፡፡ እኛ የመጀመሪያዎቹ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አግኚዎች በመሆናችን ልክ እንደ ቀደምቶቹ የአዲሱ ዓለም አሳሾች የማይታወቀውን የእምነት ግዛት ማሰስ አለብን፡፡ እኛ በብዙ መንገዶች አሜሪካውያኑን እንዳገኘው እንደ ክርስቶፈር ኮለምበስ ነን፡፡

    ክርስቶፈር ኮለምበስ፡ አሜሪካውያኑን ያገኘው አሳሽ፡፡

    ነሐሴ 3, 1492 በክርስቶፈር ኮለምበስ የተመሩ 88 አሳሽ ሰዎች በሦስት አነስተኛ የእንጨት የጉዞ መርከቦች አትላንቲክን የማቋረጥ ወሳኝ ጉዞ በጀመሩበት በፓሎስ ታሪካዊ ኩነት ተፈጠረ፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች መሬት ጠፍጣፋ ናት የሚል ትምህርት ስለተማሩ ወደ ባህሩ መጨረሻ የደረሰ ማንኛውም ሰው ከጠርዙ ተወርውሮ ይሞታል ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ነገር ግን ኮለምበስ ምድር ክብ እንደሆነች አመነ፡፡ ስለዚህ ወደ ምዕራብ ቢቀዝፍ በእርግጠኝነት ሕንድ እንደሚደርስ አሰበ፡፡ ነገር ግን ከእርሱ ጋር የነበሩት መርከበኞች በሙሉ ፈሩ፡፡ ኮለምበስ ምድር ክብ እንደሆነች ቢያምንም መርከበኞቹ በእርሱ ቃሎች አላመኑም፡፡

    ጥቅምት 20፡1492 በባህማስ ባለች አንዲት ደሴት ላይ ደረሰ፡፡ ወዲያው ሳን ሳልቫደር ብሎ ሰየማትና ስፔንን ወሰደ፡፡ ደሴቲቱ የሕንድ ክፍል ስለነበረች ነዋሪዎችዋን ‹‹ሕንዳውያን›› ብሎ ጠራቸው፡፡ በዚህ ምክንያት የአሜሪካውያኑ አገር በቀል ሕዝቦች በጥቅሉ ሕንዳውያን ተብለው ተጠሩ፡፡ ኮለምበስ ይህንን በሕይወት ዘመኑ በጭራሽ ባይገነዘበውም ከቫይኪንግ ዘመን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ውቅያኖስን አቋርጦ በመቅዘፍ በተጨባጭ አሜሪካውያኑን አግኝቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኮለምበስ ወደ ምዕራብ ኢንድስ ያደረገው የአሰሳ ጉዞ ግኝት አሜሪካዎች ለአውሮፓውያኑ እንቅስቃሴዎች ዋና ጣቢያ በመሆናቸው ከፍተኛ ታሪካዊ ፋይዳ ይዘዋል፡፡ ይህ ግኝት ስፔን አዲሱን ዓለም በቅኝ ግዛት እንድትይዝ መሠረትን ጣለ፡፡

    ኮለምበስ ከሰባት ወራት በኋላ ወደ ስፔን ሲመለስ ልክ ድል እንዳደረገ የጦር አለቃ አቀባበል ተደረገለት፡፡ ንግሥት ኤዛቤላም እርሱን እንኳን ደህና መጣህ ለማለት ትልቅ ዝግጅት አዘጋጀች፡፡ በዝግጅቱ ላይም በኮለምበስ የቀና አንድ ሰው ‹‹ማንም ሰው ወደ ምዕራብ በመቅዘፍ ቢቀጥል ሕንዶችን ማግኘት ይችላል›› የሚል አስተያየት ሰጠ፡፡

    ኮለምበስ ይህንን ከሰማ በኋላ አንድ የተቀቀለ እንቁላል አንስቶ እንዲህ አለ፦ ‹‹ይህ እንቁላል በቂጡ እንዲቀመጥ ማድረግ የሚችል ሰው አለ?›› ስለዚህ ሁሉም ሰው ሞከረ፤ ነገር ግን ማንም ሊሳካለት አልቻለም፡፡ ከዚያም ኮለምበስ እንቁላሉን አነሳና የእንቁላሉን ቂጥ ለመስበር እንቁላሉን በዝግታ በጠረጴዛው ላይ መታ አደረገውና እንቁላሉ እንዲቆም አደረገው፡፡ ይህንን ያዩ ሁሉ ሳቁበት። ኮለምበስ ግን እንዲህ አለ፦ ‹‹ስኬት ላይ ከተደረሰ በኋላ ማንም ሰው ያንን ማድረግ ይችላል፡፡ በተጨባጭ አስቸጋሪው ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ እዚያ ስኬት ላይ መድረስ ነው፡፡›› በዚያ ተገኝተው የነበሩ ሁሉ በኮለምበስ ቃሎችና ድርጊቶች ተደመሙ፡፡

    ልክ እንደዚሁ ለመጀመሪያ ጊዜ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመንና የጌታን ምሪት መከተል በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይም ፍርሃትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ ከእናንተ በፊት ጌታን የተከተሉትን የጌታን አገልጋዮች ዱካዎች የምትከተሉ ከሆነ እናንተም ደግሞ አሸናፊዎች ትሆናላችሁ፡፡ የአብርሃም እምነትና ሕይወት በእግዚአብሄር ቅቡልነትን ያገኘው ሙሉ በሙሉ በቃሉ በመታመን እግዚአብሄርን በመከተሉ ነው፡፡ እኛም ከእምነት ቀደምቶቻችን ጋር አብረን የእግዚአብሄርን ቃሎች የምንከተል ከሆንን አብርሃምን መምሰል እንችላለን፡፡ ስለዚህ ልክ እንደ አብርሃም የእምነት ድል አድራጊዎች እንሁን!

