Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

መልካም ጄነራል
መልካም ጄነራል
መልካም ጄነራል
Ebook575 pages4 hours

መልካም ጄነራል

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

በምድር ላይ የሰው ሕይወት ሰልፍ እንደሆ ታውቃለህን¬? በጦርነት ውስጥ መሆን ብትፈልግም ባትፈልግም ያለንው በጦርነት ውስጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ ነው ይላል። መልካሙን ገድል እየታገልክ ጦርነቱን ማሸነፍ አለብህ። ይህ ስለውጊያ የሚያስተምረው አዲስ መጽሐፍ መሪዎች በሙሉ ሊያነቡት የሚገባ ነው።

Languageአማርኛ
Release dateAug 14, 2018
ISBN9781641348041
መልካም ጄነራል
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to መልካም ጄነራል

Related ebooks

Reviews for መልካም ጄነራል

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    መልካም ጄነራል - Dag Heward-Mills

    …በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።

    ራዕይ 3፡1-7፣12

    ርነት ብዙ ግድያ፣ ሰቆቃ፣ ሀዘን እና ሞት ያለበት ነው። ውጊያ በሰው ልጆች ላይ ሊደርሱ ከሚችሉ እጅግ አስከፊ ነገሮች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም ውጊያ በአብዛኛው ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ አይጠቀስም። እግዚአብሔር በምን ምክንያት ውጊያ ውስጥ ሊሳተፍ ይችላል? እግዚአብሔር እንዴት ሰዎች እንዲሞቱ ይፈልጋል? እግዚአብሔር ሰዎችን መግደል ይፈልጋልን? እግዚአብሔር ሰዎችን መጉዳት ይፈልጋልን? በፍፁም!

    እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነት ክፉ እቅዶች የሉትም። ጦርነትን እንዲነሳ ምክንያት የሚሆነው መወገድ የሚገባው የጠላት መነሳት ነው። እግዚአብሔር በጽድቅ መንገድ ውጊያን አውጆ ጠላቶቹን ይደመስሳል። እኛ ክርስቲያኖች ልንደመስሰውና ልናስወግደው የሚገባ ጠላት አለን። እንደ ወንጌል አገልጋዮች ደግሞ እጅግ የበዙ ጠላቶች ስላሉን እንዴት እንደምናሸንፋቸው፣ እንደምንደመስሳቸውና ፈጽመን እንደምናጠፋቸው ማወቅ አለብን። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም። ውጊያን ለመዋጋት ጥሩ ዓይነት መንገድ አለ። ውጊያን ለማወጅ ጥበብ የተሞላ መንገድ አለ። እግዚአበሔር በእርሱ መንገድና ጥበብ ውጊያን እንድታውጅ ይፈልጋል።

        ይህ መጽሐፍ በእግዚአብሔራዊ፣ በመንፈሳዊና በጥበብ የተሞላ መንገድ እንዴት ውጊያ እንደሚታወጅ ያብራራል። በውጊያ ውስጥ አይደለንም ብሎ የሚያስብ ማንም ሰው ጥበብ ይጎድለዋል። ሰይጣን በሰላም ንጉሥ ሥር ሆነን በሰላም እየኖርን እንዳለን እንድታስብ ይፈልጋል። ሰይጣን ምንም የሚያስጨንቅ ነገር እንደሌለ እንድታስብ ይፈልጋል። የእግዚአብሔር ቃል ግን ውጊያ ላይ እንዳለን በግልጽ ይናገራል። የእግዚአብሔር ቃል መልካምን ውጊያ እንደምንዋጋ ደግሞም መልካምን ገድል እንደምንጋደል በግልጽ ያስረዳል! 

    ስለውጊያ ልንማር የሚገባባቸው አስር ምክንያቶች

    1. ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ ሠራዊትን ይመራል ደግሞም በጽድቅ ይዋጋል።

    ብዙ ሰዎች መዋጋት ስለማይፈልጉ በአገልግሎት ውስጥ ምንም አይሰሩም። ኢየሱስን መከተል ከፈለግህ የእርሱን ጦር ተቀላቅለህ መዋጋት አለብህ።

    ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።

    ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤

    በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።

    በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

    አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።

    የዮሐንስ ራእይ 19፡11-15

    2. ኢየሱስ ክርስቶስ የሚዋጋ በግ ነው

    በጉ በእርሱ ላይ በተነሱት አሥር ነገሥታት ላይ ውጊያን አድርጓል። ኢየሱስ ክርስቶስ ውጊያን የሚያደርግ በግ ነው። እንደ ኢየሱስ መሆን አትፈልግምን? እንደ ኢየሱስ መሆን የምትፈልግ ከሆነ በጦርነት ውስጥ ውጊይን መማር አለብህ! 

    ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።

    እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።

    እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።

    የዮሐንስ ራእይ 17፡12-14

    3. እግዚአብሔር ለእጆቻችን ውጊያን ያስተምራል

    እግዚአብሔር አንድን ጦርነት እንዴት እንደምትዋጋ ሊያስተምርህ ይፈልጋል። የምታምን ከሆነ መለኮታዊ ልዕለ-ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ያስችልሃል ደግሞም እንዴት እንደምትዋጋ ምሪትን ማግኘት ትችላለህ።

    እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።

    መዝሙረ ዳዊት 18፡34

    4. መልምን ገድል እንድንጋደል ታዝዘናል

    መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መጋደል እንዳለብህ የሚናገር ግልጽ ቃል አለ። እግዚአብሔር እንድትጋደል ግድ ይልሃል! መልካም ገድል መልካምነቱ አንተ ስለምታሸንፍ ነው። ምልካም ገድል መልካም ዓላማ ያለው ገድል ነው።

    መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።

    1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

    5. መልካምን ውጊያ እድንዋጋ ታዝዘናል

    እንደውም በውጊያ ብርቱ እንድንሆን ተነግሮናል። ለእያንዳንዱ የወንጌል አገልጋይ የተሰጠ መመሪያ ነው። በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጢሞቴዎስ ከቀዳሚ መጋቢዎች አንዱ ነው። እርሱም በውጊያ ብርቱ እንዲሆን ተነግሮታል።

    ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ውጊያ ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤

    1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

    6. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት በውጊያ ተመስሎአል።

    ሐዋርያው ጳውሎስ አገልግሎቱን እንደ ገድል ቆጥሮ አንድ አስፈላጊ ጥያቄ ጠይቋል። ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው?

    ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?

    1ኛ ቆሮንቶስ 9፡7

    7. ጳውሎስ ሕይወቱንና አገልግሎቱን በገድል መስሎአል።

    ጳውሎስ ያለማቋረጥ ይዋጋ ነበር። በአገልግሎት ውስጥ ካለህ እየተዋጋህ ነው! ለእግዚአብሔር የምትሰራ ከሆነ ጦረኛ ነህ! ወደድክም ጠላህም ለሕይወትህ እየተዋጋህ ነው። እኔ ሁልጊዜ ለህይወቴ እየተዋጋሁ እንዳለሁ ይሰማኛል።

    ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤

    1ኛ ቆሮንቶስ 9፡26

    ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤

    2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡7

    8. የጦር ዕቃ እንዲኖረን ታዝዘናል።

    የእግዚአብሔር አገልጋይ ጳውሎስ መልካም ገድሉን የሚጋደልባቸው የጦር መሣሪያዎች ነበሩት። ጳውሎስ መሣሪያዎች ካስፈለጉት አንተም ያስፈልጉሃል።

    በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤

    የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤

    2ኛ ቆሮንቶስ 10፡3-4

    9. ብርቱዎች እንድንሆንና ራሳችንን እንድናስታጥቅ ታዝዘናል።

    የማንዋጋ ከሆነ መታጠቅ ለምን ያስፈልገናል? ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር እየተዋጋን ነው ያለነው። ወገብህን ታጥቀህ መልካም፣ ረጅም እና አስቸጋሪ ለሆነ ትግል ተዘጋጅ!

    በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።

    ኤፌሶን 6፡10-12

    10. ከዘንዶው ጋር ውጊያ አለ እኛም ጦርነቱ ውስጥ አለን።

    ዘንዶው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ ሰዎችን ይዋጋል። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ትጠብቃለህ? ከሆነ ዘንዶው ሊዋጋህ በአንተ ላይ እንደሚነሳ ጠብቅ።

    ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤

    የዮሐንስ ራእይ 12፡17

    ምዕራፍ 2

    መልካም ጄነራል የሞኝ ትግልን ይርቃል

    መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥…

    1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

    ልካም የጦር አዛዥ የሰለጠነ ጦረኛ ቢሆንም የማይረባ ገድል አይጋደልም። መጽሐፍ ቅዱስ መልካሙን ገድል እንድንጋደል ያስተምረናል። መልሙን የእምነት ገድል መጋደል መልካም ነው። መጋደል ማለት ለአንድ ነገር ጽኑ ጥረት ማድረግ ነው። ሆኖም ግን አንድ ሰው ሊሳተፍባቸው የሚችሉ ብዙ ተራ ገድሎች አሉ። የምትፈልገው ተራ ተጋድሎን ነው ወይስ መልካምን ገድል?

    ጄነራል ፓውሉስ እና ተራው ገድል

    በ1942 (እ.አ.አ.) የጀርመን መሪ የነበረው አዶልፍ ሂትለር ሶቪየት ዩንየንን ለሁለተኛ ጊዜ ወሮ ስታሊንገራድ የተባለች ወሳኝ ከተማን ለመቆጣጠር ሞከረ። አዶልፍ ሂትለርና ስታሊን (የሩሲያው መሪ) ሁለቱም ብርቱ ኮማንደሮች ነበሩና በስታሊንግራድ አቻቸውን የገጠሙ ይመስል ነበር። የጀርመን ሠራዊት በጄነራል ፓውሉስ አመራር ሥር ነበሩ።

    ስታሊን ለወታደሮቹ አንዲትም እርምጃ ወደኋላ እንዳትሉ! የሚል ትእዛዝ አዝዞ ነበር፤ ሁሉም እስከሞት ድረስ እንዲታገል። ይህም ትእዛዝ ከበላዮቹ ፈቃድ ውጪ ማፈግፈግን የፈቀደ ማንኛውም ኮማንደር የጦር ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የሚያዝ ነበር። ትእዛዙ ወንጀለኛ ሆነው የተገኙ ወታደሮች በ ቅጣት ባታልዮን እንዲሰለፉ ያዝ ነበር። ይህም እጅግ አደገኛ ወደሆኑት የጦር ግንባር ክፍሎች ይላኩ ነበር ማለት ነው። ትእዛዙን ፈርተው የሚሸሹ የተሸበሩ ወታደሮችን ከኋላቸው እንዲተኩሱባቸው ተጨማሪ ትእዛዝ ነበር። ትእዛዙን ተከትሎ ባሉት የመጀመሪያ ሁለት ወራት ከ 1,000 በላይ ወታደሮች በአጋጅ ግብረ ኃይሎች ተኩስ ተገድለው ነበር፤ እንዲሁም ከ 130,000 በላይ ወታደሮች ወደ ቅጣት ግንባሮች ተላኩ።

