Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የቤተ ክርስቲያን እድገት
የቤተ ክርስቲያን እድገት
የቤተ ክርስቲያን እድገት
Ebook353 pages2 hours

የቤተ ክርስቲያን እድገት

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

የቤተ ክርስቲያን እድገት አስቸጋሪና የማይጨበጥ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ሁሉም መጋቢዎች ቤተ ክርስቲያኖቻቸው እንዲያድጉ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ቤተ ክርስቲያን እድገት ላለህ ጥያቄህ መልስ ይሆናል፡፡የቤተ ክርስቲያንን እድገት ለማየት እንዴት “ብዙ ነገሮች በአንድ ላይ እንደሚሰሩ " ትረዳለህ፡፡ ውድ መጋቢ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ቃሎችና ቅባቱ በልብህ ውስጥ ሲገቡ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን እድገት ትጸልይ የነበረውን በገሀድ ታየዋለህ፡፡

LanguageEnglish
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954300
የቤተ ክርስቲያን እድገት
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Read more from Dag Heward Mills

Related to የቤተ ክርስቲያን እድገት

Related ebooks

Christianity For You

View More

Related articles

Reviews for የቤተ ክርስቲያን እድገት

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

2 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የቤተ ክርስቲያን እድገት - Dag Heward-Mills

    የቤተ ክርስቲያን እድገት

    ...ይቻላል

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    CHURCH GROWTH

    ትርጉም፡- ዘላለም ቸርነት

    አርትዖት፡- መጋቢ ልዑል ኃይሉ

    ስለ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ

    በዚህ ኢሜይል ይጻፉ፡- evangelist@daghewardmills.org

    ዌብሳይታቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.

    በፌስቡክ፣ Facebook: Dag Heward-Mills

    በትዊተር፣ Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-61395-430-0

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው፡፡

    ማውጫ

    ክፍል አንድ የቤተክርስቲያን እድገት እና ጥልቅ መሻት

    1. የቤተክርስቲያን እድገት እና ጥልቅ መሻት

    ክፍል 2 የቤተክርስቲያን እድገት እና የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች

    2. ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች አማካኝነት እንዴት ታላላቅ ነገሮችን ማከናወን እንደምትችል

    3. ልዩ ክህሎት የሌላቸው ሰዎች ቤተክርስቲያናትን እንዴት እንደሚያሳድጉ

    4. ለትርፍ ጊዜ አገልጋዮች ሸክምህን ማካፈል ያለብህ ምክንያት

    5. የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች እንዴት የቤተክርስቲያንን እድገት እንደሚያመጡ

    6. የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች በአገልግሎት ውስጥ በማይሳተፉበት ጊዜ ሊበቅሉ የሚችሉ አምስት ክፋቶች

    ክፍል 3 የቤተክርስቲያን እድገትና የመጋቢነት ቴክኒኮች

    7. በትርና ምርኩዝን የመጠቀም ጥበብ

    8. ወደ ቤተክርስቲያን እድገት የሚመሩ የእረኝነት ስልቶች

    ክፍል 4 የቤክርስቲያን እድገትና ጥበብ ያለው የገንዘብ አስተዳደር

    9. ቀልጣፋ የቤተክርስቲያን የገንዘብ አስተዳደር ወደ ቤተክርስቲያን እድገት እንዴት እንደሚመራ

    10. የመባ ስጦታን እንዴት ማስተዳደር እንደሚገባህ

    11. በቤተክርስቲያን ውስጥ አስራትና መባ እንዴት ማሳደግ እንደምትችል

    12. በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዴት ገንዘብ ማሰባሰብ እንደምትችል

    ክፍል 5 የቤተክርስቲያን እድገትና የቤተክርስቲያን አባላት አያያዝ

    13. አባላትህን እወቅ

    14. ከአማካይ የቤተክርስቲያን አባል መጠበቅ የሚገባህ ነገሮች

    ክፍል 6 የቤተክርስቲያን እድገትና ድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶች

    15. ረዳት አገልጋዮችን እንዴት መምረጥ እንደሚቻል

    16. ረዳት አገልጋዮችን የምትቀጥርበት መመሪያዎች

    17. እንዴት ረዳት መቅጠር እንደሚገባህ

    ክፍል 7 የቤተክርስቲያን እድገት፣ የመነቃቂያና የካምፕ ስብሰባዎች

    18. የካምፕ ስብሰባዎች እንዴት የቤተክርስቲያን እድገትን እንደሚያመጡ

    19. የመነቃቂያ ስብሰባዎች እንዴት የቤተክርስቲያን እድገትን እንደሚያስከትሉ

    20. የተሳካ የመነቃቂያ ስብሰባ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል

    ክፍል 8 የቤተክርስቲያን እድገትና መስተጋብሮች

    21. ወዳጅነቶችና መስተጋብሮች እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን እድገት እንደሚመሩ