    Sermon0101

    አሳቦቻችሁን ጣሉ፡ ከአገራችሁ፣ ከቤተሰባችሁና ከአባታችሁ ቤት ውጡ

    ‹‹ ዘፍጥረት 12፡1-5 ››

    ‹‹እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።››

    በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ማድረግ የሚገባን የመጀመሪያው ነገር ከአገራችን፣ ከቤተሰባችንና ከአባታችን ቤት መውጣት ነው፡፡

    ዛሬ ስለ አብርሃም መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ቅዱሳት መጻህፍት አብርሃምን የእምነት ቅድመ አያት አድርገው ይጠቁሙታል፡፡ ከአብርሃም ሕይወት ማየት እንደምንችለው እርሱ ሁሌም ከእግዚአብሄር ጋር አካሄዱን አድርጓል፤ እርሱንም አምኖዋል፤ በእርሱም ላይ ተደግፏል። እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፦ ‹‹እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤›› (ዘፍጥረት 12:1-2)

    ጌታ አብርሃምን ከቤተሰቡና ከአባቱ ቤት ርቆ ከአገሩ እንዲወጣና እግዚአብሄር ወደሚያሳየው ምድር እንዲሄድ ነገረው፡፡ ይህ በሆነ ጊዜ አብርሃም 75 ዓመቱ ነበር፡፡ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በመኖር የተቆራኘበትን አገር ትቶ መሄድ በእርግጥም አዳጋችና አስቸጋሪ የሆነበት መሆን አለበት፡፡ ለማናቸውም ሰዎች ቢሆን ለረጅም ዘመን ሲኖሩበት የነበሩበትን አገራቸውን ትቶ መውጣት ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ በጥንት ዘመን ሰዎች እንደ ጦርነት ያለ አንዳች ዓይነት መዓት ካልመጣ በቀር አገራቸውን ትተው አይሄዱም ነበር፡፡ አገር ሰው የተወለደበትና ያደገበት ስፍራ ብቻ ሳይሆን ሰው የሚያርፍበት እንደ እናት እቅፍ ያለ ስፍራም ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎችና የዱር አራዊቶችም እንኳን ለመሞት ሲቃረቡ ወደ አገራቸው ለመመለስ ይናፍቃሉ፡፡ ሰዎች ወደ አገራቸው መመለስ ሳይችሉ የቀሩ ሙታኖቻቸውን ጭንቅላታቸውን ወደ አገራቸው አዙረው ይቀብሩአቸዋል፡፡

    ነገር ግን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ልናደርገው የሚገባን የመጀመሪያው ነገር ከአባታችን ቤት፣ ከቤተሰባችንና ከአገራችን ተለይተን መውጣት ነው፡፡ ከአገራችን፣ ከቤተሰባችንና ከአባታችን ቤት ካልወጣን ትክክለኛ መንፈሳዊ ሕይወት መምራት አንችልም፡፡ አብርሃም ወደ ከነዓን ምድር እንዲገባ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነበር፡፡ እግዚአብሄር አብርሃምን የአባቱን ቤት እንዲተው የነገረው ይህንን እንዲያደርግ ነው፡፡ እናንተና እኔም እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን ለመኖር በመጀመሪያ ከአባታችንና ከቤተሰባችን ቤት ተለይተን መውጣትና ሁለተኛም እግዚአብሄር ወዳሳየን ከነዓን መግባት አለብን፡፡

    የአባታችንን ቤት መተው ማለት በተጨባጭ አሁን እየኖርንበት ያለንበትን ቤት መተው ይኖርብናል ማለት አይደለም፡፡ ይህ ማለት እምነታችንን ለመኖር ደህንነትን ከመቀበላችን በፊት ይዘናቸው ከኖርናቸው ስጋዊ አሳቦቻችን መለየት አለብን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሊመራን የሚችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩን ስጋዊ አሳቦች የምንሞላ ከሆነ እግዚአብሄር ወደሚያሳየን ምድር መግባት አንችልም፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ካመነ በኋላ ይህንን መንፈሳዊ ሕይወት መምራት የሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው አሳምረን የምናውቀውን ስፍራ የአባታችንን ቤትና በአገራችን ያሉትን ቤተሰብ መተው አለበት፡፡

    በሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ የምንወስዳቸውን ኮርሶች በሙሉ ወደ ማጠናቀቁ ተቃርበናል፡፡ ለጊዜው ሦስቱ እህቶቻችን በቹን-ቺኦን ቤተክርስቲያን ይቆያሉ፡፡ ወንድሞችም ወደ ሌሎች ቤተክርስቲያኖች ይላካሉ፡፡ በቀጣዩ መንፈቅ በሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ የሚመዘገቡና ሥልጠና የሚወስዱ ሦስት ተጨማሪ ቤተሰቦች አሉ፡፡ እነርሱም እንደዚሁ በሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ ሥልጠናን ከተቀበሉ በኋላ ይህንን ስፍራ ትተው ይሄዱና በተለየ ስፍራ ያገለግላሉ፡፡ እነርሱ ወንጌልን በብዙ ተጨማሪ ስፍራዎች ለመስበክ በዚህ መልኩ ተለይተው ይሄዳሉ፡፡