    ነገር ግን ሂትለርም ወታደሮቹን በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳያፈገፍጉ ከልክሏቸው ነበር። በዚህ ምክንያት ከተማዋ ጨርሳ እክትወድም ድረስ ጦርነቱ በየጎዳናውና በየቅያሱ ቀጠለ። ጀርመኖቹ አንዳንድ ጊዜ እስከ 1,000 የሚደርሱ አውሮፕላኖችን ያካተቱ የአየር ጥቃቶች ያካሂዱ ነበር። የሁለቱም ወገን ጦር በፈራረሱ ህንጻዎች ውስጥ ተደብቀው የሩስያና የጀርመን አድፍጦ ተኳሾች የጠላት ወታደሮችን አልመው ለመምታት በፍርስራሾች ውስጥ ተደብቀው ነበር።

    ጃንዋሪ 24 ላይ ጄነራል ፓውለስ እጅ ለመስጠት ፈቃድ ጠየቀ። ለአዶልፍ ሂትለር ወታደሮች ጥይትና ምግብ የላቸውም። ከእንግዲህ ጦሩን በአግባቡ መምራት አይቻልም። 18,000 ቆስለዋል እንዲሁም ምንም ዓይነት አቅራቦት ወይም የህክምና ቁሳቁስና መድኃኒት የለም። ከእንግዲህ መከላከሉ ትርጉም የለውም። ውድቀት የማይቀር ነው። የተቀሩትን ወታደሮች ሕይወት ለማትረፍ ሲባል ጦሩ እጅ እንዲሰጥ አስቸኳይ ፍቃድ ይጠይቃል።

    ሂትለር እስከመጨረሻው ሰው ድረስ ጸንተው እንዲቆሙ በማለት ለጀርመን ወታደሮች ፍቃድ መስጠትን አሻፈረኝ አለ። በመሠረቱ አዶልፍ ሂትለር ለጄነራል ፓውሉስ እጅ እንዳይሰጥ ፈቃድ መከልከሉ የሞኝ ውጊያን እንዲዋጋ እንደማዘዝ ነበር።

    ጄነራል ፓውለስ ግን ይህንን አልተቀበለውም። ሂትለር ፊልድ ማርሻል አድርጎ ቢሾመውም በዚህ ሞኝነት አልቀጥልም አለ። በ ጃንዋሪ 31 1943 ጄነራል ፓውሉስ የአዶልፍ ሂትለርን የሞጅ ውጊያ የመዋጋት ትእዛዝ ጥሶ እጅ ሰጠ። የሩሲያ እግረኛ ጦር ከአንድ ከፈራረሰ የገበያ ማዕከል ምድር ቤት ውስጥ ካለው የጀርመን ዋና የጦር መምሪያ ሲቃረብ ፊልድ ማርሻል ፓውሉስና የተረፉ የጦር መኮንኖቹ በቀላሉ ወጥተው በጸጥታ እጅ ሰጡ። የሂትለርን የመጨረሻው ሰው እስኪቀር የሞኝ ውጊያ የመዋጋት ትእዛዝ ፈጽመው ችላ አሉ።

    በዚህም ምክንያት የስታሊንግራድ ውጊያ ጄነራል ፓውሉስ ትርጉም የለሽ የሆነን የሞኝ ውጊያ መዋጋት እምቢ በማለቱ አበቃ። ከስታሊንግራድ ሽንፈት በኋላ የተመረረው ጄነራል ፓውሉስ በሂትለር ላይ ተነሳ። ከሩሲያዎቹ ጋር በመተባበር የጀርመን ነጻ አውጪ ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም የጀርመን ወታደሮች ለሂትለር መዋጋት እንዲያቆሙ ከሞስኮ የራዲዮ ስርጭት ቅስቀሳ አደረገ።

    የእኔ የሞኝ ጥል

    ከአመታት በፊት በትምህርት ቤት ሳለሁ አንድ ያስቸግረኝ ከነበረ ተማሪ ጋር ጥል ውስጥ ገባሁ። ከድብድቡ በኋላ ሁለት ነገሮች ሆኑ። አንደኛ በድብድቡ ያሸነፍኩ ወይም ከባለጋራዬ ጋር አቻ የወጣሁ መስሎኝ ነበር። በዙሪያዬ ያለ ሰው ሁሉ ግን እየሳቀ እንደተሸነፍኩ ነገረኝ።

    ሁለተኛ ደግሞ ለዚህ ሁሉ ጥረቴ ያተረፍኩት የበለዘ ዓይን ነበር። ዓይኔ ዙሪያ ያለው አካባቢ እንዳለ ለሳምንት ያህል ጠቁሮ ቀረ። ከጥሉ በኋላ ከማይረቡ ሰዎችና የጡጫና የድብድብ ችሎታዬን ከማያደንቁ የማይጠቅሙ ተመልካቾች ጋር እንዲህ አይነት የማይረቡ ጥሎች ውስጥ መግባት እንደሌለብኝ ደመደምኩ!