    22. አስፈላጊ የሆኑ የአገልግሎት ግንኙነቶችን እንዴት ማዳበር እንደሚቻል

    ክፍል 9 የቤተክርስቲያን እድገትና ጌተሰማኒ

    23. የቤተክርስቲያን እድገት እንዴት በጌተሰማኒ እንደሚወሰን

    24. እግዚአብሔርን የመጠበቅ ጥበብ

    ክፍል 10 በአጥቢያዎች አማካኝነት የቤተክርስቲያን እድገትን ማምጣት

    25. በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ጥምረት የቤተክርስቲያን እድገት ማምጣት

    ክፍል 11 የቤተክርስቲያን እድገትና ‹አናካዞ

    26. የእድገት ቁልፎቹ፡ አናካዞ፣ ቢያዞ እና አናይዴያ

    27. ለቤተክርስቲያን እድገት የአናካዞ አስፈላጊነት

    28. አናካዞን ለቤተክርስቲያን እድገት እንዴት ማስረጽ እንደሚቻል

    29. አናይዴያ እና ቢያዞ እንዴት የቤተክርስቲያንን እድገት እንደሚያመጡ

    ክፍል 12 የቤተክርስቲያን እድገትና ጠንካራ አመራር

    30. የቤተክርስቲያንን እድገትን እንድታሳካ ለምን ጠንካራ መሪ መሆን እንደሚገባህ

    31. የታላቅ ቤተክርስቲያን መጋቢ ጥንካሬና ውሳኔዎች

    ክፍል 13 የቤተክርስቲያን እድገትና ከሌላው የመቅዳት ዘዬ

    32. ከሌላው የመቅዳት ጥበብ

    33. መቅዳት እንዴት ለአገልግሎትህ ሊጠቅምህ እንደሚችል

    ክፍል 14 የቤተክርስቲያን እድገትና ብርቱ ሥራ

    34. የቤተክርስቲያን እድገትና የማያርቋጥ ጥረት ማድረግ

    35. ለታላቅ ቤተክርስቲያንን እንዴት ጠንክሮ መሥራት እንደሚቻል

    36. የቤተክርስቲያን እድገት እና የመጋቢ ሥራ (P.V.C.I)

    37. የቤተክርስቲያን እድገትና ስለ ራስህ መጠንቀቅ (ደብሊው. ኤ. አር)

    ክፍል 15 የቤተክርስቲያን እድገትና ውጫዊ ገጽታ

    38. የቤተክርስቲያን እድገትና ውጫዊ ገጽታዎች

    ክፍል 16 የቤተክርስቲያን እድገትና ሴቶች

    39. ሴቶች የቤተክርስቲያን እድገትን የሚያመጡባቸው ሰባት ምክንያቶች

    ክፍል 17 የቤተክርስቲያን እድገት ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና አወቶብሶች

    40. ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና አውቶብሶች እንዴት ቤተክርስቲያንን እንደሚያሳድጉ

    ክፍል 18 የቤተክርስቲያን እድገት ፈተናዎች

    41. የቤተክርስቲያንን እድገት የሚሻ መጋቢ ሃያ የተለያዩ ፈተናዎች

    ክፍል አንድ

    የቤተክርስቲያን እድገት እና ጥልቅ መሻት

    ምዕራፍ 1

    የቤተክርስቲያን እድገት እና ጥልቅ መሻት

    ራእይ ባይኖር….

    ምሳሌ 29፡18

    ራእይ ቤተክርስቲያንን ወደ እድገት ይመራታልን?