    ነገር ግን ለረጅም ጊዜ የኖርንባቸውን ልቦቻችንን፣ አሳቦቻችንና ስጋችን አውጥተን መጣል በእርግጥም አስቸጋሪ ነው፡፡ አብርሃም በአገሩ ከነበሩት ቤተሰቦቹ በመለየት እንዳደረገው ሁሉ እኛም ደግሞ ከአሮጌዎቹ አሳቦቻችን መለየት አለብን፡፡ ያ ግን በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰው የሐጢያቶቹን ስርየት ከተቀበለ በኋላ መንፈሳዊ ሕይወቱን ሲመራ ማድረግ ያለበት የመጀመሪያው ነገር አሳቦቹን መጣል ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ማድረግ ምን ያህል አዳጋች እንደሆነ የሚያውቀው ይህንን የሞከረ ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህ ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችንም ተመሳሳይ ነው፡፡ ነገር ግን በሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ ሥልጠናቸውን የጨረሱ ወንድሞችና እህቶች በተለይ አሁን የቤተክርስቲያንን አቅጣጫዎች በመታዘዝ የሙሉ ጊዜ የቤተክርስቲያን ሠራተኞች በመሆን ይህንን መንፈሳዊ ሕይወት መኖር አለባቸው፡፡ እነርሱ መታዘዝ የሚያስቸግራቸው ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ብዙ ነገሮችን መተው ስለሚኖርባቸው ነው፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያን የምታዛቸውን ትዕዛዞች ሁሉ የመታዘዝ ሕይወት፣ ቤተክርስቲያን ስትመራቸው መሄድና ቤተክርስቲያን እንዲመጡ ስትመራቸው መምጣት ቀላል አይደለም፡፡ በመጨረሻ ልናደርገው የሚገባን ነገር ወንጌልን መስበክ ስለሆነ ወንጌልን መስበክ እስከቻልን ድረስ የትም እንሁን የረካን ነን፡፡ ቤተክርስቲያን እንድንሄድና በሆነ ቦታ እንድናገለግል የምታዘን ከሆነ መሄድና በዚያ ስፍራ ማገልገል አለብን፡፡

    ለረጅም ጊዜ አብረን ከኖርን በኋላ አንዳችን ከሌላችን ጋር መለያየት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይም ጌታን የሚያገለግል ሠራተኛ ብዙውን ጊዜ ወንጌልን በብዙ ስፍራዎች ለመስበክ ስለሚንቀሳቀስ እንዲህ ያለ አስቸጋሪ መለያየት ይገጥመዋል፡፡ እኔም እንደዚሁ ጌታን ከተገናኘሁ በኋላ ብዙ ጊዜያቶች ወደዚህ ስፍራና ወደዚያ ስፍራ ተንቀሳቅሻለሁ፡፡ ነገር ግን በዚህ መልኩ መንቀሳቀስ በአንዳንድ ረገድ ጥሩ ነው፡፡ በአንድ ስፍራ መቆየት አሰልቺ ይሆን ነበር። አንዳንድ ጊዜ ስፍራን መቀየር ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ከሚሽን ትምህርት ቤት የሚመረቁ ወንድሞች ብዙም ስላልተንቀሳቀሱ አንዳንድ ችግሮች እንደሚገጥሙዋቸው አውቃለሁ፡፡ በጎችም እንደዚሁ ለመጀመሪያ ጊዜ እንግዳ ወደሆነ ስፍራ ሲገቡ ብዙ ይፈራሉ፡፡ አንድ ሰው በሚሄድበት ስፍራ አንዳች የደስታ መቅበጥበጥና ተስፋ አለ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት በጭራሽ የማያውቁት ስፍራ በመሆኑም ፍርሃትና ስጋትም ደግሞ ሊኖር ይችላል፡፡ ሰው ከሚኖርበት አገር መለየቱ በጣም አዳጋችና አስቸጋሪ ነው፡፡

    ነገር ግን በመላው አገሪቱ ያለችው ቤተክርስቲያን አንድ ስለሆነች የአገልግሎቱ ሥራ አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ይልቁንም ጥሩ ነው በምትሄዱበት ሁሉ ተመሳሳይ በሆነ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለምትሠሩ መጨነቅ አይኖርባችሁም፡፡ ቤተክርስቲያን ወደ አንድ ስፍራ እንድትሄዱ ስትመራችሁ እያንዳንዱን ነገር ስላዘጋጀችና ስለምትደግፍ በአንዳች ነገር መጨነቅ አይኖርባችሁም፡፡ መጀመሪያ የሠለጠኑ ወንድሞችና እህቶች በተሰጡዋቸው የሥልጣን ቦታዎቻቸው ጌታን ያገለግላሉ፡፡ በቅርቡ የሠለጠኑ ሠራተኞችም በእነዚያ ቀደምቶች ሥር ሆነው በተለያዩ ጉዳዮች መሠልጠናቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እነርሱም ደግሞ በአገራቸው ያሉትን የአባታቸውን ቤትና ቤተሰብ መተው ይኖርባቸዋል፡፡