    ከዚያ ወዲህ ጠቃሚ የሆኑ መልካም ትግሎችን ብቻ ለመታገል ወሰንኩ። ለመልካም ዓላማ እና መልካም ውጤት ለሚያስገኙ ነገሮች ብቻ ነው የምታገለው። ዛሬ በፖለቲካ ትግል ወይም የገንዘብ ትግል ውስጥ እንኳን የማልገባው ለዚህ ነው ። ከብዙ አመታት በፊት በትምህርት ቤት ሳለሁ የሞኝ ትግሎችን መራቅ ተምሬአለሁ። ዛሬ ልታገልላቸው የሚገቡ በርካታ መልካም ዓላማዎችን አግኝቻለሁ። እነዚህ ነገሮች ተጋድሎውና ልፋቱ ሁሉ የሚገባቸው ናቸው። ለመልካም ነገር ወይም ለማይረባ ነገር ልትታገል ትችላለህ። ብዙ ሰዎች የማይጠቅሙ ትግሎች ውስጥ ይገኛሉ።

    ምዕራፍ 3

    መልካም ጄነራል መልካምን ገድል ይጋደላል

    መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥

    1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡12

    ልካም ገድሎችን የምትጋደልበት ጊዜ ሲደርስ ወደኋላ እንዳታፈገፍግ መልካም ገድሎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ልትዘጋጅባቸው የሚገቡ ገድሎች ናቸው። ክርስቲያን ስለሆንክ ለመታገል ራስህን አዘጋጅ። የወንጌል አገልጋይ ስለሆንክ ደግሞ ከዚያም በበለጠ ለመታገል ራስህን አዘጋጅ። 

    አሥራ ስምንት ወሳኝ ትግሎች

    1. ጠንካራ ክርስቲያን ለመሆን ታገል።

     ብዙ ክርስቲያኖች በጌታ ብርቱ አይደሉም። ጠንካራ አማኝ ለመሆን ትልቅ ጥረት ይጠይቃል።

     በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።

    ኤፌሶን 6፡10

    2. በመንፈስ ቅዱስ ለመመራትና በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ለመሆን ታገል።

    ተጽእኖ ሊያደርጉብን የሚጥሩ የተለያዩ ድምጾችን ለይቶ ማወቅ ትግል ነው። የሥጋን ድምጽ ከአዕምሮ ድምጽና ከመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ለይቶ ማወቅ ገድል ነው። ከመኖሪያ ከቦታዎች ሁሉ እጅግ አስፈላጊው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መኖር ነው። ብዙ ድምጾች ያተን ትኩረት ለማግኘት ይጥራሉ። ብዙ አጋንንት ከመንገድህ ሊያስቱህ ይታገላሉ። በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ መሆን የእውነት ትግል ነው። አንዳንድ ጊዜ የባለቤትህ ድምጽ ወይም የሥጋህ ድምጽ እጅግ ከማየሉ የተነሳ ልትገስጸው ትገደዳለህ። በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ለመሆን ብለህ ከቅርብ ጓደኛህ ጋር ለመታገል ዝግጁ ነህ?

    በዓለም ምናልባት ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል ቋንቋም የሌለው ሕዝብ የለም፤

    1ኛ ቆሮንቶስ 14፡10

    3. መንፈሳዊ እንጂ ሥጋዊ ላለመሆን ታገል። መንፈሳዊ ሰው መሆን ትግል ነው።

    የሥጋን ዝንባሌዎች መከተል የበለጠ ተፈጥሮአዊ ነው። መብላት፣ መተኛት፣ ማረፍ፣ እንዲሁም ወሲብ መፈጸም እነዚህ ነገሮች የማንቃወማቸው ነገር ግን በቀላሉ የምናደርጋቸው ነው። በሕይወትህ ሁሉ መንፈሳዊ ሰው ለመሆን ትታገላለህ። የጸሎት ሰው መሆንም ትልቅ ትግል ነው፤ በሌሊት ተነስቶ እግዚአብሔርን መጠባበቅ በቀላሉ የሚደረግ አይደለም። ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመግባት የእግዚአብሔርን ጸጋና የእግዚአብሔርን ኃይል ይጠይቃል።

    ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

    ሮሜ 8፡6

    4. ለመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ታገል። በፍቅር ለመመላለስ ታገል።

    የፍቅር፣ የደስታ እና የሰላም ፍሬዎችን ማፍራት ከባድ ጥረት ይጠይቃል። መናደድ፣ መራርነትና መበሳጨት የበለጠ ተፈጥሮአዊ ነው። የፍቅር፣ የደስታ እና የሰላም ፍሬዎችን ለማፍራት የገዛ ተፈጥሮህን መታገል ይኖርብሃል።

    የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።

    ገላትያ 5፡22-23

    5. ወደ አገልግሎት ለመግባት ታገል።

    ከታላላቅ ትግሎች አንዱ ወደ አገልግሎት ለመግባት ያለ ትግል ነው። ከታላላቅ ጦርነቶችህ መካከል አንዱ የሚሆነው ይህ ነው። ጥሩ ምድራዊ ሙያን ለክህነት ሥራ ብሎ መተው እጅግ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ነገር ነው። እግዚአብሔርን ለመከተልና መልካምን ገድል ለመጋደል የምትፈልግ ከሆነ እንግዲያውስ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ውስጥ ለመግባት ያለውን ገድል ተጋደል።

    ሌላውንም። ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው።

    ሉቃስ 9፡59-60

    6. በጥሪህ ውስጥ ለመቆየት ታገል።

    አንዴ አገልግሎት ውስጥ ከገባህ በኋላ በአገልግሎት ውስጥ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ መቆየት ጥረት የሚጠይቅ ነው። አንዳንድ ወጣት ሚስዮናውያን በሚያገለግሉበት የተልዕኮ ቦታ ራሳቸውን ለመደገፍ ሲሉ ሥራ ይዘው ተራ መጋብያን ሆነዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥም ልባቸው ከትክክለኛ አገልግሎት ወደ ምድራዊ ሥራ ዞሯል። በአገልግሎት ውስጥ ስትሆን ከትክክለኛ ጥሪህ ዘወር ብሎ መንሸራተት ቀላል ነው። እግዚአብሔር አገልግሎትህን ሲባርክና ትልቅ ቤተክርስቲያን ሲኖርህ ትርጉም የሌለው ነገር ሰባኪ መሆን ቀላል ነው። ትልቅ ቤተክርስቲያን ሲኖርህ መሠረታዊ የሆኑ የእግዚአብሔር ቃል እውነቶችን ለመስበክ እስከማያስፈልግ እጅግ መሰረታዊ አድርገህ ልትቆጥር ትችላለህ። አነቃቂ ንግግር ተናጋሪ ብቻ ከመሆን ለመዳን መልካም ገድል መጋደል ይኖርብሃል።

    ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፤

    2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡10

    7. ከታላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ለመጎዳኘት ታገል።

    የእግዚአብሔር ሰዎችን መቅረብ ቀላል አይደለም። ብዙ ሰዎችን ለመቅረብ ብሞክርም ሁልጊዜ ግን አይሳካልኝም።  የተቀቡ ሰዎችን ለመቅረብ የአመታት ትግል፣ መዛመድ፣ መስማማትና ጭምት መሆን ይጠይቃል። ብዙ ሰዎች ለዚህ ትግል ዝግጁ አይደሉም። ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሰዎችን ለመጎዳኘት መታገል፣ ያንን የቅርብ ግንኙነት ለመጠበቅም መታገል እንደሚያስፈልግ ሲገነዘቡ ሙከራቸውን ያቆማሉ። መጎዳኘት ቀላል አይደለም፡ ኤልሳዕ ኤልያስን ለመቅረብ መታገል ነበረበት። ያንንም ትግል አሸንፏል። ለቅባቱ ስትል ለመታገል ዝግጁ ነህ?

    እንዲህም ሆነ እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ሊያወጣው በወደደ ጊዜ ኤልያስ ከኤልሳዕ ጋር ከጌልገላ ተነሣ።

    2ኛ ነገሥት 2፡1

    ኤልያስም ኤልሳዕን፦ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ልኮኛልና በዚህ ቆይ አለው። ኤልሳዕም። ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ አልለይህም አለ። ወደ ቤቴልም ወረዱ።

    2ኛ ነገሥት 2፡2

    ኤልያስም። ኤልሳዕ ሆይ፥ እግዚአብሔር ወደ ኢያሪኮ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ አለው። እርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ አልለይህም አለ።

    2ኛ ነገሥት 2፡4

    ኤልያስም። እግዚአብሔር ወደ ዮርዳኖስ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ አለው። እርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ አልለይህም አለ። ሁለቱም ሄዱ።

    2ኛ ነገሥት 2፡6

    8. ቅባቱን ለመያዝ ታገል።

    ቅባቱን ለመያዝ ትግል ይጠይቃል። ለዚህ ነው ኤልያስ ለኤልሳዕ አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል ያለው። ቅባቱን ለመያዝና የተቀባ ለመሆን በእውነትም አስቸጋሪ ነገር ነው። ለመታገል ዝግጁ ካልሆንክ ቅባቱን ልታገኝ አትችልም። ለቅባቱ ሲሉ ለመታገል ዝግጁ የሆኑ ናቸው ሊቀቡ የሚገባቸው!

    ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፦ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን አለው ኤልሳዕም። መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ አለ።

    እርሱም፦ አስቸጋሪ ነገር ለምነሃል ነገር ግን ከአንተ ዘንድ በተወሰድሁ ጊዜ ብታየኝ ይሆንልሃል አለዚያ ግን አይሆንልህም አለ።

    2ኛ ነገሥት 2፡9-10

    9. ለሕይወትህ ጥሩ አጋር ለማግኘት ታገል።

    የትዳር አጋር ማግኘት ትግል ይጠይቃል። ሩት የቦዔዝን ትኩረት ለማግኘት ከባድ ትግል አድርጋለች። በጋብቻ ውስጥ ለመቆየትም መታገል ያስፈልጋል። ብዙ እንሰሳት አንድ አጋር የላቸውም። እንሰሳዊ ባህርያችን ከአንድ በላይ ወደሆኑ አጋሮች እንድናዘነብል ያደርገናል። ራስህን በርካታ አጋሮች ያሉት ሰው ከመሆን ለማራቅ መታገል ያስፈልግሃል።

    ወደ አውድማውም ወረደች፥ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች። ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ ሰውነቱንም ደስ ካሰኘ በኋላ፥ በእህሉ ክምር አጠገብ ሊተኛ ሄደ ሩትም በቀስታ መጣች፥ እግሩንም ገልጣ ተኛች።

    ሩት 3፡6-7

    10. ለመበልጸግ ታገል። ብልጽግና በቀላሉ አይመጣም።

    ለመበልጸግ መታገል ያስፈልግሃል። ብልጥግና የሚደበቀው በሚስጥራዊ ቦታዎች ነው። ሃብቶች የሚደበቁት በጭለማ ሥፍራ ነው። ያለትግል በዓለም ሁሉ የሞሉትን እነዚህ ሃብቶች ልታገኝ አትችልም። ዘና፣ ዝግ ያሉ እና ሰነፍ ሰዎች በቀላሉ ሃብታም አይሆኑም። ምክንያቱም ምድር ፍሬዋን እንድትሰጥ ብርቱ ትግል ስለሚያስፈልግ ነው። ትምህርት ለመማር መታገል አለብህ። ፈተና ለማለፍ መታገል አለብህ። ጥሩ ሥራ ለማግኘት መታገል አለብህ። የሥራ እድገት ለማግኘትም መታገል አለብህ። ደግሞም ገንዘብህን በአግባቡ ለመጠቀም መታገል አለብህ።

    ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።

    ማርቆስ 4፡25

    11. ቤት ለመሥራት ታገል። ቤት ለመሥራት መታገል አለብህ።

    ብዙ ሰዎች የራሳቸው ቤት የላቸውም ደግሞም መቼም አይኖራቸውም። የቤት ባለቤት መሆን ትግል ቢሆንም የቤት ባለቤት ለመሆን መታገል ግን ተገቢ ነው።

    ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በማስተዋልም ይጸናል።

    ምሳሌ 24፡3

    12. ረጅም ዕድሜ እንድትኖርና ጌታን ለብዙ ጊዜ ለማገልገል ታገል።

    ጥሩ ጤንነት እንዲኖርህ፣ በህይወት ለመቆየትና ጌታን ለብዙ ዓመታት ለማገልገል ትግል ያስፈልጋል።

    እርሱም፦ ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት።

    1ኛ ነገሥት 12፡7

    13. የተፈጥሮአዊ ባሕርያቶችህን አሉታዊ ጎኖችን ተዋጋ።

    የዝግተኛ ባሕርይህ (ፍላግማቲክ)፣ የግልፍተኛ ባሕርይህ (ኮለሪክ)፣ የተስተካከለ ባሕርይህ (ሜላኮኒክ)፣ እንዲሁም የደስተኛ ባሕርይህ (ሳንጉይን) ሁሉ አሉታዊ ገጽታዎች አላቸው።

    የዝግተኛ ባሕርይህ ዝግ ማለትና መፍዘዝ በአገልግሎት ውስጥ የትኛውንም ነገር የማከናወን ችሎታህን ይዋጋዋል። የባህርይህ ዝግ ማለትና መፍዘዝ ለመንቀሳቀስ ወይም ለመታገል እንዳትፈልግ ያደርግሃል። ይህም ወደ ድህነት ይመራል።

    የደስተኛ ባህርይህ ነጻነት ደግሞ ወደ መዝረክረክ፣ ግራ መጋባትና የሥጋ ኃጢአት ይመራሃል።

    የተስተካከለ ባህርይ መዋዠቅና መዝቀጥ ደግሞ ግንኙነቶችን ያጠፋል፤ ድባቡንም ያደምነዋል። ሀዘኑ በሰው እንድትፈርድና ጥቂት ሥህተት ሲሰሩ ሰዎችን እንድታርቅ ያደርግሃል።

    ግልፍተኛ ባሕርይ ያለው ሰው ጭካኔ፣ ቆራጥነትና ቀጥተኛነት ደግሞ ግንኙነቶችን ያጠፋል። የግልፍተኛ ሰው ፈጣን ውሳኔዎች ወደ አመጽ ሊመሩት ይችላሉ። የግልፍተኛ ሰው በሥራ መጠመድና እንቅስቃሴ እግዚአብሔርን ከመጠባበቅ ያግደዋል።

    በተፈጥሮ አዘውትረህ የምታደርገውን ነገር ላለማድረግ መወሰን ትግልን ይጠይቃል! ይህ ለብዙ ሰዎች ከምንም በላይ እጅግ ከባድ ነገር ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡- ራስን ለመካድ ያለ ትግል ነው። የውርስ የሆነውን ሰዋዊ ተፈጥሮህን ለመተው መልካም ገድልን ተጋደል።

    ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

    ማርቆስ 8፡34

    14. ከወንድነትህ ወይም ሴትነትህ ጋር ታገል።

    አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።

    ገላትያ 3፡28

    ወንድ ከሆንክ በአንድ አጋር ተወስኖ መቆየት ያስቸግርሃል። ነገር ግን ይህንን የወንድ ዝንባሌ በመታገል እንዴት ከአንድ ሰው ጋር እንደምትቆይ ማወቅ ይኖርብሃል። ለወንድ ታማኝ መሆን ትግል ነው። ነገር ግን ይህን ትግል በድል መወጣት ግድ ነው! የአንድ ሰው ወንድነት የሚገለጥበት ሌላኛው መንገድ የወሲብ ፍላጎት ነው። ይህ የጨመረ የወሲብ ፍላጎት ወሲባዊ ጽሑፎችንና ምስሎችን ወደማየት፣ ራስን በራስ ማርካት፣ መዳራትና ዝሙት ሊወስድህ ይችላል። ራስህን ለመካድ ካልታገልክ በአገልግሎት ውስጥ ከባድ ችግር ውስጥ ትገባለህ።

    ሴቶችም እንዲሁ ራሳቸውን በፍርሃት፣ በቅናትና በወቀሳዎች ተሞልተው ያገኙታል። አገልግሎትሽን እንዳይሰርዝብሽ ሴትነትሽን ማስገዛት አለብሽ። ወንድም ሆንክ ሴት ወንድነትህን ወይም ሴትነትሽን እስከ መጨረሻው መቆጣጠር አስፈላጊ ነው።

    15. የጎሳ ወይም ብሔራዊ የተወሰኑ ባህሪያትን ታገል።

    የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ። የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው ብሎአል። ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።