    ከዓመታት በፊት ለቤተክርስቲያን እድገት ራእይና ሕልም ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ የሚያወሳ የዴቪድ ዮንጊ ቾን መጽሔት አንብቤ ነበር። ያን ጊዜ ታዲያ ራእይ ምን ያህል ለቤተክርስቲያን እድገት አስፈላጊ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን የጠቃሚነቱን ምክንያትም አልተገነዘብሁም ነበር። በዓለም ላይ የትልቁ ቤተክርስቲያን መጋቢ እንዲሁም የቤተክርስቲያን እድገት ፅንሰ ሐሳብ አቀንቃኝ የሆኑት ዶ/ር ዴቪድ ዮንጊ ቾ አንድ ወቅት ሳልረዳው የኖርሁትን ሐሳብ ተናገሩ። ራእይህ ያበጅሃል እንጂ አንተ አታበጀውም። ሆኖም ያኔም አባባሉ አልገባኝም።

    እውነት ለመናገር ራእይ መያዝ የሚለው ርዕስ በሥነ አመራር ዙሪያ በሚሰጡ ትምህርቶች ላይ ሁሉ የሚነሣ ቋሚ የመክፈቻ ነጥብ እንደሆነ አስብ ነበር።

    ሰዎች የራእይ መኖርን አስፈላጊነት ሲያስተምሩ፣ ግቦችን በጽሑፍ ሲያሰፍሩ…ወዘተ፣ ስሰማቸው እንኳ እነዚህ ነገሮች እንዴት ወደ ቤተክርስቲያን እድገት ሊያመሩ እንደሚችሉ አላውቅም ነበር።

    በቤተክርስቲያን እድገት ርዕስ የሚዘጋጁ ኮንፈረንሶችን የሚካፈል እያንዳንዱ መጋቢ ውስጡ በቤተክርስቲያን እድገት ራእይ እንዲሁም መሻት የተሞላ ይመስላል።

    ለራሴ እንዲህ ስል አሰብሁ፣ ብዙ መጋቢያን ቤተክርስቲያኖቻቸው እንዲያድጉላቸው ይፈልጋሉ፤ ሆኖም ግን ቤተክርስቲያኖቻቸው ሲያድጉ አይታይም። ራእዮችና ፍላጎቶች ብቻ ወደ ቤተክርስቲያን እድገት የሚመሩ ቢሆን ኖሮ እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን ትልቅ በሆነ ነበር!

    ራእይህ ጥልቅ ራዕይ ሊሆን ግድ ይላል

    ዓመታት ሲያልፉ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ራእይህ ጥልቅ መሆን እንዳለበት ነው። እንደነገሩ የሆነ ራዕይን ይዘህ ትልቅ ቤተክርስቲያን ሊኖርህ አይችልም። ስር ያልሰደደ ራእይ ይዘህ ቤተክርስቲያንህን ልታሳድግ አትችልም። ራእይህ በነፍስህ ውስጥ ገብቶ ሊበላህ እንደ እሳትም ሊያቃጥልህ ይገባል። ያን ጊዜ ዶ/ር ቾ ያሏቸው ነገሮች ሁሉ መከሰት ይጀምራሉ። ያ ጥልቅ ራእይ ታዲያ የትልቅ ቤተክርስቲያን መጋቢ ያደርግሃል።

    በእውነቱ ትልቅ ቤተክርስቲያንን የመመሥረት ጥልቅ ራእይ በሌለበት እውነተኛ የሆነ የቤተክርስቲያን እድገት ሊኖር አይችልም። ጥልቅ የሆነ ራእይ የሰው ልጅ የተባለ በማይቋቋመው አስቸጋሪ ጎዳና ላይ እንኳ ለትክክለኛ የቤተክርስቲያን እድገት በማነሣሣት ይመራሃል።

    ጥልቅ ራእይ ለቤተክርስቲያን ስውር የእድገት ሞተር ነው

    የትልቅ ቤተክርስቲያን መጋቢ ለመሆን ጉዞው ረጅምና አድካሚ ነው።

    ጥልቅ ራእይና ሕልም አንድ አገልጋይን ከትንሽ ቤተክርስቲያን መጋቢነት ወደ ትልቅ ቤተክርስቲያን መጋቢነት የሚያሸጋግሩ የማይታዩ ሞተሮች ናቸው።

    አንዳንድ መጋቢዎች ታዲያ ለቤተክርስቲያን እድገት አስፈላጊ፣ ነገር ግን ከባድና አስቸጋሪ ነገሮችን ለማድረግ ይህንን ዓይነት ውስጣዊ ሞተር የላቸውም።