    ይህ ቃል ለመንፈሳዊው ገጽታ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በተጨባጭ ስጋዊዎቹን የቤተሰብ ግንኙነቶች እንዲበጥስ ለአብርሃም የነገረው ቃል ነው፡፡ አብርሃም የእምነት ሰው ስለነበር የተወለደበትን አገር፣ ስጋዊ ቤተሰቡ የተወለዱበትን ስፍራና ያደገበትን ስፍራ ትቶ መሄድ ነበረበት፡፡ ከሚወዳቸው ቤተሰቡ ሊነጠልና ከዚህ በፊት በጭራሽ ኖሮበት ወደማያውቀው ውጪ አገር ሊሄድ በመሆኑ ለአብርሃም ቀላል አልነበረም፡፡

    ስጋዊ ወላጆች ቢሆኑም በመንፈሳዊ መልክ ዳግመኛ ያልተወለዱ ሰዎችን ትቶ መሄድ ያን ያህል አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ዳግመኛ በተወለድንበት ስፍራ በመንፈሳዊ ሁኔታ ካደግንና ከዚሁ ስፍራ ከተላክን ልክ እንዳደገና ጎረምሳ ሆኖ ቤቱን እንደሚለቅ ሕጻን ደስ በተሰኘ ልብ ተለይተን መሄድ አለብን፡፡ ዳግመኛ የተወለዳችሁባትንና በእንክብካቤ ያደጋችሁባትን ቤተክርስቲያን ቸል ማለትና መርሳት አለባችሁ ማለቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህችን ቤተክርስቲያን መነሻችሁ አድርጋችሁ በአዲስ ስፍራ ለብዙ ሰዎች ወንጌልን መስበክ አለባችሁ ማለቴ ነው፡፡ ይህንን የምታደርጉ ከሆነ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሆናል። ይባርካችሁማል፡፡ እግዚአብሄር የሚባርካችሁን ይባርካል፡፡ በእናንተ አማካይነት ዳግመኛ የተወለዱትንም ደግሞ ይባርካቸዋል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ እግዚአብሄር የሚባርኩንን እንደሚባርክና የሚረግሙንን እንደሚረግም ተስፋ ስለሰጠ ነው፡፡

    ስጋዊ አሳቦቻችንን መጣል አለብን።

    መንፈሳዊ ሕይወታችንን ስንመራ እጅግ አስፈላጊው ነገር የራሳችንን አሳቦች መጣል ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ በመንፈሳዊ ሕይወታችን የመጀመሪያው እርምጃ የሚጀምረው ከአገራችን፣ ከቤተሰባችንና ከአባቶቻችን ቤት መውጣት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን በእርግጠኝነት መውጣት አለብን፡፡ አሮጌ ልማዶቻችንንና አሳቦቻችንን በሙሉ መጣል አለብን፡፡ ዳግመኛ የተወለደ ግለሰብ አዳዲስ አሳቦች ሊኖረውና ከእግዚአብሄር ቃል የፈለቁትን አዳዲስ ትምህርቶች በማመን ሊከተል ይገባዋል፡፡ ደህንነት ከተገኘ በኋላ እያንዳንዱ ነገር አዲስ ነው፡፡ እኛ አዳዲስ ሰዎችን እንገናኛለን፡፡ አዲስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንገኛለን፡፡ አዲስ ሥነ ምህዳር ይገጥመናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገሮች አዲስ ይሆኑብናል፡፡ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ሁሌም አዳዲስ አሳቦች ሊኖራቸውና ጌታን በአዲስ እምነት ሊከተሉ ይገባል፡፡ ጌታን በእምነት መከተል ማለት የእግዚአብሄርን ቃል መከተል ማለት ነው፡፡ ይህም ደግሞ እነርሱን በቃሉ የሚመራቸውን መሪ ቃሎች መከተልና የቤተክርስቲያንን አቅጣጫዎች መከተል ማለት ነው፡፡

    የት እንደምትገኙ ማወቅ አለባችሁ።

    ተገደው ጡረታ የወጡ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ገና ጎረምሳ ቢሆኑም ጡረታ እንዲወጡ ተገደዱ፡፡ አንዳንዶችም ጡረታ በመውጣት ፋንታ ከሥራቸው ተባረሩ፡፡ እኛ ብዙውን ጊዜ በሚሠሩበት ድርጅት ወይም ካምፓኒ ላይ በማመጻቸው የሚባረሩ ሰዎችን እናያለን፡፡ ለምሳሌ የሚያውቁትን ወይም የገጠማቸውን ንቅዘት በማጋለጥ የለውጥ ፊታውራሪ በመሆናቸው የተባረሩ ሰዎችን እናያለን፡፡ ሕጉን ተከትለው በመሄድ አሸናፊ ቢሆኑም የሥራ ቅጥር ኮንታራታቸው ካበቃ በኋላ እንደገና ከመቀጠር የተገለሉባቸውን አጋጣሚዎች እናያለን፡፡ የዚያ ካምፓኒ ‹‹ባለቤትነት›› ስለሌላቸውና ‹‹ይህ ካምፓኒ የባለቤቱ ካምፓኒ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ስለ ራሴ ማሰብ አለብኝ›› ብለው በማሰብ የዚያ ካምፓኒ ሠራተኞች የሕብረት ሥራ በማቋቋማቸውና ካምፓኒውን እስከሚያፈርሱ ድረስም የሥራ ክርክሮችን በመፍጠራቸው ካምፓኒያቸው ከሥራ ውጪ በመሆኑ ሥራ አጥ የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ በእኛ አገር ያለው የሠራተኞች ሕብረት እንቅስቃሴ በተለየ ሁኔታ በደምብ የሚታወቀው በግጭት ነው፡፡ በኮርያ የንግድ ሥራ ለመሥራት ተስፋ የቆረጡና አገሪቱን ለቀው የወጡ ብዙ የውጪ አገር ካምፓኒዎች አሉ፡፡ ሁሉም በግጭት ፈጣሪ የሠራተኞች ማህበራት ምክንያት ካምፓኒዎቻቸውን በሰላም ማስተዳደር እንደማይችሉ ይናገራሉ፡፡ በእርግጥ ተቀጣሪ ሠራተኞቻቸው አንዳች ተገቢ ያልሆነ በደል ደርሶባቸው ከሆነ ለውጥን የመሻት መብት አላቸው፡፡ ዋናው ነገር ግን የካምፓኒው ሠራተኞች የባለቤትነት ስሜት ከሌላቸው የሚሠሩበትን ካምፓኒ እንደ ጠላት ወይ የግጭት ኢላማ አድርገው ስለሚያዩት ካምፓኒዎች ከንግድ ሥራው ከመውጣት በቀር አማራጭ የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡

    ይህንን ምሳሌ መመልከት እንችላለን፡፡ እያንዳንዱ ማህበራዊ ድርጅት እንደ ጀልባ፣ የዚህ ድርጅት አባሎችም የጀልባው ተሳፋሪዎች ሆነው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ያም ማለት እያንዳንዳቸው የተለየ ቦታና ሐላፊነት አላቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉ አንድ የጋራ የሆነ የሚደርሱበት ቦታ አላቸው፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ የቡድን አባል የራሱን ጥቅም ብቻ ቢፈልግና ሳይታወቅም በዚያች ጀልባ ውስጥ ሽንቁር ለመፍጠር ቢዝቱና በእርግጥም በጀልባዋ ላይ ሽንቁርን ቢፈጥሩ ምን ይከሰታል? ድንገት ውሃ ወደዚያች ጀልባ ውስጥ ይገባና ሁሉም ይሞታሉ፡፡ ይህ እንዴት ያለ ሞኝነት ነው? ነገር ግን የሚያሳዝነው ነገር እንዲህ ያሉ ነገሮች በተጨባጭ ብዙውን ጊዜ የሚከሰቱ መሆናቸው ነው፡፡

    ይህንን እንደ ምሳሌ እየነገርኋችሁ ያለሁት ምክንያት ስላለኝ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ የሚሽን ትምህርት ቤት ሥልጠናቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ አገልግሎት ጣቢያዎች ለሚሄዱ ወንድሞችና አሁን እየሠለጠኑ ላሉ ወንድሞችና እህቶች ልናገረው የምፈልገው አንዳች ነገር ስላለኝ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እያደረገች ያለችው እያንዳንዱ ነገር ሁላችሁንም ማርካት አይችልም፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ቤተክርስቲያን በምታደርጋቸው ነገሮች አለመርካት አንገብጋቢ ጉዳይ ሊሆንና ይህ አለመርካት በሚከመርበት ጊዜም በልባችሁ ውስጥ ቤተክርስቲያንን ትቶ የመውጣት ፍላጎት ሊያስነሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ በተጨባጭ የት እንደምንገኝ ማወቅ አለብን፡፡ ከመገኛችንም መውደቅ የለብንም፡፡ ትዕቢታችንን አጥብቀን በመያዝ ፋንታ ለምንገኝበት ስፍራ የሚጠነቀቅ ልብ ሊኖረን ይገባል፡፡ በዚህ መልኩ እንድታስቡ እፈልጋለሁ፡፡ በካምፓኒ ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ ብትሆኑም ባትሆኑም የባለቤትነት ስሜት የሌለው ግለሰብ በእርግጥም ዋጋ የለውም፡፡ ሰዎች ምንም ቢሉም እናንተና እኔ ያለንባት ይህች ቤተክርስቲያን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ነች፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የሚገኝባት ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ወንጌልንም የምትሰብክ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ በመላው አገሪቱ የተላካችሁባት ቤተክርስቲያን የትኛዋም ትሁን የምትሠሩባት ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያናችሁ ነች፡፡ ልትንከባከቡዋት የሚገባችሁ ቤተክርስቲያንም ይህች ነች፡፡ ሐላፊነታችሁን መወጣት ያለባችሁ ቤተክርስቲያንም ይህች ነች፡፡ እናንተ የተገኛችሁባት ቤተክርስቲያን አካላችሁ እንደሆነችም ማሰብ አለባችሁ፡፡

    በእግዚአብሄር ሆነን አብረን ስንኖር ሳለን አንዳችን በሌላችን ላይ ድክመቶችን፣ ንቅዘቶችንና በደሎችን ለማግኘት መሞከር የለብንም፡፡ በእርግጥ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች እንዲህ ያሉ ታላላቅ ንቅዘቶች የሉባቸውም፡፡ ነገር ግን ሰው ሌሎች ሰዎች በበደሎች የተሞሉ እንደሆኑና እርሱ እንደ እነርሱ እንዳልሆነ የሚያስብና ሁሌም ወቃሽ የሚሆን ከሆነ ይህ ግለሰብ ውሎ አድሮ ብቻውን ይቀርና ችግሮች በሚገጥሙት ጊዜም የሚደርስለት አይኖርም፡፡ ማንኛውንም ሌላ ሰው የማትቀበሉ ከሆነ እናንተንም የሚቀበላችሁ እንደማይኖር ማወቅ አለባችሁ፡፡ ይህንን የምነግራችሁ በቃሉ በትክክል ማደግ የምትችሉት አብራችሁ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስትቆዩ፣ የተባበረ እምነትና አንድ ልብ ሲኖራችሁና አንድ ቤተሰብ እንደሆናችሁም አንድ የባለቤትነት ስሜት ሲሰማችሁ ስለሆነ ነው፡፡