    ቲቶ 1፡12-13

    ማንኛውም ጎሳ፣ ቤተሰብ ወይም ሀገር የራሱ የሆኑ ዝንባሌዎች አሉት። ጋና ውስጥ አሻንቲዎች በአንዳንድ ነገሮች በደንብ የሚታወቁ ሲሆን ኤዌዎች ደግሞ እንደዚሁ በሌሎች ነገሮች ይታወቃሉ። ወደ አገልግሎት ስትገባ በአቀራረብህ በጣም ኤዌ ወይም በጣም አሻንቲ እንዳትሆን መታገል አለብህ። አንደኛውን ወይም ሌላኛውን ሆነህ ከታየህ በሌላኛው ጎን ፍሬ የማፍራት ችሎታህ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። አንዳንድ መጋቢያን ሀገራቸውን እጅግ ከመውደዳቸው ተነሳ ከሀገራቸው ውጪ መድረስ አይችሉም። ብዙ አሜሪካውያን እጅግ አሜሪካውያን ከመሆናቸው የተነሳ በአሜሪካ ብቻ ተወስነው የተቀረውን ዓለም ማገልገል አልቻሉም። ሰሜን አሜሪካ ከዓለም አምስት እጅ ያህሉ ብቻ የሚገኝባት ሲሆን አብዛኞቹ አሜሪካዊ የወንጌል አገልጋዮች አሁን የዓለምን አምስት እጅ ብቻ በማገልገል ተወስነዋል። የሚገርመው ታዲያ ይህ አምስት እጅ ከወንጌል አገልጋዮች ዘጠና እጁ ያሉበት መሆኑ ነው።

    ናይጄሪያውያን በርካታ ታላላቅ ቤተክርስቲያኖችን ወልደዋል። ናይጄሪያውያን እንደዚሁ በአንዳንድ ነገሮች ይታወቃሉ። ናይጄሪያዊ አገልጋይ ከሆንክ ራስህን ከማናቸውም አሉታዊ የተወሰኑ ባህርያት ለማራቅ መጣር አለብህ። ከምንም ነገር በላይ በይበልጥ ክርስቲያን ለመሆን መጣር ተገቢ ትግል ነው።

    የፈረንሳይኛ ተናጋሪ ሃገራት በአንዳንድ ድርጊቶች ይታወቃሉ። ራስህን ከማንኛውም አሉታዊ የተወሰኑ ባህሪያት ማራቅ አስፈላጊ ነው። ከፈረንሳይኛ ተናጋሪ ይልቅ የበለጠ ክርስቲያን መሆን አለብህ።

    16. በቀለም የተወሰኑ ባህርያትን ታገል።

    እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን። እግዚአብሔርም ያፌትን ያስፋ፥ በሴምም ድንኳን ይደር ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።

    ዘፍጥረት 9፡25-27

    ጥቁር ሰዎች በኋላቀርነት፣ በድህነት፣ በጉስቁልና፣ ቁሻሻ፣ ግራ መጋባት፣ መዝረክረክና ለመበልጸግ አለመቻል ይታወቃሉ! ነጭ ሰዎች ደግሞ ገንዘብን በመውደዳቸው፣ በግንኙነት አለመኖር፣ በግብረ ሰዶማዊነት፣ ፍቺ፣ በግብረ ሰዶማዊ ጋብቻ፣ አምላክ የለሽነት፣ ማጨስ፣ አልኮል በመጠጣትና በከፍተኛ ቁጥር ራስን በማጥፋት ይታወቃሉ!

    የሚያሳዝነው ታዲያ እነዚህ የተወሰኑ ባህሪያት ልንታገላቸው የሚገቡ እውነተኛ ክስተቶች ናቸው። ነጭ ሰው ወይም ጥቁር ሰው ከሆንክ ራስህን ከእነዚህ የተወሰኑ ባህሪያት ለመነጠል ታገል። ከማናቸውም ከእነዚህ የተወሰኑ ባህሪያት ራስህን አርቅ። ከጥቁር ወይም ነጭ ሰው ይልቅ የክርስቲያንን ባህሪያት ውሰድ። ልትታገለው የሚገባ መልካም ትግል ነው!

    17. የወሲብ ምኞትን ታገል።

    ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።

    2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡22

    የወሲብ ምኞት ቅድስናህን የሚያቃጥል እሳት ነው። መንፈሳዊነትህን ይቀንሰዋል። ለዚህ ነው ጳውሎስ ከመቃጠል ማግባት ይሻላል ያለው። እየተቃጠልክ ከሆነ መልካም ያልሆነ ነገርን እየተለማመድክ ነው። መንፈሳዊ ፍላጎቶችህ ከመንፈሳዊነትህ ጋር የተያያዘ ነው። ወሲባዊነት ከተለመደው በላይ ሊባል የሚችል በሰው ልጅ ውስጥ ያለ ተጽዕኖ በመሆኑ ከተፈጥሮ በላይ ነው። የሚቃጠል የወሲብ ፍላጎት አሉታዊ ነገር ሲሆን መንፈሳዊነትህንም ይቀንሰዋል። የወሲብ ምኞትን በሙሉ ልብህ ባለህ ኃይል ሁሉ ልትታገለው ይገባል።

    የወሲብ ምኞትን የመዋጊያ የመጀመሪያው መንገድ ራስህን አንዳንድ ጣዕሞችን ከመለየት በመከልከል ነው። አንዳንድ ወሲባዊ ነገሮችን አንዴ ካጣጣምክ እነርሱን መቆጣጠር የበለጠ ያስቸግራል።

    ሁለተኛ ደግሞ የአንዳንድ እንደ ወሲባዊ ምስሎችን መመልከት፣ ራስን በራስ ማርካትና ግብረ ሰዶማዊነት ያሉ ወሲባዊ ነገሮችን ከቀመስክ ደግሞ ሕይወትህን ሙሉ እርሱን እየተቃወምክ በመጸለይ መኖር አለብህ።