    ውጪያዊ ግፊት የትልቅ ቤተክርስቲያን (mega church) መጋቢ ሊያደርግህ አይችልም

    የትኛውም ውጪያዊ ምክር ወይም ግብዓት አንድን ግለሰብ በአስቸጋሪው ጎዳና ላይ ገፍቶ የትልቅ ቤተክርስቲያን መጋቢ ሊያደርገው አይችልም። ውጪያዊ ግፊቶች ሁሉ የትልቅ ቤተክርስቲያን መጋቢ ከመሆንህ በፊት በቶሎ ይከስማሉ። ውጪያዊ ምክሮች፣ ማበራታቻዎችና ማጽናኛዎች በቤተክርስቲያን እድገት ጎዳናና በወንጌል አገልግሎት ላይ አጭር እድሜ ያላቸው ወይም የማያዛልቁ ናቸው።

    ራእይ እንድትከውን የሚያደርግህ ነገር

    የትኛውም ሰው ሊያሳካልህ የማይችለው፣ ነገር ግን ጥልቅ ውስጣዊ ራእይና ሕልም ሊሠሩት የሚችሉት አንድ ነገር አለ።

    ውስጣዊ የሆነ ጥልቅ ራእይና ሕልም ለቤተክርስቲያን እድገት ማድረግ የሚገባህን ሁሉ በትሕትና እንድትከውን ያደርጉሃል።

    ለቤተክርስቲያን እድገት ያጸልይሃል። ያለ ውስጣዊ ጥልቅ ራእይና ሕልም የእግዚአብሔርን ትኩረት መሳብ የሚችል ብርቱ ጸሎት ማድረግ የማይታሰብ ነው።

    ለትልቅ ቤተክርስቲያን ጥልቅ ራእይና ሕልም ካለህ ለቤክርስቲያን እድገት አስፈላጊ የሆኑ ጥበብና ስልቶችን ለመቀበል ትሻለህ። ያለበለዚያ ጥበብ ለመቀበል ጊዜ መውሰድ ይሳንሃል። ይልቁን ወዲያውኑ በቤተክርስቲያን እድገትና ስልቶች ዙሪያ በሚያስተምሩ መጋቢዎች መበሳጨት ትጀምራለህ። እነዚህ ትምህርቶች እንደውም እንደማይሠሩ ትናገራለህ።

    ውስጣዊ የሆነ ራእይና ሕህልም አንድ ነገር እስኪፈጠር ድረስ በዚያ ዙሪያ ያሉ ትምህርቶቹን ደጋግመህ እንድታነብ ያደርግሃል።

    ከዚህ ተቃራኒ ከሆንህ ለቤተክርስቲያን እድገት የሚረዱህን መጻሕፍቶች ለማንበብ ጊዜ አይኖርህም።

    ጥልቅ ራእይና ሕልም ሲኖርህ በቤተክርስቲያን እድገት ላይ ሊረዱህ የሚችሉ ሰዎችን እንደትገናኝ ይገፋፋሃል። በዚህም በትሕትና መንፈስ ከትክክለኛ ሰዎች ጋር ኅብረትን በማድረግ የእነርሱ በጎ ተጽዕኖ እንዲሁም ቅባት እንዲያርፍብህ ትሆናለህ።

    ትልቅ ቤተ ቤተክርስቲያን እንዲኖርህ ጥልቅ ራእይና ሕልም ከሌለህ ለቤተክርስቲያን እድገት የሚበጁ መልእክቶችን ማዳመጥ አትችልም። በጣም የሚያስፈልግህን መልእክት ተችተህ ልታልፈው፣ አልፎ ተርፎም ልትሳለቅበት ትችላለህ።

    ጥልቅ ራእይና መሻት ለቤተክርስቲያን እድገት ረጅም ጉዞ የሚያስፈልጉት ኃይል፣ ጉልበትና ጽናት የሚገኙበት ብቸኛው ትክክለኛ ምንጭ ነው።

    ክፍል 2

    የቤተክርስቲያን እድገት እና የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች

    ምዕራፍ 2

    ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች አማካኝነት እንዴት ታላላቅ ነገሮችን ማከናወን እንደምትችል