    እኛ የእግዚአብሄር አካል በሆነችው ቤተክርስቲያን ውስጥ አብረን ይህንን መንፈሳዊ ሕይወት ስንመራ አንዳችን በሌላችን ላይ አዎንታዊና አሉታዊ ነገሮችን እናገኛለን፡፡ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች መታገስ የማንችልና ሌላው ሰው የተሳሳተ እኛ ብቻ ግን ትክክል የሆንን እንደሆነ ድርቅ የምንል ከሆነ ችግሩ ሌላው ግለሰብ ሳይሆን እኛ እንደሆንን ግልጥ ነው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ይህንን መንፈሳዊ ሕይወት ስንመራ ሳለን የራሳችንን አሳቦች፣ መስፈርትና ልማዶች መተውና የእግዚአብሄርን ቃል መከተል አለብን፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ቃል አንድ አካል እንደሆንን ማወቅና ይህችም ‹‹የእኔ ቤተክርስቲያን›› መሆንዋን ማስታወስ አለብን፡፡ የሌሎች ቅዱሳኖችን በደሎች በማየት ፋንታ አዎንታዊና የሚደነቁ ነገሮቻቸውን የምናየው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በቅርቡ እንዲህ ያለውን የሚደነቅ እምነት ማየት፣ ሳናውቀውም እንኳን ከእርሱም መማርና በእርሱ ተጽዕኖ ሥር መሆንና ሳናውቃቸውም እንኳን በእነዚህ ተጽዕኖዎች ውስጥ መመሰጥ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ሰዎች እግዚአብሄር ባስቀመጣቸው ቦታዎች ላይ በትክክል ማደግና ጌታንም በታማኝነት ማገልገል አለባቸው፡፡ ስለዚህ የት እንደምንገኝ በሚገባ ማወቅ አለብን፡፡

    ስጋዊ ነገሮችን ሁሉ መተውና ከእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ጋር አንድ በመሆን መንፈሳዊ ሕይወትን መምራት አለብን፡፡

    እግዚአብሄር አብርሃምን እንዲህ ብሎ ተናገረው፡- ‹‹ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ›› እግዚአብሄር አብርሃምን ስጋዊ ነገሮቹን በሙሉ እንዲተው እየነገረው ነበር፡፡ እግዚአብሄር አብርሃምን አብሮዋቸው ሲኖር የነበሩትን እያንዳንዱን ነገርና እያንዳንዱን ሰው ማለትም ገና ዳግመኛ ያልተወለዱትን ስጋዊ ወላጆቹንና የቤተሰብ አባሎቹን እንደዚሁም አገሩን እንዲተው እየነገረው ነበር፡፡ አብርሃም የሚኖርበት አዲሱ የመቆያ ስፍራ የከነዓን ምድር ነበር፡፡ አብርሃም ይህንን አውቆ አመነና የየሆዋ እግዚአብሄርን ቃል ተከተለ፡፡ የወንድሙ ልጅ ሎጥም እንደዚሁ እርሱን ሊከተል ወሰነ፡፡ በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባ አምስት ዓመቱ ነበር፡፡

    አብርሃም ለምን ያህል ጊዜ ኖረ? በዘፍጥረት ምዕራፍ 25 ቁጥር 7-8 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ። አብርሃምም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካም ሽምግልናም ሞተ፤ ሸመገለም፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ፤ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።›› አብርሃም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፡፡ አብርሃም አገሩን ትቶ ከወጣ በኋላ ተጨማሪ 100 ዓመት ኖረ፡፡ በአብርሃም የመቶ ሰባ አምስት ዓመት ጠቅላላ የሕይወት ዘመን ውስጥ ሰባ አምስት ዓመት ልክ እንደ ጎረምሳ ነበር፡፡ በጉርምስናው ወቅት እንኳን በአገሩ ያለውን የአባቱን ቤት ትቶ መውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ለማንም ሰው በሆን ስጋዊ ወላጆቹን ትቶ መሄድ ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን አብርሃም በዚያ መንገድ ላይ የተጓዘው እግዚአብሄርን ብቻ ስላመነና ስለተከለተለ ነበር፡፡

    እኛ ሁላችን የሐጢያቶችን ስርየት ተቀብለናል፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት የተቀበለ እያንዳንዱ ሰውም የእርሱን ወይም የእርስዋን ስጋዊ ወላጆች ይተዋሉ፡፡ እኔም እንደዚሁ በዚህ መልኩ ቤቴንና ቤተሰቤን ትቻለሁ፡፡ እናንተም እንደዚሁ አብርሃም አገሩን ትቶ በመውጣቱ እውነታ ላይ በማተኮር ይህንን መንፈሳዊ ሕይወት መኖር አለባችሁ፡፡ አብርሃም በዚህ ተመሳሳይ መንገድ ቃሉን ከመከተሉና ቃሉንም ደግሞ ከመናፈቁ እውነታ ጋር ልቦቻችንን ማገናኘት አለብን፡፡ እምነትና አመኔታ ማለት ቃሉን መከተል ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ሰው ቃሉን የማይከተል ከሆነ እምነቱና አመኔታው ውሸት ነው፡፡ ሁላችሁም እግዚአብሄርን እንድትከተሉና በእምነት እንድትኖሩ እፈልጋለሁ፡፡ ይህንን መንፈሳዊ ሕይወት በተጨባጭ በታማኝነት ለመምራት የእግዚአብሄርን ቃል መከተል እንዳለባችሁ ማስታወስ አለባችሁ፡፡