    የወሲብ ምኞትን ለመዋጋት ማድረግ ያለብህ ሦስተኛው ነገር ደግሞ ለወሲባዊነትህ ማስተንፈሻ መስጠት ነው። ይህ ማስተንፈሻ ደግሞ መደበኛ የወሲብ ግንኙነት ልትፈጽም በምትችልበት በትዳር አማካኝነት ሊገኝ ይችላል። የሚያሳዝነው ግን በጋብቻ ውስጥም ቢሆን መጥፎ ሚስት ካለችህ ያንን ማስተንፈሻ እንደምታገኝ ዋስትና ላይኖርህ ይችላል። ምንም ቢሆን ግን ሕይወትህን በሙሉ የወሲብ ምኞትን መታገል ይኖርብሃል።

    18. ለፍሬአማነት ታገል

    እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤

    2ኛ ጴጥሮስ 1፡8

    መንፈሳዊ መካንነት ላይ የሚደረገው ትግል ረጅምና አስቸጋሪ ነው። በርካታ ድብቅ ችሎታዎችን በማነሳሳት እግዚአብሔርን እያገለገልክ ሕይወትህን ማቃናትን ያካትታል። ፍሬአማነት ከትጋት፣ እምነት፣ መንፈሳዊነት፣ ባህርይ፣ ዕውቀት፣ ደግነትና ትዕግስት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታስተውላለህ። እነዚህ ሁሉ ከፍሬአማነት ጋር ግንኙነት ያላቸው የማይመስሉ መንፈሳዊ ችሎታዎች ናቸው። ነገር ግን ናቸው! ፍሬአማነትህን በትክክል የሚወስኑት እነዚህ ናቸው። ሕይወትህን ሙሉ ለትጋት፣ ባህርይ፣ እምነት፣ ዕውቀት፣ ወንድማዊ ደግነትና ችሮታ ትታገላለህ።

    ይህ ለፍሬአማነት የሚደረግ ትግል በመሆኑ መልካምና ተገቢ ትግል ነው።

    ምዕራፍ 4

    የውጊያን ድባብ ልመደው

    የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።

    ኢሳይያስ 9፡5

    ለሰዎች ነፍስ በሚደረግ የመጨረሻ ተጋድሎ ውስጥ እንገኛለን። የውጊያን ድባብ ካልተለማመድነው ፈጽመን በሚገባ አንንቀሳቀስም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ስማ፡- የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል። ይህ ጸጥታ የሰፈነበት የሰላም፣ የመረጋጋትና የፍሰሃ አየር አይደለም።

    ይህ አደጋ፣ ስጋት፣ ግራ መጋባት፣ መደናገር፣ አቅጣጫን መሳት፣ መጨነቅ፣ ውጥረት፣ ደስተኛ አለመሆን፣ ፍርሃት፣ ሞት፣ ሰቆቃ፣ ህመም፣ ቅሬታ እና ከባድ ድንጋጤ የሞላበት የውጊያ አየር ነው። እግዚአብሔር ቃሉን ለማዳረስና ብዙሃኑን ወደ ሲኦል እየመሩ ያሉትን ሽንገላዎችና ማጭበርበሮች ለመዋጋት እኛን እየተጠቀመብን ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት በመስፋቷ የማይደሰት ጠላት አለን። ኢየሱስ ወደሥፍራው እንደደረሰ በዲያብሎስ በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶበታል። ኢየሱስ ክርስቶስ የኖረው በውጊያ አየር ውስጥ ነው። ዲያብሎስም በፍጹም ከኛ ርቆ አያውቅም። ኢየሱስ ከማደጉ በፊት ሊያጠፋው በተነሳ የነፍስ አጥፊ መንፈስ ጥቃት ደርሶበት ነበር። ኢየሱስ ሲጾምና ሲጸልይ በምድረበዳ ጥቃት ደርሶበት ነበር። በፈሪሳውያን ተጠቃ ደግሞም በስተመጨረሻ በአስቆሮቱ ይሁዳ ጥቃት ደርሶበት ነበር።

    የአገልግሎት ድባብ የውጊያ ድባብ ነው።

    የእግዚአብሔርን ታላቅ ጥሪ ከተቀበልክ ማለት ለእግዚአብሔር መንግስት በሚደረግው የመጨረ ውጊያ ውስጥ ገባህ ማለት ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሞተ ጊዜ ይህንን ዓለም እጅግ ክፉ ከሆነ ዲያቢሎስና ከመላዕክቱ ለማዳን ቆራጥ ዘመቻ ተጀመረ። ዓለምን ለብዙ ዓመታት ያሳተው የቀደመው እባብ ዲያብሎስ ነው።

    እውነተኛ አገልግሎት ውጊያ ነው። የእውነተኛ አገልግሎት ድባብ የውጊያ ድባብ ነው። የውጊያ ድባብ ምን ይመስላል? የጸጥታ፣ የመረጋጋትና የሰላም ነው? በፍጹም! የምትፈልገው ሰላምና መረጋጋት ከሆነ እባክህ ወደ አገልግሎት አትግባ። እግዚአብሔርን መታዘዝና የእርሱን ሕይወት መኖር እንደጀመርክ የውጊያ ድባብን የተለያዩ ክፍሎች መለማመድ ትጀምራለህ። በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።(2ኛጢሞቴዎስ3፡12)

    ውጊያ ሲጀምር አየሩ ወዲያውኑ ወደ ሁከት፣ ድብልቅልቅ ወዳለ ግራ መጋባትና መደናበር ይለወጣል። ውጊያ ላይ ስትሆን ሁልጊዜም በጭንቀት ውስጥ ትሆናለህ። ፍርሃት ይኖራል፣ ውጥረት ይኖራል እንዲሁም እርግጠኛ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1