    ሌይኮስ - ልዩ ክህሎት የሌለው ሰው

    ታሪክ እንደሚያስተምረን ታላላቅ ነገሮች ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ተከናውነዋል። ተራ የሚባሉትን ወይም ልዩ ክህሎት የሌላቸውን ሰዎች ስኬቶች በመመልከት ብቻ ቤተክርስቲያንህን ለማሳደግ ትነቃቃለህ።

    ሌይማን የሚለው ቃል ሌይኮስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ምንም ዓይነት ልዩ ክህሎት የሌለው ማለት ነው። የሚከተሉት ጥቂት ትርጉሞች ሌይማንን የሚገልጹ ናቸው።

    1. ሌይማን ተራ ሰው ነው።

    2. ሌይማን ለውጥ የማይታይበት ሰው ነው።

    3. ሌይማን ያው የሆነ ሰው ነው።

    4. ሌይማን የተለመደ ሰው ነው።

    5. ሌይማን መደበኛ ሰው ነው።

    6. ሌይማን የሚታወቅ ሰው ነው።

    7. ሌይማን የእለት ተእለት ሰው ነው።

    8. ሌይማን መካከለኛ ግምት የሚሰጠው ሰው ነው።

    9. ሌይማን ባለ ሞያ ያልሆነ ሰው ነው።

    10. ሌይማን በእውቀት ያልተካነ ሰው ነው።

    11. ሌይማን በአንድ መስክ በሚገባ ያልተማረ ሰው ነው።

    12. ሌይማን ክህሎት የሌለው ነው።

    13. ሌይማን ያልሠለጠነ ሰው ነው።

    14. ሌይማን በትምህርት ያልተመረቀ ሰው ነው።

    15. ሌይማን የሞያ ፈቃድ የሌለው ሰው ነው።

    ታላላቅ ክንውኖች በቤተክርስቲያን ዙሪያ

    1. ልዩ ክህሎት የሌላቸው ሰዎች በታላቁ የቤተክርስቲያን ተሐድሶ ዘመን ዐምዶች ነበሩ።

    ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱስን ተራው ሕዝብ ወደሚናገርበት ቋንቋ መተርጎሙ የዓለምን መልክ ለውጧል። በላቲን የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ በተራው ሕዝብ ቋንቋ ማዘጋጀቱ ሕዝቡ በቀላሉ እንዲያነበውና እንዲጠቀምበት አስችሎታል።

    ተራ ሰዎች የመገለጥ እውቀት በእጃቸው በገባበት አጋጣሚ የዓለምን መልክ ለውጠዋል። ደህንነት በእግዚአብሔር ጸጋ ለሁሉም ሰው እንደሆነ ሲገነዘቡ አቋም ይዘው በመነሣትና በማሸነፍ ተሐድሶ ብለን የምንጠራውን ለውጥ አምጥተዋል።

    2. ልዩ ክህሎት የሌላቸው ሰዎች የታላቋ ሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ዐምዶች ነበሩ።

    በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ሜቶዲዝም በዩናይትድ ስቴትስ ትልቁ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ነበር። ይህ ታላቁ የሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ታዲያ እዚያ ደረጃ ላይ የደረሰው ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ብርታት ነበር።

    በጥንታዊው የሜቶዲስት ቤተክርስቲያናት ልማድ መሠረት ልዩ ክህሎት የሌለው ሰው ተመርጦ የአምልኮ አገልግሎቱን እንዲሁም ሰርኪዩት በመባል በሚታወቁት በቡድን የሆኑ ቤተክርስቲያናትን ውስጥ ስብከቱን እንዲያካሄድ ይደረግ ነበር።

    ሰባኪው በእግሩ ወይም በፈረስ ተቀምጦ ወደ ተጠቀሰው የስብከት ሰርኪዩት በመሄድ በተመደበው ሥርዓትና ጊዜ ስብከቱን ይከውናል።

    ሌሎች አገልጋዮችና መጋቢዎች ከተመደቡ በኋላም ቢሆን በእነዚህ ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች የመጠቀም ልማድ አልቀረም፡፡ ሜቶዲስት ሎካል ፕሪቸርስ በሚል ስያሜ በአጥቢያዎች የስብከት አገልግሎታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ሌሎችም በቅርበት ያሉ ቤተክርስቲያናት እውቅና የሰጧቸው ሲሆን አስፈቅደው በሚቀሩ አገልጋዮቻቸው ፈንታም ይጋብዟቸው ነበር፡፡