    የአባታችሁን ቤት መተው እንዳለባችሁም ማስታወስ አለባችሁ፡፡ አሳቦቻችሁን መተው፣ ስጋዊ ነገሮቻሁን መተውና የቀድሞ ነገሮቻችሁን በሙሉ መተው አለባችሁ፡፡ እግዚአብሄርን ማመን፣ ቃሉን መከተልና ከቤተክርስቲያን ጋር አብራችሁ መሆን እንዳለባችሁ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ፡፡ እውነተኛ አመኔታና እምነት ያ ነው፡፡ እንድታምኑም እፈልጋለሁ፡፡

    Sermon0202

    የሚቃጠለው ቁርባን መሠውያ እምነት

    ‹‹ ዘፍጥረት 12፡1-9 ››

    ‹‹እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ። አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና። ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ። ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ። አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ።››

    ብሉይ ኪዳን ከአዳም ክፍለ ጊዜ እስከ ኖህ ክፍለ ጊዜና እስከ ሴም ክፍለ ጊዜ ድረስ ቀጠለ፡፡ ከሴም ክፍለ ጊዜ በኋላም የአብርሃም ክፍለ ጊዜ መጣ፡፡ የዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ አስራ ሁለት የአብርሃምን ክፍለ ጊዜ ያብራራል፡፡ በዚህም እግዚአብሄር ለሕዝቡ መሪዎችን ሾመና በመሪዎቹ አማካይነትም ፈቃዱን አሳየ፡፡ መሪው ሊሞት ሲቃረብም እግዚአብሄር ሌላ መሪ ሾመላቸው፡፡ የእርሱ ቀደምት እንዳደረገውም እርሱም በእምነት መራቸው፡፡

    የአብርሃም አባት ታራ ከሞተ በኋላ እግዚአብሄር አብርሃምን እንዲህ አለው፡- ‹‹ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ›› (ዘፍጥረት 12፡1) አብርሃምም የእግዚአብሄርን ቃል ተከተለና ወደ ከነዓን ተጓዘ፡፡ አብርሃም ቤተሰቡንና አገሩን ትቶ ሲወጣ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበር፡፡

    አብርሃም ለየሆዋ አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያን ሠራ፡፡

    እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፡- ‹‹አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገኙትን ከብት ሁሉና በካራን ያገኙአቸውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ወጣ፤ ወደ ከነዓንም ምድር ገቡ።›› ቅዱሳት መጻህፍት ያንን መዝግበዋል፡፡ እንደዚህም ደግሞ ተጽፎዋል፡- ‹‹አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና። ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው።››

    እግዚአብሄር አብርሃምና ቤተሰቡ ወደ ከነዓን በገቡ ጊዜ ተገለጠላቸው፡፡ በዚህ ምክንያት አብርሃም በዚያ ለተገለጠለት ለየሆዋ አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ሠራና የስግደት አገልግሎት አቀረበ፡፡ እርሱ በዚያ መሠውያ የሠራው ለምን ነበር? ይህ መሠውያስ ምን ዓይነት መሠውያ ነበር? ይህ መሠውያ የአብርሃም ቅድመ አያቶች አዳምና ሔዋን ከሠሩትና ለእግዚአብሄርም የሚቃጠል መሥዋዕት ካቀረቡበት የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ጋር ተመሳሳይ ዓይነት መሠውያ ነበር፡፡ ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ አቤል በጎችንና ፍየሎችን ባረደና ለእግዚአብሄር ባቀረበ ጊዜ ሲጠቀምበት የነበረው ያው ዓይነት ተመሳሳይ መሠውያ ነበር፡፡ ኖህ ከታላቁ የጥፋት ውሃ በኋላ ከመርከቡ ከወጣ በኋላ የሠራው ያው ዓይነት ተመሳሳይ መሠውያ ነበር፡፡ አብርሃም ይህንን መሠውያ የሠራው የአብርሃምን ክፍለ ጊዜ ለማንበር የውርስ እምነት ምልክት አድርጎ ነው፡፡

    ቃሉ አብርሃም ለየሆዋ አምላክ መሠውያን እንደሠራ ይነግረናል፡፡ የእርሱ ቅድመ አያቶችም ገና በሕይወት ሳሉ የዚህ ዓይነት መሠውያ ሠርተዋል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ምን ይመስላችኋል? የመሠውያው አገልግሎት በዚህ መልኩ ከመሞትና ፍርድን ከመቀበል በቀር ምንም ማድረግ የማይችሉትን ሰዎች ላዳናቸው አምላክ ምስጋናን ለመስጠትና ስግደትን ለማቅረብ ነበር፡፡ እነርሱ ይህንን ስግደት ለእግዚአብሄር ሲያቀርቡ፣ ክብርን ለእግዚአብሄር ሲመለሱ፣ የእግዚአብሄርን ስም ሲያስቡና አዳኛቸው የነበረውንም ይህንን አምላክ ሲያስታውሱ ነበር፡፡ ይህ መሥዋዕት ይመስላል፤ ዛሬ ግን ይህ ለእግዚአብሄር ከምናቀርበው የአምልኮ አገልግሎት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡

    አብርሃም እግዚአብሄር በተገለጠለት ጊዜ ሁሉ በዚህ መልኩ ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ሠራ፡፡ እኛም ደግሞ ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ለማቅረብ የመሥዋዕት ቁርባን ያስፈልገናል፡፡ አብርሃም ሐጢያቶቹን ወደ መሥዋዕቱ ቁርባን እያስተላለፈና ከዚያ በኋላም የመሥዋዕቱን እንስሳ እያረደ፣ እየበለተና በመሠውያው ላይ እያቃጠለ ይህንን በማድረግ የቅድመ አያቶቹና የእርሱም አምላክ በመሆኑ ለየሆዋ አምላክ የእምነትን ኑዛዜ እየተናዘዘ ነበር፡፡

    የእምነት ቅድመ አያቶች በሙሉ ይህንን የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ሠሩ፡፡

    እያንዳንዱ የእምነት ቅድመ አያት ይህንን መሠውያ ሠርቶ ለእግዚአብሄር የሚቃጠሉ ቁርባኖችን አቅርቦዋል፡፡ በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር ገና የመገናኛውን ድንኳን የመሥዋዕት ስርዓት ስላልሰጣቸው የተብራራ መሥዋዕቶችን የማቅረብ ሕግ አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን የሚቃጠለው ቁርባን መሥዋዕት በአዳምና በሔዋን ዘመን ቀድሞውኑም ተጠናቆ ነበር፡፡ መልካምንና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ እንዳይበሉ የተነገራቸውን የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ላልታዘዙት ለአዳምና ለሔዋን የሐጢያቶችን ስርየት ለመስጠት እግዚአብሄር ከእንስሳ የተሠራን ቁርበት አለበሳቸው፡፡ አዳምና ሔዋንም በዚያን ጊዜ ከተሠዋው እንስሳ የሚቃጠል ቁርባን አቀረቡ፡፡ አዳምና ሔዋን ልጆቻቸው ሲያድጉ ይህንን ታሪክ ነገሩዋቸው፡፡ አቤል ይህንን ሰማና ለእግዚአብሄር መሥዋዕትን ለማቅረብ ይህንን የሚቃጠል ቁርባን ማቅረብ እንዳለበት በሚገባ ተረዳ፡፡

    እርሱ ይህንን ያወቀው በአጋጣሚ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ይህንን ከወላጆቹ ተማረ፡፡ በሌላ በኩል ግን ይህንን መሥዋዕት ብዙ ጊዜ የሰማው ቃየን የመሥዋዕቱን ትርጉም ስላልተረዳ በራሱ አስተሳሰቦች መሠረት ለእግዚአብሄር የምድርን ፍሬ አቀረበ፡፡ እግዚአብሄር ግን አልተቀበለውም፡፡

    አዳም በዚህ የሚቃጠል ቁርባን አማካይነት ከእግዚአብሄር ጋር የማይታይ ሕብረት ነበረው፡፡ እነርሱ ይህንን መሥዋዕት ለምን የሚቃጠል ቁርባን አድርጎ ማቅረብ እንዳለበት፣ በእግዚአብሄርም ፊት ለምን የመሥዋዕት እንስሳ ማቅረብ እንዳስፈለገውና እግዚአብሄር ምን ያህል አዳምን እንደወደደው የግል ውይይት ነበራቸው፡፡ በዚህም በአዳምና በሔዋን የጀመረው የሚቃጠለው ቁርባን ለልጆቻቸውና ለእምነት ዝርያዎች ሁሉ መድረሱን ቀጠለ፡፡ የሚቃጠለውን ቁርባን ለኖህ ማን አስተማረው? ኖህ ከመርከብ ከወጣ በኋላ ያደረገው የመጀመሪያው ነገር ለሚቃጠል ቁርባን የሚሆን መሠውያ መሥራት ነበር፡፡ ለዚህ ምክንያቱ የእርሱ ቅድመ አያቶች እርሱን ማስተማራቸው ነበር፡፡ ኖህ ከመርከብ እንደወጣ ወዲያውኑ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠውያ ሠራ፡፡ ይህም እርሱ የሚቃጠለውን ቁርባን ምስጢር የተረዳው በቅድመ አያቶቹ አማካይነት እንደነበር በግልጥ ያሳየናል፡፡ ስለዚህ እርሱ ከመርከቡ ከወጣ በኋላ ያደረገው የመጀመሪያው ነገር ይህንን የሚቃጠል ቁርባን ማቅረብ እንደነበር እናያለን፡፡ ይህ ማለት ገና በመርከብ ውስጥ ሳለ ማድረግ ቢፈልግም እንኳን ማድረግ ያልቻለውን የመጀመሪያ ነገር ማድረግ ፈለገ ማለት ነው፡፡

    የእምነት ቅድመ አያቶች የሚቃጠል ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ እጆቻቸውን በመሥዋዕቱ እንስሳ ላይ ጭነዋል ወይስ አልጫኑም? ስለዚህ ጉዳይ አብረን ማሰብ ያስፈልገናል፡፡ በእርግጥ ቅዱሳት መጻህፍት እነርሱ በመሥዋዕቱ እንስሶች ላይ እጆቻቸውን ጭነው እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ በግልጥ አይናገሩም፡፡

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1