    3. ልዩ ክህሎት የሌላቸው ሰዎች በዓለም ላይ ትልቅ የሆነው ቤተክርስቲያን ዐምዶች ናቸው።

    የዮይዶ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከተመሠረተባቸው ዋነኛ መርሆዎች ውስጥ አንደኛው ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች መጠቀም ነው።

    የዮይዶ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መጋቢዎች በነበሩት ዴቪድ ያንግ ቾ እና በአማቱ ቾይ ጃ-ሺል፣ እንዲሁም በሌሎች አራት ሴቶች በቾይ ጃ-ሺል የቤት ውስጥ የአምልኮ ፕሮግራም በሜይ 15/1958 ተጀመረ።

    በ1977 የቤተክርስቲያኒቱ አባላት 50,000 ደረሱ። በሁለት ዓመታት ውስጥ አሐዙ በእጥፍ አደገ። በኖቬምበር 1981 የአባላቱ ቁጥር 200,000 ደረሰ። በዚህ ጊዜ በምዕመናን ቁጥር የዓለም ትልቁ ቤተክርስቲያን ለመሆን የበቃ ሲሆን ይህም በሎስአንጀለስ ታይምስ ተዘግቧል።

    በ2007 የአባላቱ ብዛት 830,000 የደረሰ ሲሆን እሁድ ቀን በ7 ፈረቃ መርሐ ግብር የሚከናወነው አገልግሎት በ16 ቋንቋ ይተረጎም ነበር።

    4. ልዩ ክህሎት የሌላቸው ሰዎች በናይጄሪያና ጋና ላሉት ቤተክርስቲያናት ጠንካራ ኅብረት ዐምዶች ናቸው።

    በናይጄሪያ ያሉት የተዋጁት ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንና በጋና የሚገኘው የጴንጤቆስጤ ዋና ቤተክርስቲያን ቢሮ ልዩ ክህሎት የሌላቸውን ሰዎች በሚገባ ይጠቀማሉ። እነዚህ ሁለት አገልግሎቶች ጠንካራ ትስስር ያላቸውን መረቦች የፈጠሩት ልዩ ክህሎት በሌላቸው መጋቢዎችና ሰባኪያን አማካኝነት ነው።

    የጴንጤቆስጤ ቤተክርስቲያን የተመሠረተችው በብሪታኒያ ብራድ ፎርድ ከምትገኝ ሐዋርያዊ ቤተክርስቲያን በጊዜው ወደ ጎልድ ኮስት (ጋና) በተላከ አንድ አየርላንዳዊ ሚሲዮናዊ ነው።

    አሁን የአባላቷ ብዛት ከ1.7 ሚሊየን በላይ ሲሆን በአጠቃላይ በዓለም ላይም በሁሉም አሕጉራት በሚገኙ 70 አገራት የቤተክርስቲያኗ አጥቢያዎች ብዛት ከ13,000 በላይ ሆነዋል፡፡

    በ1952 ሪዲምድ ክርስቲያን ቸርች ኦፍ ጋድ (የተዋጁ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን) በናይጄሪያ በፓ ጆሲያ አኪንዳዮሚ ተመሠረተች። የበላይ ተቆጣጣሪ በሆነው ሬቨረንድ ኢ.ኤ. አዴቦዬ አማካኝነት ቤተክርስቲያኗ ከ140 በላይ አገሮች ውስጥ ያደገች ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተካፋዮች አሏት።

    በእውነቱ ከሆነ እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ስኬቶች ሲሆኑ ለውጤትም ሊበቁ የቻሉት ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ግብዓት ነው።

    በነባራዊው ዓለም የተከናወኑ ታላላቅ ድርጊቶች

    1. ታላቁ የመንግሥት ስልት የሚባለው ዲሞክራሲ የተፀነሠውና የተወለደው ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ነው።

    ዲሞክራሲ ለተራው ሕዝብ ውሳኔ የሚያሳልፉበትንና ባሰኛቸው ጊዜ መንግሥት የሚለውጡበትን እድል ይሰጣቸዋል።

    ዲሞክራሲ ለተራው ሰው የማይፈለጉ ሁኔታዎችን እንዳይቀበል የሚያስችለው ጉልበት ነው።

    ዲሞክራሲ ለተራው ሰው በአገሩ ላይ ተሳትፎንና በጎ ተፅዕኖን ማሳረፍ የሚችልበት መንገድ ነው።

    ዲሞክራሲ የሚገነባው ለሁሉም ተራ ሰው እኩል እድል በመስጠት መርሕ ላይ ነው።

    2. ታላቁ ልዕለ ኃይል የተወለደው ልዩ ክህሎት በሌላቸው ሰዎች ነው።

    የአሜሪካን አብዮት ተራ ሰዎች እንዴት ታሪክ እንደሚሠሩ የሚያሳይ ዓይነተኛ ምሳሌ ነው።

    ተራው ሰው ልዕለ ኃይልን ወለደ። በመጨረሻው ክፍለ ዘመን ግድም የአሜሪካን አብዮት በጥቂቶች ቁጥጥር ስር የነበረው እንዴት በብዙዎች ስር መሆን እንደሚችል ያሳየ የተሳካ ሠርቶ ማሳያ ነው።

    አብዮቱ የተቀረጸው ግን ሰንስ ኦፍ ሊበርቲ (የነጻነት ልጆች) በተሰኙት እና በሌሎች ትናንሽ አብዮታዊ ድርጅቶች ነበር። እነዚህ ድርጅቶች በባለጠጎቹና በኃይለኞቹ የመሬት ባላባቶች የተያዙ አልነበሩም። ነገር ግን በመካከለኛው የኅብረተሰብ ክፍል የሚገኙ ተራ ሰዎች ተሰባስበው የአብዮትን ዘር ዘሩ።

    3. ታላቁ የምርጫ ድል የመጣው በተራ ሰዎች አማካኝነት ነው።

    በሜይ 2008 ባራክ ኦባማ የዲሞክራቲክ ፓርቲውን በመወከል የፕሬዝደንትነቱን ወንበር ሲረከብ የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ጥቁር ፕሬዝደንት ነው።

    ምንም እንኳ የአሜሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ የዲሞክራሲ አራማጆችና ባለጸጎች የክሊንተን ደጋፊዎች በመሆናቸው ሚሊዮን ዶላሮችን በመስጠት ቢደግፉትም ኦባማ የተራውን ሰው ጉልበትና አቅም በመጠቀም በታሪክ ከየትኛውም ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ በላይ ብዙ ገንዘብ አሰባስቧል።

    ኦባማ ለምርጫ ቅስቀሳ ከ80 ሚሊየን ዶላር በላይ ያሰባሰበ ሲሆን አብዛኛውን ገንዘበ ያገኘው ታዲያ የአቅማቸውን አስተዋጽኦ ካደረጉ ተራ ግለሰቦች ነው።

    ምዕራፍ 3

    ልዩ ክህሎት የሌላቸው ሰዎች ቤተክርስቲያናትን እንዴት እንደሚያሳድጉ

    በአገልግሎት ዓለም ውስጥ ሁለት ዓይነት አገልግሎቶች አይቻለሁ፤ እነዚህም የሙሉ ጊዜና የትርፍ ጊዜ አገልግሎቶች ይባላሉ። ብዙ መጋቢያን የሚያውቁት የሙሉ ጊዜ አገልግሎትን ነው። የእኔ ዓላማ ግን የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች ቤተክርስቲያንን በማሳደግ ያላቸውን የአስተዋጽኦ መጠን ማሳየት ነው።

    የትርፍ ጊዜ አገልጋይ በገሃዳዊው ዓለም ያለውን ሥራውን እየሠራ በጌታ ኢየሱስ አገልግሎት ውስጥ በንቃት የሚሳተፍ ነው። የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ደግሞ የገሃዳዊውን ዓለም ሥራውን ትቶ ሙሉ ትኩረቱን በአገልግሎት ላይ ያደረገ ነው።

    ብዙዎቹ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉ አገልጋዮች የትርፍ ጊዜ አገልጋዮችን ማሳተፍ የሚለው ሐሳብ አይመቻቸውም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ እነርሱ ብቻ ጥቂትና የተጠሩ የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለው አገልግሎቱን ጠቅልለው መያዝ ስለሚፈልጉ ነው።

    ጥቂት የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሌሎች የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች በአገልግሎት ውስጥ ተጨባጭ የሆነ (ከገንዘብ ውጪ) አስተዋጽኦ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1